ቀን 21 /1/ 2014 ዓ.ም
የአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ጽህፈት ቤት የ2013 ዓ.ም አፈጻጸሙንና የ2014 ዓ.ም እቅዱን የገመገመበትን ጉባኤ የተለያዩ የትምህርት ባለድርሻ አካላት በተገኙበት አካሄደ።
የክፍለ ከተማው ትምህርት ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ አለልኝ ወልዴ በውይይቱ የክፍለ ከተማውን የ2013 ዓ.ም የትምህርት ዘመን አፈጻጸም ያቀረቡ ሲሆን በሪፖርታቸውም በበጀት አመቱ በክፍለከተማው ሁሉንም ባለድርሻ አካል በማሳተፍ በተከናወኑ የተለያዩ ተግባራት በ2013 ዓ.ም በ8ኛ ክፍል የተማሪዎች ውጤት ክፍለከተማው በከተማ ደረጃ ግንባር ቀደም መሆኑን ገልጸው በ2014 ዓ.ም የትምህርት ዘመንም ውጤታማነታቸውን አጠናክረው በማስቀጠል የትምህርት ቤቶችን ደረጃ ከማሻሻል አንጻር የታዩ ክፍተቶችን በመገምገም ውጤታማ ስራ መስራት እንደሚጠበቅባቸው አስረድተዋል።
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ምክትል ቢሮ ኃላፊ አቶ ሳምሶን መለሰ በበኩላቸው በ2013 ዓ.ም የትምህርት ዘመን የትምህርት ሴክተሩ በኮቪድ 19 ወረርሽኝ የተፈተነበት አመት ቢሆንም የአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ ትምህርት ጽህፈት ቤት ሁሉንም የትምህርት ባለድርሻ አካላት አስተባብሮ ባከናወናቸው ተግባራት ውጤታማ መሆን መቻሉን ጠቁመው ውጤቱ ቀጣይነት እንዲኖረው ዘንድሮም ጽህፈት ቤቱ ከሁሉም ባለድርሻ አካላት ጋር ትስስር ፈጥሮ መስራት እንደሚጠበቅበት አስገንዝበዋል።
በጉባኤው በ2013 ዓ.ም በክፍለ ከተማው የላቀ አፈጻጸም ያስመዘገቡ የመንግስትና የግል ትምህርት ቤቶችን ጨምሮ የወረዳ ትምህርት ጽህፈት ቤቶች ከክፍለ ከተማው የብልጽግና ፓርቲ ጽህፈት ቤት ምክትል ኃላፊ ከአቶ መዝገቡ ይስማው እና ከትምህርት ቢሮ ምክትል ኃላፊ ከአቶ ሳምሶን መለሰ የተዘጋጀላቸውን ሽልማት ተቀብለዋል።