"ሞት ወደሌላ ዓለም የሚደረግ ጉዞ ከሆነ ከዚህስ በላይ ታላቅ ነገር ከወዴት ይኖራል? ከዚህ ዓለም ተጉዞ ወደሌላው ዓለም የሚደርሰው ሰው ከእናንተ ፍርድ የተሻለ ወደሚያገኝበት ዓለም ተሻግሯልና ሞቱ መልካም ነገር አመጣለት እላለሁ። ሞት እንዲህ ከሆነም ደግሜና ደጋግሜ እሞት ዘንድ እሻለሁ። በሞቴም የማገኘው ቀጣይ አለም ውስጥ እውነትና ሀሰትን መመርመሬን እቀጥላለሁ። ከእኔ በፊት እንደእናንተ ባሉት ዳኞች የሞቱትን ጠቢባን አግኝቼም የምጠይቃቸው ብዙ ቁምነገሮች አሉኝ። በዚያ ዓለም ጥያቄ በመጠየቁ ብቻ የሚገደል ሰው አይኖርም። "የመሄጃ ሰዓቴ ደርሷል፤ እኔም ሆንኩ እናንተን በየራሳችን መንገድ ልንሄድ ነው- እኔ ወደሞት ፣ እናንተ ደግሞ ወደመኖር። የትኛው እንደሚሻል አምላክ ያቃል።"
የሶቅራጠስ የመጨረሻ ቃል
ከጥበብ የተወሰደ
@denaway
የሶቅራጠስ የመጨረሻ ቃል
ከጥበብ የተወሰደ
@denaway