📌ከብአዴን ማእከላዊ ኮሚቴ የተሰጠ መግለጫ
.
.
.
.
.
👉የብሄረ አማራ ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ (ብአዴን) ማእከላዊ ኮሚቴ ነሃሴ 17 እና 18 ቀን 2010 ዓ.ም ለሁለት ቀናት ባካሄደው መደበኛ ስብሰባ በብአዴን 12ኛ መደበኛ ድርጅታዊ ጉባኤ ረቂቅ ሪፖርትና ለጉበዔው በሚቀርቡ ሌሎች ወቅታዊና መደበኛ ጉዳዮች ላይ ተወያቶ የተለያዩ ውሳኔዎችን አሳልፏል፡፡
የብአዴን 12ኛ ድርጅታዊ ጉባኤ በህዝቡ ሁለንተናዊ ተሳትፎና ባለቤትነት በሀገር ደረጃና ብአዴን በሚመራው የአማራ ክልል የተጀመረውን የለውጥ ጉዞ አጠናክሮ ለማስቀጠል ወሳኝና ታሪካዊ ጊዜ ላይ የሚካሄድ መሆኑን ታሳቢ በማድረግ ድርጅቱ የመሪነት ሚናውን ከምንጊዜውም በላይ አጠናክሮ ለማስቀጠል የሚያስችሉ አቅጣጫዎችና ውሳኔዎች ለጉባኤው እንዲቀርቡ ጥልቀት ያለው ውይይት ካካሄደ በኋላ በጉበዔ አጀንዳወችና በሌሎች ጉዳዮች ስምምነት ላይ በመድረስ የሚከተሉትን ውሳኔወች አስተላልፋል፡፡
1⃣በመቀጣጠል ላይ ያለውን ክልላዊና ሃገራዊ ለውጥ ለመጠበቅ፣ መሰረቱን ለማስፋትና ቀጣይነቱን ለማረጋገጥ እንዲቻል ትልቅ ፋይዳ ያላቸው ፖለቲካዊ፣ ኢኮኖሚያዊና ሕጋዊ የለውጥ እርምጃዎች በተከታታይ ይወሰዳሉ፡፡ በዚህ ሂደት ብአዴን የደረስንበት መድረክ የሚጠይቀውን ደረጃ ያሟላ ተመራጭ የፖለቲካ ድርጅት ሆኖ በመገኘት የክልሉን፤ ብሎም የሃገራችንን ህዝብ የዲሞክራሲና የልማት ጥያቄወች ከፍ ባለ ደረጃና በዘላቂነት እየመለሰ ግንባር ቀደም አታጋይ ድርጅት ለመሆን ቆርጦ የተነሳ መሆኑን ለመላው የአማራ ህዝብ፣ ለድርጅቱ አባላትና አመራሩ በዚህ ታሪካዊ አጋጣሚ ያበስራል፡፡
2⃣የአማራን ህዝብ ታሪክ፣ ትግል፣ ባህል እና ስነ ልቦና በአግባቡ የተገነዘበና የተረዳ፣ እንዲሁም አሁን ከተፈጠረው አዳጊ ሀገራዊና ክልላዊ ሁኔታ ጋር አብሮ የሚራመድ የፖለቲካ ፕሮግራምና መተዳደሪያ ደንብ እንዲኖር ማድረግ አስፈላጊ ሆኖ በመገኘቱ ድርጅቱ ቀደም ሲል ሲመራበት የነበረው ፕሮግራምና መተዳደሪያ ደንብ የህዝቡንና የአባላቱን ፍላጎት መሰረት በማድረግ ግለጽ በሆነ ተሳትፎ እነዲሻሻል ይደረጋል፡፡ በዚህ ረገድ የጉዳዩ ባለቤት የሆኑት የድርጅታችን አባላት ጥያቄ እስከሆነ ድረስ የድርጅቱን ስያሜ ጨምሮ ሌሎች ፖለቲካዊ ጉዳዮችም በአግባቡ እየተፈተሹ ሥርዐቱን በጠበቀ መንገድ ማሻሻያ ሊደረግባቸው እነደሚችል መዕ/ኮሚቴው ያምናል፡፡
