DARU-TAUHEED(ዳሩ-ተውሒድ)


Гео и язык канала: не указан, не указан
Категория: не указана


كن سلفيا علـى الجادة(በፍትህ ላይ ቀጥ ያልክ ሰለፊ ሁን)
for any comments use this link👇
@AbuNuhibnufedlu

Связанные каналы  |  Похожие каналы

Гео и язык канала
не указан, не указан
Категория
не указана
Статистика
Фильтр публикаций


ጥቆማ

  ውድ ወንድምና እህቶች ምናልባትም ከማዕዱ እየተቋደሳቹ ካልሆነ ልጠቁማችሁና እናንተም ማዕዱን እንድትቋደሱ ነው።እሱም ምንድ ነው ካላችሁኝ  አሁን ላይ በመካሪያችንና በዉዱ ኡስታዛችን ኢብኑ ሙነወር በሚገርም አቀራርና ሽርህ በነዛ ውብ አንደበቶቹ ! እየተቀራ ያለውን የሸርሁ ሱና ሊልበርበሃሪይ ኪታብ ደርስ ኪታቡን መቅራት ያልጀመራችሁ ወንድምና እህቶች ኪታቡን በመግዛት እንድትከታተሉትና እንድትጠቀሙበት ስል ወንድማዊ መልዕክቴን አስተላልፋለሁ ምናልባትም ኪታቡ ያልጀመራችሁና ለመጀመር ያሰባችሁ ኡስታዙና አሁን ላይ እያሰቀራ የደረሰበትን ቦታ ለመግለፅ ያክል ክፍል 20 ወይም ገፅ 20 ላይ ይገኛል።ኪታቡ አንገብጋቢና የአቂዳም ሆነ የፊቂህ ርእሶችን ያቀፈ በመሆኑ አብረን ከማዕዱ እየተቋደስን  እንጠቀምበት እላለሁ ሠላም።
  
    ✍ወንድማችሁ ሙሐመድ ኢብኑ ፈድሉ

          https://t.me/Darutewhide


ተውሒድ እና ሽርክ
   
      ክፍል ሀያ አንድ

16.አላህ በላጭ ነውን ?ወይስ ያ የሚያጋሩትን ?
      
    ከአላህ ጋር ሌላ አምላክ አለን ?
قُلِ ٱلْحَمْدُ لِلَّهِ وَسَلَٰمٌ عَلَىٰ عِبَادِهِ ٱلَّذِينَ ٱصْطَفَىٰٓ ۗ ءَآللَّهُ خَيْرٌ أَمَّا يُشْرِكُونَ
(ሙሐመድ ሆይ) በል «ምስጋና ለአላህ ይግባው፡፡ በእነዚያም በመረጣቸው ባሮቹ ላይ ሰላም ይውረድ፡፡ አላህ በላጭ ነውን ወይስ ያ የሚያጋሩት (ጣዖት)፡፡
أَمَّنْ خَلَقَ ٱلسَّمَٰوَٰتِ وَٱلْأَرْضَ وَأَنزَلَ لَكُم مِّنَ ٱلسَّمَآءِ مَآءًۭ فَأَنۢبَتْنَا بِهِۦ حَدَآئِقَ ذَاتَ بَهْجَةٍۢ مَّا كَانَ لَكُمْ أَن تُنۢبِتُوا۟ شَجَرَهَآ ۗ أَءِلَٰهٌۭ مَّعَ ٱللَّهِ ۚ بَلْ هُمْ قَوْمٌۭ يَعْدِلُونَ
ወይም ያ ሰማያትንና ምድርን የፈጠረና ከሰማይም ለእናንተ ውሃን ያወረደው (ይበልጣል ወይስ የሚያጋሩት) በእርሱም ባለውበት የኾኑትን የታጠሩ አትክልቶችን ዛፍዋን ልታበቅሉ ለናንተ ችሎታ ያልነበራችሁን አበቀልን፡፡ ከአላህ ጋር ሌላ አምላክ አለን (የለም)፡፡ ግን እነርሱ (ከእውነት) የሚያዘነብሉ ሕዝቦች ናቸው፡፡
أَمَّن جَعَلَ ٱلْأَرْضَ قَرَارًۭا وَجَعَلَ خِلَٰلَهَآ أَنْهَٰرًۭا وَجَعَلَ لَهَا رَوَٰسِىَ وَجَعَلَ بَيْنَ ٱلْبَحْرَيْنِ حَاجِزًا ۗ أَءِلَٰهٌۭ مَّعَ ٱللَّهِ ۚ بَلْ أَكْثَرُهُمْ لَا يَعْلَمُونَ
ወይም ያ ምድርን መርጊያ ያደረገና በመካከሏም ወንዞችን ያደረገ፣ ለእርሷም ጋራዎችን ያደረገ፣ በሁለቱ ባሕሮችም (በጣፋጩና በጨው ባሕር) መካከል ግርዶን ያደረገ (ይበልጣልን ወይስ የሚያጋሩት) ከአላህ ጋር ሌላ አምላክ አለን ግን አብዛኞቻቸው አያውቁም፡፡
أَمَّن يُجِيبُ ٱلْمُضْطَرَّ إِذَا دَعَاهُ وَيَكْشِفُ ٱلسُّوٓءَ وَيَجْعَلُكُمْ خُلَفَآءَ ٱلْأَرْضِ ۗ أَءِلَٰهٌۭ مَّعَ ٱللَّهِ ۚ قَلِيلًۭا مَّا تَذَكَّرُونَ
ወይም ያ ችግረኛን በለመነው ጊዜ የሚቀበል፣ መከራንም የሚያስወግድ፣ በምድርም ላይ ምትኮች የሚያደረጋችሁ፤ (ይበልጣልን ወይስ የሚያጋሩት) ከአላህ ጋር ሌላ አምላክ አለን ጥቂትንም አትገሠጹም፡፡
أَمَّن يَهْدِيكُمْ فِى ظُلُمَٰتِ ٱلْبَرِّ وَٱلْبَحْرِ وَمَن يُرْسِلُ ٱلرِّيَٰحَ بُشْرًۢا بَيْنَ يَدَىْ رَحْمَتِهِۦٓ ۗ أَءِلَٰهٌۭ مَّعَ ٱللَّهِ ۚ تَعَٰلَى ٱللَّهُ عَمَّا يُشْرِكُونَ
ወይም ያ በየብስና በባሕር ጨለማዎች ውስጥ የሚመራችሁ ነፋሶችንም ከዝናሙ በፊት አብሳሪ ኾነው የሚልክ (ይበልጣልን ወይስ የሚያጋሩት) ከአላህ ጋር ሌላ አምላክ አለን አላህ (በእርሱ) ከሚያጋሩዋቸው ሁሉ ላቀ፡፡
أَمَّن يَبْدَؤُا۟ ٱلْخَلْقَ ثُمَّ يُعِيدُهُۥ وَمَن يَرْزُقُكُم مِّنَ ٱلسَّمَآءِ وَٱلْأَرْضِ ۗ أَءِلَٰهٌۭ مَّعَ ٱللَّهِ ۚ قُلْ هَاتُوا۟ بُرْهَٰنَكُمْ إِن كُنتُمْ صَٰدِقِينَ
ወይም ያ መፍጠርን የሚጀምር ከዚያም የሚመልሰው ከሰማይና ከምድርም ሲሳይን የሚሰጣችሁ አምላክ (ይበልጣልን ወይስ የሚያጋሩት) ከአላህ ጋር ሌላ አምላክ አለን «እውነተኞች እንደኾናችሁ፤ አስረጃችሁን አምጡ» በላቸው፡፡[አን-ነምል:59-64]
  
        ✍ሙሐመድ ኢብኑ ፈድሉ
   (ተውሒድ እና ሽርክ  ገፅ 42-44)
 
     “ኢንሻ አላህ ይቀጥላል”

የቴሌግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ👇
https://t.me/Darutewhide
https://t.me/Darutewhide


ድሮ ወንድ ልጅ፣ሴት ልጅ ከቤት ከወጡ ይበላሹ ነበር ዛሬስ ?

