የነብዩንﷺ ውልደት አሏህ ከፍ አድርጎ አክብሮታል:: አሏህ ለውልደታቸው የጀሃነም በሮች እንዲዘጉ የጀሃነሙን መላኢካ ማሊክን አዘዘው ፣ ለውልደታቸው ጀነት እንዲዘይን የጀነቱ መላይካ ሪድዋንን አዘዘው ፣ ለሺ አመታት ሲቀጣጠል የነበረው እሳት ለክብራቸው አጥፋው ፣ እብሊስ ተወገረ.... በነብዩﷺ ውልደት እጅግ ብዙ ብዙ ጉዳ ጉዶች ሆኑ
ነቢ ﷺ ቢወለዱ
አብሮ የመጣው ኑር አለሙን አበራ
በየኮረምታው ላይ ሀቲፉ ተጣራ
ተወለዱ እያለ የከውኑ ሙሽራ
መላይካውም ቆሞ እየተሰለፈ
በየኮረምታው ላይ ሀቲፉን አጠፈ
ተወለዱ ማለት ባገር ተረፈፈ
የምስራች ማለት እጀነት አለፈ
ማሊክ ታዘዘና አዛብ ተቆለፈ
ጅብሪል ታቀፈና በጀነቱ ሀር
ያዘውና ሄደ በሀዋ ሲበር
አግብቶ አስጠወፈው በጀነት ሀገር
ስንት አጃኢብ ታየ ለቁጥር የጠፋ
ሺ አመት የበራው እሳትም ጠፋ
እብሊስ ይሄድ ነበር ሰማይ እየወጣ
ወሬ እየሰረቀ ለሰዉ ሊያመጣ
ያንን እያወራ ተመንገድ ሊያወጣ
ነቢﷺ ቢገኙ ይሄን ሹመት አጣ
ነቢ ﷺ ቢወለዱ
አብሮ የመጣው ኑር አለሙን አበራ
በየኮረምታው ላይ ሀቲፉ ተጣራ
ተወለዱ እያለ የከውኑ ሙሽራ
መላይካውም ቆሞ እየተሰለፈ
በየኮረምታው ላይ ሀቲፉን አጠፈ
ተወለዱ ማለት ባገር ተረፈፈ
የምስራች ማለት እጀነት አለፈ
ማሊክ ታዘዘና አዛብ ተቆለፈ
ጅብሪል ታቀፈና በጀነቱ ሀር
ያዘውና ሄደ በሀዋ ሲበር
አግብቶ አስጠወፈው በጀነት ሀገር
ስንት አጃኢብ ታየ ለቁጥር የጠፋ
ሺ አመት የበራው እሳትም ጠፋ
እብሊስ ይሄድ ነበር ሰማይ እየወጣ
ወሬ እየሰረቀ ለሰዉ ሊያመጣ
ያንን እያወራ ተመንገድ ሊያወጣ
ነቢﷺ ቢገኙ ይሄን ሹመት አጣ