👉 ስለ ቬትናም 10 አስገራሚ ነገሮች
1⃣ ውሻ እና ድመት
ውሻ እና ድመት የቬትናም ምርጥ ምግብ ናቸው። አንድ ቱሪስት ሬስቶራንት ቢገባ አብዛኛው ሰው ሚመገበው ውሻ ወይም ድመት መሆኑ ሊዘጋው ይችላል። የሚገርመው በቬትናም ውሻና ድመት ልክ እንደሌላው አለም የቤት እንስሳት ናቸው። አስፈላጊው እንክብካቤ ይደረግላቸዋል። ሁለት አመት ሲሞላቸው ግን ያለ ምንም ርህራሄ ለምግብነት
ይውላሉ።
2⃣ ጮክ ብሎ መብላት እና ማጋሳት።
ቬትናም ሬስቶራንት ለገባ ሰው ከውሻና ድመት ይልቅ ጮክ ብለው ሲያላምጡ እና ሲያጋሱ ይዘጋዋል። ይህ ለነሱ ምንም ማለት አይደለም።
3⃣ ሚሊየነር በ ዶንግ (የቬትናም ገንዘብ)
ቬትናምውስጥ አንድ ሰው በቬትናም ገንዘብ ሲከፍል እንደ ሚሊየነር ነው። 100 የኢትዮዽያ ብር 83,000 የቬትናም ዶንግ ነው። ስለዚህ ምሳ ለመብላት ከ 50,000 እስከ 100,000 ዶንግ ያወጣል። በሆቴል ደረጃ የሚዝናና ሰው በሜሊየን የሚቆጠር ዶንግ ያወጣል ማለት ነው። ስለዚህ ቬትናም ውስጥ ተራ ሰው ሚሊየነር ነው።
4⃣ ዋና ከተማ
አብዛኛው የአለም ሀገራት የሀገሪቱ ትልቅ ክፍል ወይም ብዙ ህዝብ ያለበት ክፍል ዋና ከተማ ይደረጋል። በቬትናም ግን ዋና ከተማዋ ሀኖይ ትንሽ ግዛት ስትሆን ከ92 ሚሊየን የቬትናም ህዝብ 7 ሚሊየን ብቻ ነው ሚኖርባት። (በዚህ ዙሪያ ተመሳሳይ የሆኑ ሀገራት
አሉ )
5⃣ የቬትናም ሰው አሜሪካን አይጠላም
የአሜሪካ—ቬትናም ጦርነት በብዙ ሰዎች ልብ ውስጥ አለ። በጦርነቱ አሜሪካ ትልቁን ድርሻ ተወጥታለች። ቢሆንም ቬትናሞች አሜሪካውያንን አይጠሉም። ሩቅ እንዳይመስላቹ ጦርነቱ የ40 አመት ብቻ እድሜ ነው ያለው። ምክንያቱ ደሞ የቬትናም የምንግዜም ታላቅ መሪ የነበረውና ትልቅ ቦታ የሚሰጡት መሪያቸው ሆ ቺ ሚንህ አሜሪካውያንን ለጦርነቱ ተጠያቂ ስለማያደርግ ነው። መሪያቸው እንዲህ ይላል… "ሁሉም ነገር አሜሪካውያን ላይ የተመረኮዘ ነበር። 20 አመት መዋጋት ቢፈልጉ 20 አመት መዋጋት እንችል ነበር። 20 አመት ሰላም ቢፈልጉ 20 አመት ሰላም ሆነን ቡና እንጋብዛቸው ነበር። "
እንዲህም ይል ነበር… "ራስህን እንደምትወድ ሁሉ ሌሎችንም ውደድ" ይህ ፍቅርን የማስተማር ችሎታው ቬትናማውያንን ሁሉንም የውጭ ዜጋ (ጠላታቸው አሜሪካን ጨምሮ) እንዲወዱና እንዲያከብሩ አድርጓቸዋል።
6⃣ ኤሊ በ ቬትናም
ቬትናማውያን ኤሊ የጥሩ እድል እና የጤንነት ምልክት እንደሆነች ያምናሉ። አራት ከሀይማኖታቸው ጋ የሚያያዙ እንስሳዎች አሉ። ኤሊ ድራጎን የተረት ወፍ እና ዩኒኮርን።
7⃣ የሲጋራ ገነት
ስለ ቬትናም ሰዎች ከማያውቋቸው 10 ነገሮች ውስጥ አንዱ ቬትናም የአጫሾች ገነት መሆኗን ነው። እንደ የአለም የጤና ማዕከል(WHO) ዘገባ 25% የሚሆነው የቬትናም ህዝብ የሲጋራ ተጠቃሚ ነው። ከ4 ሰዎች አንዱ ማለት ነው። ቬትናም ውስጥ ሴት ልጅ ሲጋራ ስታጨስ ማየት የተለመደ ነው።
8⃣ ጣፋጭ ለውዝ
ቬትናም ጣፋጭ ለውዝ አምርታ ኤክስፖርት በማድረግ ግንባር ቀደም ነች። 33% የሚሆነውን አለም ላይ ያለ ጣፋጭ ለውዝ ከቬትናም ይገኛል።
9⃣ አስፈሪ መጠጥ
የ"እባብ ወይን" ሲባል ሰምተው ያውቃሉ? ቬትናም ውስጥ ግን የታወቀ መጠጥ ነው።
አሰራሩ እንደዚህ ነው። አንድ ጠርሙስ ውስጥ ሙሉ እባብ (ጊንጥ)ይከታሉ። ከዛም ወይን የሞሉታል። ጥቂት ቆይቶ መጠጣት ነው። ብዙ ቱሪስቶች ሞክረውታል። አስደናቂ ጣዕም አለው ሲሉ ገልፀውታል። ሌላም አላቸው። ቡና በ እንቁላል ወተትም ይጨምሩበታል።
ወተቱ ከስር የቬትናም ታዋቂ ቡና ከመሀል እንቁላል ከላይ ይንሳፈፋል። ሲታይ በጣም ያምራል። የቀመሰው ሁሉ አድናቆቱን ይቸረዋል። ልዩ ነው።
🔟 አዲስ አመት
የቬትናማውያን አዲስ አመት የተወሰነ ቀን የለውም።
በየአመቱ የተለያየ ቀን ነው ሚከበረው። በጃንዋሪ ወይም ፌብሩዋሪ። የሚገርመው በዚህ ቀን ዋዜማ በእያንዳንዱ ቤት በር ላይ ጠረዼዛ ይቀመጣል። ከዛም ሙሉ የተጠበሰ ዶሮ
(ከነ ጭንቅላቱ) እና መጠጥ ኮካ ቢራ የመሳሰሉት ይቀመጣል። በየቤቱ ለሚኖረው ፈጣሪ ተብሎ። ግን ለሊት እራሳቸው ይመገቡታል።
#Share #Share #Share
@Swithen OR
@Lanchisel