Ethiopian Universities Muslim Association /Ethio-UMA/


Гео и язык канала: не указан, не указан
Категория: не указана


ሙስሊም ተማሪዎች በያሉበት ትስስር ማድረግ: ተውሒድና ሱናን መሰረት ያደረገ ኢስላማዊ እውቀትን መገብየት: ብሎም እርስ በርሳቸው መተዋወቅና መወዳጀት!
"ቁርአን እና ሱናን በሰለፎች አረዳድ"

Связанные каналы

Гео и язык канала
не указан, не указан
Категория
не указана
Статистика
Фильтр публикаций


ዚክርን የጥሪ ማሳመሪያ ማድረግ አይቻልም!

ሸይኽ ፈዉዛን እንድህ አሉ
ዚክር ቁርአን፣ ሓዲስ፣ ተክቢር፣ አዛን፣
የጥሪ ማሳመሪያ የደዉል ማንቂያ አይደረግም
ምክኒያቱም ይህ በዉስጡ የአሏህን ዚክር ማሳነስ አለበትና
توجيهات للجند المسلم 23




👉👉ሚስት እንዳገባ ተመኘሁ ፡ አገባሁም
ግን ትዳር ያለ ልጆች አያምርምና ፡ ልጅ እንዲሰጠኝ ተመኘሁ፡ ልጆችም አገኘሁ።
ትንሽ ሳልቆይ የቤቱ ግድግዳ እይታው ሰለቸኝ፡
ሌላ ሰፊ ቤትም እንዲኖረኝ ተመኘሁ፡ ከብዙ ልፋትና ትጋት በኋላም ቤቱን አገኘሁ፡ ልጆቼ ግን አደጉ!
እንዲያገቡም ተመኘሁ፡ እነሱም አገቡ፡ ስራዬ ግን እያደከመኝ መጣ ፡ አስጠላኝ!
ጡረታ መውጣት አማረኝ ፡ ትንሽ ቆይቼም ወጣሁ ፡ህይወትም መልሳ አስጠላችኝ ፡ ልክ ገና አሁን ስራ ምፈልግ መሰለኝ!
ልዩነቱ ግን ያኔ ወደ ህይወት እየመጣሁ ነበር ፡ አሁን ግን ልሰናበታት ነው፡ አሁንም ግን ምኞቴን አልጨረስኩም!
👉ቁርኣን መሀፈዝ ተመኘሁ፡ ትውስታዬ ግን ከዳኝ
👉ለአላህ ፊትም መጾም ተመኘሁ፡ ጤናዬ ግን አልቻለም
👉ለሊቱን ቆሜ መስገድ ተመኘሁ፡እግሮቼ ግን እኔንም ማቆም አልቻሉም
እኔም ረሱል ( ﺻﻠﻰ ﺍﻟﻠﻪ ﻋﻠﻴﻪ ﻭﺳﻠﻢ ) ያለውን አስታወስኩ፥
5 ነገር ከ 5 ነገር አስቀድም(ተጠቀምበት)
1)ጡንቻክን ከ ድካም
2)ጤናክን ከ ህመም
3)ንብረትክን ከ ማጣት
4)ሰፊ ጊዜክ ከ መጥበብ
5)ኑሮክን ከ ሞትክ
ስለዚህ ለምን አላህን አትፈራም? ለምንስ ወደ አላህ አትመለስም? መካሪ አልመከረህም? አስታዋሽ አላስታወሰህም? ሰው ሲሞት በአይንህ አልተመለከትክም? ቀብር አልጎበኘህም? ወዳጅ ዘመዶችህን አልቀበርክም?
ዛሬ ሒጃብ በሥርኣት አልለብስ ያለው ገላ ነገ ከፈንን በግድ ይለብሳል፡፡ ዛሬ መሬት ላይ ሥርኣት ያልያዘን ወጣት ነገ መሬት ሥር መቃብር ሥርኣት ያስይዘዋል፡፡
✔️-->እንደ ዩሱፍ መሸሽ የሚችል ወጣት ጠፋ!
✔️-->እንደ መርየም ለንጽህናዋ የምትጨነቅ ሴት ታጣች፡፡
✔️-->አንድ ቀን እስከመጨረሻው ትሄድና አትመለስም ይሆናል።
✔️-->አንድ ቀን አይኖችህ እስከዘላለሙ ጨፍነው ይቀሩ ይሆናል። በዚያን ጊዜ ከቀናቶች በኋላ ሁሉም ሰው ይረሳህ ይሆናል።
✔️-->ለጀነት አልጓጓህም ሑረል አይን አልናፈቀችህም?

👇👇👇👇👇
ሁላችንም ወደ አላህ እንመለስ

t.me/EthioUMAGroup


ሴት ልጅ የተሟላ ሂጃብ ባለመልበስዎ ለስሜታቸው ላደሩት መቀለጂያና መጠቋቆሚያ ሆናለች!

እኒህ አይነቶቹ ቂሎች ለራሳቸው ተጃጅለው እሷንም ለማደንዘዝ አይንሽ፣ ከንፈርሽ፣ ዳሌሽ ውብ ነው ቅብርጥሴ እያሉ በማማለል ለማይረግበው ስሜታቸው ማርኪያ ሎሌ አድርገዋታል፡፡

እርሷም እነዚህ መርዘኛ ቃላቶች ባሳደሩባት ተፅዕኖና ባሳረፉባት ጠባሳዎች ተደንቃ ውብ መሆኗ የተነገረላት እስኪመስላት በሐሴት ተሞልታ እነሱ ለፈለጓት አላማ በማደር የወሲብ መግነጢሳቸው ሰለባ ሆናለች።