ጓደኛሞች ከፊሉን ለከፊሉ ጠላት ሚሆኑበት ቀን እነማን ሲቀሩ ?

🎙በኡስታዝ ሳዳት ከማል ሀፊዘሁላህ

https://t.me/Darutewhide


ተውሒድ እና ሽርክ

      ክፍል ሀያ

14.የአባቶቻችን መንገድ

       አብዛኛዎቹ ህዝቦች መልክተኞች ምን ይዘውላቸው እንደመጡ ገብቷቸዋል።ሆኖም ግን መልክቱን ላለመቀበል ካዳገዳቸው ምክንያቶች ውስጥ አንዱ የአባቶቻቸውን ውርስ ለመተው አለመፍቀዳቸው ነው ።አላህ እንዲህ ይላል፦
قَالُوٓا۟ أَجِئْتَنَا لِنَعْبُدَ ٱللَّهَ وَحْدَهُۥ وَنَذَرَ مَا كَانَ يَعْبُدُ ءَابَآؤُنَا ۖ فَأْتِنَا بِمَا تَعِدُنَآ إِن كُنتَ مِنَ ٱلصَّٰدِقِينَ
«አላህን ብቻውን እንድንገዛ አባቶቻችንም ይገዙት የነበረውን (አማልክት) እንድንተው መጣህብን ከውነተኞች ከኾንክ የምታስፈራብንን (ቅጣት) አምጣብን» አሉ፡፡ [አል-አዕራፍ :70]

     አባቶቻችንን ተምሳሌት ልናደርግ የሚገባው በተውሒድ፣በሱንና በሐቅ ላይ ሲሆን ብቻ ነው።የአላህ ነብይ ዩሱፍ ምን እንዳሉ አላህ እንዲህ ይላል፦

وَٱتَّبَعْتُ مِلَّةَ ءَابَآءِىٓ إِبْرَٰهِيمَ وَإِسْحَٰقَ وَيَعْقُوبَ ۚ مَا كَانَ لَنَآ أَن نُّشْرِكَ بِٱللَّهِ مِن شَىْءٍۢ ۚ ذَٰلِكَ مِن فَضْلِ ٱللَّهِ عَلَيْنَا وَعَلَى ٱلنَّاسِ وَلَٰكِنَّ أَكْثَرَ ٱلنَّاسِ لَا يَشْكُرُونَ
«የአባቶቼንም የኢብራሂምንና የኢስሐቅን፣ የያዕቆብንም ሃይማኖት ተከትያለሁ፡፡ ለእኛ በአላህ ምንንም ማጋራት አይገባንም ያ (አለማጋራት) በእኛ ላይና በሰዎቹ ላይ የአላህ ችሮታ ነው፡፡ ግን አብዛኞቹ ሰዎች አያመሰግኑም፡፡❨ዩሱፍ 38)

     የታዘዝነው ከሽርክ እና ከቢዳዓ የፀዱትን የቀደምቶቹን የነብዩ ﷺ ፣ሰሃቦቻቸው ፣እና ሰለፉነ ሷሊሁንን መንገድ እንድከተል ነው።

15.አማኞቹ ጂኖች በአላህ ላይ አናጋራም ማለታቸው።

      አማኝ ጂኖች በነብዩ ሙሐመድ ﷺ ላይ የወረደውን የአላህ ቃል ቁርአን ከሰሙ ቦኋላ በጌታችን አላህ ላይ አናጋራም በማለት እንዲህ ሲሉ መመስከራቸውን ጌታችን አላህ ይነግረናል ፦
قُلْ أُوحِىَ إِلَىَّ أَنَّهُ ٱسْتَمَعَ نَفَرٌۭ مِّنَ ٱلْجِنِّ فَقَالُوٓا۟ إِنَّا سَمِعْنَا قُرْءَانًا عَجَبًۭا
(ሙሐመድ ሆይ!) በል «እነሆ ከጂን የኾኑ ጭፈሮች (ቁርኣንን) አዳመጡ፡፡‹እኛ አስደናቂ የኾነን ቁርኣን ሰማንም› አሉ ማለት ወደእኔ ተወረደ፡፡
يَهْدِىٓ إِلَى ٱلرُّشْدِ فَـَٔامَنَّا بِهِۦ ۖ وَلَن نُّشْرِكَ بِرَبِّنَآ أَحَدًۭا
ወደ ቀጥታ መንገድ የሚመራን (ቁርአን ሰማን)፡፡ በእርሱም አመንን፡፡ በጌታችንም አንድንም አናጋራም፡፡› [አል-ጂን:1-2]

    ቀደም ብለን እንዳሳለፍነው ጂኖችም ልክ እንደ ሰው ልጅ አላህን በብቸኝነት ለማምለክ ነው የተፈጠሩት።ልክ ከሰው ልጅ አማኝ፣ከሃዲ፣አመፀኛ እንዳለ ሁሉ ከነሱም ውስጥ እንዲሁ አማኝ፣ከሃዲ፣ እና አመፀኞች አሉ። አማኞቹ ጂኖች   ይኸው “በጌታችን ላይ አናጋራም” ማለታቸውን አላህ ነገረን።በሌላ ቦታ ላይ አማኝ ጂኖች ለህዝቦቻቸው ነብዩን ﷺ እንዲከተሉ እንዲህ ሲሉ ጥሪ ማቅረባቸውን አላህ እንደሚከተለው ይነግረናል፦
يَٰقَوْمَنَآ أَجِيبُوا۟ دَاعِىَ ٱللَّهِ وَءَامِنُوا۟ بِهِۦ يَغْفِرْ لَكُم مِّن ذُنُوبِكُمْ وَيُجِرْكُم مِّنْ عَذَابٍ أَلِيمٍۢ
ወገኖቻችን ሆይ! የአላህን ጠሪ ተቀበሉ፡፡ በእርሱም እመኑ፡፡ (አላህ) ከኀጢአቶቻችሁ ለእናንተ ይምራልና፡፡ ከአሳማሚ ቅጣትም ያድናችኋልና፡፡
وَمَن لَّا يُجِبْ دَاعِىَ ٱللَّهِ فَلَيْسَ بِمُعْجِزٍۢ فِى ٱلْأَرْضِ وَلَيْسَ لَهُۥ مِن دُونِهِۦٓ أَوْلِيَآءُ ۚ أُو۟لَٰٓئِكَ فِى ضَلَٰلٍۢ مُّبِينٍ
የአላህንም ጠሪ (ነብዩ ሙሐመድ ﷺ)የማይቀበል ሰው በምድር ውስጥ የሚያመልጥ አይደለም፡፡ ከእርሱም ሌላ ለእርሱ ረዳቶች የሉትም፡፡ እነዚያ በግልጽ ስሕተት ውስጥ ናቸው» (አሉ)፡፡ [አል አሕቃፍ :31-32]

        ✍ሙሐመድ ኢብኑ ፈድሉ
   (ተውሒድ እና ሽርክ  ገፅ 40-42)
 
     “ኢንሻ አላህ ይቀጥላል”

የቴሌግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ👇
https://t.me/Darutewhide
https://t.me/Darutewhide


📢ታላቅ የዳዕዋ ፕሮግራም

☞ውድ የተከበራቹ ወንድም እና እህቶች በአሏህ ፍቃድ
ነገ ማለትም ቅዳሜ ከቀኑ 10:30 ጀምሮ የዳዕዋ ፕሮግራም
በቴሌግራም ቀጥታ ስርጭት አዘጋጅተን ስንጋብዛቹ በታላቅ ደስታ ነው

ተጋባዣ ዱዓቶች
↓↓↓↓↓↓
🎤ኡስታዝ ሳዳት ከማል

🎤ኡስታዝ ኢብኑ ሙነወር

🎤ኡስታዝ ሙሐመድ ሲራጅ


ዳዕዋው የሚተላለፍበት ቻናል
https://t.me/MedrestuImamuAhmed
https://t.me/MedrestuImamuAhmed
https://t.me/MedrestuImamuAhmed


ቤታችንን ከሙንከር ነገሮች መጠበቅ

ሲጃራን፣ጫት፣ነሺዳ ሚባሉ ነገሮችን ከቤትሽ አጥፊ

ቀማቴ ባል፣የቃመ ተለቀመ፣ያልቃመ ተጠቀመ !

