Millennium Covid Care Center (MCCC) | ሚሊኒየም ኮቪድ 19 ህክምና ማእከል


Гео и язык канала: не указан, не указан
Категория: не указана


ይህ የሚሊኒየም ኮቪድ 19 ህክምና ማእከል የመረጃ ማቀበያ ቻናል ነው።

Связанные каналы

Гео и язык канала
не указан, не указан
Категория
не указана
Статистика
Фильтр публикаций


My Hero is You, Storybook for Children on COVID-19 (Amharic).pdf
3.6Мб
"ይህ መጽሀፍ፡ በአለም ዙርያ ላሉት፡ በኮቪድ-19 ለተቸገሩ ህጻናት ተብሎ የተዘጋጀ ነው።
መጽሀፉ፡ በወላጆች፣ ባለ ሙያ በሆኑ አግልግሎት ሰጪዎች፣ ወይም ደግሞ በአስተማሪዎች ሊነበብ ይገባዋል። ለአንድ ህጻን ወይም ደግም አነስተኛ ለሆነ የህጻናት
ቡድን ሊነበብ ይችላል። ህጻናት፡ ያለ ወላጅ፣ ባለ ሙያ፣ ወይም አስተማሪ ለብቻቸው እንዳያነቡት ቢሆን ይመረጣል። በቅርቡ ሊታተም በዝግጅት ላይ የሚገኝ፡
“የጀግኖች ግብር” የሚል ማጣቀሻ፡ ከኮቪድ-19 ጋር ተያያዥ በሆኑ ጉዳዮች ላይ ተጨማሪ ትምህርት የሚሰጥ ሆኖ፡ ህጻናት ስሜቶቻቸውንና አስተያየቶቻቸውን
እንዴት ሊቆጣጠሯቸው እንደሚችሉ የሚረዳ ከመሆኑ ባሻገር፡ ሌሎች ማብራርያዎችንም ያካተተ ነው። "




ውድ የሚሊኒየም ኮቪድ ህክምና ማዕከል ሰራተኞች በሙሉ፤
እንኳን ለ2014 የዘመን መለወጫ በዓል በሰላም አደረሳችሁ፡፡
በ 2013 ከነበረን ከባድ ችግር ተሻግረን አዲሱ አመት የሰላም፤የፍቅር የመተሳሰብ እና የብልጽግና እንዲሆንልን መልካም ምኞታችንን እንገልጻለን


አይነቶች ፤ ምንነት እና ውጤት

የኮቪድ 19 አይነት (variant) ስንል ምን ማለታችን ነው?

ኮቪድ 19 ወይም በህክምና መጠሪያው SARS-COV 2 በዋነኝነት የመተንፈሻ አካላት ላይ እክል የሚያመጣ፣ በቀሪዎቹ የአካላዊ ስርዓቶቻችንም ላይ ችግር ሊያስከትል የሚችል ደቂቅ ህዋስ ሲሆን የሚመደበውም ቫይረስ ከሚባሉት የደቂቅ ተዋህሲያን ፈርጅ ነው።
እነዚህ በጥቅሉ ቫይረስ ተብለው የሚጠሩት ተዋህሲያን ባህሪ ውስጥ አንዱ እና ዋነኛው ከአካባቢያችው ጋር በሚኖራቸው መስተጋብር ሂደት ፈጣን የገጽታ ለውጥ ማስተናገዳቸው ነው። የኮቪድ 19ም ቫይረስ በዚህ የተፈጥሮ ህግ መሰረት ቫይረሱ ከተለየበት ዲሴምበር 2019 ጀምሮ በርካታ ለውጦችን አስተናግዷል። ባለሙያዎችም በዘረ መል ጥናት እንዚህን ለውጦች በመከታተል ተመሳሳይ ለውጥ ያላቸውን ቫይረሶች ወደ አንድ ግንድ እያመጡ ስም እየሰጡ ይገኛሉ። ይህንንም ጥናት እያካሄዱ ያሉ የተወሰኑ ተቋሞች ያሉ ሲሆን በስፋት የሚታወቀው ግን በዓለም ጤና ድርጅት የተዋቀረው ቡድን እና ቡድኑ የቫይረሱን ግንዶች የሚጠራባቸው ስያሜዎች ናቸው። እነዚህም አልፋ፣ ቤታ፣ ጋማ እንዲሁም ዴልታ የተባሉት የኮቪድ 19 አይነቶች ናቸው።

ታዲያ በዚህ አመት ውስጥ ቫይረሱ በብዙ አይነቶች ካለ/ከተፈጠረ፤ ለምን እነዚህ አራቶቹ ተለይተው ወጡ?

