ደቡብ ያስታውሳል 3
==============
ምስጋና ከሱ በሆነ እዝነት ፍጡራኑን ባማረ አለም ላይ አመቻችቶ ለፈጠረው... በመልአክቶች ፣ በነብያቶች እንዲሁም በሷሊህ ባሪያውች (አውሊያ) ወደራሱ ሰዎችን ላመላከተው ለመራው አላህ...
የአበል ራሙዝ ሀገር ሀበሻ ሆይ... ሰማይሺን እወደዋለሁ... አፈርሽን እወደዋለሁ... አየርሽን እወደዋለሁ... የሚኖሩብሽን እወዳቸዋለሁ... ሰላምሽን ያብዛልኝ... ማን ያውቃል ሰው በዱአ ከበረታ በአጭር ቀኖች የነስር ዜና እንሰማ ይሆናል...
ካለፈው የቀጠለ....
የመፃይ ቀን ቀጠሮ
💚🌹የአብሬት እንዲሁም የአቅራቢያዎቿን ነዋሪዎች ሰብስቡና "ጉራጌ ከየአቅጣጫው የፊታችን ቅዳሜ ወደቀያቹ ሊመጣ ነው... አብዛኛው የቀናት መንገዶች አቋርጦ ስለሚመጣ እዚህ ሲደርስ ተርቦ ነው... ከየጓሮአቹ የተስተካከለ አንድ አንድ ስር አምቾና አንድ ጀበና ቡና ላስቸግራቹ... ጀንበር ከርማ መመለስ የማይችሉም ስላሉ ቤቶቻቹን ክፈቱ አልጋዎቻቹን ልቀቁላቸው..." የሚል ጥሪ ለአካባቢው ነዋሪ አስተጋቡ... ተስማማም...
የቀጠሮ ቀኑም ደረሰ... የሚገኘው ሰፊ ሜዳም በአግድም ወንበሮች ቁም በተፈለጡ እንጨተቶች ተሞሉ... የአካባቢው ማህበረሰብ ቤቱን ከፍቶ ለእንግዳው በየ መንገዱ የሚጠጡ የሚበሉ ነገሮችን ማደል ጀመረ... በቅጡም ሳይነጋ በፈረስ፣ በበቅሉ ፣ በእግር ፣ አንድ ፣ ሁለት ፣ ሶስት ከዛም በላይ ሆነው እየተሳሳቁ እና እየተጨዋወቱ በመጡ የጉራጌ ተወላጆች ሜዳው ተሞላ... ጉራጌ ከየአቅጣጫው እንደ ጅረት ፈሰሰ... ያሰፊ ፈረስ የሚያስጋልብ ሜዳ ከመጣው ጉራጌ ጋር መስተካከል አቃተው...
ግን አንዱ ሌላውን ላለማየት ፊት ተነፊፈገ... ጌታ ለኧኖር ፣ እዣ ለቸሀ ፣ ጉመር ለሞህር ጀርባ ተሰጣጠ...
አዝማች ጨረቶ ብድግ አሉና "ዛሬ የሰበሰቡን ሸሆች የሚሉን ነገር ካለ እንስማቸው..." ብለው ሸሆችን ወደ መድረክ ጋበዙ...
💕ሸሆችም ህዝብን ከአንድ ዳር እስከ ሌላው ቃኙት... መቃቃሩንም አስተዋሉና እንደ ሁሉ ግዜው "ያ-ሃቅ ሀቅን አናግረኝ..." በሚለው በተለመደው ዱአቸው ንግግራቸው ከፈቱ "ጉራጌ አንድ አንዱ 15 ሌላው 20ም ድረስ አባቱን በጉራጌ ይቆጥራል... ሞህር ከኧኖር ፣ እዣ ከቸሀ ፣ ጌታ ከጉመር... ያልተዛመደ አለ?... ከሌላ አላገባክም?... ለሌላም አልዳርክም?... ለዘመናት ጠላት ያልካቸውን አንዱ በሌላው ትከሻ ስር ተደብቆ ተዋግ^ቶዋል... በአንድ ሃያቱ ያልተገናኘ በሌላ ሃያቱ ይገናኛል... አሁን ዘር ቁጠሩ... ሞህር ብቻ... ቸሀ ብቻ... ጌታ ብቻ... ኧኖር ብቻ... ከሆንን እናንተ ጀርባ ትሰጣጣላችሁ... እኛም እንደ እናንተው ጀርባ እንሰጣለን..." አሉ...
