https://t.me/joinchat/Uv_qgPdMztgg-0_i
“የሕዳሴ ግድብ 2ኛ ዙር የውሃ ሙሌት በቅርቡ ይጀመራል” -
የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር
መንግስታዊ ያልሆኑ 36 የተለያዩ ተቋማት ምርጫውን
ለመታዘብ እየተዘጋጁ መሆኑን ሚኒስቴሩ አስታውቋል
ለግድቡ ግንባታ በሀገር ውስጥ እና በውጭ ከሚኖሩ
ኢትዮጵያውያን እስካሁን 15 ቢሊዮን ብር ተሰብስቧል
የሕዳሴ ግድብ ሁለተኛ ዙር የውሃ ሙሌት በቅርቡ እንደሚጀመር
የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታወቀ።
የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ አምባሳደር ዲና ሙፍቲ
በተለያዩ ወቅታዊ ጉዳዮች ላይ በዛሬው እለት ሳምንታዊ መግለጫ
ሰጥተዋል።
ከግድቡ ጋር በተያያዘ አምባሳደር ዲና ሙፍቲ በሰጡት መግለጫ
“ሁለተኛው ዙር የውሃ ሙሌት በቅርቡ ይጀመራል” ብለዋል፡፡
ግድቡ ከፖለቲካ በላይ የሆነ የባንዲራ ፕሮጄክት መሆኑን የተናገሩት
ቃል አቀባዩ የህዳሴ ግድብን የድርድር ሂደት ፣ ድጋፍና የግንባታ
ደረጃ የተመለከተ ውይይት ከፖለቲካ ፓርቲዎች እንዲሁም
ከኃይማኖት ተቋማት ተወካዮች ጋር ሲደረግ እንደነበረም
አስታውቀዋል።
ቃል አቀባዩ አምባሳደር ዲና ፣ የግድቡ ግንባታ 80 በመቶ
መጠናቀቁን ያነሱ ሲሆን እስካሁን ለግድቡ ግንባታ 15 ቢሊዮን ብር
በሀገር ውስጥ እና በውጭ ከሚኖሩ ኢትዮጵያውያን መዋጣቱን
አስታውቀዋል።
የግብፅ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሳሚ ሹክሪ የግድቡ ሁለተኛ ዙር
ሙሌት በግብፅ ላይ ጉዳት እንደማያስከትል መናገራቸውን
በተመለከተ በሰጡት አስተያየት ሳሚ ሹክሪ ይህን ያሉት
“እንደማይጎዳቸው ስለተረዱ ነው” ብለዋል አምባሳደር ዲና።
ከግድቡ እና ከሌሎች ወቀወታዊ ጉዳዮች ጋር በተያያዘም ተገቢ
ያልሆኑ ጫናዎች እየተደረጉ መሆናቸውንም አምባሳደር ዲና
እታውቀዋል።
ከጫናዎቹ መካከልም በግድቡ ዙሪያ ከስምምነት በፊት መሙላት
አትችሉም፤ ምርጫውን አታካሂዱ የሚሉ የሴናተሮች ጫናዎች፣
የሰብዓዊ መብት ጥሰት ክስ እና ሕወሓትን በሚደግፉ ቡድኖች
የሚደረጉ ጫናዎች እንደሚገኙበት አስታውቀዋል።
የአሜሪካ የአፍሪካ ቀንድ ልዩ መልዕክተኛ አምባሳደር ጄፍሪ
ፌልትማን ከምርጫ ጋር በተያያዘ “ምርጫ አታካሂዱ አንልም፤
የአሜሪካ መንግስትም ለዚህ አላከኝም” ማለታቸውንም
አስታውሰዋል። ይሁንና ግን “ከሕወሓት ጋር ጭምር ተነጋገሩ የሚል”
ሀሳብ ማንሳታቸውን አምበሳሳደር ዲና ገልጸዋል።
ከቀጣዩ ሀገራዊ ምርጫ ጋር በተያያዘ በሰጡት ማብራሪያ ደግሞ
የተለያዩ የሀገር ውስጥ እና ዓለም አቀፍ ተቋምት ምርጫውን
እንደሚታዘቡ ነው የገለጹት።
እንካሁን ባለው ሁኔታም 36 የውጭ ሀገራት እና የሀገር ውስጥ
መንግስታዊ ያልሆኑ ተቋማት ምርጫውን ለመታዘብ እየተዘጋጁ
መሆኑን አስታውቀዋል።
ሌሎች ታዛቢዎችም ሊኖሩ እንደሚችሉ አምባሳደር ዲና ሙፍቲ
ጠቁመዋል፡፡
ምርጫው በተያዘለት ጊዜ እንደማይካሄድ መገለፁ እና ቦርዱ
ምርጫውን ለማድረግ የሦስት ሳምንታት ተጨማሪ ጊዜ መጠየቁ