ይባስ ብላም አሁን አሁን ለዚህ አባዜያቸው የህይወት መስዋዕትነትም እየከፈለችበት ይገኛል፡፡

እንደምን ይሆን ብትሉኝ ለዚሁ ከንቱ አላማ ስትል ባላት ውበትና መስህብ አልብቃቃ ብላ ከሜካፕ ተሻግራ የአካል ለውጥ ለማድረግ አፍንጫዋን፣ አይኗን፣ ከንፈሯንና ቅርፅዋን ለማሳመር በሚልም ሆድና የመሳሰሉትን አካላቷን በቀዶ ጥገና መዘልዘልን ተያይዛዋለች።

የሚገርመው ነገር ይህ አምሮና ሸንቅጦ መቅረብ ላገባችው ባል ወይም በቁምነገር ለጋብቻ ላጫት ወንድ ሳይሆን ለተመልካችና ለሌሎች ፈላጊዎች ለውድድር ለመቅረብ ነው።


Репост из: ጀግና ሴቶች
بسم الله الرحمن الرحيم

✍ጀነትና የተሳካ የትዳር ህይወት ለምትፈልጉ ሴቶች✍

وهذه مجموعة من الاحاديث في اجر خدمة المرأة لزوجها وبيتها

ለአሏህ ብለሽ ባለቤትሽን እና ቤትሽን ብትንከባከቢ በአሏህ ፈቀድ ባልሽንም እንደምትፈልጊው አስተካክለሽ የምታገኚውን ሽልማት ከሚያረጋግጡ ሀዲሶች የሚከተሉትን ነጥቦች ልብ በይ=👌👌👌👌

وعن حصين بن محصن رضي الله عنه أن عمة له أتت النبي صلى الله عليه و سلم فقال لها أذات زوج أنت قالت نعم قال فأين أنت منه قالت ما آلوه إلا ما عجزت
عنه قال فكيف أنت له فإنه جنتك ونارك
رواه أحمد والنسائي بإسنادين جيدين والحاكم وقال صحيح الإسناد
صحيح الترغيب والترهيب للعلامة الألباني ١٩٣
(… እርሱ (ባልሽ) እኮ ጀነትሽ ወይም እሳትሽ ነው…)

👉ባልሽ ጀነት ወይም እሳት ለመግባት ትልቅ ሰበብ መሆኑን ተረዳሽ❓‼️

عَنْ أَبِي هُرَيْرَةَ رضي الله عنه قَالَ: قَالَ رَسُولُ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم: (إِذَا صَلَّتِ الْمَرْأَةُ خَمْسَهَا، وَصَامَتْ شَهْرَهَا، وَحصّنت فَرْجَهَا، وَأَطَاعَتْ بَعْلَهَا، دَخَلَتْ مِنْ أَيِّ أَبْوَابِ الْجَنَّةِ شَاءَتْ) رواه ابن حبّان (1296) وَصححه الألباني فِي "صحيح الجامع" (660).

( ሴት ልጅ አምስቷን ከሰገደች ፣ ወሯን ከፆመች ፣ ብልቷን ከጠበቀች ፣ ባሏን ከታዘዘች ከጀነት በሮች በየትኛውም በፈለገችው ገባች። )

👉 ከእነዚህ ታላላቅ ተግባራት ተርታ የተጠቀሰ የትልቅ ስኬት ቁልፍ የሆነው የባልሽ ጉዳይ እንዴት ችላ ይባላል ❓‼️ ልበ በይው

3231 أَخْبَرَنَا قُتَيْبَةُ ، قَالَ : حَدَّثَنَا اللَّيْثُ، عَنِ ابْنِ عَجْلَانَ ، عَنْ سَعِيدٍ الْمَقْبُرِيِّ ، عَنْ أَبِي هُرَيْرَةَ قَالَ : قِيلَ لِرَسُولِ اللَّهِ صَلَّى اللَّهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ : أَيُّ النِّسَاءِ خَيْرٌ ؟ قَالَ : " الَّتِي تَسُرُّهُ إِذَا نَظَرَ، وَتُطِيعُهُ إِذَا أَمَرَ، وَلَا تُخَالِفُهُ فِي نَفْسِهَا وَمَالِهَا بِمَا يَكْرَهُ "
حكم الحديث: حسن صحيح
قال الألباني في " السلسلة الصحيحة " 4 / 453 :
رواه النسائي ( 2 / 72 ) و الحاكم ( 2 / 161 ) و أحمد

( የትኛዋ ሴት ነኝ ምርጥ ተብለው ነብዩ صَلَّى اللَّهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ ሲጠየቁ:
=ከሴቶች ምርጥ ያች (ባሏ) ሲመለከታት የምታስደስተው፣ ሲያዛት የምትታዘዘው፣ በራሷም ይሁን በንብረቷ በሚጠላው ነገር የማትፃረረው አሉ።)
👉 ከምርጥ ሴቶች ለመሆን ውድ ባልሽ ሲያይሽ ለማስደሰት፣ትዕዛዙን ለማክበር እና ላለመፀራር በተቻለሽ ሁሉ ጥረት አታደርጊምን ❓‼️
( 3490 ) ( الصحيحة ) لا آمر أحدا أن يسجد لأحد ولو أمرت أحدا أن يسجد لأحد لأمرت المرأة أن تسجد لزوجها)
سنن الترمزي 1159 السلسلة الصحيحة للعلامة الألباني
(ማንም ለማንም እንዲሰግድ አላዝም።አንድን አካል ለሌላው እንዲሰግድ ባዝ ኖሮ ሴትን ለባሏ እንድትሰግድ ባዘዝኳት ነበር)

👉 አክብሮ መከበር ተናንሶ አሏህ ዘንድ ከፍ ማለት ትልቅነት መሆኑ ገባሽ ?
✍ይህን ያክል ክብር የሚገባውን ውድ ባልሽን ምን የክል ታከብሪዋለሽ❓‼️
ወይስ የነፍስሽ ኩራት አሸንፎሽ ጉዳዩ በተቃራኒው ሆኗል ❓‼️