አዝማች ጨረቶ ብድግ ብለው ሞህሩ ፣ ቸሀው ሌላውም ክብ ሰርቶና ሌላውን አግሎ በተቀመጠበት ሁሉ ዘር የሚያስቆጥር ሰው መደቡ...
ከቆይታዎች በውሃላ 'አግኝተናል... አግኝተናል...' የሚል ድምፅ ከየታዳሚው መሰማት ጀመረ... እየተነሳ ቸሀ ጌትነቱን፣ ኧኖር ኧዣነቱን፣ ሞህር ጉመርነቱን ቆጠረ... ሁሉም ጀርባ የሰጠው ወንድሙን እንደሆነ ሲያውቅ እየዞረ ሳመው... ከጎኑ ተቀመጠ...
💕ሸሆች አሁንም ተነሱ "ጉራጌ እግር ጌህ... ተጎራብቶ አልያም ወንዝህን ተሻግሮ ያለው ወንድምህ ጠላትህ አይደለም... ሰፊ ሆነህ ተጎራብተህ... ተወዳጅተህ... ተዛምደህ ኖረሀል... ዛሬ ሀገራችን ምላስ ከሚቆጥራት እግር ተጉዞ ከሚጨርሳት በላይ ስትሰፋ አንተም መስፋት ሲገባህ አትቀነስ... አንዱ ጋር ያለ ጋሻ ጦ^ር ለአንድ መመኪያው ሊሆን ይገባል..." አሉና የተሰበሰበውን በሺ የሚቆጠር ህዝብ ተመለከቱ... ጥሞናውን ሰቷቸዋል... ቀጠሉ "አላህ ያለ እንደው ተፊትህ የሀቂቃ ጠላት ወደ አንተ እየገሰገሰ ነው... አላህ ያለ እንደው ጣሊያን የተሰኘ በሀገርህ ልግዛህ ብሎ ወንዝህን አቋርጦ ድንበርህን ተሻግሮ ቤትህ ሊደርስ ወራት ቀርተዋል..." ብለው ሸሆች ዝም አሉ...
የተሰበሰበውም ህዝብ ተደናገጠ... ምን ይሻላልም አለ...
💕ሼሆች ከሴንጤ እስከ መ^ድፍ ያለን መሳ^ሪያ በየ ቁመታቸው እና ግዝፈታቸው አስደረደሩ... ከየ ቤቱ የተከበሩ ሽማግሌዎች እንዲሁም ባለአባቶች እየወጡ በወንድማቸው ቸሀ በሞህር ፣ ኧኖር በኧዣ ፣ ጌታ በጉመር... በቂም አሳልፎ እንደማይሰጥ " እከሌ ላይ ከጠቆምኩ ከሴንጤው ባልፍ ከጦ^ሩ አልለፍ... ከጦ^ሩ ባልፍ ከጎራ^ዴው አልለፍ ... ከጎራደው ባልፍ...... ከመ*ድፉ አልለፍ..." እያለ እንዲምል አደረጉት...