3⃣የአማራ ብሄርተኝነት በህብረ-ብሄራዊነትና በዲሞክራሲያዊ የኢትዮጵያ አንድነት መርህ ለይ ተመስርቶ እንዲገነባ ብአዴን በጽናት ይታገላል፡፡ በፌደራል ሥረዐቱ ውስጥ የህዝቦች እራስን በራስ የማስተዳደር፣ የእኩልነትና የፍትሃዊ ተጠቃሚነት፣ ከቦታ ቦታ ተንቀሳቅሶ በነጻነት የመስራትና የመኖር መብቶች ሁሉ በትክክለኛው ገጽታና በተሟላ መንገድ እንዲከበሩና ኢትዮጵያ ለሁላችንም የተመቸች ሃገር እንድትሆን ብአዴን ከሌሎች እህት ድርጅቶችና ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በጋራ በመሆን ይሰራል፡፡ ከዚህ አኳያ የኢትዮጵያ ፌደራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፑብሊክ መንግስት አባላት የሆኑ ክልሎች አከላለል በህዝቦች እውነተኛ ፍላጎትና ንቁ ተሳትፎ፣ ብዝሃነትንና ሃገራዊ አንድነትን በሚያጠናክር አግባብ ሕገ መንግስቱን መሰረት አድርጎ እንዲከለል እንታገላለን፡፡ ባለፉት የትግል ዓመታት ክልላችንን ጨምሮ በመላ ኢትዮጵያ ለህዝቦች መፈናቀልና መሰደድ፣ ለህይወት መጥፋትና ንበረት መውደም ምክንያት የሆኑ የወሰንና የማንነት ጥያቄወች ትኩረት ተሰጥቷቸው በህዝብ ነጻ ተሳትፎ እንዲፈቱ ብአዴን በምክነያት ለይ የተመሰረተ ዲሞክራሲያዊ ትግል ያካሂዳል፡፡
4⃣የሃገሪቱም ሆነ የክልሉ ሕግጋተ መንግሥታት ዘመናዊ፣ ዓለም ዓቀፍ የሰብአዊ መብት ድንጋጌወችንና መሰረታዊ የዲሞክራሲ መብቶችን አሟልተው የያዙ፣ የዜጎች የቃል ኪዳን ሰነድ እንደመሆናቸው መጠን ለህገ መንግሰታዊ መብቶች መከበር ብአዴን በጽናት ይታገላል፡፡ ከሩብ ምዕተ ዓመት በላይ ማሻሻያ ሳይደረግበቸው የዘለቁት ህገ መንግስታዊ ድንጋጌወቻችን ውስጥ አንዳንዶቹ አገራችን ዛሬ ከደረሰችበት የዲሞክራሲ እድገት ደረጃ ጋር ተጣጥመው መሄድ አለባቸው የሚለውን የህዝብ አስተያየትና ጥያቄ ብአዴን በበጎ ጎኑ ይመለከተዋል፡፡ ስለሆነም እንዲህ አይነት ጥያቄወች ሕገ መንግስቱ ራሱ ያስቀመጠውን ሥርዐት ጠብቀው እስከቀረቡ ድረስ የሚነቀፉበት ምክንያት የለምና ሕጋዊና ትክክለኛ ምላሽ አግኝተው በሃገራችን የተጀመረው የዲሞክራሲ ስረዓት ግንባታ የበለጠ እንዲጠናከር ብአዴን በቁርጠኝነት ይሰራል፡፡
5⃣የህግ የበላይነት መከበር ለዲሞክራሲ ሥርዓት ግንባታ ወሳኝ እንደሆነ ብአዴን በጽናት ያምናል፡፡ እስካሁን በተካሄደው ትግል በዜጎች ለይ የተፈጸመን ማንኛውንም ሓላፊነት የጎደለው ኢ-ሕገ መንግስታዊ ተግባር እያወገዝን በእንዲህ አይነት ድርጊት ውስጥ ገብቶ የተገኘ ማንኛውም ቡድን፣ የመንግስት ባለስልጣንና ግለሰብ የሃገሪቱ ህግ በሚፈቅደው አኳኋን ለህግ ቀርቦ ተጠያቂ እንዲሆን በጽናት እንታገላለን፡፡ ከዚህም በኋላ በሃገራችን ሰብአዊና ዴሞክራሲያዊ መብቶች በተሟላ መንገድ እንዲከበሩ፣ ዜጎች በገዛ ሃገራቸው ተዋርደው ሊኖሩ እነደማይገባ፣ በዚህ ረገድ የሚፈጸምን ማነኛውንም ኢ-ሕገ መንግስታዊ ድርጊትም ውጉዝ እንደሆነ ብአዴን አጥብቆ ያምናል፡፡ የተጀመረውን የለውጥ ጉዞ ፈር ለማሳት የሚፈጸም ማንኛውንም ሕገ ወጥ ተግባር በመታገል በሃገራችንና በክልላችን ዋስትና ያለው ዲሞክረሲ እንዲገነባ ይደረጋል፡፡
6⃣የግለሰብና የቡድን መብቶች ተጣጥመው መከበር እንዳለበቸው እናምናለን፡፡ የግለሰብ መብት ባልተከበረበት የቡድን መብት ቦታ እንደማይኖረው፣ የቡድን መብት ባልተከበረበትም የተሟላ ዲሞክራሲ እነደማይኖር የታወቀ ነው፡፡ ሁለቱን መብቶች አጣጥሞ በመሄድ ረገድ ሕገ መንግስታችን ብዙ እርቀት ተጉዟል፡፡ በመሆኑም በሃገራችን ትክከለኛ ዲሞክራሲ እንዲገነባ ትልቅ መሰረት ተጥሏል፡፡ ይሁን እንጅ ባለፉት ዓመታት በሁሉም መስክ በቂ ሥራ ካለመሠራቱም በላይ በተለይ ደግሞ ለቡድን መብት መከበር የተሰጠውን ትኩረት ያክል ለግለሰብ መብትም ስላልተሰጠ የተጀመረው የቡድን መብት የማስከበር ሥራ ወደፊት ተጠናክሮ የሚቀጥል መሆኑ እንደተጠበቀ ሆኖ ትኩረት ተነፍጎት የቆየው የግለሰብ መብት በሚዛናዊነት የሚከበርበት ሥረዐት እውን እንዲሆን ይደረጋል፡፡
7⃣ብአዴን በውስጡ ጤናማ የሆነ የአመራር ቅብብሎሽ ሥርዐት ይኖር ዘንድ ለአመራር ግንባታ ሥራ በቂ ትኩረት ሰጥቶ ይሰራል፡፡ በተለይም አሁን እየታየ ያለውን ከፍተኛ የፖለቲካ ንቃትና ምርጥ ህዝባዊ መዕበል በእድልነት በመጠቀም በድርጅቱ ውስጥ በብቃት የተገነባ ብልህ፣ አርቆ አሳቢና አስተዋይ ተኪ አመራር እንዲኖር የተማረውን ወጣት መዕከል ያደረገ የአመራር ምልመላና ግንባታ ስራ ያካሂዳል፡፡ በአነጻሩም አሁን ከተደረሰበት የትግል መድረክና ከለውጡ እንቅስቃሴ ጋር አብረው መጓዝ በተሳናቸውና ህዝባዊ ሃላፊነታቸውን በብቃት መወጣት ባልቻሉ የድርጅቱ ከፍተኛ አመራሮች ለይ እርምጃ የተወሰደ ሲሆን ድርጅቱ ራሱን የማጥራት እንቅስቃሴውን አጠናክሮ ይቀጥላል፡፡ የብአዴን 12ኛ ድረጅታዊ ጉበኤም ይህንኑ ግምት ውስጥ ያስገባ ውሳኔ የሚተላለፍበት እንዲሆን በዚህ አጋጣሚ ለመላ አባላችንና አመራራችን ጥሪ እናቀርባለን፡፡
8⃣ሁለተኛው የእድገትና ትራንሰፎርሜሽን እቅድ በብቃት እንዲመራና በቀሪ ጊዚያት በሚሰራ ስራ ያለፈውንም ማካካስ በሚችልበት ደረጃ ለይ እንዲደርስ ህዝቡን፣ ወጣቶችን፣ ባለሃብቱንና ምሁራንን በማረባረብ ክልላዊና ሃገራዊ እድገት እንዲረጋገጥ ይደረጋል።
@Et_all_in_one