እስቲ ባልሽን የኔ ፍቅር፣የሀቢቢ
፣ያ ሀያቲ፣እወድሃለሁ የሚል ቃል ተጠቀሚ ምንም አትሆኚም ወሏሂ !

🎙በኡስታዝ አቡ ሙስሊም ሀፊዘሁላህ

https://t.me/Darutewhide


ተውሒድ እና ሽርክ

    ክፍል አስራ ዘጠኝ

12.8 ሺርክ ህይወትና ገንዘብን ሀላል ያደርጋል

      የአላህ መልክተኛﷺአንድ ሰው ገንዘቡ እና ህይወቱ በምን መንገድ ጥበቃ እንደሚነሳበት እንዲህ ሲሉ ይነግሩናል ፦

     “ሰዎችን እንድታገላቸው ታዝዣለሁ።ከአላህ በስተቀር በሀቅ የሚመለክ እውነተኛ አምላክ የለም ብለው እስኪመሰክሩ ድረስ።ይህን ካሉ ነፍሳቸው፣ገንዘባቸው የተጠበቀች ትሆናለች።የእስልምና መብት ሲቀር(የገደለ መገደልን ይመስል)...”

  12.9 ሺርክ ምድርንያበላሻል፣ያወድማል

    በዋናነት ምድር የምትበላሸው በሽርክ ነው።ይህን አስመልክቶ አላህ እንዲህ  ይለናል፦

وَلَا تُفْسِدُوا۟ فِى ٱلْأَرْضِ بَعْدَ إِصْلَٰحِهَا وَٱدْعُوهُ خَوْفًۭا وَطَمَعًا ۚ إِنَّ رَحْمَتَ ٱللَّهِ قَرِيبٌۭ مِّنَ ٱلْمُحْسِنِينَ
በምድርም ውስጥ ከተበጀች በኋላ አታበላሹ፡፡ ፈርታችሁና ከጅላችሁም ተገዙት፡፡ የአላህ ችሮታ ከበጎ አድራጊዎች ቅርብ ነውና፡፡(አል አዕራፍ 56)

      
ምድር የምትስተካከለው ነብያት ይዘውት በመጡት መልክት ነው።ነብያት ይዘውት የመጡት መልክት ደሞ ተውሒድ ነው ። ዛሬ አለም ሰልጥኗል ይባላል ነገር ግን አብዛኛው ሰው ብቸኛው ፈጣሪ በብቸኝነት ያመልካል ወይ?ፈጣሪውን ይፈራል ወይ ? ብቸኛውን ሲሳይን እና ሌሎች ነገሮችን ለጋሽ የሆነውን ብቸኛ አምላክ ያመሰግነዋል ወይ ?ፈጣሪውን ያውቀዋል ወይ ? አላህ  ለአለማት እዝነት አድርጎ በላካቸው ነብዩ ﷺ መልክት ይሠራበታል ወይስ ስሜቱን ተከትሎ ያልታዘዘውን ይሰራል ? እና የመሳሰለው ተብሎ ቢጠየቅ መልሱ አሳዛኝ ነው ሚሆነው።ዝሙት፣ገብረሰዶም፣ቁማር፣ ወለድ መስፋፋታቸው ምድርን ካበላሸ፣በአላህ ላይ ማጋራት እማ የባሰ ምድርን ማበላሸት ነው የሚሆነው። አላህ ምድርን ከማበላሸት ይጠብቀን።

13. በችግር ጊዜ አላህን እያመለኩ በሰላሙ ጊዜ ማጋራት ተውሒድ አይባልም

    ነብዩ ﷺ ጋር የተዋጉት የመካ አጋሪያን በችግር ጊዜ አላህን ብቻ የጠሩ ነበር ።ሆኖም ግን ይህ  በችግር ጊዜ ብቻ እሱን (አላህን ብቻ) መለመናቸው አማኝ አላስባላቸውም።አላህ ይህን አስመልክቶ እንዲህ ይላል፦
فَإِذَا رَكِبُوا۟ فِى ٱلْفُلْكِ دَعَوُا۟ ٱللَّهَ مُخْلِصِينَ لَهُ ٱلدِّينَ فَلَمَّا نَجَّىٰهُمْ إِلَى ٱلْبَرِّ إِذَا هُمْ يُشْرِكُونَ
በመርከቦች ውስጥ በተሳፈሩ ጊዜም አላህን መገዛትን ለእርሱ ብቻ ያጠሩ ኾነው ይጠሩታል፡፡ ወደ የብስ (በማውጣት) ባዳናቸው ጊዜም ወዲያውኑ እነርሱ (ጣዖትን) ያጋራሉ፡፡(አል ዐንከቡት 65)

በዘመናችን ሺርክ ላይ የወደቁ ሰዎች ግን ጥፋታቸው ቦታና ጊዜ እንኳን አይመርጥም። ከሳምንቱ ቀናት ውስጥ በሰላሙም ጊዜ በችግርም ጊዜ ከአላህ ውጭ ላሉ አካላት አምልኮን ሲፈፅሙ ይታያሉ።ቀናትን ማምለክ አስመልክቶ እንደ አካባቢው ቢለያይም ዋና ዋና የሆኑት የሚከተሉት ናቸው። ለምሳሌ ፦ሰኞ እስነይን፣ማክሰኞ የመገርገቢያው ፣እሮብ የጄይላኒ፣ሃሙስ የነቢ እድሪስ፣ቅዳሜ  የሰይድና ኸድር፣እሁድ የፈቂህ አሊ ሙዝ ወዘተ በማለት ያለገደብ ሺርክ ይፈፅማሉ።የተፈጠሩት ግን በሰላሙም በችግሩም ጊዜ አላህን በብቸኝነት እንዲያመልኩ ነው።

         ✍ሙሐመድ ኢብኑ ፈድሉ
   (ተውሒድ እና ሽርክ  ገፅ 38-40)
 
     “ኢንሻ አላህ ይቀጥላል”

የቴሌግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ👇
https://t.me/Darutewhide
https://t.me/Darutewhide


ሳምንትን እየጠበቁ ጁመዓ ሙባረክ ማለት ይቻላልን?

🎙 በኡስታዝ ሳዳት ከማል ሀፊዘሁላህ

https://t.me/Darutewhide


ዳእዋ ሰው አይቀይርም ደርስ ነው ሚያስፈልገው ይህ ምን የሚሉት ቋንቋ ነው ?


