የተዋሕዶ ፍሬዎች


Гео и язык канала: не указан, не указан
Категория: не указана


🎯 በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሀዱ አምላክ አሜን::
👉 መዝሙር
👉ብሒለ አበው
👉ስብከት
🎯የሚለቀቅበት ቻናል ነው ወዳጅ ዘመድዎን ይጋብዙ :: https://t.me/yetewahedofera

Связанные каналы  |  Похожие каналы

Гео и язык канала
не указан, не указан
Категория
не указана
Статистика
Фильтр публикаций


💠💠💠💠💠💠💠💠💠💠
            
              #ፆም    

በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን እምነትና ትምህርት መሰረት ጾም የማህበርና የግል ተብሎ በሁለት ይከፈላል፡፡

          ፆም ምንድ ነው?

#ጾም ማለት ሰው ምግብ ወይም ሰውነት ከሚፈለጋቸው ነገሮች መካከል መወሰን ማለት ነው፡፡ ጾም በጥንተ ፍጥረት አትብላ ተበሎ የህግ መጠበቅም ሆኖ ለሰው ልጅ ከተሰጠው ትዕዛዝ ጾም ከሃይማኖት ጋር የተያያዘ ስርአት ስለሆነ ሃይማኖት በለበት ሁሉ አለ፡፡ ጾም ለተውሰነ ጊዜ ከእህልና ውሀ መከልከል ብቻ ሳይሆን ለሰውነት የሚምረውን ለማየት እና ለመፈጸም የሚያስጎመጀውን ነገር ሁሉ መፈጸም ነው፡፡በተግባራዊ ትርጉም የተረዱና የተጠቀሙበት ሰዎች ጾምን ‹‹ለፀሎት እናቷ፣ ለእንባ መፍለቂያዋ ለበጎ ስራ ሁሉ መሰረት ›› በማለት ተርጉመውታል፡፡

#የፆም_አስፈላጊነት
ሃይማኖት መሰረት ነው ነገር ግን ቤት በመስራት ብቻ የተሟላ እንደማይሆን ሃይማኖትንም ፍጹም የሚያደርጉት በእርሱ መሰረትነት ነው የመሚታነጹ ስነ   ምግባራት ናቸው፡፡ ጾም፣ ጸሎት ምጽዋት ስግደትን የመሰሉት ምግባራት ሃይማኖትን እንዲሰራ ያደርጉታል፡፡

ጾም የስጋን ምኞትን እናፈቃድን ለማስታገስ ይረዳል፡፡ መዝ 34፡13፣ ሮሜ 8፡12-14፣ 1ኛ ቆሮ 6፡12  ‹‹ ለሚጠፋ ምግብ አትስሩ ይልቅስ የሰው ልጅ ለሚሰጣቹህ የዘለዓለም ህይወት ለሚሆን ምግብ ስሩ›› ዮሐ 6፡7 . ጾም በአምሮት በምኞትና በስስት ጸባዮች ላይ የበላይነት ያስገኛል፡፡

          #በፆም_የተጠቀሙ_ሰዎች

ሀ. #በብሉይ_ኪዳን
የሰማርያው ንጉስ አክአብ  1ኛ ነገ 20፡27
የእስራኤል ሰዎች       2ኛ ዜና 20፡1-23
በጉዞ ላይ የነበሩ ሰዎች  እዝ 8፡21
የነነዌ ሰዎች              ዮናስ 3፡3
ነብዩ ነሕምያ             ነህ 1፡2
ሀማ በተነሳ ጊዜ አስቴር 3፡9 የመሳሰሉት፡

ለ. #በሐዲስ_ኪዳን
በሐዲስ ኪዳን ጾም የጀመረው ክርስቶስ ነው፡፡ ክርስቶስ ከጾም በኋላ 3 ነገሮችን ድል ነስቷል፡፡   1. ስስት      2. ትእቢት    3. ፍቅረ ነዋይ
መላእክትም ቀርበው አገልግለውታል፡፡ መዝ 90፡11 ፣ ማቴ 4፡1 ፣ ሮሜ 14፡1-6

        #የአዋጅና_የግል_ጾም
፩.#የአዋጅ_ጾም
በአባቶቻችን የተደነገጉ ሰባት አጽዋማት አሉ፡፡
፩ ዐብይ ጾም               
፪.ጾመ ነብያት   
፫.ሐዋርያት
፬.ፍልሰት
፭.ገሃድ
፮.ነነዌ
፯.ፆመ ድህነት         

#ዐብይ_ጾም
ሙሴ በሲና ተራራ ህጉን ከማቅረቡ በፊት 40 ቀን 40 ሌሊት ጾሟል፡፡ ጌታም ወንጌል ከመስበኩ በፊት በገዳመ ቆሮንጦስ 40 ቀን 40 ሌሊት ጾሟል፡፡
. ይህ ጾም አብይ ወይም ሁዳዴ በመባል ይታወቃል፡፡ አብይ የሚሰኘው ዐብይ ነብያት የጾሙት በሐዲስ ኪዳንም ጌታም የኦሪተንና የነቢያትን ህግ ለመጠበቅና ለመፈጸም ሲል የጾመው በጾሙ ፍጻሜ ከሰይጣን የመጣውን ፈተና ድል የነሳበት በመሆኑ ነው፡፡
. በአብይ ጾም ሰባት ቅዳሜ ስምንት እሁድ ይገኛሉ፡፡ ይህም የጾሙን ጊዜ ስምንት ሳመንታት ያደርገዋል፡፡ የመጀመርያው ሳምንት ህርቃል ተብሎ ይታወቃል ወደ ጾሙ መግቢያ መለማመጃ ማለት ነው፡፡ የመጨረሻው ሳምንት ሕማማት ነው ክርስቶስ መከራ የተቀበለበት ቀን በመሆኑ ነው፡፡

