ሞሮ
ክፍል 19
በእጄ የያዝኩትን ፌሮ በንዴት ኤቤጊያ ፊት ላይ ቀስሬው እንዳለ ራስታው ልጅ እኔን ለማረጋጋት ወደኔ ሲጠጋ ኤቤጊያ ፊት ላይ ተቀስሮ የነበረው ፌሮ እሱ አናት ላይ በሃይል ተሰነዘረ ራስታው ወዲያው ደምበደም ሆኖ መሬት ወድቆ ተዘረረ ኤቤጊያ ይህንን ስታይ ጩኀቷን አቀለጠችው አብረውት ቆመው የነበሩት ጓደኞቹ ደንግጠው እንደድንጋይ ደርቀው ቀሩ ከወር በፊት ያደረጉት ትዝ ብሏቸው ለመሮጥ ሲዘጋጁ ሁለቱንም በፌሮው እንደ እባብ አናት አናታቸውን ቀጠ አጥኳቸው ወዲያው ሰዉ ተሰብስቦ ገላገለን ንዴቴን መቆጣጠር አልቻልኩም ብንን!! እላለው ይህ ሁሉ ጉድ በሰመመን በቁሜ ስቃዥ ነው!!! ይበልጥ ተበሳጨው ኪያር ከኃላዬ ሆኖ እንሂድ በቃ እያለኝ ነው ኤቤጊያ አሁንም በራስታው እቅፍ ውስጥ ናት በሰመመን ያየሁትን ልደግም ፌሮውን በሃይል እንደጨበጥኩ እንዴቴ ሊወጣ እየተፍለቀለቀ በፍጥነት እነኤቤጊያ ወደቆሙበት ቦታ ሄድኩ ልክ አጠገባቸው ስደርስ ንዴቴ እንደቅቤ ቅልጥ ብሎ ጠፋ አንደበቴ ተሳሰረ ወንድነቴ ከዳኝ አጠገባችው ዝም ብዬ ስቆም ኤቤጊያ ድንገት ስትዞር አይታኝ በጣም ደነገጠች ራስታው እና ጓደኞቹም አዩኝ ኤቤጊያ ዝም አለች ራስታው ኮስተር ብሎ አንተ በሽተኛ ዛሬም በሺሻ እቃ ልትደበድበኝ ነው አለ ሁለቱ ጓደኞቹ ከት ብለው እየተሳሳቁ አረ እሱ በሽተኛ አይደለም ጀዝባ ነው ሞሮ! አሉት እየተሳለቁብኝ በግ ተራ አከባቢ ያሉት ሰዎች እንዳለ ቀስ በቀስ ድራማውን ለመታደም መሰብሰብ ጀመሩ። መንቀሳቀስ አልቻልኩም መላ ሰውነቴ አንደበቴን ጨምሮ ተሳሰረ ሁሉም ሰው ሞሮ ሞሮ ሞሮሮሮሮ.... እያለ መሳሳቅ ጀመሩ ምንም ግድ አልሰጠኝም ነበር ነገር ግን በዚ ሁሉ ወከባ መሃል ኤቤጊያ ሞሮ ብላ ስትስቅ አየኃት ልቤ ተሰበረ እምወዳት ሴት እኔ ላይ ተሳለቀች እንባዬ መጣ በንዴት ጨ ብጬው የነበረውን ፌሮ መሬት ላይ ለቀቅኩት ወደ ኤቤጊያ እያየው በግድ አንድበቴ እየተፋተገ ለ..ለምን! አልኳት እንባ ከአይኔ እንደጅረት እየፈሰሰ። ኪያር የተሰበሰበውን ተማሪ ሰንጥቆ እየገባ በግድ ጎትቶ ሊወስደኝ ሲል እምቢ አልኩት ኤቤጊያ ወደኪያር እያየች ወይኔ በናትህ ኪያር ውሰደው አሄንን ልጅ እንዴ... እኔ በቃ ከዚ በላይ ማስመሰል አልችልም ከእንደዚ አይነት ጀዝባ ሰው ጋር መሆን አልፈልግም አለችው ውስጤ በጣም ተጎድቶ ይበልጥ ሲጠዘጥዘኝ ተሰማኝ ኪያር የኔን እጅ ለቆ እሳት ለብሶ እሳት ጎርሶ ወደ ኤቤጊያ ምን አልሽ አንቺ ቅሌታም! ብሏት ሲጠጋት ራስታው እና ጓደኞቹ ከፊቷ ቆመው ምን ልትሆን ነው ብለው አፈጠጡበት። ኪያር ከነሱ ይከራከራል የተሰበሰበው ህዝብ ይስቃል ይሳለቃል ኤቤጊያ ተደብቃለች እኔ እንባ ከአይኔ እንደጅረት ይወርዳል ድንገት ራስታውና ጓደኞቹ ዞር ሲሉ ኤቤጊያን እጇን ያዝኳትና መሬት ላይ ተንበርክኬ እየተነፋረቅኩ እኔ እኮ አፈቅርሻለው አቢ ከማንም በላይ አፈቅርሻለው አልኳት ሁሉም ሰው ኮሜዲ ፊልም እንደሚያይ ይበልጡኑ ሳቁ ኤቤጊያም ሳቀች እኔና አንተ እንመጣጠንም በደረጃህ ፈልግ በላ እጇን በግድ አስለቀቀችኝ።
ቀና ብላ የሆነ ነገር ያየች ይመስል በአንዴ ፈገግታዋ ውሃ እንዳጣ ተክል ድርቅ ብሎ ስትደነግጥ አየኋት ኪያር በግድ ከተደፋሁበት መሬት ጎትቶኝ ቀና አልኩ የኤቤጊያን ሳቅ ምን እንዳደረቀው ለማየት እሷ ወደምታይበት አቅጣጫ አየው ከኃላ ከሁሉም ራቅ ብላ ሰምሃል ቆማ እሚሆነውን ሁሉ እያየች ነበር ልክ እኔ ሳያት በፍጥነት ሰዉን እየገፈታተረች ወደኛ መጣች ኤቤጊያ ይበልጥ ስትጨነቅ አየው ልክ አጠገባችን ስትደርስ ሰምሃል ኤቤጊያን በጥፊ......
ይቀጥላል ....
https://t.me/New_life_20