ግንቦት 16 በዓሉ ለቅዱስ ዮሐንስ ወንጌላዊ
በዚህ ዕለት ሐዋርያው ቅዱስ ዮሐንስ በብዙ ምክንያቶች ዓመታዊ መታሰቢያ ክብረ በዓሉ እንደሆነ የቤተ ክርስቲያን መጻሕፍት ያስረዳሉ
1 በእስያ በኤፌሶን በዙሪያው ሁሉ ዞሮ ወንጌልን ማስተማሩ መስበኩ ተዝካረ በዓል ለስብከቱ ነው (መጽሐፈ ስንክሳር የግንቦት 16 ንባብ)
2 በትምህርቱ በአምልኮተ ጣዖት የነበሩትን እስኪመልሳቸው ከሰይጣን ወጥመድ እስኪያድናቸው ድረስ በክፉዎች እጅ የተቀበለው መከራ ይታሰብበታል
በመጽሐፈ ገድሉ እንደተጻፈው ቅዱስ ዮሐንስ ወንጌላዊ ወንጌልን ለመስበክ ወደ ኤፌሶን ሲሄድ ጀምሮ ከደቀ መዝሙሩ ከአብሮኮሮስ ጋር ብዙ መከራዎችን ተቀብለዋል በዚህ ዕለት ይህን እናስባለን
3 ሦስቱ ወንጌላውያን ያስቀሩትን በማካተት ወንጌልን መጻፉ ይታሰባል
ቅዱስ ዮሐንስ ወንጌሉን ከሁሉ መጨረሻ የጻፈ በመሆኑ ሦስቱ ወንጌላውያን ያላካተቱትን የጌታን ትምህርቶች እና ተአምራቶች አካቶ ልዩ ወንጌል ጽፎልናል
ከመጽሐፈ ስንክሳር ጋር አብሮ የሚገኘው የምስጋና መጽሐፍ መጽሐፈ አርኬ ላይ እንዲህ ተብሎ ተጽፏል
ሰላም ለከ ሶበ ሰማዕከ ዐዋዴ፡
እምቃለ ወንጌል ዘወርቅ እንበለ ተምያን ወመፍዴ፡
ዮሐንስ ዘኮንከ በእንተ ጽድቅ ነጋዴ፡
መኒነከ እመ ወላዲተ ወአበ ወላዴ፡
ምስለ ነዳያን ነበርከ በዴዴ፡፡
(አዋጁን በሰማህ ጊዜ ያለ ግብዝነትና ያለ ክፍያ ወርቃማ ስለሆነው የወንጌል ቃል ብለህ የምትወልድ እናትና የሚወልድ አባትን ትተህ ስለጽድቅ ነጋዴ የሆንክና ከነዳያን ጋር በደጅ የኖርክ ዮሐንስ ሆይ ሰላም ላንተ ይሁን)
4 ራእዩን ያየበት ዕለት መታሰቢያ ነው
ሊቃውንት ቅዱስ ዮሐንስን ከሚጠሩባቸው ስያሜዎች መካከል አንዱ አቡቀለምሲስ ነው ባለራእይ ማለት ነው የሐዲስ ኪዳን የትንቢት መጽሐፍ የሚባለውን ራእይ ዮሐንስን የጻፈ ወደ ፊት የሚሆነውን አስቀድሞ በራእይ የተመለከተ በመሆኑ የተሰጠ ስያሜ ነው
5 በእስክንድርያ ሀገር ውስጥ ቤተክርስቲያኑ የከበረችበት ቀን ነው
የግንቦት 16 ስንክሳር የአርኬ ምስጋና ላይ
ሰላም ለቅዳሴ ቤትከ በእለእስክንድርያ ሀገር፡
እለ ሐነፅዋ ኬነዉት ወጠበብተ ምክር፡
ወእንዘ ትበውእ ዮሐንስ ውስተ መቃብር፡
ተኀባዕከ ወተሠወርከ በሥልጣነ ኀይል መንክር
ባሕቱ ልብስከ ዘተርፈ ለዝክር፡፡
ተጠባቢዎች በጠቢባኑ ምክር በእስክንድርያ ሀገር ላነፁት ቅዳሴ ቤትህ ሰላም እላለሁ፤ ዮሐንስ [ሆይ] ወደ መቃብር በገባህ ጊዜ ለመታሰቢያ እንዲሆን ልብስህ ብቻውን ቀርቶ በሚደንቅ ኃይል ባለው ስልጣን ተሰውረህ ታጣህ) ተብሎ እንደተጻፈ ቅዳሴ ቤቱ የከበረበትን ዕለት በዓል አድርገን እናከብራለን
♦ በአዲስ አበባ በሐዋርያው ስም በተሰየመው ብቸኛ ደብር በደብረ ነጎድጓድ ቅዱስ ዮሐንስ ቤተ ክርስቲያን በዓሉ ታቦት ወጥቶ በንግስ ባይከበርም ለሊት በማሕሌት ጠዋት በቅዳሴ ማታ በልዩ የሠርክ ጉባኤ ታስቦ ይውላል
የሐዋርያው አባታችን ምልጃ እና ጸሎት አይለየን