#ጾመ_ሐዋርያት
ጾመ ሐዋርያት ሀብተ መንፈስ ቅዱስን ከተቀበሉ በኋላ ወንጌልን ለሕዝብ ከማስተማራቸው አስቀድመው ጾመዋል፡፡ የሰኔ ጾም ይባላል፡፡ ይህ ጾም ከፍና ዝቅ ስለሚል የተወሰነ ቀን የለውም አንዳንድ ጊዜ ከአርባ ይበልጣል ሌላ ጊዜ ደግሞ ከሰላሳ ያንሳል፡፡

#ጾመ_ነብያት
ለአዳም የተሰጠው ተስፋ ይጠብቁ የነበሩ ነብያት የጾሙት ነው፡፡ ነብያት ስለመሲህ መምጣት በናፍቆት ይጸልዩ ነበር፡፡

#ጾመ_ፍልሰታ
ጾመ ማርያም ይባላል፡፡ የእመቤታችን የዕረፍት፣ ትንሳኤና ዕርገት ምስጢር ለሐዋርይት የተገለጠበት ታሪክ መታሰቢያ ጾም ነው፡፡
ሐዋርያት ከሐምሌ 1-14 ድረስ ጾመው ድንግል ማርያም ተገልጣላቸዋለች በ 16ኛው ቀን አርጋለች፡፡

#ጾመ_ገሃድ
ገሃድ ማለት ግልጥ ይፋ፣ በገሃድ የሚታይ ማለት ነው፡፡ መለኮት የተገለጠበት ጌታ ልዩ የሆነ የአንድነትና የሶስትነት ምስጢር የተገለጠበት ስለሆነ ይህን ስያሜ አግኝቷል፡፡ ማቴ 3፡16  ዮሐ 1፡29

#ጾመ_ሰብአ_ነነዌ
ይህ የነነዌ ሰዎች የጾሙት ነው፡፡ የዚያች አገር ሰዎች የፈጸሙት በደል በእግዚአብሄር ፊት ታላቅ ሆኖ በመገኘቱ ቅጣት ታዝዞባቸው ነበር፡፡ የነነዌ ጾም  ሰኞ፣ ማክሰኞ እና ዕረቡ  ሶስት ቀን ነው፡፡

#ጾመ_ድህነት (የዕረቡና የአርብ)
ከትንሳኤ በኋላ ከሚኖሩት 50 ቀኖች በቀር ዕረቡና አርብ ዓመቱን በሙሉ የጾም ቀኖች ናቸው፡፡ እንደጾሙአቸው የተደረገው አርብ እና ዕሮብ፤ ዕሮብ የተፈረደበት አርብ የተሰቀለበት ቀን መሆኑን አስመልክቶ ነው፡፡

፪. #የግል_ጾም
በሕግ የታወቁ አጽዋማት በግልጥ በማህበር ይጾማሉ፡፡ የግል ጾም ግን ከዚህ የተለየ ነው፡፡ በሰዎች የግል ፍላጎትና የሕሊና ውሳኔ ሚጾም የፈቃድና የንስሐ ጾም ነው፡፡ ማቴ 5፡6 ማቴ 6፡18 
በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን፡፡
❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️
    ከእናንተ የመጣ ጥያቄ
     አርብ እና ዕሮብ ለምን እንፆማለን?
       መልስ ✅
ዕሮብን የምንፆምበት ምክንያት ሊቃነ ካህናት ጌታችንን ለመያዝ የተነጋገሩበት ዕለት / ምክረ አይሁድ /ስለሆነ ነው
አርብን የምንፆመው ደግሞ ጌታችንና አምላካችን እየሱስ ክርስቶስ በመስቀል ተሰቅሎ ዓለምን እኛን ያዳነበት ቀን ስለሆነ እንፆማለን ማለት ነው።
 

   ዲ/ን ፍቅረአብ ወ/ሀና

ጥያቄ ለመጠየቅ ከፈለጉ👇
        👉  @fikreabe ይላኩልን


❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️
https://t.me/yetewahedofera
💙💙💙💙💙💙💙💙

አገልግሎቱን መደገፍ መርዳት ለምትፈልጉ ሃሳብ አስተያየት ጥያቄ ካላችሁ  በዚህ በኩል ያናግሩን!
👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇
👉👉 @Fikreabe 👈👈👈👆👆👆👆👆👆👆👆👆👆


በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን፡፡
❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️
    ከእናንተ የመጣ ጥያቄ
     አርብ እና ዕሮብ ለምን እንፆማለን?
       መልስ ✅
ዕሮብን የምንፆምበት ምክንያት ሊቃነ ካህናት ጌታችንን ለመያዝ የተነጋገሩበት ዕለት / ምክረ አይሁድ /ስለሆነ ነው
አርብን የምንፆመው ደግሞ ጌታችንና አምላካችን እየሱስ ክርስቶስ በመስቀል ተሰቅሎ ዓለምን እኛን ያዳነበት ቀን ስለሆነ እንፆማለን ማለት ነው።
 

   ዲ/ን ፍቅረአብ ወ/ሀና

ጥያቄ ለመጠየቅ ከፈለጉ👇
        👉  @fikreabe ይላኩልን


❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️
https://t.me/yetewahedofera
💙💙💙💙💙💙💙💙

አገልግሎቱን መደገፍ መርዳት ለምትፈልጉ ሃሳብ አስተያየት ጥያቄ ካላችሁ  በዚህ በኩል ያናግሩን!
👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇
👉👉 @Fikreabe 👈👈👈👆👆👆👆👆👆👆👆👆👆






