ጳጉሜን እኔና ጓደኞቼ
*~★★~*
… ዘንድሮም እንደተለመደው ፌስቡክ ጳጉሜን መድረሷን ጠብቆ ከገጹ ቢያግደኝም። እኔ በቴሌግራም ቻናሌ እናንተ ደግሞ በፌስቡክ ገጻችሁ ማጥለቅለቃችንን እንቀጥላለን።
•••
እኔ ዘመዴ የፌስቡክ እና የቴሌግራም ጓደኞቼ በሙሉ አንድ ላይ ሁነን መጪውን የወርሀ ጳጉሜን ፭ቱን ቀናት ልክ እንደ አምናው ካቻምናው ሁሉ ዘንድሮም ዘመነ ማቴዎስን አሳልፈን ዘመነ ማርቆስን ለመቀበል በዝግጅት ላይ እንገኛለን። ዘንድሮ እንዲያውም በቋሚ ሲኖዶሳችን ጭምር ወርሀ ጳጉሜን በጾም፣ በጸሎትና በምህላ እንድናሳልፍ ሁሉ ዐዋጅ ታውጇል። አዲሱን ዓመትም በዚህ መልኩ እንቀበላለን ማለት ነው። እናም እኛም ከጾም ጸሎት ምህላው ጎን ለጎን አምስቷን ቀናት እንደልማዳችን በዚህ መልኩ እናሳልፍ ዘንድ አስበናል። ወስነንም ተዘጋጅተናል።
፩፥ ጳጉሜ ፩ የማዕተብ ቀን።
፪፥ ጳጉሜ ፪ የክብረ ክህነት ቀን።
፫፥ ጳጉሜ ፫ የፊደል ገበታ ቀን።
፬፦ ጳጉሜ ፬ የሰንደቅ ዓላማና የቅድስት ቤተክርስቲያን ቀን።
፭፦ ጳጉሜ ፭ ከሱስ ሁሉ የመላቀቂያና ለአቅመ ደካሞች የሥጦታ ቀን።
•••
ጳጉሜ ፩ ፥ የማዕተብ ቀን ነው።
… የተዋሕዶ ልጆች አንገት በሙሉ በአንገት ማዕተብ ክር ያሸበርቃል። የመስቀል ዓይነት የፌስቡክና የቴሌግራም ቻናሎቻችንንም ያጥለቀልቃል። በዕለቱ ፌስቡክ ሌላ ወሬም የለም፣ ሌላ ፎቶም አይለጠፍበትም። ተዘጋጁ፣ ጳጉሜ ፩ እየጾምን፣ እየጸለይንም፣ ማዕተባችንንም አጥብቀን እናስራለን። የአንገት ማዕተብ የሌላችሁ ከወዲሁ ግዙ፣ አስባርካችሁም እሰሩም። አንገታችሁ ባዶ አይሁን።
•••
ጳጉሜ ፪ ፥ የክብረ ክህነት ቀን ነው።
… ለንስሐ አባቶቻችን፣ ለካህናት አባቶቻችን፣ ፍቅራችንን፣ አክብሮታችንን የምንገልጽበት ዕለት ነው። እንኳን አደረሳችሁ የምንልበት፣ ቡራኬ የምንቀበልበት፣ ለበዓሉም ለአባቶቻችን ስጦታ የምንሰጥበት፣ ዕለትም ነው። እኔም አደርገዋለሁ። እናንተም አድርጉት። ተዘጋጁ።
•••
ጳጉሜ ፫፥ የፊደል ገበታ ቀን።
… አከተመ የዚያለት ፌስቡክ በኢትዮጵያ ፊደላት ሲያሸበርቅ ይውላል። የዚያን ዕለት ልብሱ ሁሉ የፊደል ገበታ ነው የሚሆነው። በዓለሙ ሁሉ ስንነበብ እንውላለን። ፊደላችን የፌስቡክን ግድግዳ አጥለቅልቆት ይውላል።
•••
ጳጉሜን ፬ ፥ የሰንደቅ ዓላማና የቅድስት ቤተ ክርስቲያን ቀን።
… ይሄ ምንም ማብራሪያም ዝርዝርም አያስፈልገውም። በዚህ ዕለት ፌስቡክ በአረንጓዴ ቢጫ ቀይ የነፃነት ሰንደቅ ዓላማና በቅድስት ቤተ ክርስቲያን ፎቶ አሸብርቆ የሚውልበት ቀን ነው ማለት ነው።
•••
ጳጉሜ ፭ ፥ ከሱሶች ሁሉ የመላቀቂያና፣ የመገላገያ ለአቅመ ደካሞችም የሥጦታ መስጫ ቀን እናደርገዋለን። እነ ሲጋራ በአደባባይ ይረገጣሉ። አልኮል፣ ጫት፣ ሺሻና ሀሺሽም ይወገዳሉ፣ ይረገማሉ። ከዝሙት እንሸሻለን። በአዲስ መንፈስ አዲሱን ዘመን ዘመነ ማቴዎስ፣ ዘመነ ሰማዕታትን፣ እንቀበለዋለን፣ እንቀላቀለዋለንም። ታዲያ እኛ ደስስ ሲለን ሌላ የሚከፋው እንዳይኖር ጉረቤቶቻችንን በዓሉን አዲሱንም ዓመት በደስታ ይቀበሉ ዘንድ ያለንን የምናካፍልበት ዕለትም ነው። ቢያንስ ቅቤ፣ ዘይት፣ ዱቄት፣ ዶሮና እንቁላል እናበረክትላቸዋለን።
•••
ሰምታችኋል ጓደኞቼ ተዘጋጁ። ደግሞም እናደርገዋለን። አባቴ ይሙት እናደርገዋለን። ይሄን መልእክት የጻፍኩት ለጓደኞቼ መሆኑ ይሰመርበት። መንገደኞችን አይመለከትም። አከተመ።
ዘመድኩን በቀለ (ዘመዴ)