👌አሏህን ለሚፈሩ ጀግና ሴቶች ቢሆን እንጂ ሀቅ ለብዙኃን ነፍሶች መራራ ነች።

ሸይጣኖችን እና ክፉ ነፍስን እምቢ ብለሽ ጀግና ሁኚ ‼️

✍አቡ ሀመዊያ
https://t.me/joinchat/AAAAAEP0OfkzzNtGHLxVeQ


👉👉 ጥያቄ መጠየቅ የምትፈልጉ እህት እና ወንድሞች ሁሉ ይሄንን ቻናል በመቀላቀል ኡአፈለጋቹሁትን ጥያቄ መጠየቅ ትችላላቹህ ። ስለ ፈትዋ ግሩፕ ማንኛውም ጥያቄ ካላቹህ @LeHakBchaMewegen

"ፈትዋ መጠየቅ ስትፈልጉ ጉሩፑ ሲከፈት ብቻ በዚሁ ግሩፕ ላይ ጥያቄዎቻቹሁን የምንቀበል ይሆናል። እዚሁ ቀጥታ ነው ምትጠይቁት ግልፅ በሆነ አማርኛ ወይም አረበኛ ቋንቋ ።
ጥያቄዎቻቹህ እውቀት ተኮር ፣ እና ሸሪዓዊን ብያኒን የተመረኮዘ እንጂ ሰዎችን መመዘኛ አይነት ጥያቄዎችን አንቀበልም ።
ከ2 በላይ ጥያቄ 1 ሰው መላክ አይቻልም


ኡስታዝ አህመድ ሸኽ አደም
ወቅታዊ ጉዳይ በተመለከተ ያስተላለፈው መልዕክት ሁላችንም እናንብብ ።

ኢትዮጵያውያን ሆይ!

🔹እልህና ቂም ለማንም አይጠቅምም፤በደልም መጨረሻው የከፋ ነው!

🔸እንደ በደል የአጸፋ ቅጣቱ የሚፈጥን ኀጢአት የለምና ማንም ማንንም አይበድል። በደለኛ ሰው ከጠላቱ ይልቅ ዛሬ ወይም ነገ ሴራው የሚጎዳው እራሱን ነው!!

🔹ጠባብነትና እኔ ብቻ ልብላ እኔ ብቻ ልኑር ማለት የሰው ሳይሆን የእንስሳት ባህሪይ ነው።

▪️ሁላችንም የሰው ልጅ ነንና የዘርና የሀይማኖት መለያየት ፈጽሞ ለበደል ምክንያት ሊሆን አይገባም!

🔸አብረው በሚኖሩ ሰዎች መካከል አለመግባባቶች የማይቀሩ ናቸው።

▪️መፍትሄው በሰከነ መንፈስ ተነጋግሮ ችግሮችን መፍታትና ከየትኛውም ወገን ይሁኑ አጥፊዎችን ማረም እንጂ መበዳደልና መገዳደል መፍትሄ አይደለም።

🔹ኢትዮጵያ ውስጥ ያሉ ህዝቦች በስጋ ወይም በአማችነት ወይም በጉርብትና በሌሎችም ገመዶች የተሳሰሩ ናቸው።
በዘር ወይም በሀይማኖት ምክንያት ከሀገሪቱ ህዝቦች መካከል አንዱን ለማጥቃት የሚደረግ ማንኛውም ሙከራ አደጋው የከፋ ነው። ጥቃት ፈፃሚው በዝምድና ወይም በጉርብትና ከሱ ጋር የሚተሳሰሩ ሰዎችንም ጭምር ነው የሚያጠቃው።
አንድ ቤተሰብ ውስጥ የተለያየ ሀይማኖትን የሚከተሉ፣ ከተለያዩ ብሄሮች ጋርም የጋብቻ ትስስር የፈጠሩ ሰዎችስ ቁጥር ቀላል የሚባል ነውን?!

🔹በአንድ ግቢ ውስጥ ፎቅና ምድር ላይ የሚኖሩ፤ አንድ ኩሽና አብረው የሚጠቀሙ ሙስሊምና ክርስቲያኖች እንዳሉስ ከማን ይሰወራል?

ለመሆኑ ማነው ወንድሞቹና አማቾቹን ማጥቃት የሚፈልገው? ማንስ ነው ለብዙ አመታት በመልካም ጉርብትና የተኗኗረውን ጎረቤቱን መበደል የሚሻ?!

🔸በሰላምና በመልካም መኗኗርን የሚያደፈርሱት፤ ጥቂት ክፉ አላማ ያላቸው፣ ከመኖር ተስፋ የቆረጡ፣ ያሰቡትን ማሳኪያ መንገዶች የተዘጋጉባቸው፣ ስብእና የጎደላቸው ሰው መስል አውሬዎች ናቸው።

♦️ኢትዮጵያዊያን ሆይ:-
ሀገራችን ሰፊና ለም ሀገር ናት፣እኛ ጥፋትን ትተን ለልማት ከሰራን ከተመካከርንና መብትና ግዴታን አውቀንና ጠብቀን ከኖርን ሀገሪቱ ከእኛ አልፋ ለሌሎችም በቅታ ትተርፋለች።ቅንነትና ሆደ-ሰፊነት ከጠፋ ግን ለአንድ ቤተ-ሰብ እንኳ ትጠባለች!

▪️አላህ ሆይ ሀገራችንን ሰላም አድርግልን!
▪️ለሀገርና ለህዝብ ክፉ የሚያስበጉርብት ተው ያዝልን! ኣሚን


✍ኡስታዝ አሕመድ ሸይኽ ኣደም

@EthioUMAGroup

@EthioUMAchannelኡስታዝ አህመድ ሸኽ አደም
ወቅታዊ ጉዳይ በተመለከተ ያስተላለፈው መልዕክት ሁላችንም እናንብብ ።

ኢትዮጵያውያን ሆይ!