🕊

† እንኳን ለታላቁ ክርስቲያናዊ ንጉሥ ቅዱስ ቆስጠንጢኖስ ዓመታዊ የዕረፍት በዓል በሰላም አደረሳችሁ ፤ አደረሰን። †

† በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን! †

🕊  †   ቅዱስ ቆስጠንጢኖስ    †    🕊

† ቅዱስ ቆስጠንጢኖስ ለቤተ ክርስቲያን የፈፀመውን መልካም ተግባር ያሕል መሥራት የቻለ ንጉሥ በሐዲስ ኪዳን የለም:: ጻድቁ ንጉሥ ከቅድስት እናቱ እሌኒና ከአረማዊ አባቱ ቁንስጣ በበራንጥያ ተወለደ::

ዘመኑ ዘመነ ዐጸባ [የመከራ ጊዜ] ወይም የሰማዕታት ዘመን በመሆኑ ክርስቲያኖች በግፍ የሚጨፈጨፉበት ወቅት ነበር:: ክርስቲያኖችን ከምድረ ገፅ ለማጥፋት በተደረገው የ፵ [40] ዓመታት ዘመቻ አብያተ መቃድስና መጻሕፍት ተቃጠሉ:: ብዙዎቹ በየበርሃው ተሰደዱ:: ሚሊየኖች በግፍ አለቁ::

የዚሕን ዘመን መከራ በውል ያልተረዳ ሰው ቅዱስ ቆስጠንጢኖስን ሊያከብር አይችልም:: ምክንያቱም ይህን የመከራ ዘመን በፈቃደ እግዚአብሔር አስቁሞ : ቀርነ ሃይማኖት የቆመው : ብዙ ሥርዓት የተሠራው : ቤተ ክርስቲያንም ያበራችው በዘመኑ ነውና::

ቅዱሱ ንጉሥ ለሁሉም ነቢያት : ሐዋርያትና ሰማዕታት አብያተ ክርስቲያናትን ራሱ በመሠረታት በቁስጥንጥንያ አንጿል:: በዘመኑ ቤተ ክርስቲያን በሰላም ኖራለት : በኃይለ መስቀሉ ጠላት ጠፍቶለት ኑሮ በዚህች ቀን አርፏል:: "ቆስጠንጢኖስ" ማለት "ሐመልማል" ማለት ነው::

††† ዳግመኛ በዚሕ ቀን የዓለማት ፈጣሪ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ስለ እኛ በሆነው ሞቱ በመቃብር ውስጥ አድሯል::

††† ጌትነት ያለው አምላካችን በይቅርታው ይጐብኘን:: መልካም መሪንም ይስጠን::

🕊

† መጋቢት ፳፰ [28] ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት

፩. ታላቁ ቅዱስ ቆስጠንጢኖስ (ጻድቅ ንጉሥ)
፪. ቅድስት እሌኒ ንግስት

† ወርኀዊ በዓላት

፩. አማኑኤል ቸር አምላካችን
፪. ቅዱሳን አበው [አብርሃም: ይስሐቅና ያዕቆብ]
፫. ቅዱስ እንድራኒቆስና ሚስቱ ቅድስት አትናስያ
፬. ቅድስት ዓመተ ክርስቶስ
፭. ቅዱስ ቴዎድሮስ ሮማዊ [ሰማዕት]

† "እንግዲህ እግዚአብሔርን በመምሰልና በጭምትነት ሁሉ: ጸጥና ዝግ ብለን እንድንኖር: ልመናና ጸሎት: ምልጃም: ምስጋናም ስለ ሰዎች ሁሉ: ስለ ነገሥታትና መኳንንትም ሁሉ እንዲደረጉ ከሁሉ በፊት እመክራለሁ:: ሰዎች ሁሉ ሊድኑና እውነቱን ወደ ማወቅ ሊደርሱ በሚወድ በእግዚአብሔር በመድኃኒታችን ፊት መልካምና ደስ የሚያሰኝ ይህ ነው::" † [፩ጢሞ. ፪፥፩-፬

† ወስብሐት ለእግዚአብሔር †
† ወለወላዲቱ ድንግል †
† ወለመስቀሉ ክቡር †

[ ዲ/ን ዮርዳኖስ አበበ  ]

         †              †               †
▬▬▬▬▬ ▬▬▬ ▬▬▬▬▬
💖                   🕊                    💖


ሰላም እደሩ ❤️❤️
ዲ/ን ፍቅረአብ ወ/ሀና


""አንድነታችንን አንተው"" ዕብ መልዕክት 10:25
ይህ ግሩፕ ላይ አድ በማድረግ ተባበሩን
https://t.me/workamu_tewlde

እንኳን ደና መጣችሁ
"ሁለት ወይም ሦስት በስሜ
በሚሰበሰቡበት በዚያ በመካከላቸው እሆናለሁ"(የሉቃስ ወንጌል ፮፥፵፷)

የተለያዩ መንፈሳዊ ጥያቄና መልሶችን፣
ኪነ ጥበብ፣ ዝክረ ቅዱሳን፣ኦርቶዶክሳዊ አስተምሮዎች፣ የእመቤታችን ታሪክ
እና ዝማሬዎችን  እያነሳሳን እናመሰግናለን እንወያያለን

ሁላችሁም ተሳታፊ እንድትሆኑ
እናም የኦርቶዶክስ ተዋህዶ
ልጆችን አድ ይህንን መልዕክት ሼር እንድታረጉ
በእግዚአብሔር ሰም እንጠይቃለን
https://t.me/workamu_tewlde
https://t.me/workamu_tewlde


 
❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️
       በዲ/ን ፍቅረአብ ወ/ሀና

ጥያቄ ለመጠየቅ ከፈለጉ👇
        👉  @fikreabe ይላኩልን

ሼር ሼር ይደረግ
❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️
https://t.me/yetewahedofera
💙💙💙💙💙💙💙💙

አገልግሎቱን መደገፍ መርዳት ለምትፈልጉ ሃሳብ አስተያየት ጥያቄ ካላችሁ  በዚህ በኩል ያናግሩን!
👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇
👉👉 @Fikreabe 👈👈👈👆👆👆👆👆👆👆👆👆👆


በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስቅዱስ አሀዱ አምላክ አሜን

ሴት በወር አበባ ጊዜ መጸለይ ትችላለች?