🎙በኡስታዝ ኢብኑ ሙነወር ሀፊዘሁላህ

https://t.me/Darutewhide


ተውሒድ እና ሽርክ

  ክፍል አስራ ስምንት


     12.5 የሺርክ አደጋ አስከፊነት

    የሺርክ አደጋው እጅግ ዘግናኝ ስለሆነ ነው ነብዩላህ ኢብራሂም እኔንም ልጆቼንም ጣኦትን ከማምለክ ጠብቀኝ ማለታቸው።

   የሺርክን አስከፊነት ለመረዳት ከሚረዱ ዋና ዋና ነጥቦች ውስጥ አንዱ አላህን ፍፁም ወዳጅ አድርጎ የያዛቸው፣ የነብያት አባት፣ነብዩላህ ኢብራሂም እኔንም ልጆቼንም ከሺርክ(ከጣኦት አምልኮ) አርቀን ማለታቸው ብቻ ይበቃል ። ነብዩላህ ኢብራሂም (አለይሂ ሠላም) ጌታቸውን ከሺርክ እንዲጠብቃቸው እንደለመኑት አላህ እንዲህ ሲል ይነግረናል ፦
وَإِذْ قَالَ إِبْرَٰهِيمُ رَبِّ ٱجْعَلْ هَٰذَا ٱلْبَلَدَ ءَامِنًۭا وَٱجْنُبْنِى وَبَنِىَّ أَن نَّعْبُدَ ٱلْأَصْنَامَ
ኢብራሂምም ባለ ጊዜ (አስታውስ) «ጌታዬ ሆይ! ይህንን አገር (መካን) ጸጥተኛ አድርገው፡፡ እኔንም ልጆቼንም ጣዖታትን ከመገዛት አርቀን፡፡
رَبِّ إِنَّهُنَّ أَضْلَلْنَ كَثِيرًۭا مِّنَ ٱلنَّاسِ ۖ فَمَن تَبِعَنِى فَإِنَّهُۥ مِنِّى ۖ وَمَنْ عَصَانِى فَإِنَّكَ غَفُورٌۭ رَّحِيمٌۭ
«ጌታዬ ሆይ! እነርሱ (ጣዖታት) ከሰዎች ብዙዎችን አሳስተዋልና፡፡ የተከተለኝም ሰው እርሱ ከኔ ነው፡፡ ትእዛዜንም የጣሰ ሰው አንተ መሓሪ አዛኝ ነህ፡፡[ኢብራሂም 35-36]

ዛሬ አንዳንድ “ዘመናዊ ነን፣ሰልጥነናል፣የዱንያ ትምህርት አለን፣የከተማ ሰዎች ነን”የሚሉ  ሸይጧን እና ነፍስያ የተጫወቱባቸው ግለሰቦች “ዘመን ሰልጥኗል፣“እንደኔ የተማሩት ን ሽርክ አያሰጋንም ወይንም የዚህን ቃል ፅንሰ  ሀሳብ የመሰለ የሚናገሩ ”፣ “ሽርክ እኮ ገጠር  ያሉ ሰዎች ላይ ነው ያለው ”እና የመሳሰለውን ምክንያት በመደርደር የሽርክን ነገር አቅልለው ሲያዩ ይታያሉ።ለነዚህ የዲን እውቀት አልባ ለሆኑ ሰዎች የምንላቸው መጀመሪያ ዲንን  ጠንቅቃችሁ እወቁ።አላህ ፍፁም ወዳጅ አድርጎ የያዘው ነብዩላህ ኢብራሂም “እኔንም ልጆቼንም ጣኦትን ከመገዛት አርቀን” ካለ እኛ ማን ነንና ሽርክን ለነፍሳችን እና ለቤተሰባችን ማንሰጋው ?አለ ማወቅ ከባድ አደጋ ነው።እጥፍ ድርብ የሆነው ከባድ አደጋ ደሞ እውቀትም እንደሌለንም አለማወቃችን ነው።

      12.6 ሺርክ ዘላለማዊ የጀነም ማገዶ      ያደርጋል

    ለዚህም ማስረጃው አጋሪያን ጀነት እንደማይገቡና ዘላለማዊ መኖርያቸው ጀሐነም እንደሆነ አላህ እንዲህ ሲል ይነግረናል፦
إِنَّهُۥ مَن يُشْرِكْ بِٱللَّهِ فَقَدْ حَرَّمَ ٱللَّهُ عَلَيْهِ ٱلْجَنَّةَ وَمَأْوَىٰهُ ٱلنَّارُ ۖ وَمَا لِلظَّٰلِمِينَ مِنْ أَنصَارٍۢ
እነሆ! በአላህ የሚያጋራ ሰው አላህ በርሱ ላይ ገነትን በእርግጥ እርም አደረገ፡፡ መኖሪያውም እሳት ናት፡፡ ለበዳዮችም ምንም ረዳቶች የሏቸውም፡፡

     የአላህ መልክተኛ ﷺ እንዲህ ይሉናል “ከአላህ ሌላ ያለን አካል (አጋርን) እየጠራ (እያመለከ) የሞተ እሳት ገባ ።” (ቡኻሪ ዘግበውታል)

   12.7 ሺርክ ከእስልምና ውጭ ያደርጋል

     ለዚህም ማስረጃው የሚከተለውን የአላህ (ሱብሃነሁ ወተአላ) ንግግር ነው።

وَلَا تَدْعُ مِن دُونِ ٱللَّهِ مَا لَا يَنفَعُكَ وَلَا يَضُرُّكَ ۖ فَإِن فَعَلْتَ فَإِنَّكَ إِذًۭا مِّنَ ٱلظَّٰلِمِينَ
«ከአላህም በቀር የማይጠቅምንና የማይጎዳን አትገዛ፡፡ ብትሠራም አንተ ያንጊዜ ከበደለኞቹ ትሆናለህ» (ተብያለሁ በላቸው)፡፡ (ዩኑስ:106)

     ታላቁ የተፍሲር ሊቅ ኢብኑ ጀሪር አጥ-ጦበሪይ እና ሌሎችም እንዳብራሩት “ከበደለኞች” የሚለው ቃል  ከአጋሪዎች ማለት እንደሆነ ጠቁመዋል።በዚህም የተነሳ ነው የኢስላም ሊቃውንቶች ሺርክ ከእስልምና ያስወጣል የሚሉት ።

         ✍ሙሐመድ ኢብኑ ፈድሉ
   (ተውሒድ እና ሽርክ  ገፅ 36-38)
 
     “ኢንሻ አላህ ይቀጥላል”

የቴሌግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ👇
https://t.me/Darutewhide
https://t.me/Darutewhide


ኡስታዝ ኢብኑ ሙነወር

ወከባ የለመዱ ሰዎች የሱና መርከዞች ዉስጥ እየተማሩ የለመዱትን ወከባ ሲያጡ እነዚህ ሙመይዐ ናቸዉ እያሉ ይከሳሉ

https://t.me/NABAWITUBE


ተውሒድ እና ሽርክ

    ክፍል አስራ ሰባት

   12.2. አብዛኛዎቹ የጠፉት አጋሪ ስለነበሩ ነው

    ሺርክ የአላህን ቁጣ መከናነቢያና የመጥፊያ ሰበብ መሆኑን አላህ እንዲህ ሲል ይነግረናል፦

ٱللَّهُ ٱلَّذِى خَلَقَكُمْ ثُمَّ رَزَقَكُمْ ثُمَّ يُمِيتُكُمْ ثُمَّ يُحْيِيكُمْ ۖ هَلْ مِن شُرَكَآئِكُم مَّن يَفْعَلُ مِن ذَٰلِكُم مِّن شَىْءٍۢ ۚ سُبْحَٰنَهُۥ وَتَعَٰلَىٰ عَمَّا يُشْرِكُونَ
አላህ ያ የፈጠራችሁ፣ ከዚያም ሲሳይን የሰጣችሁ፣ ከዚያም የሚገድላችሁ ከዚያም ሕያው የሚያደርጋችሁ ነው፡፡ ከምታጋሯቸው (ጣዖታት) ውስጥ ከዚህ ነገር አንዳችን የሚሠራ አለን ለአላህ ጥራት ይገባው፡፡ (በእርሱ) ከሚያጋሩትም ሁሉ ላቀ፡፡