🔹እልህና ቂም ለማንም አይጠቅምም፤በደልም መጨረሻው የከፋ ነው!

🔸እንደ በደል የአጸፋ ቅጣቱ የሚፈጥን ኀጢአት የለምና ማንም ማንንም አይበድል። በደለኛ ሰው ከጠላቱ ይልቅ ዛሬ ወይም ነገ ሴራው የሚጎዳው እራሱን ነው!!

🔹ጠባብነትና እኔ ብቻ ልብላ እኔ ብቻ ልኑር ማለት የሰው ሳይሆን የእንስሳት ባህሪይ ነው።

▪️ሁላችንም የሰው ልጅ ነንና የዘርና የሀይማኖት መለያየት ፈጽሞ ለበደል ምክንያት ሊሆን አይገባም!

🔸አብረው በሚኖሩ ሰዎች መካከል አለመግባባቶች የማይቀሩ ናቸው።

▪️መፍትሄው በሰከነ መንፈስ ተነጋግሮ ችግሮችን መፍታትና ከየትኛውም ወገን ይሁኑ አጥፊዎችን ማረም እንጂ መበዳደልና መገዳደል መፍትሄ አይደለም።

🔹ኢትዮጵያ ውስጥ ያሉ ህዝቦች በስጋ ወይም በአማችነት ወይም በጉርብትና በሌሎችም ገመዶች የተሳሰሩ ናቸው።
በዘር ወይም በሀይማኖት ምክንያት ከሀገሪቱ ህዝቦች መካከል አንዱን ለማጥቃት የሚደረግ ማንኛውም ሙከራ አደጋው የከፋ ነው። ጥቃት ፈፃሚው በዝምድና ወይም በጉርብትና ከሱ ጋር የሚተሳሰሩ ሰዎችንም ጭምር ነው የሚያጠቃው።
አንድ ቤተሰብ ውስጥ የተለያየ ሀይማኖትን የሚከተሉ፣ ከተለያዩ ብሄሮች ጋርም የጋብቻ ትስስር የፈጠሩ ሰዎችስ ቁጥር ቀላል የሚባል ነውን?!

🔹በአንድ ግቢ ውስጥ ፎቅና ምድር ላይ የሚኖሩ፤ አንድ ኩሽና አብረው የሚጠቀሙ ሙስሊምና ክርስቲያኖች እንዳሉስ ከማን ይሰወራል?

ለመሆኑ ማነው ወንድሞቹና አማቾቹን ማጥቃት የሚፈልገው? ማንስ ነው ለብዙ አመታት በመልካም ጉርብትና የተኗኗረውን ጎረቤቱን መበደል የሚሻ?!

🔸በሰላምና በመልካም መኗኗርን የሚያደፈርሱት፤ ጥቂት ክፉ አላማ ያላቸው፣ ከመኖር ተስፋ የቆረጡ፣ ያሰቡትን ማሳኪያ መንገዶች የተዘጋጉባቸው፣ ስብእና የጎደላቸው ሰው መስል አውሬዎች ናቸው።

♦️ኢትዮጵያዊያን ሆይ:-
ሀገራችን ሰፊና ለም ሀገር ናት፣እኛ ጥፋትን ትተን ለልማት ከሰራን ከተመካከርንና መብትና ግዴታን አውቀንና ጠብቀን ከኖርን ሀገሪቱ ከእኛ አልፋ ለሌሎችም በቅታ ትተርፋለች።ቅንነትና ሆደ-ሰፊነት ከጠፋ ግን ለአንድ ቤተ-ሰብ እንኳ ትጠባለች!

▪️አላህ ሆይ ሀገራችንን ሰላም አድርግልን!
▪️ለሀገርና ለህዝብ ክፉ የሚያስበጉርብት ተው ያዝልን! ኣሚን


✍ኡስታዝ አሕመድ ሸይኽ ኣደም

@EthioUMAGroup

@EthioUMAchannel


👉ትዳር ማግባት ወይስ ግራ መጋባት👈~~=> ክፍል 1⃣
.............👇👇............⬇
አወ ይሄን የመረጥኩት ብዙዎቻችን መልክቱና ሀሳቡን ሳንረዳ ከሁለቱም ወጥተው በመጥፎ አንግል የሚመለከተው በዝቶ ስላየሁነው....
ይህም አንዳንድ ሰወች
---- ማግባት ግራ መጋባት
---ማግባት እዳ መግባት
----ማግባት ወህኒቤት እንደ መግባት ወ.ዘ.ተ

የመሳሰሉትን ቃላት ይጠቀማሉ እናማ ይህን በቀላል ላልፍ አልወደድኩምና ያለውን ዘርዘር ላድርገው ።ነገሩ እንድህ ነው

ትዳር በኢስላም ከፍተኛ ክብርና ለሰው ልጅ ውጤታማነት ፣ ስኬታማነት ደረጃ እንደሚያደርስ ምንም ጥርጥር የለለው አጉሊ መነፀር ነው።👁
ኢስላም ለትዳር ትልቅ ቦታ ሰትቶታል ...

ይሁንና ይህን የተሰጠውን እድል ወይም ፎርሳ እንዴ አሉቧልታ ችላ ተብለው ይታለፋሉ.

ይሁንም እንጅ ማለፋቸው ብቻ ሳይሆን ለመጭውም ትውልድ ጫና እና ለሰው ልጅ እንቅፋት ሆነው *ግራ* መንገድ ላይ የቆሙት እንቅፋት ይሆኑት ብዙ እየሆኑ መጥታዋል..
*ግራ መጋባት
ለሆነባቸው*

ሰበቡ ምንድን ነው
ይህም ግራ የተጋቡት ገብተው አይተውት ሳይሆን የአንዳንድ ስኬታማነት ባልተላበሰ ትዳር ውስጥ የሚያዩት ተልካሻ ንነገርና ለቁስ አዳሪ መሆን ብቻ ነው...