            👉በወር አበባ ጊዜ የሚከለከልስ ጸሎት አለ?

👉ተወዳጆች ሆይ ሴት ልጅ በሱባኤ ወቅት የወር አበባ/ደመ ፅጌ/ ቢታያት ከሱባኤ የመውጣትና የመቆየቷ ነገር እንደ ገዳሙ ሥርዓት ይወሰናል፡፡ ከሱባኤ ትወጣለች ማለት ሱባኤን (አርምሞን) ትፈታለች፣ተአቅቦዋን ትተዋለች ማለት ሳይሆን እስከምትነፃ ድረስ ገዳሙ ባዘጋጀው ቦታ ቆይታ መጨረስ ትችላለች፡፡ በሱባኤው አጋማሽ ላይ ወይንም መውጫው ሲቃረብ የወር አበባ ቢታያት ሱባኤውን ማቋረጥ ሳይሆን በጊዜያዊ ቦታ መጨረስ ይገባታል፡፡
ብዙዎች እህቶቻችን ሱባኤ የምንይዙት በድንገት ነው፡፡
👉ይህ ችግር እንዳይገጥማችሁ ሱባኤ ከመግባታችሁ በፊት ቀናችሁን ቆጥራችሁ አስተካክላችሁ ብትይዙ የበለጠ ትጠቀማላችሁ፡፡ ሰይጣን ያለጊዜው በወር አበባ ሊፈትናችሁ ስለሚችል ቀናችሁን እንደጨረሳችሁ ሱባኤ ብትይዙ ይመረጣል፡፡ በተለይ ዓይነ ጥላ ከዓይነ ጥላም ገርግር ዓይነ ጥላ ያለባቸውና መተት እና ድግምት የተደገመባቸው እህቶቻችን ያለ ጊዜና ያለ ቀኑ በሚመጣ የወረር አበባ በሱባኤ ወቅት ይፈተናሉ፡፡ ምስጋና ለእመቤታችን ይሁንና እመቤታችን ንፁህ አይደላችሁም በማለት ጸሎታችሁን ቸል ስለመትል የያዛችሁትን ሱባኤ ቀጥሉ፡፡ ምክንያቱም የእኛ ርኩሰት የእመቤታችንን ንፅህና ስለማያሳድፍ ጸሎታችንን ትሰማናለች፡፡

👉ጸሎት ከፈጣሪ የምንገናኝበት መንገድ ስለሆነ እግዚአብሔር ጊዜን እየጠበቀ በዚህ ጊዜ እሰማችኋለሁ በዚህን ጊዜ አልሰማችሁም አይልም፡፡ በወር አበባ ጊዜ አይጸልይም ማለት የቤተ-ክርስትያን አስተምህሮ ሳይሆን የሰነፉ ሰይጣን የተንኮል እና የእንቅፋት ስብከት ነው፡፡ የሰይጣንን እንኳን ጸሎት ትተን ቀርቶ እየጸለይን ፈተናችንን እኛና እግዚአብሔር ነው የምናውቀው፡፡ ቅዱስ ጳውሎስ በዘመኑ እንደ እኛ ግራ ለተጋቡት የተሰሎንቄ ምእመናን "ሳታቋርጡ ፀልዩ" በማለት ፀሎት በየትኛውም ሁኔታ እና አጋጣሚ ማቋረጥ እንደሌለባቸው ፅፎላቸዋል።
👉/1ኛ ተሰሎ 5÷18/
ወዳጆቼ ፀሎትን የለመደች ሴት በወር አበባዋ ምክንያት ለሰባት ቀን ፀሎትዋን ብታቋርጥ ስንፍናን ትለምዳለች፡ትዘናጋለች አጋንንቱም በዚህ አጋጣሚ ፈተናዋን ያበዛል።

ሴት በወር አበባዋ ጊዜ እስከ መንጻቷ ቤተ-ክርስትያን ነው መግባት የማትችለው እንጂ፣ ጸሎት ማቋረጥ የለባትም፡፡ ጊዜን ተብቆ አለመጸለይ ለሰይጣን በር መክፈት ነውና ትንሿን ጸሎታችንን ማቋረጥ የለብንም፡፡
👉እኛ በወር አበበ ጊዜ ንፁህ አይደለንም ብለን ሥጋዊ ምግብ እንደማንተው ሁሉ ጸሎት የነፍስ ምግብ ነውና ነፍሳችን ለ7 /ሰባት/ ቀን ከውዳሴ ማርያም ፣ ከሰኔ ጎለጎታ ፣ከአርጋኖን፣ከሰይፈ ሥላሴ፣ከሰይፈ መለኮት እና ከተለያዩ የጸሎት ማዕድ እየከለከልን ሕያዊት ነፍሳችንን ማስራብ የለብንም፡፡ ይልቁንም ዘወትር በመጸለይ ነፍሳችንን መመገብ ይገባናል፡፡

