«አማዞን ኖቫ የሚል መጠሪያ የሰጠው የባለብዙ አገልግሎት የአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ሞዴል ይፋ አደረገ፡፡
ሞዴሉ ጽሑፍ ማመንጨት፣ ምስሎችን እና ተንቀሳቃሽ ምስልን (ቪዲዮ) መፍጠር የሚችሉ ማይክሮ፣ላይት፣ፕሮ እና ፕሪሜር የተባሉ ጥምር ሞዴሎች ውጤት ነው፡፡
በተጨማሪም ምስል እና ቪዲዮን ለመፍጠር ጥቅም ላይ የሚውሉ ኖቫ ካንቫ እና ኖቫ ሪል የተባሉ ሞዴሎች ለአገልግሎት እንደሚበቁ የአማዞን ዋና ስራ አስፈፃሚ አንዲ ጃሲ መናገራቸውን ባሮን ድረገፅ ዘግቧል፡፡
ኖቫ ለጊዜው በ15 የተመረጡ ቋንቋዎች አገልግሎት እንደሚሰጥ ተመላክቷል፡፡ ከአገልግሎቶቹም መካከል ጥያቄዎችን መመለስ፣ ፎቶን ወደ ተንቀሳቃሽ ምስል መቀየር፣ ቪዲዮዎችን ማመንጨት እና መተንተን፣ ሀሳቦችን ማሳጠር እና መግለጫዎቸን ማጠቃለል ይገኝበታል፡፡
አማዞን ዌብ ሰርቪስ ቀደም ብሎ ከሚታወቅበት የክላውድ ወይም የዳታ ማከማቻ አገልግሎቶቹ በተጨማሪ በጄኔሬቲቭ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ቴክኖሎጂ በኩል እየተካሄደ ያለውን ፉክክር በመቀላቀል ተወዳዳሪነቱን ለማስጠበቅ እየሰራ ስለመሆኑ ተዘግቧል፡፡»