💓💓💓💓💓ሞሮ💓💓💓💓💓
💓💓💓💓 ክፍል 35 💓💓💓💓
ፀሃፊ ረምሃይ
መቀመጫ ቦታ ፍለጋ ወደያ ወዲህ ስትዞር ከኛ ጋር ተገጣጠምን ልክ ስታየኝ ናዲ....! ብላ እየጮኀች እኛ ወደተቀመጥንበት ቦታ ሮጣ መጥታ ተጠመጠመችብኝ ሰሙንና ኪዩንም ሞቅ አድርጋ ሰላም አለቻቸውና ወዲያው ወደኔ ዞራ አንተ.... እንዴት ነው ያማረብህ በናትህ በጣም ወፍረሃል ቀልተሃል ደግሞ አረ... የምር ናዲዬ ደስ ይላል በጣም ሸበላ ቆንጅ...ዬ ሆነሃል አለችኝ እኔም እየሳቅኩ አመሰግናለው አቢ ሰላም ነዋ ተጠፋፋን አልኳት። ምን ተጠፋፋን ትላለህ አንተ ነህ የኮራኀው እንጂ እኔማ ስንት ግዜ ላግኝህ ብዬህ ነበር አለችኝ። እየሳቅኩ አ..ይ ... ምነው ብቻሽን እንዲ ዘንጠሽ አልኳት ውይ ረስቼው አለችኛ ወደኃላ ዞራ ናታን ብላ ራስታውን ልጅ ጠራችው ቀስ እያለ እኛ ወደተቀመጥንበት ቦታ መጣና ሰላም አለን። ኤቤጊያ እየተፍለቀለቀች ከናንተጋ ብንቀመጥ አይደብራችሁም አይደል ያው ቦታም የለም ደሞ አለችኝ ወደ ሰሙና ኪያር እየዞርኩ አየኃቸው ኪያር ምንም አልመሰለውም ሰሙ ግን እንዲው የደበራት መሰለኝ። እንቢ ማለቱ ስለከበደኝ አረ ተቀመጡ ችግር የለውም አልኳት እየተፍለቀለቀች ወንበር ስባ አጠገቤ ተቀመጠች ናታንም ወንበር ስቦ ተቀመጠ እሱም የደበረው ይመስላል።
እኛ ምግብ በልተን ጨርሰን ስለነበር እኔ ሰሙን እንነሳና እጃችንን ታጥበን እንምጣ አልኳት ኤቤጊያ ፈጠን ብላ ና ከኔ ጋር እንሂድ እኛም አሁን ስለምንበላ ልታጠብ አለችኝ ሰምሃልን ዞር ብዬ አየኃት በእጇ እንድሄድ ነገረችኝ እሺ ብያት ተነሳው ኤቤጊያ እጄን ይዛኝ ሄድን። በኔ እቅድ ሰሙን ይዣት ሄጄ ምን እንደደበራት ልጠይቃት ነበር ያሰብኩት ግን አልተሳካም። እጃችንን እየታጠብን እያለ ወደ መስታወቱ እያየች ናዲ ግን ምን አጊንተህ ነው እንዲ ያማረብህ ቆይ የእውነት በጣም ነው ያማረብህ አለችኝ እየተገረምኩ አመሰግናለው አልኳት ራሴን በመስታወቱ አየሁት አምና የነበረው ለመሞት አንድ ሃሙስ የቀረው ናኦድ አልነበረም። በመስታወቱ ራሴን ትክ ብዬ እያየሁት እያለ ኤቤጊያ ወደታች ስባኝ ጉንጬን ግጥም አድርጋ ሳመችኝ እየሳቅኩ ምን ተገኘ ስላት እንዲው... ናፍቀኀኝ ስለነበር ነው የዛኔ ከግቢ ስመጣ የተገናኘን እኮ ነው አልናፈቅኩህም ኣለችኝ። አረ እንሂድ እየጠበቁን ነው አልኳት ስንቆይ ሌላ ነገር እንዳያስቡ ብዬ ፈጠን ብዬ ከመታጠቢያው ቀድሚያት ወጣው። ከኃላ ሮጥ ብላ ተከተለችኝ ሄደን ቦታችን ላይ ስንቀመጥ ኪያር እና ናታንን እያወሩ ነበር ተነስ ታጥበን እንምጣ አለውና ተነሳ በእጁ ሰሙ እንድትነሳ ነገራት ታጥባቹ ኑ እኔ ቀጥሎ እሄዳለው አለችው እሺ ብሏት ሄዱ። ቤቱ በሙዚቃ ይናጣል ወደ ሰምሃል ጆሮ ጠጋ ብዬ ምናው ሰሙ ደና አይደለሽም እንዴ የደበረሽ ነገር አለ ኣልኳት። አይ ምንም የለም አለችኝ አነጋገሯ እንደደበራት ይበልጥ ያሳብቅባታል እነኪያር ሲመለሱ እሷ ልትታጠብ ሄደች እሷ እንደሄደች ትንሽ ቆይቼ እኔም ተነሳው ኤቤጊያ እጄን ያዝ አድርጋኝ የት ልትሄድ ነው ናዲ አለችኝ ኣንዴ ሽንትቤት ደርሼ መጣው አልኳትና ሄድኩ። መታጠቢያ ክፍል ውስጥ ስገባ ሱሙ እያለቀሰች ነው ደንግጬ ምነው ሰሙዬ ምን ሆንሽብኝ አልኳት ድምፃን ሳግ እያነቀው ም..