ሰሞኑን በዩንቨርስቲ ተማሪዎች እየተነሱ ያሉት ተቃውሞዎች ምንን በማስመልከት ተጀመሩ??
⚡️በተለይም #መቀሌ፣ #ደባርቅ እና #ደብረብርሃን ዩኒቨርስቲዎች ውስጥ ተማሪዎች ተቃውሞዋቸውን ሲገልፁ እንደቆዩ በተለያዩ የሶሻል ሚድያ ገፆች ሰምተናል።
⚡️በቅርቡ የወጣው የት/ት ሚኒስቴር የምግብ በጀት ማሻሻያ አዋጅ ለአብዛኛው የዩንቨርስቲ ተማሪ እንደ ታላቅ የምስራች ሆኖ ቢቀርብም የአዋጁ ትክክለኛ ትግበሯ ከታሰበው ተቃራኒ ለውጦችን ይዞ መቷል።
⚡️ተማሪዎች አዲሱን አዋጅ በማስመልከት የተደረገውን የበጀት ጭማሪ እለታዊ የምግብ አገልግሎቱን በዓይነትም ሆነ በጥሬ ገንዘብ ለሚጠቀሙ ሁሉ መሻሻሎችን ይዞ ይመጣል ብለው ቢጠብቁም በተለይም በነዚህ 3 ዩንቨርስቲዎች አጅግ ከፍቶ አግኝተውታል።
⚡️በደስታው ብዛት አዋጁን ያልመረመረው ተማሪ የበጀት ማሻሽያው አስከዛሬ በመንግስት ይደረግ የነበረን ድጎማ ማቋረጥ ላይ የተመሰረተ አንደሆነ ዘንግቶት ቆይቷል። በአንድ እለት ለአንድ መአድ ከተመደበው 22 ብር በላይ እስከ 150 ብር ድጋፍ ያቀርብ የነበረ መንግስት እጁን ሰብስቦ 100 ብር ብቻ ሲመድብ በምግቡ ጥራትም ሆነ ብዛት ላይ ሊያስከትል የሚችለው ጉዳት ሳይታለም የተፈታ ነው።
💥ነገር ግን ከዚህ በፊት ለመንግሥታት ውድቀት ምክንያት አንደኛ ረድፍ ተሰላፊ የሆነውን ተማሪ አና የተማሪ ህብረት በዚህኛው መንግስት ስርስ አንዴት አንደሚስተናገድ መረዳት የመንግስቱን ቀጣይ አጣ ፋንታ ይጠቁመን ይሆን?
#ዩኒቨርስቲ #ኢትዮጵያ #ምግብ
©Tikvah
Join Us
https://t.me/+6HHF7MBj0VUyMjVk