ስም= ኑር አህመድ
ኮድ= 0012
__
ተውሂድና ሽርክ
እባክህ ወንድሜ ስማኝ ልምከርህ
ተውሂድና ሽርክን ትንሽ ላስረዳህ
ከተውሂድ ልጀምር ከሆነችው ጠቅላይ
የኢስላም መሠረት ከተባለው ጉዳይ አንቢያዋች ሁሉ ከተላኩባት
ነብዩ ሙሀመድ (ሰ.ዐ.ወ)ብዙ ከለፉባት
ተውሂድ ብሎ ማለት ጠንቅቆ ማመን ነው የአላህን አንድነት
የፍጥረተ አለሙን የበላይ ገዚነት
ጌታችንም ብሏል በቅዱስ ቁርዐን
በሱረቱል ኢህላስ ተውሂድን ሲነግረን
በል አላህ አንድ ነው የሁሉ መጠጊያ
አንድም ቢጤ የለው የሚሆን አምሳያ
ደሞም አሎለደም ብሎ አልተወለደም
ከሱ የሚመሳሰል አንድም ፍጡር የለም
በሱረቱል ዛሪያት ሲያረጋግጥ ዳግም
ሰውና ጋኔን እኔን ሊገዙ እንጂ አልፈጠርኳቸውም
የተውሂድን ነገር እንደው ባነሳሳው
ውቅያኖስ ባህር ነው በትንሻ ኢልሜ ዝቄም አልጨርሰው
እስቲ ደሞ ሽርክን ትንሽ ላስተንት ነው
ከበደሎች ሁሉ ትልቅ በደል ነው
ከበደሎች ሁሉ ትልቅ በደል ነው
በሀያት እያለ ሽርክን የሚፈፅም
ሳይቶብት ከሞተ ፈፅሞ አይማርም
ጌታችን ነግሮናል የሽርክን ክብደት
በጣም አስጠነቀቀ በቁርአን አያት
አንቢያዋች እኳ በጣም ቢፈሯት
ያረቢ አማና ጠብቀን አሉት
ሽርክን በጥፋቱ ከፋፍለን ስናየው
ሽርኩል አክበርና አሽርኩል አስገር ነው
የማይጠቅምና ምንም የማይጎዳ አካልን መጣራት
እርድንም በማረድ በሱ ላይ ማጋራት
ከአሽርኩል አክበር ነው እኚ እሚመደቡት
እነዚህን የሰራ ቅጣቱ ከባድ ነው
በዛው ላይ ከሞተ ከሳት ዘውታሪ ነው
ከአላህ ውጪ ሌላ በለ አካል መማል
ለበሽታ ብሎ እርዝንም ማንጠልጠል
ከአላህ ውጪ ያለን የሩቅ ያውቃል ማለት
በአሽርኩል አስገር ነው እኚ የሚታወቁት
ሽርክ ከሚያመጣው ከዚ ሁሉ ችግር ለመዳን ከእሳት
በደንብ አስረግጠን ተውሂድን እንማር እያለን በሀያት
_
@Tefekur_Centerተፈኩር ሴንተር // Tefekur Center