በ2017 የትምህርት ዘመን አዲስ የዩኒቨርሲቲዎች የቀን የምግብ በጀት ዋጋ ተመን ይፋ እንደሚደረግ ትምህርት ሚኒስቴር ባለፈው ሐምሌ መግለፁ ይታወቃል።
ይሁን እንጂ የ2017 ትምህርት ዘመን መጀመርንም ተከትሎ ዩኒቨርሲቲዎች አሁንም ቀድሞ በነበረው የበጀት አሰራር ተማሪዎቻቸውን እየመገቡ ይገኛሉ።
በጉዳዩ ላይ አስተያየታቸውን ለኢትዮጵያ ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ተማሪዎች ህብረት የሰጡት የትምህርት ሚኒስትር ዴኤታ ኮራ ጡሹኔ፣ የተሻሻለው አዲስ የበጀት አሰራር በቅርቡ ይለቀቃል ብለዋል።
"ለሁሉም ዩኒቨርሲቲዎች አንድ አይነት የሜኑ በጀት ይሁን ወይስ በየአካባቢው የሚገኘውን ሀብት መሠረት ያደረገ በጀት ይሁን" በሚለው ላይ ውይይት እየተደረገ መሆኑን ጠቁመዋል።
ይሁን እንጂ የተሻሻለው አዲስ የሜኑ አሰራር በቅርቡ ይለቀቃል ያሉት ሚኒስትር ዴኤታው፤ በዚህም የአንድ ተማሪ የቀን ወጪ ከ100 ብር በላይ እንደሚሆን ገልፀዋል።
ዩኒቨርሲቲዎች በቀን አንድ ተማሪ ቁርስ፣ ምሳ እና እራት ለመመገብ በመንግሥት የሚመድብላቸው 22 ብር በጀት በቂ አለመሆኑን በተደጋጋሚ ያነሳሉ፡፡
ከፍተኛ ትምህርት ተቋማቱ ከተለያዩ በጀቶች በማዛወር በቀን እስከ 80 ብር በመመደብ ተማሪዎቻቸውን እየመገቡ እንደሚገኙ ይገልፃሉ፡፡
የዋጋ ትመናው ጊዜውን ያላገናዘበ በመሆኑ ማስተካከያ ሊደረግበት እንደሚገባ የተለያዩ አካላት ሲጠይቁ ይደመጣል፡፡
የትምህርት ሚኒስትሩ ብርሃኑ ነጋ (ፕ/ር)፣ ጥናቶች "እስከ ነሐሴ 2016 ዓ.ም ድረስ ሥራዎች ተጠናቀው በአዲሱ የትምህርት ዘመን አዲስ የቀን ዋጋ ተመን ይፋ ይደረጋል" ብለው እንደነበር አይዘነጋም፡፡
@Freshmanshortnote