💓💓💓💓💓ሞሮ💓💓💓💓💓
💓💓💓💓 ክፍል 26 💓💓💓💓
ፀሃፊ ረምሃይ
ከሰሙ ጋር ተያይዘን ከግቢ ከወጣን በኃላ ፊት ለፊት አስፓልቱን ተሻግረን የኃና ሆቴል ገባን ቤቱ ጨለምለም ያለ ነው ውጪ አንድ ጥግ ላይ ተቀመጥን የቤቱ ሙዚቃ ጆሮ ያደነቁራል ማንም ዘፈኑን የሚሰማ የለም ሁሉም በየፊናው በቢራ ጠርሙስ ተደብቆ የግል ጨዋታን በየጠረጴዛው ያደራል። የሆቴሉ የውጪኛው አጥር አጭር ስለሆነ ውጪ ያለው ወከባ እና ግርግር በደምብ ይታያል ተሜ ከታክሲ ከባጃጅ ይወርዳል ከታክሲ እንደወረዱ ወደ የኃና እሚገብ ብዙ ናቸው የኃና ባርና ሬስቶራንትም ስለሆነ እንደጉድ ይጠጣበታል። የነበረውን ወከባ እና ጫጫታ እረስቼ እዚ እንምጣ ስላልኳት ደበረኝ እንደ ሰምሃል ላለ ፀጥ ያለ ቦታ ለሚወድ ሰው ብዙም ደስ እሚል አይደለም ስገምትም ደብሯታል ትንሽ ቆይታ አስተናጋጇ መጥታ ታዝዛን ሄደች ግዜው መሽቶ ጨልሟል ድንገት የሰሙ ስልክ ከጠረጳዛው ላይ ኡኡኡ.... ብሌ ቀወጠው አንስሥታ ስታየው ሊዲያ ናት የደወለችላት ወዲያው አነሳችውና ወዬ ሊዱ አለቻት። ከየኃና የሚወጣው ጫጫታና የዘፈኑ አደንቁር ሞገድ ሊዲያ ምከወዲያኛው መስመር እምትላትን መሰማማት ስላልቻለች ስልኩን ስፒከር ላይ አድርጋ ማውሯ ጀመረች ሊዲያ እየተነጫነጨች ጮክ ብላ የት ነው ያለሽው ከላይብረሪ ስንመጣ ዶርም የለሽም ደሞ የታባሽ ሁነነሽ ነው ይሄ ሁሉ ጫጫታ ያለበት ቦታ የገባሽው አለቻት እኔ ሳቅኩኝ ሊዲያ ደግማ ማነው አጠገብሽ ሆኖ እሚስቀው አለቻት ሰሙ እሳቀች ናዲ አለ ከሱ ጋር እራት ልንበላ ወጥተን ነው የኃና ነው ያለነው አለቻት ሊዲያ ከት ብላ ስትስቅ ሰማኃት አንቺ በቃ ልጁን ጠዋትና ማታ አትፋቺውም እንዴ መዠገር ሆንበት እኮ ደሞ ከመች ጀምሮ ነው አንቺ የኃና የምትገቢ ያልመደብሽን ሃ..ሃ..ሃ..ሃ... አይ ናኦድ የሌለ ገብቶልሻ.... ሰምሃል ወዲያው ስልኩንን ጥርቅም አድጋ ዘጋችው ምነው እላታለው በድንጋጤ ውይ ካርድ ዘግቶ ነው አለችኝ ከት ብዬ ሳቅኩና ያንቺ ካርድ እሚያልቀው ቀዩን ስነኪው ነው እንዴ አልኳት ይበልጥ ፊቷ ቀልቶ እእእ ሳላውቅ ነው አለች ቅልቃላዋ ሊዲያ መልሳ ደወለች ሰምሃል ስልኩን አየችውና ዝም አለች። ሁኔታዋን አይቼ አረ ሰሙ ይደብራል አንሺውና አናግሪያት አልኳት እሺ አለችኝና አንስታው አንቺ ክፍት ላውድ ስፒከር ላይ አድርጌ ከናዲ ጋር አንድ ላይ ሆኜ ነው ማዋራሽ አለቻት ምንም ሳትናገር ሊዱ ወይኔ....እሺ እኔማ እራት አንድ ላይ እንድንበላ ነበር የደወልኩልሽ ራኪ አለች ተይው በቃ ከሷ ጋር እበላለው አለች ማን እንዳዘዘኝ አላውቅም.ድንገት ስልኩን ወደኔ ከነእጇ አስጠጋሁትና ኑ እኛጋ ሊዱ አብረን እንብላ እጋብዛቹሃለው አልኳት እውነ...