ወይም ደግሞ በአቅሙ መኖር ሲገባው ካቅሙ በላይ የሰውን ቤትና ንብረት እያየ እሱ በአቅሙ መኖር እና መብቃቃት አለመቻሉ ትልቁን ሚና ይጫውታል

ይህም አንዳንድ ሰዎች የበታየቸውን ማየት ይሳናቸውና የበላይን እያዩ ግራ ገብቷቸው ሰውንም ግራ

ለማጋባት ይሞክራሉ።ቢሆንም ግን ሁሌም በቅም መኖርና መብቃቃት ካልቻልን ግራ እንደገገባን እንኖራለን።አንዳንዱ ደግሞ ባገባስ ሁሉንም ነገር ማድረግ ባልችልስ ሀቋን

ባላሟላስ እያለ ግራ የገባውም አይጠፋም ።ሌላኛው ደግሞ አላፊ አግዳሚወችን እያየ ይችን ላግባ ይችን እርረረረ ይችን እያለ ግራ የገባውም አለ

ከባዱ ግን በተንሸዋረረ መነፀር እያየ የሚፈልገውን የሀራም ሴቶችን እያስተናገዴ ባገባ ቤት መያዝ ፣አስቤዛ፣ ቁጥጥር ይመጡብኛል ሲል በሀራም ላይ እድሜ ልኩን ይኖራል

ለሰወችም ግራ መጋባት ነው እያለ በቀኝ መጓዝን ትቶ በግራ የሚጓዝም ቀላል እና ውስን አይደሉም። እናም ትዳር ማለት እንዴየ አመለካከቱ ፣እንደየ

ባህሪው ፣ ልዩ ነዉ ይሁሉም ቤት አንድ አይደለም ..አንዳንድ ሰወች ተጋብተው እንዴየ አቅማቸው መኖር ሲገባቸው አሻገርው የሰውን እያዩ የራሳቸውን ቤት ይረሱና ።ለዘወችም ትዳርን መጥፎ እይታ እንዲኖራቸው ሰበብ ይሆናሉ

እርግጥም የአላህ ምልክተኛ صلى الله عليه وسلم ሲናገሩ የቻለ ያግባ ያልቻለ ደግሞ ይፁም እሚለውን ሀድስ ሁላችነም እናቃል ግን ተግባር

ላይ ይከብደንና ለሰወች መጥፎ እይታችንን እንሰነዝራል ።.
እናም ትዳርን ግራ መግባት ነው እሚሉ ሰዎች እይታቸው ትክክል
አይደለም ..ትክክለኛው ግን
እሪዝቅን በትዳር ውስጥ ፈልጓት የተባለውን ሀድስ አሚን ብሎ መቀበልና መተግበር ግድ ይላል..የዛኔ
የአላህንና የመልክተኛውን صلى الله عليه وسلم
ትእዛዛት የምንተገብርና ልባችን አምኖ ከተቀበልነው

*ግራ ቀርቶ ቀኝ መግባት ይመጣል*.....

እናም ለትዳር ምንም አይነት መስዋትን ሳንከፍልለት ግራ ነው ቀኝ እያልን እራሳችንንም ሰወችንም በአጉሊ መነፀር ማየቱን መቀጣል የለብንም

ማንኛውም ነገር ከትንሽ እስከ ትልቅ መስዋት መክፍለ ግድ ነውና። እናም ሁላችንምም በተደናበር አስተያየት ማየታችን መቀጠል የለብነም።በስከ ጀርባ ምርጥና ውብ ነገር እንዳለው ልንረዳ ግድ ነዉ✔✔.


ይቀጥላል... ክፍል2⃣
"
"
Copy

t.me/EthioUMAchannel

t.me/EthioUMAGroup


አስታውስ/ሺ/

☞አንድ ቀን ይመጣል አንተ እራስህ የለበስከውን ልብስ ሰዎች አገላብጠው የሚያውለወቁልህ ቀን

☞የተከፈተ አፍ እና አይንህን ሰዎች የሚዘጉልህ ቀን

☞ተራምደህ ከሄድክበት ቦታ ሰዎች ተሸክመው የሚያስወጡህ ቀን

☞ ቤተሰብሽን እንኳን ታፍሪ የነበርሽው በሰው እጅ ገላሽ የሚታጠብበት ቀን

☞ጌጣጌጥሽ ሁሉ ከላይሽ ላይ የሚወልቅበት ቀን


ሸይኽ ፈውዛን ሐፊዘሁላህ እንዲህ አሉ:-
አንድ ወንድምህ አምኖ የሆነ ሚስጥሩን ቢነግርህ አደራህን ይሄን ሚስጥሩን ለሰዎች እንዳትበትንበት ።
ምንጭ:- ሸርሁል ከባኢር (416)


ውርደት እና ክብረቢስነት ትእዛዜን በጣሰ ላይ ይሁን
https://t.me/EthioUMAGroup


ውድዋ ሙስሊሟ እህቴ ደግሜ ደግሜ ካንቺ ጋር ባዋራ የማይሰለችኝ ያንቺ ነገር ሁሌ እንዳስጨነቀኝ

≈ውድዋ እህቴ ዛሬ ስለምን እንድናወራ እደፈለኩ ታውቂያለሽ?

