+ በርባን ይፈታልን +
ሕዝቡ ‹በርባን ይፈታልን! ክርስቶስ ግን ይሰቀል!› ማለታቸውን ስንሰማ መቼም ሁላችንም ማዘናችንና ‹ምን ዓይነት ክፉዎች ናቸው?!› ብለን መውቀሳችን አይቀርም፡፡ ወዳጄ ሆይ! እባክህን እስቲ አይሁድንና ጲላጦስ ለአፍታ እንተዋቸው! አንተ ብትሆን ኖሮ ከጌታና ከበርባን ማናቸውን ትፈታለህ? የእስክንድርያው ትምህርት ቤት ዲን የነበረው ሊቅ ‹‹በሥጋው ክፉ ነገርን የሚሠራ ሁሉ በርባንን ፈትቶ ክርስቶስን አሰረው ፤ መልካም ነገርን የሚያደርግ ደግሞ ክርስቶስን ፈትቶ በርባንን አስሮታል›› ይላል፡፡
ወዳጄ ሆይ! አንተ በሰውነትህ ላይ ፈትተህ የለቀቅከው ማንን ነው? በርባንን ነው ወይንስ ጌታን ነው? በርባንን ፈትተኸው ከሆነ ዛሬውኑ በንስሓ ተመልሰህ ፈጣሪህን በሰውነትህ ውስጥ አክብረው፡፡ ‹በርባንን የፈታሁት እኮ ወድጄ አይደለም! ሁኔታዎች አስገድደውኝ ነው› ብለህ እንደ ጲላጦስ ለራስህ ይቅርታ ማድረግና እጅህን መታጠብ አይበጅህም፡፡ ይልቅስ አሁኑኑ ጌታህን ፈትተህ በርባንን የተባለ ኃጢአትን ስቀለው! ያን ጊዜ የክርስቶስ መሆንህ ይታወቃል፡፡ ‹‹የክርስቶስ ኢየሱስ የሆኑቱ ሥጋን ከክፉ መሻቱና ምኞቱ ጋር ሰቀሉ›› ተብሎ ተጽፎአልና፡፡ (ገላ. ፭፥፳፬)
ሕዝቡ ‹በርባን ይፈታ› ብለው ቢጮኹም ሁሉም ለበርባን ፍቅር አላቸው ማለት አይደለም፡፡ ሊቃነ ካህናቱ ባያባብሏቸው ኖሮ በዚያች ዕለት ሊያስፈቱት የሚፈልጉት ሌላ እስረኛ ዘመድ ያላቸውም ሰዎች መኖራቸው አይቀሬ ነው፡፡ ሆኖም ሊቃነ ካህናቱ ለጌታችን ካላቸው ጥላቻ የተነሣ ሕዝቡን ተለማምጠው በርባን እንዲፈታ አስደረጉ፡፡ ዛሬ በርባንን አግኝተን ‹በርባን ሆይ ማን ነው ያስፈታህ?› ብለን ብንጠይቀው ምናልባትም ‹የሰው መውደድ ይሥጥ ማለት ነው! የሚወደኝ ሕዝብ ነዋ ጮኾ ያስፈታኝ!› ማለቱ የማይቀር ነው፡፡ ሆኖም ሊቃነ ካህናቱና ተከታዮቻቸው ግን ‹በርባን ይፈታ› ብለው የጮኹት ለበርባን ፍቅር ኖሯቸው ሳይሆን በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ላይ በነበራቸው ጥላቻ ምክንያት ነው፡፡ ስለዚህ በርባንን ከሞት ፍርድ አድኖ ያስፈታው ሕዝቡ ሳይሆን ጌታችን ነበር፡፡
ጌታችን በዚያች ዕለት የበርባንን ሞት ወስዶ የእርሱን ሕይወት ለበርባን ሠጠው ፤ የበርባንን ሰንሰለት አስፈትቶ እርሱ ታሰረ ፤ ከበርባን ጓደኞች ጋር በርባን ሊሰቀል በነበረበት ቦታም ተሰቀለ፡፡ ወዳጄ ሆይ! ልብ ብለህ ከተረዳኸው በርባን እኮ አንተው ነህ! ለበርባን ከተደረገለት ለአንተ ያልተደረገ ነገር ካለ እስቲ ንገረኝ! እንደ በርባን ክርስቶስ ሞትህን ወስዶ ሕይወቱን ፣ እስራትህን ወስዶ ነጻነትን አልሠጠህምን?
ይህንን ያደረገውም ለአንተ ብቻ ሳይሆን ለአዳም ልጅ ሁሉ ነው ፡- ‹‹የእስረኛው በርባን (ወልደ አባ) መፈታቱ አምላካዊ ምሥጢርን የሚያስታውስ ነው፡፡ በኃጢአቱ ምክንያት በሲኦል ውስጥ ታሥሮ የነበረው አዳምን በአዳኙ መሰቀል ምክንያት መድኃኒት አግኝቶ ነጻ መውጣቱን ያስታውሳል›› / ‹‹እስመ ተፈትሕዎቱ ለወልደ አባ ሙቁሕ ያዜክር ምሥጢራተ አምላካዊ ያሌቡ ግዕዛነ አዳም ዘኮነ ሙቁሐ ውስተ ሲኦል በእንተ ኃጢአቱ ወረከበ መድኃኒተ በስቅለተ መድኅን›› እንዲል፡፡
በዚያች የዕለተ ዓርብ ረፋድ ላይ ያስፈታውን የማያውቀው ይህ ወንበዴ ሰንሰለቱ ተፈትቶ ወደ ቤቱ ሲሔድ ጌታችን ግን ለመከራና ለመስቀል ተሠጠ፡፡ እውነቱንስ ለመናገር እኛ ክርስቲያኖች በርባን በመፈታቱ ላይ ላዩን ብናዝንም ውስጥ ውስጡን ግን ደስ ብሎናል!
‹‹…በርባን ቢሰቀል ኢየሱስ ቀርቶ
ምን ይጠቅመናል ሽፍታ ሞቶ
እንኳን ኢየሱስን ሰቀሉት
የሞቱን መድኃኒት …››
ብለው መሪጌታ ፍቅሩ ሣህሉ በበገናቸው ጨርሰውታል፡፡
(ሕማማት ከሚለው መጽሐፍ ለመድኃኔ ዓለም የስቅለቱ መታሰቢያ የተወሰደ)
የተዋህዶ ልጆች በቴሌግራም መንፈሳዊ ትምህርቶችን ለመከታተል የቴሌግራም ቻናላችን ቤተሰብ ይሁኑ!
ጠላትን በጋራ ከእግዚአብሔር ጋር ድል እናደርገው ዘንድ እናንተም የቴሌግራም ቻናላችንን ተቀላቀሉ
እምዬ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ለዘላለም ትኑር 🙏🙏🙏 ❤❤❤
ለኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ልጆች👇
•➢ ሼር // SHARE
https://t.me/yetewahedofera
https://t.me/yetewahedofera
https://t.me/yetewahedofera
. 🔸 🔸
🔸🔹🔸 🔸🔹🔸
🔸 🔸
🔸