ምትኩ ሲሳይ😂😂😂
ምትኬ ምትኩ አንተ አንተን እንኮ ነው ምትኩ😡😡😳 አንተን አይደል ማዋራህ 👊
እረ ይሄ ዶሮ ሊሞት ነው መሰለኝ እየተዝረከረከ ነው አይኑንም ጨፍኗል ምንሼ ነው እንቀይረው እንዴ ኩኩሉ አንተ አንተን አይደል እንዴ ማዋራህ😳 የስ አይኑን ገለጠ እረ ጨፈነ ተመልሶ🙈 እንዲ የተሳቀቅንበትንና የተሳሳቅንበትን የእሁድ ለታውን የስለኛ ጉዞ ና ያጋጠመንን ነገር ላጫውታችሁ ብዕሬን አነሳሁ✍✍✍ማን አንሳ አለህ🤨 እንዲ ያላችሁ ልጆች ወየሁላችሁ ፀጥ ለጥ ብላችሁ አንብቡ ፈተና ከዚ ነው ሚወጣው🧐😂😂😂 መልካም ንባብ
በእለተ ሰንበት ከረፋዱ 4 ሰዓት ገደማ አንዲት ምስኪን እናት ልንጎበኝ መገናኛ ተቀጣጠርን። ግን የሃበሻ ቀጠሮ ሚባለው ነገር ገና አልቀረም መሰለኝ የ 4 ሰዓቱ ቀጠሮአችን ተጎትቶ ተጎትቶ ወደ 6 ሰዓት አካባቢ ሁሉም ተሰበሰበና ጉዞ ወደ ሃና ማርያም አደረግን እየተሳሳቅን እየተጨዋወትን አንድ የገብያ ቦታ ላይ ስንደርስ ታክሲያችን፡መጨረሻው ነው ውረዱ ሚል ትዛዝ በረዳቱ(ዲጄው) በኩል አስተላለፈልንና ልንወርድ ተገደድን ገብያው ውስጥ አንዳንድ ነገሮች እንግዛ ብለን እኔ መሲና ቃል ወደ ሽንኩርት ተራው ዘለቅን ተከራክረን ተከራክረን አንድ መደብ አስመርቀን የሽንኩርት እዳችንን ከፍለን ሽንኩርቱን ለነበምኒ ሰጥተን ጉዞ ወደ ዶሮ ተራ አደረግን🙈 የዶሮ ተራውን ቦታ በጥየቃ አገኘነውና አይናችን ስረፈበት የዶሮ ማስቀመጫ ቅርጫት አመራንና አሪፍ ዶሮ እንዲሰጠን ሻጩን ጠየቅን ይች ትሁንላችሁ ይች በጣም አሪፍ ናት ያች ትሁን ወይስ ይሄኛው የቱ ይሁንላችሁ አቤት ነጋዴ የሞተ ዶሮ ተኝቶ ነው ብሎ ቢሸጥላችሁ ደስታው ነው😂😂😂ከዛ መሲ አይኗ ያረፈባትን አንድ አውራ ዶ... ሮ ምትለዋን ለመጥራት ሁሉ ይከብዳል ብቻ እሱን ተከራክረን ሸምተን እግሮቹን ወደላይ ይዤ ማንቁርቱ ወደታች ተንዘላዝሎ ይዘነው እላይ ከሚጠብቁን ጋ ተገናኝተን ስኳር ቡና ዱቄት ምናምን ጨማምረንበት ጉዟችንን ቀጠልን ከበስተኋላችን ግን አንድ ድምፅ ሁላችንንም እንድንጨነቅ አደረገን"እረ ዶሮው ሊሞት ነው" ሚል ድምፅ😔ሁላችንም ቀልባችን ዶሮው ላይ አረፈ በሚያሳዝን ሁኔታ ዶሮ'ችን ለሃጭ በለሃጭ ሆኗል ሚተርፍ አልመስል አለን አንስቼ አቀፍኩት አይኑን ገለጠ ተመስገን አልሞተም ጉዟችንን ቀጠልን እኔ ጨዋታዬ ከዶሮው አይን መጨፈንና መግለጥ ጋር ሆነ ሲጨፍን እየቀሰቀስኩ ኩኩሉ እያልኩ ለማዝናናት ሞከርኩ ግን አልተሳካም ዶሮ'ችን አቅም አንሶታል ይነቃል ይተኛል ይሄ ነገር ሲደጋገምብን እኔና ቃል ልንቀይረው