ظَهَرَ ٱلْفَسَادُ فِى ٱلْبَرِّ وَٱلْبَحْرِ بِمَا كَسَبَتْ أَيْدِى ٱلنَّاسِ لِيُذِيقَهُم بَعْضَ ٱلَّذِى عَمِلُوا۟ لَعَلَّهُمْ يَرْجِعُونَ
የሰዎች እጆች በሠሩት ኃጢኣት ምክንያት የዚያን የሠሩትን ከፊሉን ያቀምሳቸው ዘንድ መከራው በየብስና በባሕር ተገለጠ፤ (ተሰራጨ)፡፡ እነርሱ ሊመለሱ ይከጀላልና፡፡

قُلْ سِيرُوا۟ فِى ٱلْأَرْضِ فَٱنظُرُوا۟ كَيْفَ كَانَ عَٰقِبَةُ ٱلَّذِينَ مِن قَبْلُ ۚ كَانَ أَكْثَرُهُم مُّشْرِكِينَ
«በምድር ላይ ኺዱ የእነዚያንም በፊት የነበሩትን ሰዎች መጨረሻ እንዴት እንደነበረ ተመልከቱ» በላቸው፡፡ አብዛኞቻቸው አጋሪዎች ነበሩ፡፡[አል ሩም 40-42]

12.3 ሺርክ ዘላለማዊ ህይወትን ያጠፋል

          አላህ በእሱ ላይ እያጋሩ የሞቱ ሰዎችን መኖርያቸው የጀሃነም እሳት ውስጥ እንደሆነ ብሎም መውጫ እንደሌላቸው እንዲህ ሲል ይነግረናል፦
لَقَدْ كَفَرَ ٱلَّذِينَ قَالُوٓا۟ إِنَّ ٱللَّهَ هُوَ ٱلْمَسِيحُ ٱبْنُ مَرْيَمَ ۖ وَقَالَ ٱلْمَسِيحُ يَٰبَنِىٓ إِسْرَٰٓءِيلَ ٱعْبُدُوا۟ ٱللَّهَ رَبِّى وَرَبَّكُمْ ۖ إِنَّهُۥ مَن يُشْرِكْ بِٱللَّهِ فَقَدْ حَرَّمَ ٱللَّهُ عَلَيْهِ ٱلْجَنَّةَ وَمَأْوَىٰهُ ٱلنَّارُ ۖ وَمَا لِلظَّٰلِمِينَ مِنْ أَنصَارٍۢ
እነዚያ «አላህ እርሱ የመርየም ልጅ አልመሲሕ ነው» ያሉ በእርግጥ ካዱ፡፡ አልመሲህም አለ፡- «የእስራኤል ልጆች ሆይ! ጌታዬንና ጌታችሁን አላህን ተገዙ፡፡» እነሆ! በአላህ የሚያጋራ ሰው አላህ በርሱ ላይ ገነትን በእርግጥ እርም አደረገ፡፡ መኖሪያውም እሳት ናት፡፡ ለበዳዮችም ምንም ረዳቶች የሏቸውም፡፡[አል ማኢዳህ 72 ]

        12.4 ሺርክ ሰላምን ያሳጣል

ነብዩላህ ኢብራሂም ለተላኩባቸው አጋሪያን  ምን እንዳላቸው ጌታችን እንዲህ ሲል ይነግረናል  ፦
وَكَيْفَ أَخَافُ مَآ أَشْرَكْتُمْ وَلَا تَخَافُونَ أَنَّكُمْ أَشْرَكْتُم بِٱللَّهِ مَا لَمْ يُنَزِّلْ بِهِۦ عَلَيْكُمْ سُلْطَٰنًۭا ۚ فَأَىُّ ٱلْفَرِيقَيْنِ أَحَقُّ بِٱلْأَمْنِ ۖ إِن كُنتُمْ تَعْلَمُونَ
«በእናንተ ላይ በእርሱ ማስረጃን ያላወረደበትን እናንተ ማጋራታችሁን የማትፈሩ ስትኾኑ የምታጋሩትን (ጣዖታት) እንዴት እፈራለሁ! የምታውቁም ብትኾኑ ከሁለቱ ክፍሎች በጸጥታ ይበልጥ ተገቢው ማንኛው ነው» (አለ)፡፡

ٱلَّذِينَ ءَامَنُوا۟ وَلَمْ يَلْبِسُوٓا۟ إِيمَٰنَهُم بِظُلْمٍ أُو۟لَٰٓئِكَ لَهُمُ ٱلْأَمْنُ وَهُم مُّهْتَدُونَ
እነዚያ ያመኑና እምነታቸውን በበደል ያልቀላቀሉ እነዚያ ለእነርሱ ጸጥታ አላቸው፡፡ እነሱም የተመሩ ናቸው።[አል አንዓም :81-82]

         ✍ሙሐመድ ኢብኑ ፈድሉ
   (ተውሒድ እና ሽርክ  ገፅ 34-36)
 
     “ኢንሻ አላህ ይቀጥላል”

የቴሌግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ👇
https://t.me/Darutewhide
https://t.me/Darutewhide


ተውሒድ እና ሽርክ
 
     ክፍል አስራ ስድስት


    እስቲ ልብ ብለን እንመልከት ነብዩ

✅ ለተውሒድ ሲሉ አገር ለቀው ተሰደው ፣

✅ ሴት ልጆቻቸው ትዳራቸው ተፈቶ ፣

✅ ጥርሳቸው ተሰብሮ ፣

✅ እግራቸው ደምቶ ፣

✅ ማንም ላይ ያልደረሰ ፈተና ደርሶባቸው ፣

✅ ለአላህ በማመስገን ሰላት ላይ
ከመቆማቸው ብዛት የተነሳ እግራቸው
ተሰነጣጥቆ ፣

✅ ስንት መከራዎችን ታግሰው ፣

✅ ስንት መልካሞችን ሰርተው ፣

✅ በሰሃቦች አንደበት  “(ከአላህ)  የተላክበትን መልክት አድርሰሃል ፣ አደራህን ተወጥተሀል ፣ኡማውን መክረሃል ” ተብሎላቸው፣ይህ  ሁሉ ከመሆኑ ጋር አላህ “ብታጋራ ስራህ ሁሉ ውድቅ ይሆናል ” አላቸው።ታድያ የአላህ ባርያዎች ሆይ !እኛስ ምን ይዋጠን ? ለምንድ ነው ለተውሒድ ትምህርት ተገቢው ትኩረት የማይሰጠው ? ለምን ይሆን ስራን ሁሉ አመድ የሚያስገባውን ሽርክ ከምንም በላይ የማንጠነቀቀው ?

