#አሳዛኝ_ዜና
#በቤተክርስቲያን_ላይ_ጥቃት_ደረሰ
በዴሞክራሲያዊት ኮንጎ ሪፓብሊክ ቤኒ በተባለ አካባቢ በሚገኝ ካቶሊካዊ ቁምስና እሑድ ሰኔ 20/2013 ዓ. ም የጦር መሣሪያ ጥቃት መድረሱ ታውቋል።
በጥቃቱ ሁለት ሰዎች መቁሰላቸውን ከሥፍራው የወጣ ዘገባ አመልክቷል። የአገሪቱ ካቶሊካዊ ብጹዓን ጳጳሳት ጥቃቱን አውግዘው “በዚያ አካባቢ አንድም ቀን የሰው ሕይወት ሳይጠፋ የሚያልፍበት ቀን የለም” ብለዋል።
ከአካባቢው የተሰራጨው ዘገባ እንዳመለከተው እሑድ ሰኔ 20/2013 ዓ. ም በቡቴምቦ-ቤኒ ወረዳ በሚገኝ ካቶሊካዊ ቁምስና ላይ የተፈጸመው የከባድ ጦር መሣሪያ ጥቃት ከደረሰው በላይ ከፍተኛ ጉዳት ሊያስከትል ይችል እንደነበር ተገልጿል። እሑድ ማለዳ ላይ በቤተክርስቲያኒቱ ውስጥ በመንበረ ታቦት አካባቢ የተጠመደው ቦምብ ፈንድቶ በሁለት ሰዎች ላይ ከፍተኛ የመቁሰል አደጋን ማድረሱ ታውቋል።
ፍንዳታው እሁድ በቀረበው የመስዋዕተ ቅዳሴ ጸሎት ሥነ-ሥርዓት ላይ ለሚሰጥ የቅዱስ ሜሮን ምስጢር ሥፍራን በማዘጋጀት ላይ በነበሩ ሁለት ሴቶች ላይ ከባድ የመቁሰል አደጋን ያደረሰ መሆኑ ታውቋል። አደጋው የደረሰባቸው ሴቶች በአካባቢው ወደሚገኝ ሆስፒታል ተወስደው ሕክምና የተደረገላቸው መሆኑ ታውቋል።
በሰሜን ምሥራቅ ዴሞክራሲዊት ኮንጎ ሪፓብሊክ የምትገኝ ቡቴምቦ-ቤኒ ቁምስና
ከረጅም ዓመታት ወዲህ ጥቃት ሲደርስባት በነበረው በሰሜን ኪቩ ክፍለ ሀገር የምትገኝ ወረዳ መሆኗ ታውቋል።
ፈጣን ወቅታዊ ታማኝ ሀገርኛ እና አለማቀፍ የክርስቲያናዊ ዜናዎችን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለመከታተል የቴሌግራም ቻናሌን በዚህ ሊንክ ይቀላቀሉ።
https://t.me/TCNEW
በኢንስታግራም ቤተሰብ እንሁን
https://www.instagram.com/thechristiannews1/