የሚከሰቱት አይነቶች በባህሪያቸው ከሰው ሰው የመተላለፍ አቅማቸው ከፍተኛ የሆነ፣ የሚያስከትሉት የህመም ሁኔታ ጫን ያለ ወይም ለየት ያለ ሆኖ ከተገኘ ‘አሳሳቢ አይነት’ / Variant of Concern ተብለው ይመደባሉ። ከላይ የተጠቀሱትም አይነቶች በእነዚህ መስፈርቶች ላይ ተንተርሶ አሳሳቢ የህመም እና ስርጭት ሁኔታ ላይ በመድረሳቸው ከፍተኛውን የአለም የጤና ድርጅት የአመዳደብ ደረጃ ይዘዋል። ከዚህ ዝቅ ስንል ‘ክትትል የሚያስፈልጋቸው አይነቶች’ / Variant of Interest ተብሎ የሚጠራው መደብ ሲገኝ እነዚህንም በባህሪያቸው የመተላለፍ አቅማቸው መጠነኛ መጨመር ካሳየ ነገር ግን የሚያመጡት ህመም ላይ መጨመርም ወይም መለየት ከሌለ ከዚህ ደርጃ ላይ እናስቀምጣቸውለን።

አልፋ/ Alpha - B.1.1.7

መጀመሪያ የተለየው: ዩናይትድ ኪንግደም
ስርጭት: ከሌሎች አይነቶች አንጻር በጣም ከፍተኛ በሆነ መጠን እና ፍጥነት ይሰራጫል
ከባድ ህመም እና ህልፈት: በአንጻራዊነት የበለጠ ቁጥር ያላቸው ሰዎች ላይ ህመም እንዲሁም ህልፈት ያስከትላል
ክትባት: በአሁኑ ሰአት እየተሰጡ ያሉ ክትባቶች ይሄንን አይነት በሚገባ ይከላከላሉ፤ ከከባድ ህመም እና ህልፈትም ይጠብቃሉ።

ቤታ/ Beta - B.1.351

መጀመሪያ የተለየው: ደቡብ አፍሪካ
ስርጭት: በመጠኑ ከፍ ያለ አንጻራዊ የስርጭት መጠን ይኖረዋል
ከባድ ህመም እና ህልፈት: እስካሁን ባለው መረጃ በግልጽ የተለየ የጨመረ ከባድ ህመም እና ህልፈት አያስከትልም
ክትባት: በአሁኑ ሰአት እየተሰጡ ያሉ ክትባቶች ይሄንን አይነት በሚገባ ይከላከላሉ፤ ከከባድ ህመም እና ህልፈትም ይጠብቃሉ።


ጋማ/Gamma - P.1

መጀመሪያ የተለየው: ጃፓን/ ብራዚል
ስርጭት: በመጠኑ ከፍ ያለ አንጻራዊ የስርጭት መጠን ይኖረዋል
ከባድ ህመም እና ህልፈት: እስካሁን ባለው መረጃ በግልጽ የተለየ የጨመረ ከባድ ህመም እና ህልፈት አያስከትልም
ክትባት: በአሁኑ ሰአት እየተሰጡ ያሉ ክትባቶች ይሄንን አይነት በሚገባ ይከላከላሉ፤ ከከባድ ህመም እና ህልፈትም ይጠብቃሉ።

ዴልታ/ Delta - B.1.617.2

መጀመሪያ የተለየው: ህንድ
ስርጭት: ከሌሎች አይነቶች አንጻር በጣም ከፍተኛ በሆነ መጠን እና ፍጥነት ይሰራጫል
ከባድ ህመም እና ህልፈት: በአንጻራዊነት የበለጠ ቁጥር ያላቸው ሰዎች ላይ ህመም እንዲሁም ህልፈት ያስከትላል
ክትባት: ከዴልታ አይነት አዲስ ከመሆን ጋር ተያይዞ በኮቪድ ክትባት እና በዚህ አይነት መካከል ያለው ቁርኝነት ሙሉ ለሙሉ ግልጽ አይደለም። ይህም ሆኖ እስካሁን እየወጡ ያሉ ጥናቶሽ የሚያመለክቱት የኮቪድ 19 ክትባት አሁንም ቢሆን ጠቃሚ እንደሆነ ነው