        አለማዊ ስሌት።
 
     በሂሳብ ትምህርት እንደሚታወቀው ማባዛት ሚባል ነገር አለ ማንኛውም ቁጥር በዜሮ ከተባዛ እራሱን ዜሮን ነው የሚሰጠው። ለምሳሌ፦

                     1×0=  0

                  100×0= 0

              100,000×0= 0
           
         1,000,000×0=  0

     1,000,000,000×0= 0

     የሽርክም መጨረሻው ይህ ነው። ሰውየው እምነቱ ሳይስተካከል ቢለፋ ቢለፋ መጨረሻው ላይ ይኸው ለፍቶ መሆን ነው።ሰውየው ሽርክ ሳይቀላቀልበት ተሰርቶ የተቀመጠ መልካም ስንትና ስንት ምንዳ ያለው ስራ ቢኖረውም ትልቁ ሽርክ ሲቀላቀልበት እንዲሁ ዜሮ ያስቀረዋል። ሽርክ ስራችንን አመድ እንዳያደርግብን ከባድ ጥንቃቄ ማድረግ ግድ ይላል። በእምነት መካድ ምን እንደሚያስከትል አላህ እንዲህ ይለናል ፦

وَمَن يَكْفُرْ بِٱلْإِيمَٰنِ فَقَدْ حَبِطَ عَمَلُهُۥ وَهُوَ فِى ٱلْـَٔاخِرَةِ مِنَ ٱلْخَٰسِرِينَ
ከእምነትም የሚመለስ ሰው በእርግጥ ሥራው ተበላሸ፡፡ በመጨረሻም ቀን እርሱ ከከሳሪዎቹ ነው፡፡[አል-ማኢዳህ:5]

አላህ ሆይ !ወደ ወዱ የተውሒድ መንገድ ምራን ፣ ከእርኩሱ ሺርክም እኛንም ዝርያዎቻችንንም ጠብቀን። በተውሒድ መንገድ ላይ ግደለን።

          ✍ሙሐመድ ኢብኑ ፈድሉ
   (ተውሒድ እና ሽርክ  ገፅ 32-34)
 
     “ኢንሻ አላህ ይቀጥላል”

የቴሌግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ👇
https://t.me/Darutewhide
https://t.me/Darutewhide


ሸርን የፈጠረው አላህ ነው ወይስ ሸይጣን ?

ከኡስታዝ ኢብኑ ሙነወር ጋር የተፋጠጠው ቁርአኒ ግለሰብ

🎙በኡስታዝ ኢብኑ ሙነወር ሀፊዘሁላህ

https://t.me/Darutewhide


ተውሒድ እና ሽርክ

ክፍል አስራ አምሰት


12 የሺርክ አደጋዎች

     12.1  ስራዎችን ሁሉ ያበላሻል

መቼም የምርጥም ምርጥ አለው። አላህ የአደምን ልጅ አልቆታል። ከአደም ልጆች ውስጥ ደግሞ መልክተኞቹና ነብያቱን አስበልጧል።ነብያቱና መልክተኞቹ ከሰዎች ጥቅምን ሳይፈልጉ ከአዛኙ አላህ የሚወርድላቸውን መለኮታዊ ራእይ ለፍጡራኑ ለማድረስ በድብቅም በግልፅም፣በቀንም በማታም ደፋ ቀና ያሉና የለፉ ናቸው።የአላህን መልእክት ለማድረስ ሲሉ ስንት ከባድ አደጋ በህይወታቸው፣በንብረታቸው፣በቤተሰቦቻቸው ላይ የደረሰባቸውና ስንት መስዋእት የከፈሉ፣ስንትና ስንት ገደል የፈፀሙ ናቸው።

ግን ይህ ሁሉ ከመሆኑ ጋር ሺርክ የሚባለው ነገር ቢፈፅሙ ስራቸው ሁሉ እንደሚታበስ ጌታችን እንዲህ ሲል ነግሮናል፦

ذَٰلِكَ هُدَى ٱللَّهِ يَهْدِى بِهِۦ مَن يَشَآءُ مِنْ عِبَادِهِۦ ۚ وَلَوْ أَشْرَكُوا۟ لَحَبِطَ عَنْهُم مَّا كَانُوا۟ يَعْمَلُونَ
ይህ የአላህ መምሪያ ነው፡፡ በእርሱ ከባሮቹ የሚሻውን ሰው ይመራል፡፡ ባጋሩም ኖሮ ይሠሩት የነበሩት ከነሱ በታበሰ ነበር፡፡(አል -አንዓም :88)

የአላህ ባርያዎች ሆይ! ከአንቀፁ በፊት ልብ እንበል አላህ የነዚህን ነብያት ገድል ተናግሮላቸዋል።አላህ እዚህ ጋር  ቢያጋሩም ኖሮ ይሰሩት የነበሩት ከነሱ በታበሰ ነበር ብሎ የጠቀሳቸው 18 ነብያት የሚከተሉት ናቸው ፦

   አላህ ፍፁም ወዳጅ አድርጎ የያዛቸው ነብዩላህ ኢብራሒም- አል ኸሊል ፣ነብዩላህ ኢስሐቅ ፣ነብዩላህ ያዕቁብ፣ነብዩላህ ኑሕ፣ነብዩላህ ዳውድ፣ነብዩላህ ሱለይማን፣ነብዩላህ አዩብ፣ነብዩላህ ዩሱፍ፣ አላህ ያናገራቸው ነብዩላህ ሙሳ፣ነብዩላህ ሃሩን፣ነብዩላህ ዘከሪያ፣ከሳቸው በፊት ሞክሼ የሌላቸው ነብዩላህ የሕያ፣ በአላህ ፍቃድ ለምጣምን ያዳኑት ፣የሞተን የቀሰቀሱት የመርየም ልጅ ነብዩላህ ዒሳ፣ነብዩላህ ኢልያስ፣ካዐባን ከአባታቸው ኢብራሒም ጋር የገነቡት፣ከአባታቸው ጋር ለአላህ ትዕዛዝ እጃቸውን በመስጠት ሊታረዱ የነበሩት ነብዩላህ ኢስማኤል፣ነብዩላህ የሰዕ፣ ነብዩላህ ዩኑስ፣ነብዩላህ ሉጥ ናቸው።እሺ እኛስ ከዚህ ምን ትምህርት እንወስዳለን ?

    ምንም አይነት ምድራዊ ጥቅምን ሳያልሙ “አላህን ብቻ በብቸኝነት አምልኩ ከእርሱ ውጭ ያሉትን ማንንም ይሁን ምንንም ራቁ ”፣ ወገኖቼ ሆይ ! አላህን በብቸኝነት አምልኩ። ከእርሱ ሌላ ምንም አምላክ የላችሁም” እያሉ ለተውሒድ የተዋደቁ የአላህ ምርጥ ባሮች እንዲህ ከተባሉ እኛስ ምን እንባል ? ሌላ ምሳሌ አላህ ሊጨምርልን ነው ።የአላህ ውድ፣የነብያት ሁሉ መደምደሚያ ፣የታላቁ ምልጃ ባለቤት፣ለአለማት እዝነት የተላኩ፣የአደም ልጆች ሁሉ ምርጥ፣ታላቁ የተውሒድ አስተማሪ ፣የኢብራሒም መንገድ ተከታይ ፣ነብዩ ሙሐመድ አበል ቃሲም  አላህ እንዲህ አላቸው፦

وَلَقَدْ أُوحِىَ إِلَيْكَ وَإِلَى ٱلَّذِينَ مِن قَبْلِكَ لَئِنْ أَشْرَكْتَ لَيَحْبَطَنَّ عَمَلُكَ وَلَتَكُونَنَّ مِنَ ٱلْخَٰسِرِينَ
ብታጋራ ሥራህ በእርግጥ ይታበሳል፡፡ በእርግጥም ከከሓዲዎቹ ትኾናለህ ማለት ወደ አንተም ወደእነዚያም ካንተ በፊት ወደነበሩት በእርግጥ ተወርዷል፡፡

ይሄ እኛን ለማስተማሪያ እንጂ እሳቸው ከሺርክ የፀዱ ናቸው።እንዲያውም እኛን በአላህ ፍቃድ ከሽርክ ጨለማ አውጥተው ወደ ተውሒድ ብርሀን ( በማስተማር) ሊመሩ የመጡ ናቸው።ግን ሱብሃነላህ ሺርክን ምን ያህል ከባድ እንደሆነና ስራን ሁሉ ድምጥማጡን እንደሚያጠፋ ከእንደዚህ አይነት ምሳሌዎች በላይ ምን ይምጣ ? !!!