≈አሁን ነግርሻለሁ አንቺ ግን ለደቂቃዎች ጆሮ እና ልብሽን ከፍተሽ እድታደምጪኝ በአለማቱ ጌታ አላህ ስም እጠይቅሻለሁ

≈ነይልኝ እዚህ ጋር አድምጪኝ ወንዶች እዳይሰሙ ማባረር ብንችል እና ባራቸው ነበር አይሰሙንም እና ተያቸሁ

≈ልብሽን አስጨነኩት አይደል............? ይገባኛል በዚህ አፉ በይኝና ወደ ጉዳዬ ልሻገር

≈ሃቢቢቲ የትዳር ጊዜ የገፍ እና የረዘመ በቆየ ቁጥር ከእኔ እንከን ስላለ ነው ያልሽ የተጨነቀሽ ይሆን?

≈ላንቺ ከንቺ በላይ አዋቂ የሁነው አላህ ላንቺ መች ትዳርን መማምጣት እዳለበት ያውቃል።

≈ጓደኞችሽ ከዙሪያሽ ቢዳሩ ምንም አይድነቅሽ የአላህን ውሳኔ እስክትፈፀም በሰብር ታጋሽ ሆኝ ስለ ብቸኝነት እያሰብሽ አቻ ፈለጋ አትውጪ

≈ውድ እህቴ በሃራሙ መንደር ገብተሽ የጌታሽን ቁጣ ሣታተርፊ ሰብርን አድርገሽ በሃላሉ አለም ገብተሽ የጌታሽን ውዴታ አትርፊ

≈ሃቢቢቲ ወላሂ ትዳር እስኪመጣ ብቸኝነት ለሙስሊሟ እህት ጌጥ ነው ፣ ክብር ነው ፣ ውበት ነው ።

≈ትዳር ያላት ጓደኛሽ ስትደሰት ባየሻት ቁጥር የሷን ያክል አንቺም ተደሰቺ ራስሽን ተመልከቺ አንቺ የአላህ ራህመት ያካበበሽ ነሽ

≈ወድ እህቴ ወደ ኋላሽ ተመልክተሽ መንደርሽን ቃኚ ወደ ሃራም ገብተው እንደ እብድ የሚኖሩ እህቶችን ላያቸው ደሰተኛ እና የሚፍቀሩ የሚመስሉ ውስጣቸው ግን የጐመንዘር ፊሬ ታክል ደስታ የሌላቸው።

≈ሰላም እና መረጋጋት እንደ ሰማይ የራቃቸው
አንቺ ራስሽን አሰከብረሽ እና ተቆጥበሽ የምትኖሪ ከሆነ ወድ እህቴ አንቺ ማንም ወንድ ሊያገኛት የሚመኛት አይነት ሴት ነሽ

≈ከውድም ውድ የሆንሽ አንቺ ሙስሊም ሴትነሽ ያንቺ ብቻ ሳይሆን የዲንሽም ክብርን ይዘሻል አንቺ ከተበላሸሽ የሙስሊም ሴቶች የተባለ የብዙ እህቶችሽም ስም አብሮ ይወርዳል

≈የአዛኞች ሁሉ አዛኝ የሆንከው የአለማቱ ጌታ ሆይ!
ሙስሊም እህቶቼን አንተው በራህመት ከምጠላው መንገድ ጠብቃቸው
ሷሊህ ከሆነው ያንተ ባሪያ ጋር ደስተኛ የትዳር ህይወትን ስጣቸው

≈ለተገባቸው እስቲቃማውን ላለገባቹ ሰብር አላህ እድሰጣቹ የዘውትር ዱዓችን ነው ።

ኮፒ


Видео недоступно для предпросмотра
Смотреть в Telegram
{ إِنَّ اللَّهَ وَمَلائِكَتَهُ يُصَلُّونَ عَلَى النَّبِيِّ يَا أَيُّهَا الَّذِينَ آمَنُوا صَلُّوا عَلَيْهِ وَسَلِّمُوا تَسْلِيمًا} [ الأحزاب: ٥٦ ]

▫عَنْ أَنَسٍ رضي الله عنه قَالَ : قَالَ رَسُولُ اللهِ صَلَّى اللهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ : ( أَكْثِرُوا الصَّلَاةَ عَلَيَّ يَوْمَ الْجُمُعَةِ وَلَيْلَةَ الْجُمُعَةِ ؛ فَمَنْ صَلَّى عَلَيَّ صَلَاةً صَلَّى الله عَلَيْهِ عَشْرًا ) .
حسنه الألباني في " الصحيحة " (١٤٠٧) .

اللهم صل وسلم وبارك على نبينا محمد ﷺ وعلى آله وصحبه أجمعين .

➲ከጁምዓህ ቀን ሱናዎች ውስጥ:-
① ሲዋክ መጠቀም
➁ ገላን መታጠብ
③ ሽቶን መጠቀም(ለወንዶች)
④ ሱረቱል ከህፍን መቅራት
⑤ ያማረን(ጥሩ) ልብስ መልበስ
⑥ ወደ መስጂድ
በጊዜ(በማለድ)መሄድ
⑦ ዱዓ የሚያገኝበትን(ተቀበሰይነት) ያለባትን ሰዓት መጠባበቅ
⑧ በነብዩ ﷺ ላይ ሶለዋት ማብዛት

"➦በተጨማሪ አርፍደው ከመጡ የሰው ትከሻ ላይ እየተረማመዱ ሶፍ ውስጥ ከመግባት መቆጠብ, ኹጥባን በጥሞና ማዳመጥ, ሌላ ሰው ቢያወራም ዝምበል አለማለት እና ሶላት ካለቀ በኋላ ያመለጣቸውን ሰዎች ሶላት ሳይቆርጡ ረጋ ብሎ መውጣት ያስፈልጋል"።
⚘•• t.me/TewhidSunnah




መልክተኛው ﷺ እንዲህ ብሎዋል!!

