💓💓💓💓💓ሞሮ 💓💓💓💓💓
💓💓💓💓 ክፍል 28 💓💓💓💓
በእጆቼ አንስቼ ስይዛት ደረቴ ላይ ተለጠፈች ወደ ግቢ ላስገባት ይዣት ወደበሩ አመራው ዘበኞቹ አይቻልም ብለው ተቆጡ እነስመሃል ከውስጥ ሆነው ያስገቡኝ ዘንድ አጥብቀው ቢለምኗቸውም አይቻልም ብለው ድርቅ አሉ የሰከረ ሰው አናስገባም ያቀፍካትን አረቄያም ትተህ መግባት ትችላለህ አለኝ አጠር ያለው ዘበኛ። እንዴት ነው ብቻዋን ትቻት እምገባው ሴት እኮ ናት የሆነ ነገር ብትሆንስ አልኳቸው እየተለማመጥኩ አጭሩ ዘበኛ ይበልጥ ተቆጣ ሰውዬ አትበጥብጠኝ ስራዬን ልስራበት ሂድልኝ ከዚ ብሎ አንቧረቀብኝ። ሁለታችንንም እንደማያስገቡን ሳውቅ ወደ በሩ ጋር ጠጋ አልኩና ከሰሙ ብር ጠየቅኳት እኔ ጋር የነበረውን ብር እራት ስንበላ እንዳለ ጨርሼው ነበር ከቦርሳዋ ውስጥ አውጥታ በንረት ዘንጎቹ መሃል እጇን አሳልፋ ሰጠችኝ። ልክ ብሩን እንደተቀበልኳት በቃ ሰሙ እናንተ ግቡና ተኙ እኔ እሷን አልጋ ላስይዛትና እዛው ሆኜ ልጠብቃት ጠዋት እመጣለው አልኳት ሰሙ በጣም የጨነቃት ትመስላለች ኪያር እባክህን ራስህን ጠብቅ በዚ ለሊት ጥሩ አይደለም አደራ ብሎኛል ጋሼ ራስህን ጠብቅ አለኝ እሺ ብዬ ፊቴን ወደ አስፓልቱ አዞርኩና ማደሪያ ፍለጋ ሄድኩ እነ ሰምሃል በሩ ጋር ቆመው ከአይናቸው እስከምሰወር ድረስ የበረፕን የብረት ዘንግ ተደግፈው እያዩኝ ነበር። አስፓልቱን ተሻግሬ ኤቤጊያን በክንዶቼ እንደታቀፍኩ በአከባቢው እማውቀው ፔንሲዮን አመራው እንዳጋጣሚ ሆኖ አንድ ትርፍ አልጋ ብቻ ነበራቸው ሂሳቡን ከፋፍዬ ቁልፋን ተቀብዬ ኤቤጊያን ይዣት ገባው። አልጋው ላይ አስተኛኃት እስካሁን ድረስ አልነቃችም ራሷን አታውቅም ብርድልብሱን በደምብ ካለበስኳት በኃላ አንደኛውን ተራስ ወስጄ በሩ ስር ኩርምት ምት ብዬ ለመተኛት ስዘገጃጅ ስልኬ ጠራ ሳየው ሰምሃል ናት።
ሳነሳው እእእ አገኛቹ መኝታ ምንም አልሆናችሁም አይደል አለችኝ ድምፃ ውስጥ ጭንቀት እንዳለ በደምብ ያስታውቃል። ኣው ሰሙ አጊንተናል አስተኝቻታለው በቃ አንቺም አትጨናነቂ ተኚ እኔም ልተኛ ደክሞኛል በጣም ቀኑን ሙሉ ሬጂስትራል እና ዲፓርትመንት ስመላለስ ነው የዋልኩት አልኳት እኔ እንቅልፌ አልመጣም ግን እሺ ብላኝ ተሰነባብተን ስልኩ ተዘጋ። እዛው በሩ ስር ትርሃሱ ላይ እንደተቀመጥኩ ከርምት ብዬ ለመተኛት ሞከርኩ ግን ምንም ሊመቸኝ አልቻለም.... ደቂ ቃዎች አለፉ ቢቸግረኝ ተነስቼ የኤቤጊያን ትንፋሽ መኖሩን ለማረጋገጥ እጄን አፊንጫዋ ስር ሰደድኩት አለች! ክፍሉ ውስጥ መንጎራደድ ጀመርኩ ለሊቲ ምንም አልገፋልህ አለኝ ረዘመብኝ ቢቸግረኝ በሩን ከፈትኩትና ከክፍሉ ወንበር ይዤ ወጥቼ በሩ አጠገብ በረንዳው ላይ ተቀመጥኩ ትዝ ሲለኝ ሰሙ እንቅልፌ አልመጣም ብላኝ ነበር ከሚደብረኝ ብዬ ስልኬን አውጥቼ ደወልኩላት ከመቀፅበት አነሳችው ፍጥነቷ አስገርሞኝ አንቺ አተኚም እንዴ አልኳት እየሷቅኩ እንቢ አለኝ ባክህ አልችኝና ማውራት ቀጠልን። አልገፋ ያለው ለሊት ጠቅለል ጠቅለል እያለ መሄድ ጀመረ ለሊቱን ሙሉ ከሰሙ ጋር በረንዳው ላይ ቁጭ ብዬ የባጥ የቆጡን ስናወራ አደርን። ሊነጋጋ ሲል ሰሙን እያወራኃት እንቅልፍ ይዞኝ እብስ አለ....
