#ዘማሪ_ሙሉነህ_ጩፋሞ
የተወዳጁ ኢንጅነር፤ ጸሐፊ፤ ዘማሪ ሙሉነህ ጩፋሞ አሳዛኝ የህይወት እና የአገልግሎት ጉዞ።
አንዳንድ ጊዜ እግዚያብሄር የጠራቸው ሰዎች ችግር ውስጥ ይገባሉ ነገር ግን ችግሮች ሁሉ ለመልካም ይሆንላቸዋል።
ዮሴፍን ወንድሞቹ ስለ ህልሙ ሲሉ እንደገፉት እና እንደሸጡት ሁሉ ይህ ተወዳጅ ዘማሪ በዚህ ተመሳሳይ ይህወት ውስጥ አልፏል።
የዚህ ተወዳጅ ዘማሪ ወንድሞቹ ለሊት በር ሰብረው ገብተው ሊገሉት ገብተው ነበር ድንገት ግን ጌታ እነሱ ሰብረው በገቡበት በር አስመለጠው።
ይህ ተወዳጅ ዘማሪ አዲስ አበባ በሚኖርበት ወቅት ወንድሙን ከክፍለ ሃገር አስመጥቶ ስራ ይዞ አብሮት እንዲኖር አድርጎት ነበር። ነገር ግን በጊዜ ሂደት ውስጥ ይህ ወንድሙ እየተቀየረ መምጣት ጨመረ አልፎ ተርፎ ከአገልግሎት አምሽቶ ሲመጣ በር ይዘጋበት ጀመር።
ከዚህ በኋላ በጓደኞቹ ቤት በመጠለል እና በድጋፍ ቆየ ነገር ግን ይሄም አልሆን ሲል ሁሉንም እርግፍ አድርጎ ትቶ ወደ ትውልድ ስፍራው (ክፍለ ሃገር ሄደ) ነገር ግን ይሄ ወንድሙ አሁንም አልተወውም ይልቁንስ ያገለግልበት የነበረው ቤተክርስቲያን በመደወል ጭምር ስሙን እያጠፋ እንዳያገለግል ያደርገው ነበር።
ይህ ተወዳጅ ዘማሪ ይህ ሁሉ ሳይፈጠር ከ20ዓመት ቀደም ብሎ እንዲህ ሲል ዘምሮ ነበር።
ከአንድ አባት ተወልደን
በአንድ ጉያ አድገን
ዛሬ ትልቅ ሆነን
ምነው ተለያየን
ከልጅነታን በቤቱ አድገናል
ፍቅሩ ቸርነቱን ደጋግመን አይተናል
ካልካድነው በስተቀር ውለታው አለብን
ስንት ያሳለፈንን እንዴት እንረሳለን
ሲል ዘምሮ ነበር ይህ በአንድ ወቅት የዘመረው ዝማሬ ከ20ዓመታት በኋላ በራሱ ላይ ተፈጸመ። ምንም እንኳን ዛሬ ወንድሞቹ ከጌታ ቤት ወደ ኋላ ቢመለሱም የሆነ ወቅት ግን በአንድ መድረክ ጌታን ቆመው አገልግለው ነበር።
ዛሬ ግን ወንድሞቹ እሱን ለሊት በተኛበት ሊያርዱት ሲሞክሩ እሱ አልሳካ ሲላቸው እንዲገለው ጠንቋይ ቤት እስኪሄዱ የገዛ ሰጋዎቹ ጨክነውበት ነበር።
በመላው አለም የምትገኙ ወደ The Christian News - የክርስቲያን ዜና ቤተሰቦቻችን ከዚህ ተወዳጅ ዘማሪ ህይወት ጥቂቱን ብቻ አካፈልናችሁ።
ሙሉነህ ጩፋሙ "ዘጸዓት ለኢትዮጵያ" የተሰኘ ስለ ሃገራችን የተዘመረ ተወዳጅ ዝማሬ ጨምሮ 3 ሙሉ አልበሞች አሉት። በዚህ ሰዓት ልክ ዮሴፍን የማያውቅ ትውልድ እንደተነሳ ዛሬም በኛ ትውልድ የቀደሙትን የማያውቅ እና እንዲሁም የዘነጋ ትውልድ የተነሳ ይመስላል። ለማንኛውም ሙሉነህን ለማግኘት እና ለመደገፍ የምትፈልጉ አካላት የተቀመጡትን አድራሻዎች መጠቀም ትችላላችሁ።
በቀጣይ በተመሳሳይ የተወሰነ የሱን አገልግሎት እና ህይወት በተመለከተ ሌላ ተጨማሪ መረጃ ይዘንላችሁ እንመጣለን።
ፈጣን ወቅታዊ ታማኝ ሀገርኛ እና አለማቀፍ የክርስቲያናዊ ዜናዎችን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለመከታተል የቴሌግራም ቻናሌን በዚህ ሊንክ ይቀላቀሉ።
https://t.me/TCNEW
በኢንስታግራም ቤተሰብ እንሁን
https://www.instagram.com/thechristiannews1/
አዳዲስ ዜናዎች በምስል እና ድምጽ ለማግኘት የዩቲዩብ ቻናላችንን በዚህ ሊንክ ይጎብኙ እና ቤተሰብ ይሁኑ!!!
https://www.youtube.com/channel/UCeHRJCDJ0wUDaBfAFmuMa7A?sub_confirmation=1