ተወዳጆች ሆይ ጌታችን ደመኛን እንጂ ደምን አይጠየፍም አይጠላም፡፡ ቢጠየፍማ ለአሥራ ሁለት ዓመት ሰውነቷ በደም ሲጨቀይባት የነበረችውን ምስኪን ሴት መለኮት ጋ ጠጋ ብላ ልብሱን ነክታ ልትድን ቀርቶ መርገምንና ሌላ በሽታን ሸምታ በተቀሰፈች ነበር፡፡ ጌታችን ግን መልካም አመጣጧን ፣ የዓመታት ጭንቀቷን ተመልክቶ ከነደሟ ተቀብሎ በልቧ የነበረውን አውቆ ፣ የደሟን ምንጭ አድርቆ፣ እምነቷን አድንቆ፣ ከጤናዋ ጋር በሰላም ወደ ቤቷ መልሷታል፡፡ /ማቴ. 9፣18-26, ማር. 5፣21-43, ሉቃ. 8፤41 ይመልከቱ/
ወለላይቱ የእመብርሃን ልጆች የእመቤታችንን ባህርይ አላወቅንም እንጂ፤ እርሷ ጥዩፍነት ከቶ በባህሪዋ የለም፡፡
👉የዛሬውን አያድርገውና ሁላችንም ስንወለድ እናቶቻችን በምጥ ሰዓት ከነደማቸው በጸሎትና በጭንቀት ጠርተዋት አወዋልዳቸዋለች፤ አሁንም ታዋልዳቸዋለች፡፡ በአራስራቸው ጊዜ ከእነሱ አትለይም፣ እስከ ስሙም ‹የማርያም አራስ› ተብለው በስም ይጠራሉ፡፡
አንዳንዶቹ እንኳን ሊጸለይ ቀርቶ የጸሎት መፅሐፍ አይነካም እያሉ እህቶቻችንን የሚያሳቅቁ አሉ፡፡ እባካችሁ ሰው ከምታሳቅቁ እወቁ፣ ጠይቁ፣ ጠንቅቁ፣ ያለበለዚያ ለእህቶቻችን ፈተና አትሁኑ፡፡ ባይሆን ጥሩ ስሜትና መንፈስ ካልተሰማችሁ ሰውነታችሁን መታጠብ፣አንቀጸ ሥጋችሁን/የከበረውን ቦታ/ 👉ብቻ በመታጠብ ጸሎታችሁን መቀጠል ትችላላችሁ፡፡ ምናልባት የስንፍና ምክር ሰምታችሁ ካልሆነ በስተቀር ከወር ወር ጸሎት የምናስተጓጉልበት፣የምትተዉበት ምክንያት የለም፡

ሌሎች በወር አበባ ጊዜ አይጾምም ይላሉ፣ ከየት እንዳገኙት ባይገባኝም ይህች በወር አበባ አመካኝቶ፣ለመብላት አንኩቶ ይመስለኛል፡፡ በወር አበባ ጊዜ አንዳንድ እህቶቻችን ከፍተኛ የሕመምና የስቃይ ስሜት የሚሰማቸው ብሎም እስከ ሕክምና የሚያደርሳቸው ከሆነ ምናልባት መድሃኒት ሊወስዱ ስለሚችሉ እነርሱን አይመለከትም፡፡

👉እኛ የምንረክሰው በወር አበባ ጊዜ ሳይሆን ኃጢአት በመሥራት ሥጋችንንም ነፍሳችንንም ስናደማ ነው፡፡ ያኔ በሁሉም እንረክሳለን፡፡ ጸሎታችን በእግዚአብሔር እና በእመቤታችን ፊት ስለማረጉ መመዘኛው የወር አበባ ሳይሆን የልባችን ንጽህና፣መልካምነታችን፣ቅንነታችን፣ታማኝነታችን፣እምነታችን፣መታዘዛችን ነው፡፡ በተለይ አዲስ መንፈሳዊ ሕይወት ጀማሪዎች፣ ቤተክርስትያን ሳሚዎችና አስቀዳሾች ፣ ገዳማት ተመላላሾች ስንሆን የቤተክርስትያን ሥርዓት ያወቅን፣ ያስጠበቅን እየመሰለን በወር አበባ ጊዜ እንደማይጸለይ እንደማስተማር እያደረገን ለመንፈሳዊ እህቶቻችን ማሰናከያ በመሆን የጸሎት ሥርዓት እናፋልሳለን፡፡ በዚህም የሰይጣን ስፓንሰር እንሆናለን፡፡

ተወዳጆች ሆይ ለአብነት በአዲስ አበባ ያሉትን እንጦጦ ማርያምና አራዳ ጊዮርጊስን ብንመለከት ሁለት ግቢ አላቸው፡፡ ለምን እንደዚያ የተሠሩ ይመስላችኋል?
👉ባለ ሁለት ግቢ የሆነበት ምክንያት ሴተችና ወንዶች ንፁህ በማይሆኑበት ፣ የሥጋ ድቀት በሚያገኛቸው ጊዜና በጋብቻ ተወስነው ሕጋዊ ሩካቤ ሲገጽሙ በእነዚህ ምክንያት ከቤተ-ክርስትያን ደጅ እንዳይርቁና ኪዳን፣ቅዳሴ ጸሎት እንዲያደርሱበት ነው፡፡ ይህም የሚከናወነው በመጀመሪያው (በአንደኛው) ግቢ በመሆን ነው፡፡

