📢
ዩኒቨርሲቲ እና ተግዳሮቶቹ 🎓
🤗 ዩኒቨርሲቲ ላወቀበት ተማሪ እጅግ በጣም ብዙ መልካም የሆኑ ገፀ በረከቶች አሉት፡፡
እነዚህን መልካም ገፀ በረከቶች ስትገቡ ታጣጥሙታላችሁ🤓። እኛ ግን የምንፈልገው እናንተ ተግዳሮቱቹን አውቃችሁ ፡ ራሳችሁን እንድትታደጉ ነው።
😥ተማሪዎች ግቢ ላይ መጥፎ የተባሉ ነገሮች ይገጥማቸዋል።
እስኪ የተወሰኑትን እንመልከት🔗
1ኛ) 🥺 ብዙ ግዜ ዩኒቨርስቲዎች ከከተማ ዉጭ በተወሰኑ ኪሎ ሜትሮች ራቅ ብለው ነው የሚገነቡት። ከከተማ ውጭ ስለሆኑ fresh air የተትረፈረፈበት ፡ ራስን ለማዝናናት ና ለመመሰጥ እንድሁም ለማንበብ ምቹ የሆኑ ጫካዎች ና የተፈጥሮ መስህቦች አሉ።ስለዚህ ተማሪዎች ለመዝናናት ፡ ለማንበብ እንዲሁም walk ለማድረግ ወደ ጫካዎች ና ሰው ወደማይበዛበት ቦታዎች ሊሄዱ ይችላሉ።
በዚህ ምክንያት ፡📌 ሴቶች የመደፈር አደጋ ያጋጥማቸዋል።
📌 ወንዶች ደግሞ የ መሰረቅ አደጋ ያጋጥማቸዋል ምክንያቱም ሌቦች( የዩኒቨርሲቲ ተማሪ ወይም የአካባቢው ሰው ሊሆን ይችላል) ከግቢ ተማሪዎች ስልክ ፡ ብር ና ላፕቶፕ በማስፈራራት መውሰድ ለምደዋል። ስለዚህ ፡
ከላይ የጠቀስናቸው ቦታዎች ላይ ስትሔዱ ተሰባስባችሁ መሔድ ወይም ደግሞ አለመሔድ🙅♂️🤷♀️።
2ኛ) ይሄ ደግሞ በሴቶች ላይ የሚስተዋል ሲሆን በፈቃደኝነት ስህተት በመስራት የማይመለስ ፀፀት ዉስጥ የምትገቡበት ነው።
ገና ወደ ግቢ ስትገቡ ፡ ለግቢው አዲስ ናችሁ ፡ ለአካባቢው ና ለማህበረሱ አድስ ናችሁ ፡ ለዩኒቨርሲቲ ትምህርት ና ግቢ ውስጥ ስለሚሰሩ ነገሮች አዲስ ናቸው። ስለዚህ ነባር(senior) ተማሪዎች ይኸን ደካማ ጎናችሁን( አዲስነታችሁን) ተጠቅመው የህይወት መስመራችሁን ያስቷችሗል☹️።
ምን መሰላችሁ ሴቶችዬ 🤔ገና ዩኒቨርስቲ ስትገቡ ነባር ወንዶች ተማሪዎች አፋቸውን ከፍተዉ😂 እጃቸውን ዘርግተው ይቀበሏችሗል። ምክንያቱም የመጀመሪያ አመት ሴት ተማሪዎች : ተማሪዎች ወደ ግቢ ስትገቡ ነባር(senior) ወንድ ተማሪዎች ሴት ይፈልጋሉ።
ስለዚህ ምን ያደርጋሉ መሰላችሁ🐰
🧐መጀመሪያ ልክ ግቢ ስትገቢ ያይሻል። ሻንጣሽ ትልቅ ስለሆነ ይመጣና ላግዝሽ ይላል😁....ከዛን ይሸከምና እስከ ተመደብሽበት ዶርም #Dorm(setoch_gibi) ድረስ ያወራሻል...ከዛን ግቢውን እንዳላምድሽ ስ.ቁ ስጪኝ ይልሻል። አንቺም ለሁሉም ነገር አድስ ስለሆንሽ ስ.ቁ ትሰጭዋለሽ.....ነገሩ አለቀ🔪።
😴ከዛ ምዝገባ ላይ ተሯሩጦ ያስመዘገብሻል....እሱም በዚሁ.... ይቀጥላል።
🤗ከዛ ግቢውን ያስጎበሽኛል ፡ ከተማውን ያሳይሻል ፡ Lounge ይጋብዝሻል።