የሆነ ሰአት ላይ ብንን ስል ነግቷል ስልኬ መሬት ላይ ወድቋል ሰሙን እያወራኃት እንደተኛው ገባኝ ስልኬን አንስቼ ሰአቱን አየሁት 02፡45 ይላል ብድግ ብዬ ወደ ክፍሉ ገባው ኤቤጊያ አሁንም አልተነሳችም። ወደ አልጋው ተጠግቼ ቀስ ብዬ ቀሰቀስኳት ነቅታ ስታየኝ ደንግጣ ልትጮህ ስትል ቆጣ ብዬ ተረጋጊ! ትናንት ማታ ሰክረሽ የወደቅሽበትን እንኳን ሳታውቂ በገዛ ትውከትሽ ተዘርረሽ ሁሉም ተጠይፎ ማንም እሚያነሳሽ ሰው በሌለበት ድቅድቅ ጨለማ እኔ ነኝ ያነሳሁሽ። እኔ.... ካንቺ ምንም ነገር ፈልጌ አይደለም ግን እንደሰው እሚያስብ አይምሮ ያለው ሰው ነኝ እንዲ አይነት ነገር አይቶ ማለፍ እሚችል ልብ ስለሌለኝ ነው አልኳት ቀስ በቀስ የትናንት ትውስታዋ ተመለሰ በሃፍረት ተሸማቃ ብርድልብሱንና አንሶላውን አንድ ላይ እየነከሰች ስቅስቅ ብላ ማልቀስ ጀመረች። ከዚ በላይ ልጠብቅሽ አልችልም አሁን ራስሽን አውቀሻል ጠባቂ አያስፈልግሽም ቻው ብያት ልወጣ ስል ይበልጥ እያለቀሰች ቆይ እንጂ የት ነው ጥለኀኝ እምትሄደው አለችኝ ይቅርታ ኤቤጊያ ከዚ በላይ መቆየት አልችልም ሻወር ወስደሽ ተስተካክለሽ ወደ ግቢ ተመለሽ አልኳትና ጥያት ወጣው። እየሄድኩ ስታለቅስ ይሰማኛል
ወደ ግቢ ተመልሼ ሰሙ ጋር ደውዬ በግተራ ጋር አገኘኃት እውነት በጣም ጥሩ ልብ ያለህ ልጅ ነህ ናዲ ማንም ያለደረገውን ነው ያደረከው ይህንን መልካም ስብእናህን መቼም እንዳታቆመው እሺ ሰዎች ብዙ ግዜ የዋህናትን ከሞኝነት ጋር ያመሳስሉታል አንተ ግን ሁሌም በልብህ መልካም ሁን ሰው እንደፈለገው አድርጎ ቢያይህ ቅር አይበልህ አለችኝ ፈገግ እያልኩ አረ.... ሰሙ በምክር ቁንጣን ሊይዘኝ እኮ ነው ለሊቱን ሙሉ ስትመክሪኝ አድረሽ አሁንም ትመክሪኛለሽ አልኳት እየሳቀች ሂዛ.... አለችኝ ኪያርን ጠርተነው ቁርስ አብረን ከበላን በኃላ ወደ ሸገር ለመመለስ ተነሳው ሰሙ ልክ ፋይናል እንደጨረሱ እንደምትመጣና እስከዛ በየቀኑ እንደንደዋወል አሳስባ ተሰናበተችኝ። ኪያርም ከኔጋ ሊመጣ ፈልጎ ነበር ግን አልሆነም ቤት ሰላም በልልኝ ሲለኝ እህቴን ነው ሁሉንም አልኩት አንተ እማትረባ ብሎ ሳቀ ተነቃቅተናል አልኩት ይበልጥ እየሳቅኩ እንዲ እየተሳሳቅን መኪናዋ ጋር ደረስን። ግቢ ውስጥ ከዚ በላይ መቆየት ስላልፈለኩ ረሰናብቻቸው እየናዳው ወጣው መንገዴን ወደ ሸገር አደረግኩ። ረፋድ ላይ እቤት ገባው እቤት ስደርስ ሁሉም ጨንቋቸው ነበር ምሳ ከበላን በኃላ ለሊቱን ስላልተኛው እንቅልፍ ሲያዳፋኝ ክፍሌ ገብቼ ተኛው አመሻሽ ላይ የስልክ ጥሪ ከእንቅልፌ ቀሰቀሰኝ እየተነጫነጭኩ አንስቼ ሳይ ኤቤጊያ! ናት የደወለችው።
ይቀጥላል.....
https://t.me/New_life_20