ይታወሳል።
“የሕዳሴ ግድብ 2ኛ ዙር የውሃ ሙሌት በቅርቡ ይጀመራል” -
የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር
መንግስታዊ ያልሆኑ 36 የተለያዩ ተቋማት ምርጫውን
ለመታዘብ እየተዘጋጁ መሆኑን ሚኒስቴሩ አስታውቋል
ለግድቡ ግንባታ በሀገር ውስጥ እና በውጭ ከሚኖሩ
ኢትዮጵያውያን እስካሁን 15 ቢሊዮን ብር ተሰብስቧል
የሕዳሴ ግድብ ሁለተኛ ዙር የውሃ ሙሌት በቅርቡ እንደሚጀመር
የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታወቀ።
የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ አምባሳደር ዲና ሙፍቲ
በተለያዩ ወቅታዊ ጉዳዮች ላይ በዛሬው እለት ሳምንታዊ መግለጫ
ሰጥተዋል።
ከግድቡ ጋር በተያያዘ አምባሳደር ዲና ሙፍቲ በሰጡት መግለጫ
“ሁለተኛው ዙር የውሃ ሙሌት በቅርቡ ይጀመራል” ብለዋል፡፡
ግድቡ ከፖለቲካ በላይ የሆነ የባንዲራ ፕሮጄክት መሆኑን የተናገሩት
ቃል አቀባዩ የህዳሴ ግድብን የድርድር ሂደት ፣ ድጋፍና የግንባታ
ደረጃ የተመለከተ ውይይት ከፖለቲካ ፓርቲዎች እንዲሁም
ከኃይማኖት ተቋማት ተወካዮች ጋር ሲደረግ እንደነበረም
አስታውቀዋል።
ቃል አቀባዩ አምባሳደር ዲና ፣ የግድቡ ግንባታ 80 በመቶ
መጠናቀቁን ያነሱ ሲሆን እስካሁን ለግድቡ ግንባታ 15 ቢሊዮን ብር
በሀገር ውስጥ እና በውጭ ከሚኖሩ ኢትዮጵያውያን መዋጣቱን
አስታውቀዋል።
የግብፅ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሳሚ ሹክሪ የግድቡ ሁለተኛ ዙር
ሙሌት በግብፅ ላይ ጉዳት እንደማያስከትል መናገራቸውን
በተመለከተ በሰጡት አስተያየት ሳሚ ሹክሪ ይህን ያሉት
“እንደማይጎዳቸው ስለተረዱ ነው” ብለዋል አምባሳደር ዲና።
ከግድቡ እና ከሌሎች ወቀወታዊ ጉዳዮች ጋር በተያያዘም ተገቢ
ያልሆኑ ጫናዎች እየተደረጉ መሆናቸውንም አምባሳደር ዲና
እታውቀዋል።
ከጫናዎቹ መካከልም በግድቡ ዙሪያ ከስምምነት በፊት መሙላት
አትችሉም፤ ምርጫውን አታካሂዱ የሚሉ የሴናተሮች ጫናዎች፣
የሰብዓዊ መብት ጥሰት ክስ እና ሕወሓትን በሚደግፉ ቡድኖች
የሚደረጉ ጫናዎች እንደሚገኙበት አስታውቀዋል።
የአሜሪካ የአፍሪካ ቀንድ ልዩ መልዕክተኛ አምባሳደር ጄፍሪ
ፌልትማን ከምርጫ ጋር በተያያዘ “ምርጫ አታካሂዱ አንልም፤
የአሜሪካ መንግስትም ለዚህ አላከኝም” ማለታቸውንም
አስታውሰዋል። ይሁንና ግን “ከሕወሓት ጋር ጭምር ተነጋገሩ የሚል”
ሀሳብ ማንሳታቸውን አምበሳሳደር ዲና ገልጸዋል።
ከቀጣዩ ሀገራዊ ምርጫ ጋር በተያያዘ በሰጡት ማብራሪያ ደግሞ
የተለያዩ የሀገር ውስጥ እና ዓለም አቀፍ ተቋምት ምርጫውን
እንደሚታዘቡ ነው የገለጹት።
እንካሁን ባለው ሁኔታም 36 የውጭ ሀገራት እና የሀገር ውስጥ
መንግስታዊ ያልሆኑ ተቋማት ምርጫውን ለመታዘብ እየተዘጋጁ
መሆኑን አስታውቀዋል።
ሌሎች ታዛቢዎችም ሊኖሩ እንደሚችሉ አምባሳደር ዲና ሙፍቲ
ጠቁመዋል፡፡
ምርጫው በተያዘለት ጊዜ እንደማይካሄድ መገለፁ እና ቦርዱ
ምርጫውን ለማድረግ የሦስት ሳምንታት ተጨማሪ ጊዜ መጠየቁ
ይታወሳል።