😴.....ከዛ ቡሃላ ምን ይፈጠራል መሰለሽ.......አንድ ቀን #Over እንዉጣ ይልሻል ፡ ከዛም🥃🍷🥂🍻 ትጠጣላችሁ። ከዛም በመጠጥ ሀይል አብረሺዉ ታድሪያለሽ። ካደርሽ ቡሃላ ምክንያት በመፍጠር ካንቺ ይርቃል ሌላ ይጠብሳል። በቃ ይሄው ነዉ🤢🤨☹️።
☹️ ማርገዝ የሚባል ነገር አለ ፍቅር ያሳየሽ መስሎ አታሎ...... ህይወትሽን ያጨልማል።
ከገጠር የሚመጡ ሴቶች በጣም ደስ ይላሉ ለምን ብትሉኝ አላማቸው አንድ ብቻ ነዉ። ፍቅረኛ አያቁ በትዳር ያምናሉ።
የከተማ ልጆች ደግሞ.....😂😂 ሁሉንም አይደለም።
🥺 ስለዚህ ሴቶችዬ ጠንካራ ፡ ፅኑ ፡ አላማችሁን የምታስቀድሙ መሆን አለባችሁ💃💃።
3ኛ) Over🕺💃🕺💃🕺
የዩኒቨርሲቲ ተማሪ over ካልወጣ oxygen እንዳጠረው የሚታሰብበት ጊዜ ላይ ደርሰናል።
እንደ ሰደድ እሳት የግቢ ተማሪዎችን ህይወት እያበላሸ ያለው over ነው። over ከጥቅሙ ጉዳቶች ያመዝናሉ ምክንያቱም ፡
📌#over በወንዶች ተማሪዎች ላይ ያለው ተፅዕኖ።
የግቢ ተማሪዎች over ወጥተው ይጠጣሉ ። ከዛም ሞቅ ይላቸዋል ፡ ከዛም በ ደረቅ ሌሊት ከ አካባቢው ወጣቶች ጋ ይጣላሉ ፡ ከዛም በጩቤ ይወጋሉ አልያም በጠርሙስ ይመታሉ ። ከዛም በሌሊት 6 ወይም 7 ሰአት ወደ ሆስፒታል😏። ከ አካል ጉዳት እስከ ህይወት መጥፋት የሚያስከትል ችግር በ #over ምክንያት። እንደታደል ሁኖ ካልተጣላችሁ ፡ በ ደረቅ ሌሊት 8 ሰአት ምናምን ወደ ግቢ ዘበኛ ለምናችሁ ትገባላችሁ። ከመጥን በላይ ቀላቅላችሁ ስለምትጠጡ በየ ሽንት ቤቱ ሻታ🤮🤮🤮።
👷♂ ወንዶችየ ተጠንቀቁ ነፃነት አገኘን ብላችሁ ነፃነታችሁን እንዳታጡ🤨።
📌 #over በሴቶች ተማሪዎች ላይ ያለው ተፅዕኖ ።
በተለይ የ ከተማ ሴቶች
shameless ናቸው☹️። ሲጠጡ ራሱ😴😴።
ሴቶች #over ይወጣሉ ፡በ ወንዶች ጋባዥነት ይጠጣሉ🥂🍻🍷 ፡፡ ከዛ ይሰክራሉ ። ከዛ ደግሞ አልጋ ይዘው ለማደር ብር ላይኖርቸው ይችላል። ስለዚህ ጎዳና ላይ ማደር ስለማትፈልጊ ፡ ከአንዱ ጋር ታድሪያሽ🙁። ከዛ ያልተፈለገ ዕርግዝና ሊከሰት ይችላል። ከዛ በሗላ የሚመጣውን ጣጣ አስቡት😔😱።
ሴት ልጅ ሰክራ በየ አስፓልቱ ስትወድቅ ምን ይባላል 😔 ይሄን የሚያደርጉት.... አወቅን ባይ የከተማ ልጆች ናቸው።
👷♀ሴቶችዬ ተጠንቀቁ። ነፃነት አገኘን ብላችሁ ነፃነታችሁን እንዳታጡ።🟢
👆👆እና ሰዎችዬ ከላይ የዘረዘርናቸው የግቢ ተግዳሮችን ለመፃፍ እና ለ እናንተ ለማጋራት ያሰብንበት ዋና ምክንያት ግቢ እንደዚህ አይነት ነገር ስለሚኖር ካሁን አውቃችሁት ፡ እንድትጠነቀቁ ነው እንጅ ስለ ግቢ መጥፎ ነገር መናገር ፈልገን ወይም እንድትሳቀቁ ፈልገን አይደለም።
🕺 ራሳችሁን በአግባቡ መምራት ከቻላችሁ ግን ግቢ ላይ ምርጥዬ ህይወት ይኖራችሗል።
ለፍሬሽ ተማሪዎች የተከፈተ ! 👇
Freshman Journey |
Join Now