'አንድ አንዴ ትርጉማቸውን ሳናውቅ በልምድ አሜን ብለን የምንቀበላቸው ቃላቶች አሉ ' አለኝ አንድ ጓደኛዬ ። እንዴት አልኩት ያው ሁልጊዜ መፈላሰፍ ስለሚወድ አሁንም ፍልስፍናው ሊጀምረው ነው ብዬ እያሰብኩ ። ቢሆንም ግን ፍልስፍናውን እወድለታለው ፣ ብዙ ያላስተዋልኩትን እና ያላየሁትን ነገር እንዳይ እና እንዳስተውል ያደርገኛል ። ፍልስፍና ስለሚወድ ነው መሰለኝ ስሙ በእውቀቱ የተባለው ። ስሙን መልአክ ያወጣዋል 😁 ። 'ለምሳሌ እስኪ ልጠይቅህ ' አለኝ ትንሽ ፊቱን ኮስተር አድርጎ 'ተቃራኒ የሚለው ቃል ምን ማለት ነው እስኪ ንገረኝ ' አለኝ ። ጥያቄዎቹን ከየት እንደሚያመጣቸው ባላውቅም ነገር ግን ሁሌም ግራ እንድጋባ ያደርገኛል ። የዛሬው ግን ለየት ያለ ነው ። 'ምን ማለትህ ነው አልኩት ' ጥያቄው ቢገባኝም ምን መመለስ እንዳለብኝ ስላላወኩ ። 'እየውልህ ዛሬ ወዳጄ ተገኝ መጣና ስራዬ ጠመመብኝ አለኝ ከዛም እኔ አንተ ስለጠመምክበት ነው አልኩት እየቀለድኩ ። አርሱ ግን አምርሮ ለምንድን ነው ሁሌ ተቃራኒ የምትሆነው ብሎኝ ጥሎኝ ሄደ ። ከዛም ተቃራኒ የሚለው ቃል ጆሮዬ ገብቶ ትርጉሙን እየፈልኩ ነው ' አለኝ ። 'በለው' አልኩኝ በውስጤ አሁን ምን ልመልስለት በሚል ውስጤ እያብሰለሰለ ። 'አላውቅም እስኪ ንገረኝ ' አልኩት የምር መልሱን ስላላውኩት ። 'እየውልህ እስኪ ተቃራኒ የሆኑ ነገሮች ንገረኝ ' አለኝ ። 'ብርሃን እና ጨለማ' አልኩት ሃሳቤ ላይ በፍጥነት የመጣውን ። 'ጥሩ ። አሁን ጨለማ እና ብርሃንን ካየሃቸው የአንዱ መኖር ሌላኛውን ያጠፋዋል ። የአንደኛው መጥፋት ደግሞ ሌላኛውን እንዲኖር ያደርገዋል ። አሁን የሰጠኧኝን ምሳሌ ብናይ የብርሃን መኖር ጨለማን ያጠፋዋል ። የብርሃን አለመኖር ደግሞ ጨለማን ያኖረዋል ' ሲለኝ 'ስለዚህ የተቃራኒ ትርጉሙ የአንዱ መኖር ሌላኛውን እንዳይኖር ማድረግ ነው ማለት ነው? ' አልኩት ሃሳቡን በትክክል እንደተረዳሁት ለማሳየት ። 'በትክክል ። ተረድተኧኛል ። ግን አሁንም ትክክል አይደለንም ። ለምን ብትለኝ አንድ ምሳሌ ልጨምርልህ ' አለኝ ። 'ማወቅ እና አለማወቅ ተቃራኒ ናቸው ። ነገር ግን የአንዱ መኖር ሌላኛውን አያጠፋውም ። አንድ ሰው አወቀ ማለት የማያውቀው የለም ማለት አይደለም ። ስለዚህ ተቃራኒ ለሚለው ቃል ሌላ ትርጉም ልንሰጠው ያስፈልገናል ። ' አለኝ ። እውነቱን ነው ። ታያ ተቃራኒ የምንለው ምንድን ነው ብዬ እራሴን ጠየኩት ። አሁንም ለጥያቄዬ መልስ ስላጣሁለት ወደርሱ ተመልሼ 'ታዲያ ትርጉሙ ምን ይሆናል አልክ አልኩት' ምን ሊመልስ ይችላል ብዬ በማሰብ ። 