ወሰንና የተዝረከረከውን ለሃጭ በሶፍት ጠራርጌለት ልንመልስ ጉዞ ጀመርን እንዳይሞት እየፈጠንን ጨዋታ ህይወቱን ያተርፍለት ይመስል እያጫወትነው ደረስንና ዶሮዋ አነሰች ተባልን ብለን የውሸትን ጥግ ዋሽተን ሌላ ዶሮ ብር ጨምረን ተረክበን ያ ሊሞት ያለው ወንድሞቹ እህቶቹን ሲያገኝ መፈንጠዝ ጀመረ እንኳን ሊሞት የነበረ ህመም አይቶ ማያውቅ መሰለ እኛም አፍረንና ተደስተን ጉዞ ጀመርን ስሙን ምትኬ/ምትኩ አልነው ከአባቱ ከኔ የተወለደ እስኪመስል ድረስ እንደዛኛው ዶሮ እንዳይሆንብን ታቅፌው አስሬ እየጠራሁትና እያጫወትኩት ሄድን እሽኮኮ ባረገው ሁላ ደስ ይለው ነበር ዝም ስለው ይተኛል ሳወራው ይሰማኛል😂😂😂😂 ከዛ እንቁላላችንን ገዝተን ቆሰቆስነው እዛ ስንደርስ ቆንጅዬ ድምፅ ያላት ቆንጆ ህፃን ልጅ ተቀበለችንና በመዝሙር አጅባ ወደ ቤቷ ወሰደችን ቤቷ ደርሰን የያዝነውን አስረክበን ምርቃታችንን ተቀብለን ታሪክ መስማት ጀመርን ታሪኩ ግን ያማል😔 እናት ልጇን ብዙ አትብይ እስከማለት የደረሰችበት ታሪክ ነበር ይህን ታሪክ ሰምቶ ውስጡ ያልደማ አለ ብዬ አላስብም ታሪኩ እንዲ ነው በአንድ ወቅት ደና ቦታ ላይ የነበረች እናት የድህነት አረንቋ ውስጥ ገብታ ገላዋን እየሸጠች መተዳደር ከጀመረች ቆየች በመሃል ግን ፀነሳ ወልዳ አሁን ላይ ወደ ልመና ተሰማርታለች አስቡት አንድ ልጇ ልበብርሃን ሆናባት ወደ ደብረዘይት የብሬል ትምህርት እንድትማር ተላከች አንድ ልጇ በመዝሙር አጅባ ያስገባችን ደግሞ ታይፕ 1 በሆነ የስኳር በሽታ እየተሰቃየችባት ነው ከሷም በታች ሌላ ህፃን አለ አስቡት እሷም የጭንቀትና የስኳር ታማሚ ናት ስኳር ደሞ በባህሪው ምግብ ይፈልጋል ታድያ ይቺ እናት ለልጆቿ ምን ታቅምስ ለስኳር ህመም በሽተኛዋ ክርስቲ ምን ታብላት ያላት አማራጭ ክርስቲ ልጄ ጠልቼሽ አይደለም ያለንበትን ታውቂያለሽና ምግብ ቀንሺ እየወጣሽም ለምኚ ትላታለች አስቡት በጨቅላ እድሜዋ ለምና ያገኘቻትን ለእናቷ አቀብላ የተገኘውን ተመግባ እራሷን የስኳር መርፌ ወግታ ነው ምታድገው ታድያ ይህ እንዴት አያም እንዴት አያስነባ ያውም መርፌውን ካገኘች ና ከተረዳች ነው ምትወጋው ልጄን በጉዲፈቻ አሳድጉልኝ ስትል ስኳር ህመምተኛ ልጅ አንፈልግም እያሏት አስባችሁታል ብቻ ግን ታሪኳን በሰፊው ከራሷ አንደበት ብትሰሙት እመርጣለው እኔ መፃፍም አልችልምና ያም ሆነ ይህ ግን የአቅማችንን አድርገን ምርቃት ካደረግነው በላይ ተመርቀን ሰው የራባቸውን በመጠኑ በፍቅር አጥግበን ተመለስን እላችኋለው
✍✍ለመፃፍ ተሞከረ @sisyop