☞{አንድ ወንድ} ያልተፈቀደችለትን ሴት ከሚጨብጥ ከብረት በሆነ ወሰፌ ጭንቅላቱን ቢወጋ ይሻላል።


👉👉👉አግባ__አግባ__ስትባል__አልችልም__ትላለህ !
በውስጥ(በቻት) እየገባህ ☞ ሙስሊም እህትህን
አዛ ታደርጋለህ!

እናም
ወንድሜ__ሆይ !
👉 ኒካህ እንደማታደርግላት(እንደ ማታገባት ልቦናህ እያወቀ)!

ደካማ ጎኗን ሰበብ አድርገህ የሙስሊም
እህትህን ሂጃብ አትግፈፍ + ልቧን አትሰበር
(አታድማ)!!

ያዕኔ! ምን መሰለህ?

☞ አንተ ሙስሊም እህትህን ለትዳር መልካም
(ጥሩ ናት) ብለህ ከመረጥካት + የማስተዳደር
አቅሙ ካለህ!

ለምን በበሩ ገብተህ ቤተሰቧን ጠይቀህ
አታገባትም?

☞ ለምን በቻት ጓሮ ለጓሮ ትሄዳለህ?
የእውነት ከፈለካት ማለት ነው!!

ከላይ በሚድያም ይሁን በአካል +……………
ሙስሊም ያልሆኑ አካላቶች!

☞ የሙስሊም ሴቶችን(እህቶቻችንን) ሂጃባቸውን
እየገፈፉ ነውና መቃወም አለብን ትላለህ!!

ወላኪን አንተ በውስጥ ከነሱ ብሰህ (በበለጥ)
ሂጃባቸውን የምትገፈው አንተው ሆነህ ተገኘህ!

☞ለምን ወንድሜ??

እስኪ ልጠይቅህ!

👉 በደም + በስጋ የምትገናኝህ የእናትህ የአባትህ
ልጂ እንደ ☞ዓይንህ የምትሳሳላት እህትህ!

አንተ በሌሎች ሙስሊም እህቶች ላይ
እንደምታደርገው ሁሉ!
☞ እህትህን የአንተ ተመሳሳይ የሆነ ሂጃቧን
አስገፍፎ
አላህ(ሱብሀነሁ ወተዓላ) ፊት የተዋረደች ሆና
እንድትቀርብ ትፈልጋለህን??

መቸም እፈልጋለሁ አትልም!
አወ አትልም!

ምክንያቱም!

የምትሳሳላት እህትህ ስለሆነች!

ስለዚህ! ራስህን አስተካክለህ ለሙስሊም
እህትህም ☞ ልትሳሳላት ይገባል!

በወሬ አይደለም በተግባር!!

አስብ + አስተንትን ወንድሜ!

የአላህ (ሱብሀነሁ ወተዓላን) ቃል +
የመልዕክተኛውን( ﺻﻠﻰ ﺍﻟﻠﻪ ﻋﻠﻴﻪ ﻭﺳﻠﻢ ) ንግግርን
+ ተግባርን!!

👉 አላህ (ሱብሀነሁ ወተአላ) በተከበረው ቃሉ
ዝሙትን አትስሩ አይደለም ያለው!

ጭራሽ አትቅረቡ ብሎ ነው ያስጠነቀቀን!

ﻭَﻟَﺎ ﺗَﻘْﺮَﺑُﻮﺍ ﺍﻟﺰِّﻧَﺎ ۖ ﺇِﻧَّﻪُ ﻛَﺎﻥَ ﻓَﺎﺣِﺸَﺔً ﻭَﺳَﺎﺀَ ﺳَﺒِﻴﻠًﺎ ،
ዝሙትንም አትቅረቡ! እርሱ በእርግጥ መጥፎ
ስራ ነውና! መንገድነቱም ከፋ!!
[ ﺳﻮﺭﺓ ﺍﻹﺳﺮﺍﺀ ‏( ٣٢ )]

+ የአላህ መልዕክተኛ( ﺻﻠﻰ ﺍﻟﻠﻪ ﻋﻠﻴﻪ ﻭﺳﻠﻢ )
በሀድሳቸው እንዲህ ብለዋል: -

#ﻗﺎﻝ ﺭﺳﻮﻝ ﺍﻟﻠﻪ - ﺻﻠﻰ ﺍﻟﻠﻪ ﻋﻠﻴﻪ ﻭﺳﻠﻢ -:
ﻭﻻ ﻳﺨﻠﻮﻥ ﺭﺟﻞ ﺑﺎﻣﺮﺃﺓ، ﻓﺈﻥ ﺛﺎﻟﺜﻬﻤﺎ ﺍﻟﺸﻴﻄﺎﻥ،
ﺭﻭﺍﻩ ﺃﺣﻤﺪ ﻭﺻﺤﺤﻪ ﺍﻷﻟﺒﺎﻧﻲ ،

የአላህ መልእክተኛ( ﺻﻠﻰ ﺍﻟﻠﻪ ﻋﻠﻴﻪ ﻭﺳﻠﻢ ) እንዲህ
ብለዋል:-
አንድ ወንድ ከአንዲት ሴት ጋር ለብቻ
እንዳይገለል! ሶስተኛቸው ሰይጣን ነውና!!
[ኢማም አህመድ ዘግበውታል]!!

👉 ሌላ ሀድስ ላስታውስህ!
ﻭﻗﺎﻝ ‏( ﺻﻠﻰ ﺍﻟﻠﻪ ﻋﻠﻴﻪ ﻭﺳﻠﻢ ‏) ﻻ ﻳﺨﻠﻮﻥ ﺭﺟﻞ ﺑﺎﻣﺮﺃﺓ
ﺇﻻ ﻣﻊ ﺫﻱ ﻣﺤﺮﻡ، ﻣﺘﻔﻖ ﻋﻠﻴﻪ ،
የአላህ መልዕክተኛ( ﺻﻠﻰ ﺍﻟﻠﻪ ﻋﻠﻴﻪ ﻭﺳﻠﻢ ) እንዲህ
ብለዋል :-
ወንድ ልጅ! መኽረሟ በሌለበት ከሴቷ ጋር
እንዳይገለል!
[ቡሀሪና ሙስሊም ]

ወንድሜ__ሆይ!

