ይኼ የሰውየው አንጻራዊ-እውናዊ ገጠመኝ በሰይጣንና በኢየሱስ ጨዋታ እንደተረት ተቆጥሯል፡፡ ተረቱ ኑሮን ተረት ያደርጋል፡፡ ሰውንም ጭምር፡፡ የሰው ልጅ ተረት ተራኪ ነኝ
ይበል እንጂ ራሱም ተረት ነው ይላል፡፡ በኑሮና በተረት መሃል
ፈጥረነው የቆየነው ድንበር ሙሉ በሙሉ ይጣስና ሁለቱ አንድ
ይሆናሉ፡፡
ተረቱ የሚያሳስበን ትልቅ ጥያቄ አለ፡፡ የልእለ ሰብአዊያን እና
የሰዎች ግንኙነት፡፡ ሰይጣንና እግዚአብሔር ልዕለ ተፈጥሯዊ
ኃይላት መሆናቸው ተነግሮናል፤ እነዚህ ከሰው በላይ የሆኑ
ፍጥረታት በዚህኛውም ሆነ በሌላ በማናውቀው ምድር
ተገዢዎች አሏቸው፡፡ በገዢና ተገዢ መካከል ያለው ግንኙነት
ጠንካራ እንደሆነ ይሰበካል፡፡ ለምሳሌ፣ በመጽሐፍ ቅዱስ
ምስክርነት መሠረት፣ በእግዚአብሔርና በሰው መካከል ያለው
የግንኙነት ማሰሪያ ገመድ ፍቅር ነው፤ እግዚአብሔር ሰውን
ይወዳል፡፡ ስለወደደም፣ አንድያ ልጁን ለሞት አሳልፎ
እስከመስጠት ደርሷል፡፡
የስብሃት ሰይጣንና ኢየሱስ ግን ያን ግንኙነት አልተቀበሉትም፡፡
በሰዎችና በነሱ መካከል ያለው ግንኙነት በደራሲና በሚስለው
ገፀ ባሕርይ መካከል እንዳለው ግንኙነት ነው፡፡ አማልክት
ደራሲዎች፣ ሰዎች እና ሌሎች የምድር ነዋሪዎች ደግሞ
የድርሰቶችቸው አላባዊያን የሆኑበት፡፡ የምድራዊያን ኑሮ ደግሞ
ለስብሃት ኢየሱስ እና ለስብሃት ሰይጣን “ተረት ብጤ ጨዋታ”
ነው፡፡
በአቶ አልአዛርና በሰይጣን መካከል በተደረገ የስልክ የሐሳብ
ልውውጥም ይኼ የደራሲው የ“ጠይቁ!” ግፊት ተጠናክሮ
ይቀጥላል፡፡ በዚህ ምልልስ ሰይጣን ሰው ነበርኩ ይላል፤ ሰውም
ሰይጣን ነው ይላል፡፡ በክፋትና ደግነት፣ በሰናያትና እኩያት፣
በመኖርና አለመኖር መካከል አለ ያልነውን ልዩነት አጥፍቶ
ሁሉንም አንድ ያደርጋቸዋል፡፡ ያዋሕዳቸዋል፡፡ አባ ሽንኩርት
የተባሉ (ምናልባት የሲኦል ደብተራ) ፍጡርን ጠቅሶ እንዲህ
ይላል፡-
“ምን ሰውነት ቢያምር የሚፈርስ ነውና
ምን ትልቅ ቢሆኑ ሰው ትቢያ ነውና
ምን ምስኪን ቢሆኑ ሰው ሕያው ነውና
ምን ክፋት ቢጠሉ ሰው ሰይጣን ነውና” (134)
አስቀድሞ እንዳልነው የምድር እና የአማልክቱ ግንኙነት የድርሰት
አላባዊያን እና የደራሲያንን ግንኙነት ከመሰለ፣ የምድራዊያኑ
ዕጣ ፈንታ በደራሲያኑ አስቀድሞ ይታወቃል ማለት ነው፡፡
የስብሃት ሰይጣን በዚህ ምልልስ በሃይማኖት አካባቢ
በተደጋጋሚ የሚነገሩና የሚታመኑባቸውን ታሪኮች ለውጦ
ተርኳል፡፡ ለምሳሌ ሰይጣን፣ ሳጥናኤል፣ በሚባል ስሙ መልአክ
- ሊቀመላእክት እንደነበረ ይታመናል፡፡ የስብሃት ሰይጣን ግን
ይኼን ክዶ ሰይጣን ሰው ነበር እንጂ መልአክ አልነበረም
ይላል፡፡
..ምን ክፋት ቢጠሉ ሰው ሰይጣን ነውና..
