◼️◼️ሞት ግን ምንድን ነው?◼️◼️
from-kibrom kasa
ድንገት ሲጨንቀኝ የጭንቀት ጥያቄ፡
ሞት ግን ምንድ ነው? ብየ ጠይቄ፤
፡
✍አልለይም በፍጹም ዘርና ጾታ፡
ሁሉም ነኝ ምወስደው ሳይገድበኝ ቦታ፡
ስወስድም ይለያል ከሰዎች እይታ፡
ማዳላት አላውቅም ለሁሉም እኩል ነው፡
ሃብታም ድሃ ሳልል ድንገት የምወስደው፡
ከአፈር በስተቀር አዋቂ ለሌለው፡
ዝነኛም ለሆነው ዓለም ለሚያውቀው፡
ፍጹም አላዳላም እኩል ነኝ ምፈርደው፡
፡
፡
ብሎ መለሰልኝ በሚሠራው ሥራ፡
ድምጽ ሳያወጣ ሥራው እየሠራ፡
፡
ኮርቶ ይመልሳል እኔ ስጠይቅ፡
ደጋግሞ ይለኛል፥ ወዳንተም እመጣለሁ ተዘጋጅተህ ጠብቅ፡
እልህ ስለያዘኝ እኔም መለስኩለት፡
ታድያ ለምንድነው መምጫህ ሆነ ድንገት፡
አረ ለመሆኑ እኔንስ ውሰደኝ፡
ጀግኖቻችን ግን ወስደህ አታስጩኸኝ፡
ብየ ብጠይቀው፦
አረ ማነህና እንዲህ ምትጠይቀኝ፡
ሞኝ ነህ መሰለኝ ሞትን የማታውቀኝ፡
ታሪክ ስትመረምር ያለፈውን ሁሉ፡
ትናንት የነበሩ ዛሬ እንደሌሉ፡
ልንገህ አድምጠኝ ወዴት እንዳሉ፡
በእኔ ተወስደው አርፈው ይኖራሉ፡
አንተም ስትኖር በዚህ ከንቱ ዓለም፡
ኗሪ አይደለህም እስከ ዘለዓለም፡
ለእውነተኛው ዓለም ድልድይ መሻገርያ፡
ለዚህ ከንቱ ዓለም ሞት ነኝ መሻርያ፡
የሞተውን ሁሉ ሞተ አትበሉ፡
ከድካም ከስቃይ ለተገላገሉ፡
አርፈዋል እንጂ ሞቱ አትበሉ፡
©kibrom kasa
መታሰቢያነቱ ለአርቲስት ጋሽ ፍቃዱ ተ/ማርያም ይሁንልኝ
❖አርቲስት ጋሽ ፍቃዱ፤ አረፏል እንጂ አልሞተም፤ ድካም ካለው ከዚህ ዓለም ድካም ወደሌለው ዓለም ሞት በተባለው ድልድይ ተሸጋግሯል።
ለወዳጆቹ ሁሉ መጽናናትን እመኛለሁ።
✞✞✞አምላከ ቅዱሳን በአብርሃም፣ በይስሐቅና በያዕቆብ ዕቅፍ ያኑርልን።✞✞✞
ረቡዕ፦፳፭/፲፩/፪፼፲ ዓ/ም
from-kibrom kasa
ድንገት ሲጨንቀኝ የጭንቀት ጥያቄ፡
ሞት ግን ምንድ ነው? ብየ ጠይቄ፤
፡
✍አልለይም በፍጹም ዘርና ጾታ፡
ሁሉም ነኝ ምወስደው ሳይገድበኝ ቦታ፡
ስወስድም ይለያል ከሰዎች እይታ፡
ማዳላት አላውቅም ለሁሉም እኩል ነው፡
ሃብታም ድሃ ሳልል ድንገት የምወስደው፡
ከአፈር በስተቀር አዋቂ ለሌለው፡
ዝነኛም ለሆነው ዓለም ለሚያውቀው፡
ፍጹም አላዳላም እኩል ነኝ ምፈርደው፡
፡
፡
ብሎ መለሰልኝ በሚሠራው ሥራ፡
ድምጽ ሳያወጣ ሥራው እየሠራ፡
፡
ኮርቶ ይመልሳል እኔ ስጠይቅ፡
ደጋግሞ ይለኛል፥ ወዳንተም እመጣለሁ ተዘጋጅተህ ጠብቅ፡
እልህ ስለያዘኝ እኔም መለስኩለት፡
ታድያ ለምንድነው መምጫህ ሆነ ድንገት፡
አረ ለመሆኑ እኔንስ ውሰደኝ፡
ጀግኖቻችን ግን ወስደህ አታስጩኸኝ፡
ብየ ብጠይቀው፦
አረ ማነህና እንዲህ ምትጠይቀኝ፡
ሞኝ ነህ መሰለኝ ሞትን የማታውቀኝ፡
ታሪክ ስትመረምር ያለፈውን ሁሉ፡
ትናንት የነበሩ ዛሬ እንደሌሉ፡
ልንገህ አድምጠኝ ወዴት እንዳሉ፡
በእኔ ተወስደው አርፈው ይኖራሉ፡
አንተም ስትኖር በዚህ ከንቱ ዓለም፡
ኗሪ አይደለህም እስከ ዘለዓለም፡
ለእውነተኛው ዓለም ድልድይ መሻገርያ፡
ለዚህ ከንቱ ዓለም ሞት ነኝ መሻርያ፡
የሞተውን ሁሉ ሞተ አትበሉ፡
ከድካም ከስቃይ ለተገላገሉ፡
አርፈዋል እንጂ ሞቱ አትበሉ፡
©kibrom kasa
መታሰቢያነቱ ለአርቲስት ጋሽ ፍቃዱ ተ/ማርያም ይሁንልኝ
❖አርቲስት ጋሽ ፍቃዱ፤ አረፏል እንጂ አልሞተም፤ ድካም ካለው ከዚህ ዓለም ድካም ወደሌለው ዓለም ሞት በተባለው ድልድይ ተሸጋግሯል።
ለወዳጆቹ ሁሉ መጽናናትን እመኛለሁ።
✞✞✞አምላከ ቅዱሳን በአብርሃም፣ በይስሐቅና በያዕቆብ ዕቅፍ ያኑርልን።✞✞✞
ረቡዕ፦፳፭/፲፩/፪፼፲ ዓ/ም