💓💓💓💓💓ሞሮ💓💓💓💓💓
💓💓💓💓 ክፍል 25 💓💓💓💓
ፀሃፊ ረምሃይ
ልክ ከዲፓርትመንት እንደወጣው ስልኬ ጠራ ሳየው አባቴ ነው ለምን እስካሁን አልመጣህም ሊለኝ እንደሆነ ገብቶኛል። ስልኩን አንስቼ ሄሎ አባዬ አልኩት ሰላም ካለኝ በኃላ ለምን እስካሁን እንዳልመጣው ጠየቀኝ። የዊዝድሮው ጣጣ ብጨራረስም አንድ ቀን ማደር ስለፈለግኩ እንዳልጨረስኩና ነገ ጨራርሼ እንደምመጣ ነገርኩት አጠገብህ ማን አለ አለኝ ማንም የለም አሁን ከዲፓርትመንት እየወጣው ነው ሰምሃል እና ኪያር ክላስ ነበሩ አሁን ይወጣሉ እንገናኛለን አልኩት በል ራስህን ጠብቅ ብሎኝ ተሰናብቶኝ ስልኩን ዘጋው
ወደ ዶርም መመለስ ስላልፈለግኩ ኪያር ጋር ደወልኩለት ከክላስ አልወጣም መሰለኝ ስልኩ አይነሳም ብዙ ከጠራ በኃላ አልነሳ ሲለኝ እሱን ተውኩትና ወደሰምሃል ጋር ደወልኩላት ወዲያው ስልኳን አንስታ ሄሎ አለችኝ ሰላም ከተባባልን በኃላ የእራት ሰአት እየደረሰ ስለሆነ እንድንበላ ጠየቅኳት እሺ ልብስ ልለባብና ወጣለው የት ነው ግን እምንበላው አለችኝ። ከግቢያችን ፊትለፊት ያለው የኃና ሆቴል ይሁን አልኳት ደ ይለኛል በቃ ወጣው አልችኝ ስልኩ ተዘጋ የበርኩበት ቦታ ልብ ብዬ ሳስብ ከጠቅላላ ዩኒቨርስቲ አሉኝ እምላቸው ጓደኞች ኪያርና ሰሙ ብቻ ናቸው
በቃ እውነተኛ ጓደኛ እንዲ ተረት ሆኖ ይቅር ሁሉም ሰው አስመሳይ ሆነ!እየተግረምኩ ሰሙን ከሴቶች ዶርም በሚያስወጣው አስፓልት ጥግ ላይ ሄጄ እስከምትመጣ መጠባበቅ ጀመርኩ ብዙ ተማሪ ያልፋል ያግማል የፋይናል ፈተና ሰሞን እየተቃረበ ስለነበር አብዛኛ ተማሪ ከላይረሪ ዶርም ከዶርም ስፔስ ከስፔስ ላብረሪ ይሯሯጣሉ። በግምት ወደ ሰላሳ ደቂቃ ቆሜ ጠበቅኳት ሲሰለቸኝ ስልኬን አውጥቼ ደወልኩላት ስልኳ ይጠራል ግን አይነሳም ድንገት ከኃላዬ ቀጠን ያሉ እጆች አይኔን ያዙኝ ስት ስቅ ሴት እንደሆነች ገባኝ እጇን በእጄ ለማስለቀቅ እየሞከርኩ ማን ነሽ አልኳት ቀጠን ባለ ሞዛዛ ድምፅ ኤቤጊ...ያ አለችኝ ደንግጬእጇን በሃል አስለቂያት አደኃላ ዞሬ ሳይ ሰምሃል ናት በጣም ተበሳጭቼ ልናገራት አልኩና ልብ ብዬ ሳያት ውበቷ በአንዴ ንዴቴን አቀለጠው ምን ልላት እንደነበር ራሱ ጠፋብኝ ፍዝዝ ብዬ አየኃትና ዋው በጣም አምሮብሻል ሰሙዬ እንደዚ ቆንጆ መሆንሽን አላውቅም እውነት ውብ ነሽ አልኳት ሰሙ ይበልጥ እየተሽኮረመመች ሳቀች ጥርሶቿ ቀያይ ከናፍሮቹን በግድ ፈልቅቀው ሲታዩ ልብን ያፈዛሉ። እሚያምር ቀይ የእራት ልብስ አድርጋ ውበቷን እንደፅጌረዳ አበባ እጥፍ ድርብ አሳምሯታል።
እውነት ለመናገ ሰምሃል እንዲህ ውብ መሆኗን እስከዛሬ አላውቅም ነበር ብዙ ግዜ ረጅም ሰፋፊ ቀሚስ አድጋ በክርስቲያን ስትሄድ ነበር ማያት ዛሬ ምን እንደተገኘ እንጃ በጣም አምሮባታል። ብዙ ፍዝዤ እንዳያኃት ሲገባኝ ነቃ አልኩና እንሂድ በቃ አልኳት እየተፍለቀለቀች እሺ አለችኝና እጇን በእጄ አጠላልፋ ተያይዘን ወደ ዋናው መውጫ በር አቀናን። አስፓልቱ ላይ እሚያልፍ ምድረ አዳም ሁላ አይኑ እስኪጎለጎል እኛ ላይ ያፈጣል ሴቶቹም እንደዛው አይን ሁሉ ወደኛ ሆነ ሰምሃል ቀስ ብላ ወይኔ ጉዴዴ... አለች ምነው አልኳት ሰው ሁሉ እያፈጠጠብን እኮ ነው እንደዚ ለብሼ መውጣት አልነበረብኝም አለች ገረመኝ ሰሙ አውቃ ውበቷን እንደምትደብቅና ከሰው እይታ ላለመግባት እንደምትጥር ከሁኔታዋ ተገነዘብኩ ይበልጥ በሷ ተገረምኩ ምን አይነት ምትገርም ሴት ናት ሌሎቹ ሴቶች የሌላቸውን በፓውደር በዱቄት የስእል ደብተር መስለው ሲወጡ እንኳን ምንም አያፍሩም ፓውደር ላይ በፊታቸ የወደቁ ነው ሚመስሉት ፊቷ ቀይ ሆኖ ተመችታህ ልትጨብጣት እጇን ስትዘረጋ ጥቁር ቡራቡሬ ነው ታዲያ እነሱ እንደዛ ያላፈሩ ሰምሃል እንዲ ተውባ መውጣቷ ምን ያሳፍራታል አረ... እንደው ምን አይነት ለየት ያለ ስብእና ነው ያላት።
ይቀጥላል ....
https://t.me/New_life_20