..ሰይጣንም ሰው ነውን?.. አሉት አቶ አልአዛር
..እንደ አስተያየትዎ ጌታዬ፣ እንደ አስተሳሰብዎ፡፡ አባ ሽንኩርት
እንደሚነግሩን ከሆነ ሰይጣን እጣን ቢሸተው ..እሰይ እጣን..
ቢል፣ ሰይጣን አሉት፤ ሰይጣን ሆኖ ቀረ፡፡ እንጂ ሰው ነበር፡፡
እሰይ እጣን... (134)
በሌላም በኩል በኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን
ከሚከበሩትና ታቦት ከተቀረፀላቸው፣ ደብር ከቆመላቸው
ሰማዕታት አንዱ ስለሆነው ስለ ቅዱስ ጊዮርጊስ የሚነገረውን
ታሪክ፤ የተጻፈውን ገድሉን በሌላ ለውጦ ሰይጣን ተርኮታል፡፡
በቤተ ክርስቲያን አንፃር ይኽ ታሪክ ሲተረክ የደራጐን ክፋት
የጊዮርጊስ ቅድስናና ኃያልነት ጐልቶ ይንፀባረቃል፡፡ የስብሃት
ሰይጣን ግን ያንን ይሽረዋል፡፡ ደራጐን ለጊዮርጊስ የተሸነፈችለት
ለፈረሱ ስትል እንጂ በአንድ ትንፋሽ ልታጠፋው ትችል እንደነበር
ይተርካል፡፡ እንግዲህ ተራኪው ሰይጣን በመሆኑም ይሆናል
የታሪኩ አካሔድም፣ ጭብጥም የተለወጠው፡፡
እዚህም በሰይጣኑ አማካይነት ስብሃት ጠያቂነታችንን
ያበረታታል፡፡
‹ስምንተኛው ጋጋታ› ሃይማኖትን ለመፈተሽ፣ ወይም የቆዩ
እምነቶችን ለመፈታተን የተጻፈ ድርሰት አይደለም፡፡ ወይም
በተቃራኒው እነዚህኑ ሃይማኖቶች እና እምነቶች ለማጽናት
የተጻፈም አይመስልም፡፡ ይልቁንም ዳኛቸው ወርቁ “እፎይ
ብላለች- በርጋታ፣ በዝግታ፣ ታምማለች፤ በተገማሸረ መስክ
ውስጥ እንደሚብሰከሰክ ውኃ … ” ያለላትን የልማድ ሕይወት፣
“ሰይጣን” ባለው ጠጠሩ ለማደፍረስ መሞከሩ እና እኛም
እውነትን አጥልለን እንድንጠጣ መገፋፋቱ ነው፡፡
ስብሃት እንድንመረምር ሲያበረታታን፣ “አሰናካይ፣ የሐሰት አባት”
እየተባለ ለሚጠራው ሰይጣን ሰናያት ባሕርያት አልሰጠውም፣
አምነን እንከተለውም ዘንድ አልገፋፋንም፤ ይልቅ ሰይጣን ቦታ
ብንቆም፣ ናቡከደነፆር ዙፋን ላይ ብንቀመጥ፣ ይሁዳን ብንሆን፣
ሂትለር ቦታ ብንቆም፣ … ታሪክን፣ እውነትን በምን መልኩ ነበር
የምንረዳው እንድንል አበረታቶናል፡፡
በዓለም ታሪክ ጠያቂነት ሲነወር ሲወገዝና ሲወነጀል ኖሯል፡፡
ለማወቅ የሚደረግ ጥረት ሲያስቀጣ ኖሯል፡፡ ፈላስፎች
ተመርዘዋል፤ ተፈጥሮን መርማሪዎች ተሰቅለዋል፤ የሥነ-
መለኮት ፈታሾች ተወግዘዋል - ታርደዋል፤ … ከነባር ዕውቀት፣
ከነባር እምነት፣ ከነባር ባህል እና ከነባር ልማድ ያፈነገጡ ሰዎች
በመንግሥታት እና በሃይማኖት/በእምነት ስም የሰው ልጅ
ሊያስባቸው የቻላቸውን ማሰቃያዎች እና የግፍ ግድያዎች ሁሉ
ተቀብለዋል፡፡ ሃይማኖት፣ ባህል እና ጨቋኝ መንግሥት
የመጠየቅ፣ የመመርመር ጠላት ሆነው ኖረዋል፡፡
ስብሃት ሰውን እና ኑሮውን ተረት፣ ሰይጣንን ደግሞ ተራኪ
አድርጎ ሲያመጣ፣ ሰውንም ዓለምንም የምንረዳበትን ዐይነ
ልቡናችንን የማስፋት ዓላማ ይዞ ይመስለኛል፡፡ የፊት የፊቱን