ይህ መዕልክት እኮ! በአካል ለሚገናኙት ብቻ
አይደለም!

♂ከሚድያ + ከእስክሬን + ከፕሮፋይል +
ከፓስትም በስተጀርባ ለሚከሰተው ድብብቆሽ
ነው!
☞ አባቴ + እናቴ + እህት + ወንድሜ + ጓደኛየ
+ ፉላን + ፉላኒት አያዩኝም (ማንም አያየኝም )
ብለህ ☞ አላህን ለምትወነጂለው + የእህትህን
ሂጃብ #ለምትገፈው ……………… ጭምር ነው!!
ስለዚህ! አላህን ፍራ!!!!
ወላሁ ተዓላ አዕለም!!!


👉👉✔️ጋብቻ ያሰብሽ እህቴ ከወንዶች እነዚህን ነገራቶች ተጠንቀቂ!!
👈 أبو الريس السلفي.
① ለመልክሽ ብሎ የሚያገባሽን ተጠንቀቂ, ምክንያቱም: ካንቺ የተሻለ ሲያያ ትቶ መሄዱ እርግጥ ነውና,

② ሲጃራ ፣ መጠጥ ፣ ጫት የሚመገብን ባል ተጠንቀቂ!ምክንያቱም: ገንዘብ አባካኝ ይሆንና በድህነት ትጎጂያለሽ አሊያም ጠጥቶ መቶ በዱላ መጫወቻ ያደርግሻልና,

③ ወለድ የሚበላን ተጠንቀቂ! ከአላህ ያጣላሻልና,

④ ሰላት የማይሰግድ ከሆነ ተጠንቀቂ! ምክንያቱም: ለጌታው ሀቅ ሳይቆም ላንቺ ለጊዜያዊ ሚስቱ ቆማለሁ ማለቱ ዘበት ነውና,

⑤ ቋጣሪ (የማይሰጥ)ባል ተጠንቀቂ!

⑥ ደዩስ ባል ተጠንቀቂ! ማለትም: ሚስቱ ፊልም፣ሙዚቃ፣ድራማ ወዘተ ስታይ ፀጥ የሚል ፀጥ ማለቱን ውዴታ ነው ብለሽ አትሰቢ አሰበልሽ የሚባለው አላህ ሀራም ያደረገውን ነገር ሲከለክልሽ ነውና,

⑦ ቀብር ዟሪ ባል ተጠንቀቂ! በቀብር ተወሱል፣ኢስቲጋሳ የሚያደርግ ለቀብር ዘብህ፣ነዝር የሚሳል ከሆነ ሙሽሪክ ተጠንቀቂ!

⑧ አስካሪን ነገር የሚሸጥን ተጠንቀቂ!

⑨ ደጋሚ ከሆነ ባል ተጠንቀቂ! ጀሀነም ይዞሽ ይጓዛልና,

10- ሙብተዲእ ባል ተጠንቀቂ! በሽታው መጋባቱ ይፈርልሽልና,
➧አይ እኔ አግብቼ ለውጠዋለሁ የምትይ እህት ወላሂ ከእርግብ የበለጥሽ እንጩጭ የዋህ ነሽ
من تجالس تجانس" ነውና,


አብደሏህ ኢብኑ ዑመር ረዲየሏሁ ዐንሁ
እንዲህ ይላል:-
«ቢድዓ ሁሉ ጥመት ነው።
ሰዎች መልካም ነው ብለው ቢያስቡትም።»
አህካሙል ጀናኢዝ (200)




የመከላከያ ሰራዊት በሙስሊሙ ላይ ሁለት ጊዜ ዐይን ያወጣ ሸፍጥ ሰርቷል!!

1ኛ, ባለፉት ወራት አፋር ወንድሞቻችን ላይ "ያልታወቀ" በተባለ ታጣቂ ድንገተኛ ተኩስ ተከፍቶባቸው በርካታ የአፋር ሙስሊም ወንድሞቻችን አልቀዋል። በወቅቱም ለመከላከል ጥረት ቢያደርጉም እኛ እንከላከልላችኋለን በሚል ሰበብ የመከላከያ ሰራዊት አባላት ወንጀለኞች ሳይያዙ እንዲያመልጡ አድርገዋል፣ ጉዳዩም ተድበስብሶ ቀርቷል።

2ኛ, በሰሞኑ በሀረር ወንድሞቻችን ላይ ክርስቲያኖች ለሚያደርሱት ጉዳትና የንብረት ውድመት ሙስሊሞችን እንዳይከላከሉ በማድረግ ለክርስቲያኖች ተባብሮ በሙስሊሞችና በንብረታቸው አደጋ እንዲደርስባቸው አድርጓል።
"
"
ለመከላከያ ሚኒቴር ለአቶ ለማ መገርሳና ለኢታማዡር ሹሙ ለጀነራል አደም ሙሀመድ አንድ ጥያቄ አለኝ:– ለመሆኑ ይህ የመከላከያ ሰራዊት ክፍል በእናንተ ስር የሚመራ ነው ወይስ ከናንተ ያፈነገጠ የመከላከያ ክፍል አለ?!
ሙስሊሙን መበደል የሰማይና የምድር ወታደር ባለው ፈጣሪ ዘንድ ወጋ ያስከፍላልና ቆም ብላችሁ ብታስቡበት መልካም ነው።
ኢብን ሽፋ: ጀማዱል ኡላ 26/1441 ዓ.ሂ
ጥር 12/2012

Показано 20 последних публикаций.

285

подписчиков
Статистика канала