#ወዳጅህ_ላግኝህ_ካለ
.
♻️አንዳንዴ ጊዜ አንድን ሰው ለራሱ ጉዳይ ትፈልገዋለህ። በተደጋጋሚ ብትሞክርም ስልክ አያነሳም፤ ሊያገኝህም አይፈልግም። ልታስቸግረውና ለራስህ ጉዳይ የፈለግከው ይመስለውና ይሸሻል። በዚህ መልኩ ሳያስበው ጥቅሙን ይሸሻል።
🔻#ሰውን_ስታከብረው ልትተዋወቀው ታስባለህ፣ ሠላምታ ታበዛበታለህ፣ ልትዘይረው ትከጅላለህ፣ ልታየው ትጓጓለህ፣ ልታገኘውም ትናፍቃለህ።
#እርግጥ_ነው....!
ሰው ከሆንክ ከዝምድና፣ ከእምነት፣ ከትውውቅ እና ከጓደኝነት ባለፈ ሰው በመሆኑ ብቻ ትናፍቀዋለህ።
ከአንድ አፈር ተቦክተሃልና። ሰውን ከሰው ላስተሳሰረ አሏህ ምስጋና ይገባው።
.
🔴አንድን ሰው በተለይ ትንሽ ታዋቂ የሆነን ሰው ስታገኘው አክብሮትህን ታንፀባርቅለታለህ። በደረጃው ልክም ታከብረዋለህ፣ ግና #ተሽቆጠቆጥክለት ማለት የሆነ ጥቅም ከሱ ታስባለህ ማለት አይደለም።
✅ሰውን ልታገኘው ትጓጋለህ ማለት
✅ልታስቸግረው ታስባለህ ማለት አይደለም።
🔻እንዲህ እንዲህ ማሰብ መልካም ይመስለኛል ። እንዲህ በማሰቤ #የእስልምናን_አስተምህሮ ስቼ ይሆን እላለሁ አንዳንዴ.. .
✅ኖ አይደለም እስልምና ነው እንዲህ ያስተማረኝ‼️
🔷... ሰውን አክብር፤ ራስህን አስተናንስ ይላል ኢስላም። ኢስላም ባይልም #ጤናማና_ተወዳጁ አካሄድ ይህ ነው። ተፈልጌያለሁ ብለህ አትኮፈስ። እበልጣለሁ ብለህ ዉድ አትሁን። ተጋብዣለሁ የክብር እንግዳ ነኝ ብለህ ሰዓት አታሳልፍ፤ ሰውን አታስጠብቅ።
.
♻️አክብሮህ ላግኝህ ያለን ሰው አትሽሽ።
♻️የተፈለግክ በመሆንህ አሏህን አመስግን።
ማግኘት ባትፈልግ እንኳ ቢያሳምንም ባያሳምንም ምክንያትህን አቅርብና ይቅርታ ጠይቅ። አደቡ እንዲያ ነው። በተቻለህ መጠንና አጋጣሚ ሁሉ ከታሰብክበት ከፍ ለማለት ሞክር።
✅የባህሪ ሀብታም ለመሆን ጣር።
🔻ከሌላ ፕላኔት የመጣ አንድም ሰው የለም። ሁላችንም #ከአፈር_ነን።
ብርቱ የሆነውን የዱንያ ፈተና ለማለፍ #ሰው_ለሰው የጉዞ ባልደረባው ነው።
✅ሰው ብቻውን ሲሆን አንድ፤
✅ከሰው ጋር ሲሆን ብዙ ነው።
#አይደለም___እንዴ!
ገጠመኞቻችን ናቸው የሚያናግሩን።
https://t.me/Kamilaumusaymen