አትዩ፣ መርምሩ ሊለን ይመስለኛል፡፡ “ሁሉን መርምሩ
መልካሙንም ያዙ፣” የተባለውንም ያስታውሷል፡
_______________
| @BOOKALEM |
ይበል እንጂ ራሱም ተረት ነው ይላል፡፡ በኑሮና በተረት መሃል
ፈጥረነው የቆየነው ድንበር ሙሉ በሙሉ ይጣስና ሁለቱ አንድ
ይሆናሉ፡፡
ተረቱ የሚያሳስበን ትልቅ ጥያቄ አለ፡፡ የልእለ ሰብአዊያን እና
የሰዎች ግንኙነት፡፡ ሰይጣንና እግዚአብሔር ልዕለ ተፈጥሯዊ
ኃይላት መሆናቸው ተነግሮናል፤ እነዚህ ከሰው በላይ የሆኑ
ፍጥረታት በዚህኛውም ሆነ በሌላ በማናውቀው ምድር
ተገዢዎች አሏቸው፡፡ በገዢና ተገዢ መካከል ያለው ግንኙነት
ጠንካራ እንደሆነ ይሰበካል፡፡ ለምሳሌ፣ በመጽሐፍ ቅዱስ
ምስክርነት መሠረት፣ በእግዚአብሔርና በሰው መካከል ያለው
የግንኙነት ማሰሪያ ገመድ ፍቅር ነው፤ እግዚአብሔር ሰውን
ይወዳል፡፡ ስለወደደም፣ አንድያ ልጁን ለሞት አሳልፎ
እስከመስጠት ደርሷል፡፡
የስብሃት ሰይጣንና ኢየሱስ ግን ያን ግንኙነት አልተቀበሉትም፡፡
በሰዎችና በነሱ መካከል ያለው ግንኙነት በደራሲና በሚስለው
ገፀ ባሕርይ መካከል እንዳለው ግንኙነት ነው፡፡ አማልክት
ደራሲዎች፣ ሰዎች እና ሌሎች የምድር ነዋሪዎች ደግሞ
የድርሰቶችቸው አላባዊያን የሆኑበት፡፡ የምድራዊያን ኑሮ ደግሞ
ለስብሃት ኢየሱስ እና ለስብሃት ሰይጣን “ተረት ብጤ ጨዋታ”
ነው፡፡
በአቶ አልአዛርና በሰይጣን መካከል በተደረገ የስልክ የሐሳብ
ልውውጥም ይኼ የደራሲው የ“ጠይቁ!” ግፊት ተጠናክሮ
ይቀጥላል፡፡ በዚህ ምልልስ ሰይጣን ሰው ነበርኩ ይላል፤ ሰውም
ሰይጣን ነው ይላል፡፡ በክፋትና ደግነት፣ በሰናያትና እኩያት፣
በመኖርና አለመኖር መካከል አለ ያልነውን ልዩነት አጥፍቶ
ሁሉንም አንድ ያደርጋቸዋል፡፡ ያዋሕዳቸዋል፡፡ አባ ሽንኩርት
የተባሉ (ምናልባት የሲኦል ደብተራ) ፍጡርን ጠቅሶ እንዲህ
ይላል፡-
“ምን ሰውነት ቢያምር የሚፈርስ ነውና
ምን ትልቅ ቢሆኑ ሰው ትቢያ ነውና
ምን ምስኪን ቢሆኑ ሰው ሕያው ነውና
ምን ክፋት ቢጠሉ ሰው ሰይጣን ነውና” (134)
አስቀድሞ እንዳልነው የምድር እና የአማልክቱ ግንኙነት የድርሰት
አላባዊያን እና የደራሲያንን ግንኙነት ከመሰለ፣ የምድራዊያኑ
ዕጣ ፈንታ በደራሲያኑ አስቀድሞ ይታወቃል ማለት ነው፡፡
የስብሃት ሰይጣን በዚህ ምልልስ በሃይማኖት አካባቢ
በተደጋጋሚ የሚነገሩና የሚታመኑባቸውን ታሪኮች ለውጦ
ተርኳል፡፡ ለምሳሌ ሰይጣን፣ ሳጥናኤል፣ በሚባል ስሙ መልአክ
- ሊቀመላእክት እንደነበረ ይታመናል፡፡ የስብሃት ሰይጣን ግን
ይኼን ክዶ ሰይጣን ሰው ነበር እንጂ መልአክ አልነበረም
ይላል፡፡
..ምን ክፋት ቢጠሉ ሰው ሰይጣን ነውና..
..ሰይጣንም ሰው ነውን?.. አሉት አቶ አልአዛር
..እንደ አስተያየትዎ ጌታዬ፣ እንደ አስተሳሰብዎ፡፡ አባ ሽንኩርት
እንደሚነግሩን ከሆነ ሰይጣን እጣን ቢሸተው ..እሰይ እጣን..
