🏢 አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ 🏬
አድራሻ....❓
💬 በኢትዮጽያ ዋና ከተማ አዲስ አበባ ውስጥ ይገኛል ።
የአየር ሁኔታ ...❓
💬 የመጀመሪያዎቹ ወራቶች መጠነኛ ብርዳማ ሆነው ወደ ኋላ ላይ ግን ሞቃታማ የአየር ንብረት አለው ።
የካንፓሶች ብዛት ❓
📚 በጣም ብዙ ማለትም አስራ ሰባት ይደርሳሉ ። እያንዳንዱ ካንፓስ የተለያየ ፊልድ ይሰጣል ።
ያሉት ካንፓሶች ፦
6 ኪሎ ፣
5 ኪሎ ፣
4 ኪሎ ፣
ሜክሲኮ ፣
ልደታ ፣
18 ማዞሪያ
ጥቁር አንበሳ ( hospital)
ቃሊቲ ፤
ቢሾፍቱ (ደብረዘይት) ፤
ላምበረት ......ካንፓሶችን ያካትታል ።
በካንፓሶች የሚሰጡ ፊልዶች ❓
🏠6 kilo
💡 ለሶሻል ተማሪዎች ብቻ የሶሻል ዘርፍ ትምህርቶችን ይሰጣል ።
🏠5 kilo
💡 ለኢንጂነሪግ ( Software , electrical , biomedical , mechanical , civil , chemical ..የሚሰጥበት ካንፓስ ነው ።
✅ biomedical engineering ከሚሰጥባቸው ጥቂት ዩንቨርሲቲዎች ውስጥ አንዱ አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ነው።
🏠4 kilo
💡 በዚ ካንፓስ computer science እና computer engineering ይሰጣል ።
🏠 18 ማዞሪያ
💡 የሜዲሲን ዘርፎች በ Other health የሚካተቱትን ይሰጣል ።
🏠 ጥቁር አንበሳ
💡 ይህ ካንፓስ አንጋፋ ሲሆን በውስጡም የMedicine ኮርስን ይሰጣል ፤ ተማሪዎች አፓረንትም በጥቁር አንበሳ ሆስፒታል ይወጣሉ ።
🏠 ላም በረት
💡 በሳይንስ እና ቴክኖሎጂ ላይ ብቻ አተኩሮ የሚሰራ ካንፓስ ነው ፤ AASTU የሚገኝበት ሲሆን APPLIED እና Enginering ኮርሶችን ይሰጣል ።
🏠ልደታ
💡በልደታ ካንፓስ የሚሰጡት ፊልዶች architecture ፤ cottom ፤ urban plannig እና የመሳሉትን ያካትታል ።
🏠 ሜክሲኮ
💡 ይህ ካንፓስ የcommerce ግቢ ነው ። ( marketing management , business administration, management የሚሰጥበት ካንፓስ ነው ።)
🏠 ሰፈረ ሰላም
📚 የጤና ዘርፍ ግቢ ነው ፤ ሜዲስን ነርሲንግ እና የመሳሰሉት ወደ ጥቁር አንበሳ 3ተኛ አመት ላይ ከመሄዳቸው በፊት የማሩበት ግቢ ነው ።
🏠 ቢሾፍቱ ካንፓስ
📚 AAU ደብረዘይት ላይ Veterinary medicine & Science collage አለው ። ደብረዘይት ነው የሚገኘው ካንፓሱ በጤና እና ሳይንስ ዘርፍ ይሰጣል ..!
💬ለኢንጅነሪግ ተማሪዎች ፧
➡ የdrawing መሳሪያዎች መያዝ አለባችሁ
➡ Mathematics and Mechanics Statics guide books ይዛቹህ ብትሄዱ መልካም ነው ።
የካፊው ምግብ ❓
📚 ምግቡ ለክፉ የሚሰጥ አይደለም ከሌሎች ዮኒቨርሲቲዎች የተሻለ ነው ፤ በተለይ ደግሞ ሰፈረ ሰላም ካንፓስ ደስ የሚል ነው ።
በሳምንት ውስጥ ካፌ የሚሰጡ ምግቦች ዝርዝር ስኬጁል ❓
📚 ከሌሎች ዮኒቨርስቲዎች የተለየ አይደለም ቁርስ ፍርፍር ፤ ሩዝ ፤ ሻይ በዳቦ ፤ ስልስ ይቀርባል ፤ ምሳ እና እራት በሳምንት 2-3 ቀን ስጋ ምሳ እና እራት ይኖራል ፤ ሽሮ ፤ ምስር ፤ አታክልት የመሳሰሉት ምግቦች ይቀርባሉ ። (በፎቶ የምግቡን ጥራት ማየት ይቻላል)
ከካፌ ውጪ ስለሚገኙ ምግቦች እና ዋጋቸው ❓
📚 ከሌሎች ግቢዎች የተለየ አይደለም ነገር ግን 4 ኪሎ ግቢ ምግብ ከሚታሰበው በላይ ቅናሽ ነው ። ዋጋቸው ከታች ተቀምጧል ...!
ቀላል ምግቦች ፓስታ ፍርፍር... etc 20 -30 ብር
ከባድ ምግቦች እንቁላል ፤ ስጋ ..etc 30-50 ብር
ሻይ እና ቡና ...etc 2-4 ብር ይሆናል ።
የሎከር ነገር ❓
📚 ሎከር በጣም አስቸጋሪ ነው ፤ በዶርም ውስጥ አንድም የሚሰራ ሎከር ማግኘተ ይከብዳል ። አብዛኛው ተበላሽቷል አይሰራም ።
ውሃ ❓
📚ውሃ በተደጋጋሚ ይጠፋል ፤ በተለይ ደሞ የዕረፍት ቀናት ለአንድ ሰዓት ብቻ ተለቆ ይቆማል ፤ ከተማዋ ላይ የውሃ እጥረት ስላለ ግቢ ውስጥም የተለየ ነገር የለም ..!
...ሽንት ቤት ...❓
📚 እንደ ካንፓሶቹ ቢለያይም አብዛኛው ግን በጣም አሪፍ የሚባል ነው ፤ በተለይ 4 ኪሎ በየቦታው ይገኛል ፤ የሚያስከፋ ነገር የለውም ሻል ያለ ነው ።
በግቢው ስላለ የዕቃ ስርቆት፦! ❓
📚 እንደካንፓሶቹ ቢለያይም ግርግር ፤ ረብሽ የሚባል ነገር ስለሌለ የስርቆት ነገር በጣም rare ነው ፤ ቸልተኛ ካልሆነ ስርቆቶ ብዙ የሚያሳስብ ነገር አይደለም ።
የሃይማኖታዊ ተቋማት ፦ ❓
📚 በብዙዎቹ ካንፓሶች በአቅራቢያቸው መስኪድ እና ቤተስኪያን ስላለ ሀይማኖታዊ ጉዳዮችን ለመከውን አያዳግትም ።
📚ተጨማሪ መረጃዎች በፎቶ እና ድምፅ የተቀመጡ ለማግኘት የድምፅ መረጃ ወይም የፎቶ መረጃ የሚለውን በተን ይጫኑ ።
📚 በተጨማሪም ሌሎች መረጃዎች ማወቅ እና መጠየቅ ከፈለጋችሁ ተጨማሪ የሚለውን በመጫን የዮኒቨርሲቲው ዌብሳይት እና ሬጅስትራል ስልክ የተማሪ ተወካዮች ሰልክ እንዲሁም የነባር ተማሪዎች መወያያ ግሩፖችን አቅርበንላቹሃል።
➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖
@Ethio_entrance