ብርበራ
ብርበራ የወንጀል ድርጊት ለመፈፀም ጥቅም ላይ የዋሉ መሣሪያዎችን ፣ በወንጀል ድርጊት ምክንያት የተገኙ ቁሳቁሶችን ፣ ምርመራ ለሚደረግበት ጉዳይ ጠቀሜታ ያላቸውን ሌሎች ማናቸውም ማስረጃዎች ለመፈለግ እና ለመያዝ በተጠርጣሪዎች መኖሪያ ቤት ውስጥ ወይም የተጠቀሱት ነገሮች ተደብቀውባቸዋል በሚባሉ በሌሎች ሰዎች ቤቶች ውስጥ የሚከናወን የወንጀል ምርመራ ተግባር ነው፡፡ ብርበራ ለማድረግና በሚደረግበት ወቅት የሚከተሉትን መርሆች መከተል አስፈላጊ ነው።
✔ ማንኛውም መርማሪ ፖሊስ ወይም የፖሊስ አባል በፍርድ ቤት የተሰጠ የብርበራ ማዘዣ ካልያዘ በቀር የሰዎችን ቤት መበርበር አይችልም።
✔ ብርበራ የሚደረገው ከጠዋቱ 12፡00 ሰዓት እስከ ማታ 12፡00 ሰዓት ድረስ ብቻ ነው። በፍርድ ቤት የተለየ ትእዛዝ ሲሰጥ ብቻ ከዚ ሰአት ውጭ ሊካሄድ ይችላል።
✔ ማንኛውም የብርበራ ማዘዣ የሚበረበረውን እና የሚያዘውን ዕቃ ማመልከት ያለበት ሲሆን መርማሪው ፖሊስ ወይም አብሮት ያለ የፖሊስ አባል በማዘዣው ላይ ከተመለከተው ውጭ ሌላው ዕቃ መያዝ አይችልም።
✔ መርማሪው ፖሊስ ወይም የፖሊስ አባል በማዘዣ ትዕዛዙ የተመለከተውን ዕቃ በሚይዝበት ጊዜ የተያዘውን ዕቃ ዝርዝር መዝግቦ መያዝ ያለበት ሲሆን ከተቻለ ገለልተኛ የሆነ ሰው ሊስቱ ላይ እንዲፈርምበት ይደረጋል።
✔ ብርበራ የሚያደርገው ብርበራ ከሚደረግበት ሰው ጋር ተመሳሳይ ፆታ ባለው ሰው ነው።
✔ ምርመራ በሚደረግበት ጊዜ ፖሊስ አስፈላጊውን ሀይል ብቻ ይጠቀማል።
by Daniel Fikadu
https://t.me/Ethiopialegalinfo
@Ethiopialegalinfo
#Ethiopialegalinfo