'ያንተን ባላቅም እንደኔ ግን ተቃራኒ የሚለውን ለሁለት ከፍለን ማየት እንዳለብን ይሰማኛል ። የመጀመርያው የመጠፋፋት ተቃራኒ የምንለው ሲሆን ይህ የተቃራኒ አይነት አንዱ ሲኖር ሌላኛው እንዳይኖር ያደርገዋል ። ሌላኛው አይነት ደግሞ የመረዳዳት ተቃራኒ ነው ። ይህ አይነቱ አንዱ መኖሩ ሌላኛው እንዳይኖር አይከለክለውም ።' አለኝ ። 'ቆይ ስማቸውን እራስህ ነህ ያወጣሃቸው?' አልኩ እየሳኩ ። 'ባክህ ማህበረሰቡ ሃሳቤን ከተቀበለው የተሻለ ስም እሰጣቸዋለው ። ለጊዜው ግን በዚህ እንቀጥላለን ።' 'ጥሩ ሃሳብ ታመጣና አሰያየሙ ላይ ትቸገራለክ ።'አልኩት ንግግራችንን ለመጨረስ እያልኩ ። 'ያው ሰው ሙሉ ሆኖ አይሆን ። አንድ ነገር ሲኖረው አንድ ነገር ይታጣበታል ። ደግሞ የመጨረሻ ነገር ስለ ተቃራኒ ነገር የተፈላሰፍኩትን ልንገርክ ።' ሲለኝ ሎሚ የመጠጠ ሰው የሚያሳየውን ፊት ያዝኩ። አሁን ጨረስኩ ስል ድጋሜ ሌላ ሃሳብ ሊያነሳ ነው አልኩ ። እርሱ ግን ቀጠለ ። 'የሚገርምክ ነገር ደግሞ ያለተቃራኒ የተፈጠረ ነገር የለም ። ሁሉም የየራሱ የሆነ ተቃራኒ ነገር አለው አለኝ' ። እርፍ ደግሞ ምን የሚሉት ነው ይሄ ? ሁሉም ነገርማ ተቃራኒ የላቸውም ። ይህን እርግጠኛ ነበርኩ ነገር ግን ከርሱ ቶሎ ለመላቀቅ እንዲቀጥል ዝም አልኩኝ ። 'ይኧውልህ እኛ አላስተዋልነውም እንጂ ሁሉም ተቃራኒ ነገር አላቸው ። እንዲያ ባይሆንማ 'balance'የሚባለው ነገር ይጠፋል ። ምሳሌ ልስጥክ :- ቅጠላ ቅጠል ለሚበላ ሁሉ ስጋ በሊታ አለው ። ስጋ ለሚበላው ሁሉ ሌላ ስጋ በሊታ አለ ። ለመኖር ሞት አለ ፣ ለመወለድ መቀበር ፣ ለሃዘን ደስታ ፣ ለማግኘት ማጣት ፣ ለጥሩ መጥፎ ፣ በሳይንሱ እራሱ ለacid base ፣ለmatter antimatter ፣ ለመደመር መቀነስ ፣ ለderivate integration አለው ። እንደኔ ሃሳብ ተቃራኒ የሌለው ነገር DOMINATOR (CREATER) ፣ መሆን አለበት እርሱም ፈጣሪ ብቻ ነው ። 'ሲለኝ 'በል ወንድሜ እንደዚ ነገር አይነካካኝ ደና ሁን ' ብዬ ተሰናብትኩት ። ሃሳቡ ትንሽ የሚያሳምን ቢሆንም ሁሉም ተቃራኒ አለው የሚለው ስላሳመነኝ ተቃራኒ የሌለውን ነገር በሃሳቤ መፈለግ ጀመርኩ ...
@AstrogeezChannel
@AstrogeezChannel