ምንም አልሆንኩም አለችኝ አቦ ሰሙ አትደብሪኛ እንዲ እያለቀስሽ አይቼሽ እንዴት ምንም አልሆንኩም ትይኛለሽ አልኳት። መጠጣት እፈልጋለው አለችኝ ምን? አልኳት ያልጠበቅኩት መልስ ስለነበር መ..ጠ..ጣ..ት እፈልጋለውውው አለችኝ ይበልጥ ጮክ ብላ ለምንድነው ምትጠጪው አልኳት በቃ ዝምብለህ ውሰደኝ ናዲ መጠጣት ነው ያማረኝ አለችኝ። እሺ ወስድሻለው ግን ቅድም ኪያርም ኦቫር መውጣት እፈልጋለው ስላለኝ እሱንም እንጠብቀውና አብረን እንሂድ አልኳት እሺ... እልላችኝና እንባዋን በሶፍት ጠራርጋ የተበላሸው ፊቷን አስተካክላ ወጣን። ቦታችን ላይ ስንቀ መጥ ኪያር እያጣደፈ እሺ አኖቭርም አለ ወደኔ አፍጦ እያየ ኤቤጊያ ቀበል አድርጋው ዉዉዉ.... ልቶቭሩ ነው ደስ ሲል እኔም የሌለ መጨበስ አምሮኛል አለችን ሁላችንንም እየሳቀች እያየች። እነኤቤጊያ እራት በልተው ከጨረሱ በኃላ ሁላችንም ተነሳን ወደ ኪያር ጠጋ ብዬ ሰሙ የሆነ ነገር ደብሯቷል እና እኔም አንተም በደምብ እንጠብቃት እሺ አልኩት እሺ ብሎኝ ኣምስታችንም ኮንትራት ባጃጅ ውስጥ ጥብቅብቅ ብለን ገብተን ወደ መብራት ሃይል ሄድን። ቬጋስ ክለብ ገባን ወዲያው ኪያርና ኤቤጊያ ተነስተው መጨፈር ጀመሩ እኔ ሰሙ እና ናታን መጠጥ አዘን ቀስ እያልን ስንጠጣ ሰሙ በፍጥነት የመጣውን ሶስት ደብል ጂን ሻት በአንዴ ዥው አድርጋ ላፈችው አረ ስሙ ተረጋጊ ገና እኮ ነው አልኳት ዝም ብላ አየችኝና ሌላ ጂን አዘዘች። ኪያር እና አቢጊ እየጠጡ ይጨፍራሉ ሶስታችን እነሱን እያየን እንሳሳቃለን በመሃል አቢጊ እኔን እየጎተተች ወደ ውስጥ አስገብታኝ መደነስ ጀመርን አንድ ሶስት ዘፈን ከጨፈርን በኃላ ስለደከመኝ ልቀመጥ ወደቦታዬ ስመለስ አቢጊ እእጄን ያዝ አደረገችኝና አንዴ ውጪ ደርሰን እንምጣ ንፋስ እንቀበል ጥሩ ስሜት እየተሰማኝ አይደለም አለችኝ እሺ አልኳትና ለሰሙ በእጄ ምልክት ሰጥቻት ይዣት ወጣው። ልክ በሩ ጋር ደርሰን ትንሽ ንፋስ ከተቀበለች በኃላ ከአንገቷ ቀና አድርጊያት እንዴት ነሽ አሁን ትንሽ አልተሻለሽም አልኳት። ኤቢጊያ በፍጥነት ናዲ የዛኔ ቤርጎ አብረኀኝ ካደርክ ቀን ጀምሮ ስላንተ ማሰብ አላቆምኩም ወድጄሃልው ብላ ከንፈሬን ግጥም አድርጋ ሳመችኝ ሞቅታውም ስለነበት ትንሽ እንደተሳሳምን ራሴን ተቆጣጥሬ ገፋኃትና ምን እየሆንሽ ነው ብዬ ጮኬባት ስዞር ሰምሃል በእጃ ቢራ እንደያዘች ደረጃው ላይ ሆና ሁሉንም ነገር እያየች ነበር።
ይቀጥላል....
https://t.me/New_life_20