አልሐምዲሊላህ ደህና ናት/
/አሌክስ አብርሃም/
....
እስካሁን እንደ አፍራህ ትልልቅ አይኖች እንደ ቲማቲም
የቀላ
ከንፈር ያላት ሴት አይቼ አላውቅም። ለነገሩ እኔ ትዝ
የሚለኝ ከንፈሮቿ ናቸው እንጂ አፍራህ ውብ የሚለው ቃል
የማይገልጻት ጉድ ነበረች።
ቁመቷ ምዝዝ ብሎ የወጣ ፀጉሯ መቀመጫዋ ላይ
የሚደርስ በዛ ላይ ጥቁረቱ በዛ ላይ ብዛቱ አቤት አቤት
ጥቁር ፋፋቴ ጥቁር አባይ ሲባል የአፍራህ ፀጉር
ይመስለኝ ነበር።እጆቿ እግሯ አረ.. የአፍራ ቁንጅና በመቶ
አመት አንዴ የሚከሰት አይነት ነገር ነው።
ወሎ የቆንጆች አገር ሲባል አፍራ ትዝ ትለኝና ሀቅ ነው
እላለው። እንዳውም ወሎ አፍራህ ብቻ ይዞ ከድፍን
ኢትዮጵያ ቢወዳደር አጠገቡ የሚደርስ ያለ አይመስለኝም።
ታድያ ይህን ሁሉ
ቁንጅና ይዛ ሰባተኛ እና ስምንተኛ እኛ ክፍል ነው
የተማረችው።ይህን ጉድ ችለን መማራችን ታዕምር
አይደል።
በዛ አፍላ ዕድሜ ኤርታሌ ላይ ጥደውን እኮ ነው
ያስተማሩን ።ዳኛቸው የሚባል ሌላ ክላስ የሚማር
ጓደኛችን ልክ የእረፍት ሰዓት ሲደወል እንቅፋት
እስኪደፋው እየሮጠ እኛ ክፍል ይመጣና አፍራህ እያየ
እንዲህ ይለናል።
አፍራህን ያለችበት ክፍል አንድ ቀን ብማር አንጎሌ ይከፈት
ነበር ከመቶ መቶ ነበር የማመጣው። መናፈሻ
ውስጥ እኮ ነው የምትማሩት ብርቅይ ድንቅዬ ፍጥረት
እየጎበኛቹሁ ቱሪስት እኮ ናችሁ! ቱሪስት በኢትዮጵያ ብቻ
በደሴ ብቻ በእውቀት ጮራ ትምህርት ብቻ በሰባተኛ ሲ
ክፍል ብቻ የምትገኝ ብርቅዬ ፍጥረት እየጎበኛችሁ።
እውነት አለው አፍራህ እነዛን አይኖቿን አንዴ ስታሳርፍብን
ልባችን ከቅቤ የተሰራ ይመስል ቅ ል ጥ.... ደግሞ
አይኖቿን ጨፍና
የምትስቀው ነገር አላት አቤት ሲያምርባት.. አፍራህ .
አፍራህ
አፍራህ አፍራህ አፍራህ..ሳር ቅጠሉ አፍራ እንዳለ
ይውላል።ታድያ እሷን አለማውራት ለመቀራረብ የማይጥር
ማነው?..
# አፍራህ ወይንሸትና ሰዓዳ አንድ ወንበር ላይ ነበር
የሚቀመጡት። እውነቱን ለመናገር አፍራህን አይቼ ዳርና
ዳር የተቀመጡትን ወይንሸትንና ሰዓዳን ስመለከት የምር
ሰው አይመሱሉኝም።
ይቅር ይበለኝ።አፍራህን ዙርያዋን ለመጠበቅ የተገነቡ
ግንቦች መስለው ነው የሚታዩኝ። ለነገሩ ሁላችንም
የክላሱ ልጆች ዙርያዋን የበቀልን አረም ነገሮች ነበር
የምንመስለው።አፍራህ የምትባል ጉድ እምታሳጣን
መሀላችን
ተፈጥራ ምን እናድርግ? ሰባተኛ ክፍል ማን አለ? ቢባል
አፍራህ
ብቻ። ሂሳብ አስተማሪያችን እራሳቸው ሰባት ጥያቄ
ከጠየቁ
አምስቱ ለአፍራህ ነው።በርግጥ አፍራህ አምስቱንም
አትመልስም
ግን ፈገግ ይሉላታል።
ግን እኮ #"እኛ ሀበሾች ብዙዎቻችን እናስመስላለን እንጂ
ሴትን አናከብርም የምናከብረው ቆንጆ ሴትን ነው።"
ዙቤይዳ
ቅምሻ.....
@rasnflega