ቢል፣ ሰይጣን አሉት፤ ሰይጣን ሆኖ ቀረ፡፡ እንጂ ሰው ነበር፡፡
እሰይ እጣን... (134)
በሌላም በኩል በኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን
ከሚከበሩትና ታቦት ከተቀረፀላቸው፣ ደብር ከቆመላቸው
ሰማዕታት አንዱ ስለሆነው ስለ ቅዱስ ጊዮርጊስ የሚነገረውን
ታሪክ፤ የተጻፈውን ገድሉን በሌላ ለውጦ ሰይጣን ተርኮታል፡፡
በቤተ ክርስቲያን አንፃር ይኽ ታሪክ ሲተረክ የደራጐን ክፋት
የጊዮርጊስ ቅድስናና ኃያልነት ጐልቶ ይንፀባረቃል፡፡ የስብሃት
ሰይጣን ግን ያንን ይሽረዋል፡፡ ደራጐን ለጊዮርጊስ የተሸነፈችለት
ለፈረሱ ስትል እንጂ በአንድ ትንፋሽ ልታጠፋው ትችል እንደነበር
ይተርካል፡፡ እንግዲህ ተራኪው ሰይጣን በመሆኑም ይሆናል
የታሪኩ አካሔድም፣ ጭብጥም የተለወጠው፡፡
እዚህም በሰይጣኑ አማካይነት ስብሃት ጠያቂነታችንን
ያበረታታል፡፡
‹ስምንተኛው ጋጋታ› ሃይማኖትን ለመፈተሽ፣ ወይም የቆዩ
እምነቶችን ለመፈታተን የተጻፈ ድርሰት አይደለም፡፡ ወይም
በተቃራኒው እነዚህኑ ሃይማኖቶች እና እምነቶች ለማጽናት
የተጻፈም አይመስልም፡፡ ይልቁንም ዳኛቸው ወርቁ “እፎይ
ብላለች- በርጋታ፣ በዝግታ፣ ታምማለች፤ በተገማሸረ መስክ
ውስጥ እንደሚብሰከሰክ ውኃ … ” ያለላትን የልማድ ሕይወት፣
“ሰይጣን” ባለው ጠጠሩ ለማደፍረስ መሞከሩ እና እኛም
እውነትን አጥልለን እንድንጠጣ መገፋፋቱ ነው፡፡
ስብሃት እንድንመረምር ሲያበረታታን፣ “አሰናካይ፣ የሐሰት አባት”
እየተባለ ለሚጠራው ሰይጣን ሰናያት ባሕርያት አልሰጠውም፣
አምነን እንከተለውም ዘንድ አልገፋፋንም፤ ይልቅ ሰይጣን ቦታ
ብንቆም፣ ናቡከደነፆር ዙፋን ላይ ብንቀመጥ፣ ይሁዳን ብንሆን፣
ሂትለር ቦታ ብንቆም፣ … ታሪክን፣ እውነትን በምን መልኩ ነበር
የምንረዳው እንድንል አበረታቶናል፡፡
በዓለም ታሪክ ጠያቂነት ሲነወር ሲወገዝና ሲወነጀል ኖሯል፡፡
ለማወቅ የሚደረግ ጥረት ሲያስቀጣ ኖሯል፡፡ ፈላስፎች
ተመርዘዋል፤ ተፈጥሮን መርማሪዎች ተሰቅለዋል፤ የሥነ-
መለኮት ፈታሾች ተወግዘዋል - ታርደዋል፤ … ከነባር ዕውቀት፣
ከነባር እምነት፣ ከነባር ባህል እና ከነባር ልማድ ያፈነገጡ ሰዎች
በመንግሥታት እና በሃይማኖት/በእምነት ስም የሰው ልጅ
ሊያስባቸው የቻላቸውን ማሰቃያዎች እና የግፍ ግድያዎች ሁሉ
ተቀብለዋል፡፡ ሃይማኖት፣ ባህል እና ጨቋኝ መንግሥት
የመጠየቅ፣ የመመርመር ጠላት ሆነው ኖረዋል፡፡
ስብሃት ሰውን እና ኑሮውን ተረት፣ ሰይጣንን ደግሞ ተራኪ
አድርጎ ሲያመጣ፣ ሰውንም ዓለምንም የምንረዳበትን ዐይነ
ልቡናችንን የማስፋት ዓላማ ይዞ ይመስለኛል፡፡ የፊት የፊቱን
አትዩ፣ መርምሩ ሊለን ይመስለኛል፡፡ “ሁሉን መርምሩ
መልካሙንም ያዙ፣” የተባለውንም ያስታውሷል፡
_______________
| @BOOKALEM |