💓💓💓💓💓ሞሮ💓💓💓💓💓
💓💓💓💓 ክፍል 29 💓💓💓💓
ፀሃፊ ረምሃይ
ስልኩን አነሳሁና ሄሎ ኤቤጊያ አልኳት በተለሳለሰ ድምፅ ሰላም ነው ናኦድ አለችኝ ደህና ነኝ ይመስገን አምላክ እንዴት ነሽ አንቺ አልኳት ደህና ነኝ እኔም ብላ ትንሽ ዝም ካለች በኃላ በረጅሙ ተንፍሳ እውነት ምን ማለት እንዳለብኝ አላውቅም ብቻ እማውቀው በጣም ብዙ እንደበደልኩህ እና አንተግን በደሌን በበደል ሳይሆን በመልካም ነገር መልሰህልኛል እውነት እልሃለው ከልቤ ይቅርታ ጠይቅሃለው እንደባለፈው ማንም አዞኝ ሳይሆን ውስጤን ሰላም ስለነሳኝ ነው እኔ ሳስቀይምህ አንተ ግን በዛ ጨለማ ሁሉም ንቆ ሲያልፈኝ ጓደኛዬ ያልኳቸው እንኳን ት...ተውኝ ሲሄዱ አ..አ..አንተ አነሳኀ...ኝ ድምፃ በሳግ ታፈነ ይተናነቃትና ማልቀስ ጀመረች እውነት ናኦድ አንተ ጥሩ ሰው ነህ ስለሁሉም ነገር ይቅርታ አንተ ላይ ያደረኳቸው አስቀያሚ ነገሮች በሙሉ የህሊኔ እረፍት እየነሱኝ ነው ይፀ ፅተኛል በጣም ይቅርታ ላደረግክልኝ ነገር ሁሉ አመሰግናለው ፈጣሪ እሱ ይክፍልህ አለችኝና ይበልጡኑ ስቅስቅ ብላ ማልቀስ ጀመረች። ትንሽ ላረጋጋት ከሞከርኩ በኃላ በለዘበ አንደበት እኔ አንቺ ስለሆንሽ ብዬ ያደረግኩት ነገር አልነበረም ለማንም ሰው ቢሆን መደረግ ያለበትን ነው ያደረግኩት መልካም መሆን ለራስ ነው እኔ በህይወቴ እንደ ሰምሃል ያለች መልካም ሴት ባታጋጥመኝ ኖሮ ዛሬን በህይወት አልገኝም ነበር። ሰምሃል ካስተማረችኝ መልካምነትን ተምሬ ላንቺ አደረግኩልሽ እንጂ የተለየ ነገር አላደረግኩልሽም መልካም መሆን ያለብሽ ለምትወጂው ሰው ብቻ ሳይሆን ለምትጠይውም ሰው ጭምር ነው ያኔ ክፉን በክፉ ስላልመለሽ ህሊናቸው ሰላም ያጣል አንቺም ጋር እየሆነ ያለው ይህ ነው ያለፈው አልፏል ምንም የተቀየምኩሽ ነገር የለም ይቅርታ አስፈላጊ አይደለም ነገር ግን ለወደፊቱ በህይወትሽ ለሚመጡ ሰዎች በሙሉ መልካም ሆነሽ መልካምነትን አስተምሪያቸው አልኳት እኔ እንዲ ስናገር የሰራችው ስህተት ተሰምቷት ነው መሰል ይበልት እያለቀሰች ነበር። ራሷን ካፈጋጋች በኃላ አመሰግናለው ካላስቸገርኩህ ጓደኛ መሆን እንችላለን ማለት አሉኝ ያልኳቸው ጓደኞች እንዳለ ከኔ እርቀዋል ማንም የለኝም አለችኝ።
ከብዙ ሺህ አስመሳይ ጓደኛ አንድ የልብ ጓደኛ እጅግ የከበረ ነው እኔና አንቺ ጓደኛ እንሁን አንሁን አሁንንልነግርሽ አልችልም ወደፊት ግዜ የሚያሳየን ይሆናል አልኳት እሺ ብላኝ ድጋሚ አመስግናኝ ቻው ተባብለን ስልኩ እንደተዘጋ በፍጥነት ወደ ሰምሃል ጋር ደወልኩ ልክ እንዳነሳችው ሰሙ ኤቤጊያ ደውላ ይቅርታ አልችኝ እኮ አልኳት ከት ብላ እየሳቀች ምንድነው እንዲ መቻኮል ሰላምታ አይቀድም አለችኝ እየሳቅኩ ባክሽ ስለገረመኝ ነው አልኳት። ያገጥማል አንዳንዴ ብዙ ለበደሉህ ሰዎች በበደላቸው ልክ ፈፅማው ካንተ ማይጠብቁትን ጥሩ ነገር ስታደርግላቸው ውስጣቸው ሰላም ያጣል ያስቀየሙክ ነገር ይሰማቸዋል ለዛ ይሆናል አለችኝ አው እኔም እንደዛ ነው ያልኳት ደስ ብሎኛል ብቻ ይቅርታ ስላለችኝ ሳይሆን ትንሽ ወደራሷ ስለተመለሰች በኔ ምክንያት ሰው ሲቀየር ማየት ደስ አረ ደግሞ ሳልነግርሽ ጓደኛ እንሁን አለችኝ እኮ እላኳት ስምሃል በድንጋጤ ምን!? አለችኝ ድምፃ እኔንም አስደነገጠኝ ምነው እልኳት ድምፃን እያለዘበች አይ ምንም እና ምን አልካት አለችኝ መልሱን ለመስማት እየተጣደፈች ምንድነው ምንም ማለት ምን እንደሆንሽ ንገሪኝ አልኳት ውይ ናዲ ምንም አይደለም እዚጋ ሊዱ አስደንግጣኝ ነው የጮህኩት አለችኝ። እሺም እምቢ አላልኳትም ያው በ ኖርማል ጓደኝነት ነው በሌላ ነገር አይደለም አልኳት እእእ እሺ አለችኝና ድንገት የሆነ ነገር ትዝ ያላት ይመስል አንተ ምናባክስና ነው ገብቻለው ብለህ እማትደውለው አልችኝ ትንሽ። እየተከራከርን ካወራን በኃላ ቀጣይ ሳምንት ቤተሰቦቿን ለመጠየቅ እንደምትመጣና በዛው እንደምንገናኝ ነግራኝ ስልኩ ተዘጋ
ይቀጥላል....
https://t.me/New_life_20