🔷 ሴት ልጅ ከህፃናት መቼ ነው የምትሸፈነው ?
ይህ ነጥብ ብዙዎች ዘንድ ትኩረት ያልተሰጠው ነጥብ ነው ። አብዛኞች የሚያስቡ አንድ ልጅ አካለ መጠን እስካልደረሰ ድረስ ከሱ መሸፈን ግዴታ አይመስላቸውም ። ነገር ግን ለዚህ ጥያቄ አላህ በተከበረው ቃሉ መልስ ሰጥቶበታል ::
ይኸውም በሱረቱ አንኑር 31ኛ አንቀፅ ላይ እንዲህ በማለት ነው :-
« وَقُل لِّلْمُؤْمِنَاتِ يَغْضُضْنَ مِنْ أَبْصَارِهِنَّ وَيَحْفَظْنَ فُرُوجَهُنَّ وَلَا يُبْدِينَ زِينَتَهُنَّ إِلَّا مَا ظَهَرَ مِنْهَا ۖ وَلْيَضْرِبْنَ بِخُمُرِهِنَّ عَلَىٰ جُيُوبِهِنَّ ۖ وَلَا يُبْدِينَ زِينَتَهُنَّ إِلَّا لِبُعُولَتِهِنَّ أَوْ آبَائِهِنَّ أَوْ آبَاءِ بُعُولَتِهِنَّ أَوْ أَبْنَائِهِنَّ أَوْ أَبْنَاءِ بُعُولَتِهِنَّ أَوْ إِخْوَانِهِنَّ أَوْ بَنِي إِخْوَانِهِنَّ أَوْ بَنِي أَخَوَاتِهِنَّ أَوْ نِسَائِهِنَّ أَوْ مَا مَلَكَتْ أَيْمَانُهُنَّ أَوِ التَّابِعِينَ غَيْرِ أُولِي الْإِرْبَةِ مِنَ الرِّجَالِ أَوِ الطِّفْلِ الَّذِينَ لَمْ يَظْهَرُوا عَلَىٰ عَوْرَاتِ النِّسَاءِ ۖ وَلَا يَضْرِبْنَ بِأَرْجُلِهِنَّ لِيُعْلَمَ مَا يُخْفِينَ مِن زِينَتِهِنَّ ۚ وَتُوبُوا إِلَى اللَّهِ جَمِيعًا أَيُّهَ الْمُؤْمِنُونَ لَعَلَّكُمْ تُفْلِحُونَ »
النور ( 31 )
" ለምእምናትም ንገራቸው ፡- ዓይኖቻቸውን ይከልክሉ፡፡ ብልቶቻቸውንም ይጠብቁ ፡፡ ጌጣቸውንም ከእርሷ ግልጽ ከኾነው በስተቀር አይግለጡ ፡፡ ጉፍታዎቻቸውንም በአንገትጌዎቻቸው ላይ ያጣፉ ፡፡ (የውስጥ) ጌጣቸውንም ለባሎቻቸው ወይም ለአባቶቻቸው ወይም ለባሎቻቸው አባቶች ወይም ለወንዶች ልጆቻቸው ወይም ለባሎቻቸው ወንዶች ልጆች ወይም ለወንድሞቻቸው ወይም ለወንድሞቻቸው ወንዶች ልጆች ወይም ለእህቶቻቸው ወንዶች ልጆች ወይም ለሴቶቻቸው ወይም እጆቻቸው ለያዙት (ባሪያ) ወይም ከወንዶች ለሴት ጉዳይ የሌላቸው ለኾኑ ተከታዮች ወይም ለነዚያ በሴቶች ሐፍረተ ገላ ላይ ላላወቁ ሕፃኖች ካልኾነ በስተቀር አይግለጹ ፡፡ ከጌጣቸውም የሚሸፍኑት ይታወቅ ዘንድ በእግሮቻቸው አይምቱ ፡፡ ምእመናኖች ሆይ! ትድኑ ዘንድ ሁላችሁም ወደ አላህ (በመመለስ) ተጸጸቱ " ፡፡
በዚህ አንቀፅ ላይ
" ለእነዚያ በሴቶች ሐፍረተ ገላ ላይ ላላወቁ ህፃናት " ብሎ አስቀምጦታል ።
ሸኽ ሙሐመድ ኢብኑ ሷሊህ አል ዑሰይሚን - ረሒመሁላሁ - የዚህ ህፃን መለያው ብለው አራት ነገሮችን ያስቀምጣሉ ። እነርሱም : –
1ኛ - ስለ አንድ ሴት ለሌላ መግለፁ
2ኛ - ቆንጆዋን ከፉንጋዋ መለየቱ
3ኘ - ሴቶችን በተለያየ ገፅታቸው ማነፃፀሩ
4ኛ - ሴትን በደንብ መመልከቱ
ነው ይላሉ ።
ሌላው ሸይኽ ኢብኑ ባዝ – ረሒመሁላሁ – ሴት ልጅ ለዘመዶቿ ( ለመሕረሞቿ ) ማሳየት የሚፈቀድላት የአካላቷ ክፍል የሚከተሉት ናቸው ይላሉ : –
– እጇ እስከ ክርኗ
– እግሯ እስከ ቅልጥሟ
– ከአንገቷ በላይ ፊቷ ፀጉሯ ጆሮዋና የመሳሰሉት ሲሆን
– ከአንገቷ በታች ማሳየት አይፈቀድላትም ። እንዲሁም ስስና ጠባብ ልብስም መልበስም አይፈቀድላትም ።
አላህ አውቀው ከሚሰሩት ያድርገን ።
http://t.me/bahruteka