የግዮን ት/ቤት ተማሪዎች ንቅናቄ | ባህር ዳር


Гео и язык канала: не указан, не указан
Категория: не указана



Гео и язык канала
не указан, не указан
Категория
не указана
Статистика
Фильтр публикаций


ከግዮን አጠቃላይ ፪ኛ ደረጃና ከፍተኛ ት/ም መሰናዶ ት/ቤ የተማሪዎች ንቅናቄ 'ለተማሪዎች' የቀረበ የትግል ጥሪ !!

የአማራ ሕዝብ(ፋኖ) በዚህ ወቅት በኦሮሙማው ኦነግ መራሹ ብል*ግና እና በገረዱ ብአዴን የተከፈተበትን ሀሉን አቀፍ ጦርነት በመመከትና አፀፋ በመመለስ ላይ ይገኛል።ሰው በላው አገዛዝ የመንግሥታዊ ቁመና ላይ ያለ ለማስመሰልና ለፓለቲካ ፍጆታ ያመቸው ዘንድ በጊዜያዊነት በተቆጣጠራቸው ቦታዎች የመጀመሪያ ደረጃና ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ለማስጀመር እና ለማካሄድ ሲጋጋጥ ከርሟል።

ታዲያ በሌሎች አካባቢዎች ላይ ትምህርት ቤቶችን ከነተማሪዎቻቸው በድሮን አንድዷል በከባድ መሳሪያ ደብድቧል እንዲሁም የአገዛዙ ጨፍጫፊ ወታደሮች በትምህርት ቤቶች ላይ ካምፕ አድርገው የትምህርት ቤቶቹን ንብረት ለምሽግ መስሪያ እና ለማገዶነት ሲጠቀሙ ተመልክተናል። ኦሮሙማው ኀይል ይህንን ሁሉ እያደረገ በመሆኑ ትምህርት መማር ፈፅሞ የማይቻልበት ሁኔታ መፈጠሩን ልብ ብለናል። አገዛዙ የአማራ ሕዝብ በትምህርት እንዲዳሽቅ እየሰራ መሆኑንም በሚገባ ተረድተናል።

ስለዚህ ይህ የጭቆና አገዛዝ ተገርስሶ ነፃነታችን እስክናረጋግጥ እና ለመማር ማስተማር የሚመች ምህዳር እስኪፈጠር ያለን ብቸኛው አማራጭ ትግል በመሆኑ እኛ ተማሪዎችም በንቅናቄ መነሳት ስላለብን በንቅናቄ መጥተናል። ከትጥቅ ትግል በተጨማሪ በከተማ ውስጥ በተማሪ ደረጃ የሚካሔዱ በርካታ የትግል መስኮች ስላሉ ለሚከተሉት አካላት የትግል ጥሪያችንን እናስተላልፋለን ፦

፩ኛ. ለግዮን አጠቃላይ ፪ኛ ደረጃና ከፍተኛ ት/ም መሰናዶ ትምህርት ቤት ተማሪዎች በሙሉ ፦
በትምህርት ቤታችን ተከታታይ የቦምብ ፍንዳታዎችን ማስተናገዳችን የሚታወቅ ነው በዚህም የሁለት ሰዎች ህይወት አልፏል።
በዙሪያችን ሌሎች ወንድም እህቶቻችን ትምህርታቸውን አቋርጠው ትግል ውስጥ ባሉበት ሁኔታ የኛ ብቻ መማር አግባብነት የለውም። ሲበዛ ራስ ወዳድነትም ነው። ለአገዛዙ የፖለቲካ መስሪያ ብቻ እየሆንን በመሆኑ ከዚህ በመቀጠል ለሚኖረን ማንኛውም የትግል እንቅስቃሴ እራሳችሁን እንድታዘጋጁ እንጠይቃለን።

፪ኛ. በባህርዳር ከተማ ውስጥ በሌሎች ት/ቤቶች ለምትገኙ እህት ወንድሞቻችን ፦
እናንተም ልክ እንደ እኛው ሁሉ በየትምህርት ቤቶቻችሁ ንቅናቄ በመፍጠር ለዚህ የህልውና ትግል ከእኛ ከተማሪዎች የሚጠበቀውንና የበኩላችንን ሚና በአንድነት እንድንወጣ እንጠይቃለን።

፫ኛ. ለውድ መምህራን ፦
እናንተ ነገሮችን ለመረዳት ትቸገራላችሁ ብለን አናስብም ስለሆነም ከልጆቻችሁ ከኛ ከተማሪዎች ጎን በመሆን እንደ ማንኛውም የአማራ ሕዝብ ለዚህ የህልውና ትግል የድርሻችንን አስተዋጽኦ እንድናበረክት በትህትና እንጠይቃለን።

ጥቅምት ፩ቀን ፪፼፲፯ ዓ.ም
የግዮን አጠቃላይ ፪ኛ  ደረጃና ከፍተኛ ት/ም መሰናዶ ት/ቤ የተማሪዎች ንቅናቄ
"ትምህርት ከነፃነት በኋላ!!"

Показано 1 последних публикаций.