ዴልታ አይነት ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በተለያዩ አገራት በስፋት እና በፍጥነት እየተሰራጨ የሚገኝ አይነት ነው። ይህ አይነት ከአሳሳቢነቱ እና ከአዲስነቱ አንጻር በርካታ ጥያቄዎችን ያስነሳል።ከእነዚህ ጥያቂዎች መካከልም የተወሰኑትን የሚከተሉት ናቸው።

1. ክትባቱን የወሰደ ግለሰብ የዴልታ አይነትን የመከላከል አቅሙ ምን ይመስላል?
እስካሁን ባሉን መረጃዎች ክትባቱን ያልወሰደ ሰው ክትባቱን ከወሰደ ሰው ጋር ሲነጻጸር በዴልታ አይነት የመጠቃት እድሉ በስምንት እጥፍ የጨመረ ሆኖ ተገኝቷል። በተመሳሳይ ክትባቱን ያልወሰደ ሰው ክትባቱን ከወሰደ ሰው ጋር ሲነጻጸር በዴልታ አይነት ታሞ ህኪም ቤት የመግባት እና የማለፍ እድሉ በሃያ አምስት እጥፍ የጨመረ ሆኖ ተገኝቷል።

2. ከዚህ በፊት በኮቪድ 19 ተጠቅቶ ያገገመ ሰው (ነገር ግን ያልተከተበ) ግለሰብ የዴልታ አይነትን የመከላከል አቅሙ ምን ይመስላል?
ባለፉት 12 ወራቶች ውስጥ በኮቪድ 19 ተይዞ ያገገመ ሰው ሌሎቹን የኮቪድ አይነቶች የመከላከል አቅሙ ከሞላ ጎደል ከተከተበ ሰው ጋር ተመሳሳይ እንደነበር ሲነገር ቆይቷል። ነገር ግን ይህ ሁኔታ ዴልታ አይነትን እንደማያካትት ጥናቶች እያመላከቱ ነው።

3. ተጨማሪ የኮቪድ 19 አይነቶች ይፈጠራሉ?
አዎ። አሁንም ቢሆን የአለም የጤና ድርጅት ‘ሚው’ እና ‘ላምዳ’ የተባሉ አይነቶችን እየተከታተለ ይገኛል። ‘ላምዳ’ በጁን ወር 2021 እንዲሁም ‘ሚው’ በኦገስት ወር መጨረሻ ‘ክትትል የሚያስገልጋቸው አይነቶች‘ የሚለውን የአለም ጤና ድርጅት ደረጃን ተቀላቅለዋል።


የሚሊየም ኮቪድ 19 ህክምና ማእከል የህክምና አሰጣጥ/ ክፍል አንድ

ኮቪድ 19 ከቀላል ጉንፋን መሰል ሁኔታ እስከ ከባድ የአተነፋፈስ ስርዓት እክል የሚደርስ ህመም እንደሚያስከትል ይታወቃል። ከዚህም አንጻር የኮቪድ 19 ተጠቂዎች በአብዛኛው በቤት ውስጥ ውሸባ እና በቀላል የህመም ማስታገሻ መድሃኒቶች በመታገዝ የሚያገግሙ ይሆናል። ነገር ግን የህመሙ ደረጃ ከፍ በሚልበት ወቅት በህክምና ማእከል ውስጥ የሚደረግ ቀጥተኛ የህክምና ድጋፍ አስፈላጊ ይሆናል። ይሄም የህክምና ሂደት በጠቅላላው ተመሳሳይ በሆነ አደረጃጀት በተለያዩ የኮቪድ ህክምና ማእከሎች ውስጥ የሚደረግ ይሆናል።

ለምሳሌ በሚሊኒየም የኮቪድ 19 ህክምና ማእከል እስጥ የህክምና አሰጣጥ ሂደት የሚጀምረው ታካሚዎች በአንቡላንስ ከሚመጡበት ደቂቃ ጀምሮ ነው። ይሄም የሚካሄደው በታካሚዎች መቀበያ እና መለያ ክፍል ውስጥ ነው።

የታካሚዎች መቀበያ እና መለያ ክፍል/ትሪያጅ/Triage
በዚህ ክፍል ውስጥ ታካሚዎችን ከአንቡላንስ በመቀበል የህመማቸውን ሁኔታ ቅድመ ግምገማ እንከውናለን። ይህም ማለት የታካሚውን ጠቅላላ ሁኔታ፣ ተጓዳኝ ህመሞች፣ አጣዳፊ የጤና እክሎችን ፣ የአተነፋፈስ ሁኔታ እንዲሁም የኦክሲጅን ፍላጎት ይገመገማል ማለት ነው። እነዚህን መረጃዎችም በመጠቀም ታካሚዎችን ህክምናቸውን ወደሚቀጥሉበት ክፍል የመመደብ ስራ ይሰራል። ህክምናቸውን የሚቀጥሉበት ክፍሎችም በሶስት ይከፈላሉ።