አንደኛው ጊቢ የመንጻት ጊዜያቸው እስከሚያልፍ ድረስ እንዲጸልዮበትና እንዲያስቀድሱበት፣ እንዲማሩባቸው ከዚያም ግዳጃቸውን ሰጨርሱ ወደ ሁለተኛው ወይም ወደ ቤተክርስትያኑ ግቢ መግባት እንዲችሉ እንጂ ለሌላ የተሠሩ አይደሉም፡፡
👉አባቶቻችን ለተፈጥሮ ግዳጅ እንደዚህ ተጨንቀው ምዕመናን ከቤተክርስትያን ሳይርቁ እንዲገለግሉ ሥርዓት ሲሠሩ እኛ አዋቂዎች (አዋኪዎች) ትልቅ እንቅፋት እንሆናለን፡፡
ወዳጆቼ ቤተ-ክርስትያናችን ከሠራችልንና ከደነገገችልን የግል ጸሎቶች ውስጥ በወር አበባ ጊዜ ይሄ አይጸለይም ይህ የተከለከለ ብላ አላስተማረችንም፡፡
👉ስለዚህ ያስለመድናቸውን ጸሎቶች ሁሉ መጸለይ እንችላለን፡፡ እራሳችሁን ከኃጢአት እንጂ ከጸሎት አታርቁ፡፡ አንደበታችሁን ከሐሜት እንጂ ከጸሎት አታርቁ፡፡ ሥራችሁን ከወር አበባ አንጽታችሁ፣በልባችሁ ማህደር ቂም እና ክፋት ቋጥራችሁ ብትጸልዩ ምን ዋጋ አለው? ከአንድ ሳምንት ከመርገም ጨርቅ ይልቅ በኃጢአት፣በሐሜት፣በክፋት ከሚጨማለቅ ሰውነት የሚቀርብ ጸሎት ከደመና በታች ነው፡፡ የወር አበባ በአንድ ሳምንት ይነጻል፡፡
ግን ከሰውነታችን አልነጻ ያሉን ስንት ኃጢአቶች አሉ፡፡
ስለዚህ ንጹህም ሆንን አልሆንን በርትተን ተግተን ልንጸልይ ይገባል፡፡

በቀጣይ ክፍል ሴጋ/ማስተርቤሽን የፈጸመ ሰው ተክሊል መፈጸም ይችላል?
የሚለውን እንመለከታለን።

https://t.me/yetewahedofera


መልሱን አቆየሁት አደል ጠብቁኝ


ለግጥሙ አስታያየት ስጡኝ


በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን፡፡
❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️
       በእንተ ዕለተ ስቅለት
          እንጉርጉሮ
  በዲ/ን ፍቅረአብ ወ/ሀና

ጥያቄ ለመጠየቅ ከፈለጉ👇
        👉  @fikreabe ይላኩልን

ሼር ሼር ይደረግ
❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️
https://t.me/yetewahedofera
💙💙💙💙💙💙💙💙

አገልግሎቱን መደገፍ መርዳት ለምትፈልጉ ሃሳብ አስተያየት ጥያቄ ካላችሁ  በዚህ በኩል ያናግሩን!
👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇
👉👉 @Fikreabe 👈👈👈👆👆👆👆👆👆👆👆👆👆


#የሙሐመድን_ነቢይነት #የማልቀበልባቸው_12_ምክንያቶች

የመጨረሻው ክፍል

12.
#በድግምት_ቁጥጥር_ስር_መውደቁ


አይሻ እንደዘገበችው ላቢድ ቢን አል-አስማ የተባለ ሰው በሙሐመድ ላይ ድግምት በመሥራቱ ሳብያ ሙሐመድ ሚስቶቹ በሌሉበት ከሚስቶቹ ጋር እየተኛ እንደሆነ ይመስለው ነበር፡፡ እንኳንስ በእግዚአብሔር ነቢይ ላይ ይቅርና በእግዚአብሔር በእውነት ባመነ በማንኛውም ሰው ላይ አስማት እንዴት ሊሠራ ይችላል? የበለአም አስማት እንኳንስ በሙሴ ላይ ሊሠራ ይቅርና በሙሴ ከሚመራው ህዝብ መካከል በአንዱ ላይ እንኳ ሊሠራ አልቻለም፡፡ ይልቅስ ይህንን የተረዳው አስማተኛው በለአም “በያዕቆብ ላይ አስማት የለም በእስራኤልም ላይ ሟርት የለም” በማለት መስክሯል (ዘኁልቁ 23፡23)፡፡

በአዲስ ኪዳን ውስጥ ደግሞ ጌታ ኢየሱስ የአጋንንት ኃይል በስሙ ባመኑት ሰዎች ላይ እንደማይሠራና ይልቁኑ በስሙ አጋንንትን ከሰዎች ውስጥ እንዳሚያስወጡ ተናግሯል፡፡ ይህ ተስፋ በሐዋሪያት ዘመን ሲሠራ ነበር፡፡ ዛሬም ቢሆን እየሠራ እንደሆነ ማንም አይቶ መመስከር ይችላል (ማርቆስ 16፡17-18)፡፡

https://t.me/yetewahedofera




Видео недоступно для предпросмотра
Смотреть в Telegram
              †               


" ቃል ስጋ ሆነ " [ ዮሐ.፩፥፲፬ ]


" በቅዱሳን ላይ የሚያድር እግዚአብሔር እኛን ለማዳን ልዩ ከሆነች ድንግል ማርያም ሰው ሆኗልና ኑ ይህን ድንቅ እዩ። ስለተገለጠልንም ምሥጢር ምስጋና አቅርቡ።

ሰው የማይሆን ሰው ሆኖዋልና : ቃል ተዋሕዷልና። ጥንት የሌለው ጥንታዊ ቀዳማይ ሆነ : ዘመን የማይቆጠርለት [መለኮት] ዘመን ተቆጠረለት። የማይታወቅ ተገለጠ : የማይታይ ታየ። የሕያው እግዚአብሔር ልጅ በእርግጥ ሰው ሆነ።

ትላንት የነበረው ዛሬም ያለው መቼም የሚኖር ኢየሱስ ክርስቶስ እንሰግድለትና እናመሰግነው ዘንድ አንድ ባሕርይ ነው። ቅድስት ሆይ ለምኝልን። "

[ ውዳሴ ማርያም ዘረቡዕ ]

         †              †               †
▬▬▬▬ ▬▬▬▬▬ ▬▬▬▬


በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን፡፡
❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️
      የዕለቱ ጥያቄ 5
    
 1 ሴት በወር አበባ ጊዜ መፀለይ ትችላለች?
2 በወር አበባ ጊዜ የሚከለከል ፁሎት አለ?     
3 በሱባኤ ወቅት ቢገጥማትስ?