ት! አይደብራችሁም እንምጣ አለች አው ኑ ችግር የለውም አልኳት እሺ በቃ መጣን አሁኑኑ አችና እየተፍለቀለቀች ስልኩን ዘጋችው። ሰምሃልን ውውይ... እቺ ቀልቃላ ምንድነው ፍጥን ፍጥን እያሚያረጋት ቆይ አለች እየሳኩ አረ ሉዱ ደስ እምል ልጅ ናት ምን አረገችሽ አልኳት ዝም አለችኝ። ትንሽ ቆይቶ የኔ ስልክ በተራው ጠራ ሳየው ኪያር ነው ኣነሳው ሄሎ ናዲ ቅድም እኮ ክላስ ሆኜ ነው ያላነሳሁት ሶሪ አለኝና እራት ካልበላህ አብረን እንብላ አለኝ የስልኩን ማይክሮፎን በእጄ ያዝኩትና ሰሙ ናዲ ቢመጣ ይደብርሻል እንዴ አልኳት ፈገግ ብላ አረ በፍፁም እንኳን እሱ እነ ሊዱም እየመጡ አይደል እንዴ ይምጣ ደስ ይለኛል አለችኝ እሺ ብያት የኃና ከሰሙ ጋር እንደሆንን ነግሬው መጥቶ እንዲቀላቀልን ጋበዝኩት።
ብዙም ሳይቆይ ያዘዝነው ምግብ መጣ መብላ እንደጀመርን ሊዱ እና ራኪ የተጣደፉ ወደ ውስጥ ገቡ በእጄ ምልክት ሰጥቻቸው ወደኛ መጡ እኔን ሰላም ብለውኝ ሰሙን ሲያይዋት ደነገጡ አንቺ ምንድነው እንዲ የሽቀረቀርሽው አምሮብሽ የለ እንዴ አላት ተራ በተራ የለበሰችውን ልብስ እየነካኩ ከት ብዬ ሳቅኩና ምነው ሰሙ እንደዚ አትለብስም እንዴ አልኳቸው ራኪ ወደኔ ዞራ አረ በጭራሽ እዛ የፈረደበት ቦላሌ ቀሚስ አላት እሱን አድርጋ ነው እምትንቀሳቀሰው አለችኝ እኔም ስለማውቀ ከት ብዬ ሳቅኩ ሰሙ ይበልጥ ተሸማቀቀች ታያላችው ሁለትኛ እንዲ ከለበስኩ አለች እንዲ እየተቀላለድን እያለ ኪያር ከች አለ
። እኔና ሰሙ ዝም ተበን የነበረው ኪያር ራኪ እና ሊዱ ሲመጡ ጨዋታው በአንዴ ደመቀ የነበረው ምግብ ስላልቧን ሌላ ምግብ ተጨምሮ እየበላን እየጠጣን ጨዋታችንን ቀጠልን ደስ እሚል ግዜ ነበር። ለመጨረሻ ግዜ እንዲ የተደሰትኩበትን ግዜ ለማስታወስ ብሞክርም አቃተኝ ለካ እውነተኛ ጓደኛ የደስታ ምንጭ ነው እኔና ሰሙ ዝም በን ሶስቱ ሲከራከሩ እያየን እንሳሳቃለን ሶስቱም ጨዋታ አድምቅ ቀውጢ የሆኑ ልጆች ናቸው አሪፍ ግዜ አሳለፍን ሳይታወቀን መሽቶ ከግቢ መግቢያ ሰአታችን አምስት ደቂቃ አርፍደናል ሂሳብ ከፍለን እየተሯሯጥን ወደግቢ በር አመራን በሩ ተዘግቷል እኔስ ልማዴ ስለነበር ምንም አልመሰለኝም ኪያር በሩ ጋ ቆሞ ዘበኞቹ ያስገቡን ዘንድ መለማመን ጀመረ እምቢታቸው ሲበረታ ራኪ እና ሊዱም ሄደው መለመን ጀመሩ እኔና ሰምሃል ብቻችንን ቆመን ተፋጠጥን ዝምታውን ለመስበር ብላ ደስ እሚል ግዜ ነበር ያሳለፍነው ጓደኛህ ኪያር አዝናኝ ልጅ ነው አለችኝ አው ባክሽ ጥሩ ይጫወታል አልኳት እንዲ እያወራን ከኃላችን የተጋነነ ሳቅ ሰምተን ዞርን የሆኑ ልጆች ሰክረው ጥንብዝ ብለው እየተንገዳገዱ እየመጡ ነው ከነሱ መሃል አንዱ ከት ብሎ ይስቃል ሃሳባችን ወደነሱ ሆነ ጨለማ ስለነበር ማንነታቸውን መለየት አልቻልንም ልክ ባውዛው ያረፈበት ብርሃን ላይ ሲደርሱ አየናቸው ሰምሃል የሚል የሰከረች የሴ ድምፅ መጣ የኤቤጊ ድምፅ እንደሆነ ለመለየት አልከበደኝም አብረዋት ራስታውና ጓደኞቹ አሉ ፊትለፊት ተፋጠጥን
ይቀጥላል....
https://t.me/New_life_20