1. የተኝቶ ማከሚያ ክፍል/ዋርድ/Ward
ይህ ክፍል በማእከሉ ውስጥ ህክምና ከሚደረግላቸው ታካሚዎች ውስጥ በአንጻራዊነት ጥሩ ሁኔታ ላይ የሚገኙ ታካሚዎች የሚገኙበት ክፍል ነው። በዚህ ክፍል ውስጥ በአብዛኛው ቀላል የኦክሲጅን ድጋፍ የሚያስፈልጋቸው ታካሚዎች ክትትል የሚደረግላቸው ሲሆን ሄፓሪን እና ዴክሳሜታሶን የተባሉ የማገገም ሂደቱን የሚያፋጥኑ መድሃኒቶች ለታካሚዎች የሚሰጡ ይሆናል። በተጨማሪም ታካሚዎች ሊኖሯቸው የሚችሉ ተጓዳኝ ህመሞችን የማከም ስራ ይሰራል።

2. የከፍተኛ ድጋፍ ክፍል/ሃይ ዲፔንደንሲ ዩኒት/HDU
የከፍተኛ ድጋፍ ክፍል ከበድ ያለ የህመም ሁኔታ ያላቸው ታካሚዎች የሚገኙበት ቦታ ነው። እነዚህ ታካሚዎች የኦክሲጅን ፍላጎታቸው ከፍተኛ ሲሆን ፊት ላይ በሚደረግ የኦክሲጅን ማስክ በኩል ከፍተኛ የኦክሲጅን መጠን የሚሰጣቸው ይሆናል። ሄፓሪን እና ዴክሳሜታሶን የተባሉትም የማገገም ሂደቱን የሚያፋጥኑት መድሃኒቶች መሰጠት የሚቀጥሉ ይሆናል። ታካሚዎች ሊኖሯቸው የሚችሉ ተጓዳኝ ህመሞችን የማከም ስራ ይቀጥላል።

3. የጽኑ ህሙማን ክፍል/ አይ ሲ ዩ/ICU
ይክ ክፍል በማእክሉ ውስጥ ካሉ ህሙማን የጠና ደረጃ ላይ ለሚገኙ ታካሚዎች ክትትል የሚደረግበት ክፍል ነው። እነዚህ ታካሚዎች የአተነፋፈስ ስርዓታቸው የተዛባ ስለሆነ ይህንን ሆኔታ ለማስተካከል የማሽን ድጋፍ ያስፈልጋቸዋል። የማሽን ድጋፉን በሁለት ከፍሎ ማየት የሚቻል ይሆናል።
• የመጀመሪያው የድጋፍ አይነት ታካሚዎቹ ንቁ ሆነው ከማሽን ጋር በተያያዘ የኦክሲጅን ማስክ በኩል የአተነፋፈስ ድጋፍ የሚደረግላቸው ይሆናል። ይህ እርምጃም የማሽን ድጋፍ ለሚፈልጉ ታካሚዎች የመጀመሪያው ደረጃ ይሆናል።
• ሁለተኛው እንዲሁም የመጨረሻው የድጋፍ ድጋፍ የሚደረገው ታካሚዎችን የሰመመን መድሃኒት በመስጠት የመተንፈሻ ቱቦ ወደ መተንፈሻ አካት ውስጥ አስገብቶ የአተነፋፈስ ሂድቱ በማሽን እንዲካሄድ በማድረግ ነው።በዚህ ሂደት ውስጥ ታካሚው ንቃተ ህሊና ውስጥ አይሆንም ወይም ራሱን አያውቅም።




Видео недоступно для предпросмотра
Смотреть в Telegram


ለአስታማሚዎች የሚጠቅም


በኮሜንት ማብራሪያዎችን እና ተጨማሪ ጥያቄዎችን አጋሩን! በአፋጣኝ መልስ እንሰጣለን!


ለአስታማሚዎች የሚጠቅሙ መረጃዎች


Видео недоступно для предпросмотра
Смотреть в Telegram


Видео недоступно для предпросмотра
Смотреть в Telegram



Показано 13 последних публикаций.

493

подписчиков
Статистика канала