   ዲ/ን ፍቅረአብ ወ/ሀና

ጥያቄ ለመጠየቅ ከፈለጉ👇
        👉  @fikreabe ይላኩልን


❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️
https://t.me/yetewahedofera
💙💙💙💙💙💙💙💙

አገልግሎቱን መደገፍ መርዳት ለምትፈልጉ ሃሳብ አስተያየት ጥያቄ ካላችሁ  በዚህ በኩል ያናግሩን!
👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇
👉👉 @Fikreabe 👈👈👈👆👆👆👆👆👆👆👆👆👆


+  በርባን ይፈታልን +

ሕዝቡ ‹በርባን ይፈታልን! ክርስቶስ ግን ይሰቀል!› ማለታቸውን ስንሰማ መቼም ሁላችንም ማዘናችንና ‹ምን ዓይነት ክፉዎች ናቸው?!› ብለን መውቀሳችን አይቀርም፡፡ ወዳጄ ሆይ! እባክህን እስቲ አይሁድንና ጲላጦስ ለአፍታ እንተዋቸው! አንተ ብትሆን ኖሮ ከጌታና ከበርባን ማናቸውን ትፈታለህ? የእስክንድርያው ትምህርት ቤት ዲን የነበረው ሊቅ ‹‹በሥጋው ክፉ ነገርን የሚሠራ ሁሉ በርባንን ፈትቶ ክርስቶስን አሰረው ፤ መልካም ነገርን የሚያደርግ ደግሞ ክርስቶስን ፈትቶ በርባንን አስሮታል›› ይላል፡፡

ወዳጄ ሆይ! አንተ በሰውነትህ ላይ ፈትተህ የለቀቅከው ማንን ነው? በርባንን ነው ወይንስ ጌታን ነው? በርባንን ፈትተኸው ከሆነ ዛሬውኑ በንስሓ ተመልሰህ ፈጣሪህን በሰውነትህ ውስጥ አክብረው፡፡ ‹በርባንን የፈታሁት እኮ ወድጄ አይደለም! ሁኔታዎች አስገድደውኝ ነው› ብለህ እንደ ጲላጦስ ለራስህ ይቅርታ ማድረግና እጅህን መታጠብ አይበጅህም፡፡ ይልቅስ አሁኑኑ ጌታህን ፈትተህ በርባንን የተባለ ኃጢአትን ስቀለው! ያን ጊዜ የክርስቶስ መሆንህ ይታወቃል፡፡ ‹‹የክርስቶስ ኢየሱስ የሆኑቱ ሥጋን ከክፉ መሻቱና ምኞቱ ጋር ሰቀሉ›› ተብሎ ተጽፎአልና፡፡ (ገላ. ፭፥፳፬)  

ሕዝቡ ‹በርባን ይፈታ› ብለው ቢጮኹም ሁሉም ለበርባን ፍቅር አላቸው ማለት አይደለም፡፡ ሊቃነ ካህናቱ ባያባብሏቸው ኖሮ በዚያች ዕለት ሊያስፈቱት የሚፈልጉት ሌላ እስረኛ ዘመድ ያላቸውም ሰዎች መኖራቸው አይቀሬ ነው፡፡ ሆኖም ሊቃነ ካህናቱ ለጌታችን ካላቸው ጥላቻ የተነሣ ሕዝቡን ተለማምጠው በርባን እንዲፈታ አስደረጉ፡፡ ዛሬ በርባንን አግኝተን ‹በርባን ሆይ ማን ነው ያስፈታህ?› ብለን ብንጠይቀው ምናልባትም ‹የሰው መውደድ ይሥጥ ማለት ነው! የሚወደኝ ሕዝብ ነዋ ጮኾ ያስፈታኝ!› ማለቱ የማይቀር ነው፡፡ ሆኖም ሊቃነ ካህናቱና ተከታዮቻቸው ግን ‹በርባን ይፈታ› ብለው የጮኹት ለበርባን ፍቅር ኖሯቸው ሳይሆን በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ላይ በነበራቸው ጥላቻ ምክንያት ነው፡፡ ስለዚህ በርባንን ከሞት ፍርድ አድኖ ያስፈታው ሕዝቡ ሳይሆን ጌታችን ነበር፡፡

ጌታችን በዚያች ዕለት የበርባንን ሞት ወስዶ የእርሱን ሕይወት ለበርባን ሠጠው ፤ የበርባንን ሰንሰለት አስፈትቶ እርሱ ታሰረ ፤ ከበርባን ጓደኞች ጋር በርባን ሊሰቀል በነበረበት ቦታም ተሰቀለ፡፡ ወዳጄ ሆይ! ልብ ብለህ ከተረዳኸው በርባን እኮ አንተው ነህ! ለበርባን ከተደረገለት ለአንተ ያልተደረገ ነገር ካለ እስቲ ንገረኝ! እንደ በርባን ክርስቶስ ሞትህን ወስዶ ሕይወቱን ፣ እስራትህን ወስዶ ነጻነትን አልሠጠህምን?
ይህንን ያደረገውም ለአንተ ብቻ ሳይሆን ለአዳም ልጅ ሁሉ ነው ፡- ‹‹የእስረኛው በርባን (ወልደ አባ) መፈታቱ አምላካዊ ምሥጢርን የሚያስታውስ ነው፡፡ በኃጢአቱ ምክንያት በሲኦል ውስጥ ታሥሮ የነበረው አዳምን በአዳኙ መሰቀል ምክንያት መድኃኒት አግኝቶ ነጻ መውጣቱን ያስታውሳል›› / ‹‹እስመ ተፈትሕዎቱ ለወልደ አባ ሙቁሕ ያዜክር ምሥጢራተ አምላካዊ ያሌቡ ግዕዛነ አዳም ዘኮነ ሙቁሐ ውስተ ሲኦል በእንተ ኃጢአቱ ወረከበ መድኃኒተ በስቅለተ መድኅን›› እንዲል፡፡ 