    ✍ሙሐመድ ኢብኑ ፈድሉ
   (ተውሒድ እና ሽርክ  ገፅ 30-32)
 
     “ኢንሻ አላህ ይቀጥላል”

የቴሌግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ👇
https://t.me/Darutewhide
https://t.me/Darutewhide


ኢኽዋን ስንት አመት ሆነው ከመጣ?

ተብሊግ ስንት አመት ሆነው ከመጣ?

ይደመጥ ከኡስታዝ ጋር ፈገግ እያላችሁ

🎙በኡስታዝ ሳዳት ከማል ሀፊዘሁላህ

https://t.me/Darutewhide


ተውሒድ እና ሽርክ
 
      ክፍል አስራ አራት

የሽርክ ምሳሌዎች ፦

   11.1.  በውዴታ ማጋራት

      ውዴታ ከአምልኮ ክፍሎች ውስጥ ነው።አምለኮታዊ ውዴታ ለአላህ ብቻ ነው የሚገባው። ከአላህ ወጭ ያሉትን ለአላህ ስንል ነው የምንወዳቸው። ለምሳሌ መላኢካዎችን ጅብሪልን ይመስል፣ነብያትን፣ነብዩ ሙሐመድን ﷺ  ይመስል፣ደጋጎችን አቡ - በክር፣ዑመር፣ዑስማን፣ዐልይ፣ሰሃባዎች እና የመሳሰሉትን አማኞች የምንወዳቸው ለአላህ ስንል ነው።

        ከሰዎች ግን በውዴታ የሚያጋሩ አሉ።አላህ እንዲህ ይላል፦

وَمِنَ ٱلنَّاسِ مَن يَتَّخِذُ مِن دُونِ ٱللَّهِ أَندَادًۭا يُحِبُّونَهُمْ كَحُبِّ ٱللَّهِ ۖ وَٱلَّذِينَ ءَامَنُوٓا۟ أَشَدُّ حُبًّۭا لِّلَّهِ
ከሰዎችም ከአላህ ሌላ ባለንጣዎችን (ጣዖታትን) አላህን እንደሚወዱ የሚወዷቸው ኾነው የሚይዙ አልሉ፡፡ እነዚያ ያመኑትም አላህን በመውደድ (ከነርሱ) ይበልጥ የበረቱ ናቸው፡፡[አል-በቀራህ:165]

     እዚህ ጋር አንድ ልብ ሊባል የሚገባው ነገር አለ ወዴታ ሁለት አይነት ነው።

አምልኮታዊ ውዴታ፦  አምልኮታዊ ላይ አላህ ብቻ ነው ለዛቱ ሲባል ሊወደድ የሚገባው

ተፈጥሯዊ ወዴታ ፦አላህ የሰው ልጅ ላይ ስሜትና ባህርይ አድርጎለታል። ሰለዚህ አንድ ወንድ ሚስቱን ቢወድ ሺርክ ሰራ አይባልም።አንድ ሚስት ባልዋን ብትወደው፣ቤተሰብ ልጁን ቢወድ፣ልጆች ወላጆቻቸውን ቢወዱ ሺርክ ሰሩ አይባልም።ምክንያቱም ይሄ ተፈጥሯዊ ህግ ነውና።

      ለአላህ እና ለመልክተኛው ﷺ  ያለንን ውዴታ የምንገልፀው እነሱ ያዘዙንን በመፈፀም ፣የከለከሉንን በመከልከል ነው።ሰለ ወዴታ ከተነሳ አይቀር ከሱና ጋር የተቆራኘውን የፈተና አንቀፅ እንያት።

قُلْ إِن كُنتُمْ تُحِبُّونَ ٱللَّهَ فَٱتَّبِعُونِى يُحْبِبْكُمُ ٱللَّهُ وَيَغْفِرْ لَكُمْ ذُنُوبَكُمْ ۗ وَٱللَّهُ غَفُورٌۭ رَّحِيمٌۭ
በላቸው፡- «አላህን የምትወዱ እንደኾናችሁ ተከተሉኝ፤ አላህ ይወዳችኋልና፡፡ ኀጢኣቶቻችሁንም ለናንተ ይምራልና፡፡ አላህም መሓሪ አዛኝ ነው፡፡»[አል-ኢምራን

     11.2. በመታዘዝ ማጋራት

        በመታዘዝ ማጋራት የሚለው ላይ መጠቆም የፈለኩት በብዛት ከጭፍን ተከታይነት የሚመጣውንና ሰዎች ሸይክ፣ዑለማ ወይንም አሚር ብለው የወሰዱትን አካል  አላህ ሀራም ያደረገውን ሃላል ሲያደርግላቸው አሚን ብለው ይቀበሉታል። ከዛም አልፎ ይፈፅሙታል።ይሄ በአላህ ላይ ከማጋራት ውስጥ ነው። እስቲ የሚከተለውን ግልፅ መለኮታዊ ቃል በደምብ እንየው፦

ٱتَّخَذُوٓا۟ أَحْبَارَهُمْ وَرُهْبَٰنَهُمْ أَرْبَابًۭا مِّن دُونِ ٱللَّهِ وَٱلْمَسِيحَ ٱبْنَ مَرْيَمَ وَمَآ أُمِرُوٓا۟ إِلَّا لِيَعْبُدُوٓا۟ إِلَٰهًۭا وَٰحِدًۭا ۖ لَّآ إِلَٰهَ إِلَّا هُوَ ۚ سُبْحَٰنَهُۥ عَمَّا يُشْرِكُونَ
ከእርሱ በቀር ሌላ አምላክ የሌለውን አንድን አምላክ ሊገዙ እንጂ ያልታዘዙ ሲኾኑ ሊቃውንቶቻቸውንና መነኮሳታቸውን፣ የመርየምን ልጅ አልመሲሕንም ከአላህ ሌላ አማልክት አድርገው ያዙ፡፡ ከሚያጋሩት ሁሉ የጠራ ነው፡፡[አት-ተውባህ:31]

የተሰመረበትን በደንብ መመልከት ይሻል።የታዘዙትን አላህ ሃላል ያደረገውን ሃላል በማድረግ፣አላህ ሃራም ያደረገውን ሃራም በማድረግ፣ያለ ማጋራት አንድን አምላክ ሊገዙ ነው።እነርሱ ግን ይህን ትተው ከአላህ ውጭ ያሉትን ተገዙ።ይህ ትምህርት በደንብ እንዲገባን ታላቁ አስተማሪያችን ነብዩ ሙሐመድ ዘንድ ዐዲይ ኢብን ሃቲም የተባለ ሰሃባ መጥቶ እሳቸው ይህንን አንቀፅ ሲያነቡ“እነሱ እኮ አያመልኳቸውም ” አላቸው። ነብዩም ﷺ  “አላህ ሐራም ያደረገውን ሐላል ሲያደርጉላቸው አላህ ሐላል ያደረገውን ሐራም ሲያደርጉባቸው ይቀበሉ የለምን? አሉ። እርሱም “አዎን” አለ። እሳቸውም፦  “ታድያ ይህ እኮ ነው እነሱን ማምለክ ማለት” አሉ። ስለዚህ ከዚህም ኡማ ይህን ተግባሮ የሚፈፅም ካለ ተመሳሳይ ጥፋት (ማጋራት) ላይ ወድቋል ማለት ነው።

    እንግዲህ ነብዩ ﷺ የሺርክን አይነቶች አንድም ሳይቀር እንዲህ ፍንትውና ብትንትን አድርገው አስረድተዋል።

        ✍ሙሐመድ ኢብኑ ፈድሉ
   (ተውሒድ እና ሽርክ  ገፅ 27-30)
 
     “ኢንሻ አላህ ይቀጥላል”

የቴሌግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ👇
https://t.me/Darutewhide
https://t.me/Darutewhide


አህለል ሱንና ወልጀመዓ መለያቸው ምንድን ነው?