"በል ጉራጌ እምነትህን የሚያስጥል... ሀገርን የሚያ^ስክድ ጠ^ላት እየመጣ ነው ለጦ^ርነት ተዘጋጅ... በየ ቤቱ ያስቀመጣችሁትን መሳሪያዎች አምጣ ሰለሚል... እንደ ሹልኪት፣ባለነሀስ፣ ዘመን... ያሉ እርካሽ ሽጉ^ጦች ግዙ ጣሊያኖች ሲጠይቁ እሱን ታስረክባላቹ... እንደ እስኮልት እና ጠመ^ንጃ ያሉ ሽጉ^ጦችን በጓሮአቹ ቅ^በሩ ወይንም በምሰሶዎቻቹ ስር ደብቁ... ጦ^ርነት ይጠብቀናል..." አሉና ጉራጌን አስጠነቀቁ...
ብዙም ሳይቆይ ከወራት በሁዋላ ጣሊያን ኢትዮጵያን ወ^ረረ... የጉራጌ ህዝብም በሼሁ እየተመራ የጣሊያንን ጦር ሰላም ነሳው...
ጣሊያን የሸሆችን ቀድሞ መገኘት ተከትሎ በጉራጌ ከሁለት ኧዣ ባለአባቶች በስተቀር አንድም ሰውን አልገደለም... ይህንን ተከትሎ በጥልቅ ምርምር ያልሰሩ ድርሳኖች በዶሴያቸው ጉራጌ ባን^ዳ ስለነበር ነው ይላሉ... አይ ጉራጌ ሸህ ስለነበረው ነው!!!
**************************************
በአንድ አጋጣሚ እንድብር ላይ ሱሩር ዲገታ የተባለ ግለሰቡን ሊሰ^ቅል እንጨት መቶ ጣሊያን መዘጋጀቱን ሲሰማ ፍጡር ተበድሎ የማታርፈው በቅሎአቸውን ዳግም ነድተዋታል... " ጣሊያን ለደሀ ፍትህን ሊሰጥ መምጣቱን እንጂ ደሀን የተቀዳደደን ልብስ የለበሰ... አዋራ የለበሰው ሰው ሊሰ^ቅል መምጣቱን አናውቅም ነበር... " ብለው ሸሆች አስጥለውታል... ከማስጣልም አልፎ ልብስ ከጣሊያን እልፍኝ ለሱሩር ዲገታ አሰጥተውታል...
መ^ረር ያለ እርምጃ ህዝቡ ላይ እንዳይወስድ በፖለቲካ... ሀገርን ለመታደግ ጦ^ር ሆነው ዘም^ተውበታል...
ይዞ ሊገ^ላቸው ሲያሴር ጉራጌ ከየ አቅጣጫው ሲ^ዘምት "ለኔ ግድ የለም ጌታዬ በነገሬ ላይ አዋቂ... በሚበጀኝ ላይ ፈራጅ ነው... ተመለስ..." ብለው በየ አቅጣጫው መልእክተኛ ልከዋል... ጉራጌ "ከሞ^ትንም፣ ተኖርንም ተእርሶ...." ብሎ ዘ^መተ እንጂ...
እናም... ደቡብ ጌታው(አላህ) በሰጠው ሁሉ ሳይሰስት የሰጠውን ዛሬም አልረሳም... እንደምንስ ከፅልመት ሊያድኑት አስተማሪ... መላ ሊያበጁለት ሽማግሌ... እንዳይበደል ጦ^ረኛ... እንዳይገፋ ፖለቲከኛ... ሸሪዓን እንዳይጥስ ቃዲ ሆነው ያገለገሉትን ገበና ከታቹን ይረሳ...
ለጌታቸው(አላህ) እራሳቸውን ፍፁም ሰተውት ነበር... ከተናገሩ አላህ የሚወደውን... ከሮጡ አላህ ለሚወደው ጉዳይ... ከተጓዙ ወደ ሚወደው ቦታ... ከሰሩ የሚወደውን... ፍፁም የአላህ ነበሩ... አላህም ፍፁም የነሱ ነበር...
ጊዜያት ነጉደው... ያሁሉ ዘመናት አልፈው... ዛሬም ላይ ኸውላን ግራ ገብቶታል... አንደምን ለሁሉ ጎኑ በቃከው...👇🏽