በዚያች የዕለተ ዓርብ ረፋድ ላይ ያስፈታውን የማያውቀው ይህ ወንበዴ ሰንሰለቱ ተፈትቶ ወደ ቤቱ ሲሔድ ጌታችን ግን ለመከራና ለመስቀል ተሠጠ፡፡ እውነቱንስ ለመናገር እኛ ክርስቲያኖች በርባን በመፈታቱ ላይ ላዩን ብናዝንም ውስጥ ውስጡን ግን ደስ ብሎናል!

‹‹…በርባን ቢሰቀል ኢየሱስ ቀርቶ
ምን ይጠቅመናል ሽፍታ ሞቶ
እንኳን ኢየሱስን ሰቀሉት
የሞቱን መድኃኒት …››
ብለው መሪጌታ ፍቅሩ ሣህሉ በበገናቸው ጨርሰውታል፡፡

(ሕማማት ከሚለው መጽሐፍ ለመድኃኔ ዓለም የስቅለቱ መታሰቢያ የተወሰደ)
የተዋህዶ ልጆች በቴሌግራም መንፈሳዊ ትምህርቶችን ለመከታተል የቴሌግራም ቻናላችን ቤተሰብ ይሁኑ!
ጠላትን በጋራ ከእግዚአብሔር ጋር ድል እናደርገው ዘንድ እናንተም የቴሌግራም ቻናላችንን ተቀላቀሉ
እምዬ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ለዘላለም ትኑር 🙏🙏🙏 ❤❤❤

ለኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ልጆች👇
                •➢ ሼር // SHARE
https://t.me/yetewahedofera
https://t.me/yetewahedofera
https://t.me/yetewahedofera
.    🔸          🔸
🔸🔹🔸 🔸🔹🔸
     🔸          🔸
     🔸                       






🕊

ሕማማተ እግዚእነ በልሳነ አበው [ የጌታችን መከራ በሊቃውንት አንደበት ]


የእስክንድርያው ሊቀ ጳጳሳት ቅዱስ ቄርሎስ እንዲህ አለ ፦

" ታመመ ፤ ሞትን ከተቀበለበት ከሥጋ ተዋሕዶ በመስቀል ላይ በፈቃዱ ለሥጋውያን ሞተ ፣ ባሕርየ መለኮት ሥጋን ተዋሕዶ በማኅፀን ካደረ ጀምሮ ሥጋ ገንዘቡ እንደመሆኑ በሥጋ ይኸንን ሥርዓት ፈጸመ፡፡ ለማይመረመር ለመለኮቱ ባሕርይ እንደሚገባ ደግሞ እርሱ ኅብስት አበርክቶ ሁሉን ያጠግባል፡፡ አይራብም ፣ አይጠማም ፣ አይደክምም ፣ አያንቀላፋም ፣ አይታመምም፣ አይሞትም ሕይወትን ለሁሉ ይሰጣል፡፡ ዳግመኛ በዚያ በሲኦል ተገዝተው ያሉ ነፍሳትን ያድን ዘንድ በአካለ ነፍስ ወደ ሲኦል ወረደ በመለኮቱም ሲኦልን በዘበዘ፡፡"


የአንጾኪያው ሊቀ ጳጳስ ቅዱስ ዲዮናስዮስ ከላከው ሲኖዶሳዊ መልእክት የተገኘ ፦

" እርሱ መቼም መች ከመለኮቱ ሳይለይ የሰውነትን ሥራ ሁሉ ገንዘቡ አደረገ፡፡ ይኸውም መራብ፣ መጠማት ፣ መንገድ በመሔድ መድከም፣ በመስቀል ላይ መሰቀል ፣ በብረት ችንካር መቸንከር ነው፡፡ በሰውነቱ መቸም መች ሰው ነው ፣ በአምላክነቱም ሰውን የፈጠረ ነው፡፡ ግን ከማይከፈል ተዋሕዶ በኋላ መከፈል የለበትም፡፡ ሰው እንደ መሆኑ ስለ እኛ የታመመው የሞተው እርሱ ነው፡፡ በመለኮቱ ግን መቸም መች አይታመምም አይሞትም ፣ ሕማምንና ሞትንም አይቀበልም፡፡ በሞቱ ሞትን ያጠፋው እርሱ ነው፡፡ ሲኦልንም የበዘበዘው እርሱ ነው፡፡"

🕊

በእንተ ማርያም ወላዲትከ ፤
ወበእንተ ዮሐንስ መጥምቅከ ፤
ወበእንተ ኲሎሙ ቅዱሳኒከ ፤
ርድአነ ወትረ በኃይለ መስቀልከ ፤
ኢታስተኃፍረነ እግዚኦ በቅድሜከ።

እንኳን አደረሳችሁ !

†                     †                        †
💖                    🕊                     💖

Показано 20 последних публикаций.

454

подписчиков
Статистика канала