ሰለፊ ነን ሲሉ ትሰማቸዋለህ

ጣሀም እኮ ጀለቢያ ያደርጋል ጥምጣም ያደርጋል ከነ ሽርኩ ጋር ማለት ነው

🎙 በኡስታዝ ሳዳት ከማል ሀፊዘሁላህ

https://t.me/Darutewhide


መንገደኛ ሰው መፆሙ ነው ማፍጠሩ በላጩ ?

ስንት ኪሎ ሜትር የተጓዛ ሰው ነው ማፍጠር ሚቻልለት ?

🎙በኡስታዝ ኢብኑ ሙነወር

https://t.me/Darutewhide


ተውሒድ እና ሽርክ

    ክፍል አስራ ሶስት

   የማይሞተው ህያው አላህን ትተው ሙታንን የሚያመልኩ ሰዎች “ከአላህ ውጭ ያለን ምንንም አትጥሩ፣አትለምኑ ይህ ተግባራችሁ ሽርክ ነው።አላህ ብቻ ነው በሃቅ ሊመለክ የሚገባው ”ሲባሉ አሻፈረን ይላሉ። ዘወትር በሰላታቸው፦ “አንተን ብቻ እናመልካለን።በአንተም ብቻ እንታገዛለን” ማለታቸውን ይዘነጋሉ። በዚህ መልኩ ሲገሰጹም  “ለምንድን ነው ታድያ ወደ ዶክተር የምትሄዱት” ሲሉ የሚመልሱ አሉ። የእኛ መልስ ግን “ታድያ ለምንድን ነው ወደሞተ ዶክተር የማትሄዱት?የሚል ነው?

     ሙታን አምላኪዎች ተውሒድን አልተረዱም።እንዲህ አይነት የማይገናኝ ጥያቄ እያነሱ ፈተና ውስጥ ይድቃሉ።እውነትም ከኢብራሂም አለይሂ ሰላም መንገድ ከተውሒድ ያፈነገጠ ቂል ነው።

   ሰዎችን ሺርክን በሚገባ እንዳይጠነቀቁት የሚያደርጋቸው ጉዳዩን አርቀው መመልከታቸው ነው። እውነታው ግን ከምናስበው የቀረበ ነው።እስኪ ይህን በርካታ ሙስሊሞች የሚያደምጡትን መንዙማ እንታዘብ ፦

     “ያቀመረል መካ አሰላሙ አለይካ፣
     
      ልቤ ባንቱ በእርሶ ተመካ

ሌላ የሺርክ አዋጅ በስፋት ከሚደመጡ መንዙማዎች ውስጥ

     “ሰለፍም ኸለፍም ማወረአል በህር ፣
      በሁሉም ሸሸሁኝ አንድ እንኳን ሳይቀር
      ከዛፍ ከቅጠሉ በዝትብኛል ነውር ፣
     እሜዳው ላይ ሆኜ ወድቄ በዱር ፣
     መግቢያ በር አጥቼ ታግቼ ባጥር፣
    አልሄድ ወደ ፊት ዘደ ኅላ አልበር ፣
    በቀኝ በግራዬ እሳት ገደል ባህር፣
   አቤት ጠራኋችሁ ጌቶቼ  ዱስቱር ፣
  ረዳቴ ማን ነው ከናንተ በቀር።”

  አሁንም ሌላኛው የሽርክ መንዙ
ማ እንዲህ ይላል

        “ሀቢቢ ሀቢቢ ሀቢቢ ፣
         መዲና ና ይበሉኝ።”

ይህን አደጋ ተመልከቱ ።የፍጡራን ሁሉ ረዳት አላህ ብቻ ነው።የፍጡራን ሁሉ መጠጊያ አላህ ብቻ ነው።አለምን የሚያስተናብረው አላህ ብቻ ነው።አላህ እንዲህ ይላል፦

أَلَيْسَ ٱللَّهُ بِكَافٍ عَبْدَهُۥ ۖ وَيُخَوِّفُونَكَ بِٱلَّذِينَ مِن دُونِهِۦ ۚ وَمَن يُضْلِلِ ٱللَّهُ فَمَا لَهُۥ مِنْ هَادٍۢ
አላህ ለባሪያውን በቂ አይደለምን? በእነዚያ ከእርሱ ሌላ በኾኑትም (ጣዖታት) ያስፈራሩሃል፡፡ አላህ የሚያጠመውም ሰው ለርሱ ምንም አቅኚ የለውም፡፡[አዝ-ዙመር:39]
አማኞች ሰላት ላይ ሆነው በተደጋጋሚ እንዲህ ሲሉ ቃል ይገባሉ ፦

إِيَّاكَ نَعْبُدُ وَإِيَّاكَ نَسْتَعِينُ
አንተን ብቻ እንግገዛለን፤ አንተንም ብቻ እርዳታን እንለምናለን፡፡

وَتَوَكَّلْ عَلَى ٱلْحَىِّ ٱلَّذِى لَا يَمُوتُ وَسَبِّحْ بِحَمْدِهِۦ ۚ وَكَفَىٰ بِهِۦ بِذُنُوبِ عِبَادِهِۦ خَبِيرًا
በዚያም በማይሞተው ሕያው አምላክ ላይ ተመካ፡፡ ከማመስገንም ጋር አጥራው፡፡ በባሮቹ ኀጢኣቶችም ውስጠ ዐዋቂ በእርሱ በቃ፡፡[አል ፉርቃን:58]

       በየትኛውም ዘመን ከአላህ ውጭ የሚመለኩት ሁሉ ይህንን የሚያሟሉ አይደሉም።ሁሉም  የአላህ ፍጡሮች ናቸው፣ሁሉም ሟቾች ናቸው፣ ሁሉም ጠፍተው የልቅናና የንግስና ባለቤት የሆነው የጌታ የአላህ ፊት ይቀራል።
   አማኞች በአላህ ላይ ብቻ መመካት እንዳለባቸው አላህ እንዲህ ሲል ይነግረናል ፦
إِن يَنصُرْكُمُ ٱللَّهُ فَلَا غَالِبَ لَكُمْ ۖ وَإِن يَخْذُلْكُمْ فَمَن ذَا ٱلَّذِى يَنصُرُكُم مِّنۢ بَعْدِهِۦ ۗ وَعَلَى ٱللَّهِ فَلْيَتَوَكَّلِ ٱلْمُؤْمِنُونَ
አላህ ቢረዳችሁ ለእናንተ አሸናፊ የለም፡፡ ቢያዋርዳችሁም ያ ከርሱ (ማዋረድ) በኋላ የሚረዳችሁ ማነው በአላህም ላይ ብቻ ምእምናን ይመኩ፡፡[አል-ኢምራን:160]

  ልክ እንዲሁ አላህ ብቻ ሊፈራ ሲገባው ከአላህ ውጭ ያሉ አካላትን መፍራት ለምሳሌ ፦ጂንን ይመታኛል፣ ሸሆቹ ልጄን ይቀሙኛል፣ ሃብቴን ያወድሙብኛል፣እንዲህ ያደርጉኛል ብሎ መፍራት ሺርክ ነው

           ✍ሙሐመድ ኢብኑ ፈድሉ
   (ተውሒድ እና ሽርክ  ገፅ 25-27)
 
     “ኢንሻ አላህ ይቀጥላል”

የቴሌግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ👇
https://t.me/Darutewhide
https://t.me/Darutewhide

Показано 20 последних публикаций.

234

подписчиков
Статистика канала