Golden WCU Students💡


Гео и язык канала: не указан, не указан
Категория: не указана


Welcome! This channel helps you thrive at university. Get study tips, resources, and crypto connect with fellow students. Let's ace exams and succeed together.

Связанные каналы

Гео и язык канала
не указан, не указан
Категория
не указана
Статистика
Фильтр публикаций


የሀዘን መግለጫ

በዋቸሞ ዩኒቨርሲቲ ከ2012 ዓ/ም ጀምሮ በሠላምና ደህንነት አገልግሎት ስራ አስፈፃሚ ስራ ክፍል ካምፓስ ፖሊስ ሠረተኛ የነበሩ ሃ/አለቃ አለሙ አቡረ ባጋጠማቸው ህመም ምክንያት በህክምና ሲረዱ ቆይተው በዛሬው ዕለት መስከረም 24/2019 ዓ.ም ከዚህ ዓለም በሞት ተለይተዋል ።

በሃ/አለቃ አለሙ አቡራ ሞት ምክንያት የዩኒቨርሲቲው አስተዳደር በመላው የተቋሙ ማህበረሰብ ስም የተሰማውን ጥልቅ ሀዘን እየገለፀ፤ ለቤተሰቦቹ፣ ለወዳጅ ዘመዶቹ ፣ ለስራ ባልደረቦቹ፣ ለጓደኞቹ ሁሉ መፅናናትን ይመኛል።

ፈጣሪ ነፍሱን በገነት ያኑርልን!
RIP!


Репост из: Golden fresh and Remedial materials
ፅድት ያለች Tablet for Sell!!

..........📍𝐒𝐚𝐦𝐬𝐮𝐧𝐠 𝗔𝟵+𝟱𝗚
👉 𝗥𝗔𝗠 & 𝗦𝘁𝗼𝗿𝗮𝗴𝗲▫️8𝗚𝗕 & ▫️𝟭𝟮𝟴𝗚𝗕
👉
𝗗𝘂𝗮𝗹 𝘀𝗶𝗺 𝗰𝗮𝗿𝗱
👉 𝟱𝗚 𝘀𝘂𝗽𝗽𝗼𝗿𝘁𝘀
👉 𝗕𝗮𝘁𝘁𝗲𝗿𝘆 𝗟𝗶𝗳𝗲 ▫️ 4𝗗𝗮𝘆
👉 𝗕𝗼𝗱𝘆&𝗤𝘂𝗮𝗹𝗶𝘁𝘆 ▫️ 𝐅𝐥𝐚𝐭
👉 𝗣𝗿𝗶𝗰𝗲 ▫️ 𝗡𝗲𝗴𝗼𝘁𝗶𝗮𝗯𝗹𝗲
🔥መግዛት የሚፈልግ ቀደም ብሌ ያግኘኝ...።

✨Contact
      ......🗯Telegram ➣ @sisay0119
      ......🗯Call Us ➣ 0924149344
      ......🗯Call Us ➣ 0920652321


#ለሚፈልግ share...
#GoldenShop


የምግብ ቤት ክፍያዎች በ ወንዶች ብቻ እንዲከፈሉ ተደርገው የተነደፉ ናቸው ለዚህም ነው MEN_U የተባለው የሴቶችን እኩልነት የሚጋፍ ተግባር በመሆኑ wo Men_u በሚል መስተካከል አለበት 🤲


Non Cafe ምዝገባ ጊዜ ስለማሳወቅ

የ2019 ዓ/ም Non Cafe ምዝገባ የሚደረገው መስከረም 29 እና 30 ብቻ መሆኑን አውቃችሁ ፍላጎት ያላችሁ ተማሪዎች አስፈላጊውን መረጃ አሟልታችሁ እንድትቀርቡ እናሳስባለን።

ለምዝገባ ስትመጡ
1/ በዚህ አመት የተመዘገባችሁበትን Registration Slip ፎቶ ኮፒ
2/ የዋቸሞ ዩኒቨርስቲ የተማሪዎች መታወቂያ ፎቶ ኮፒ
3/ የንግድ ባንክ ደብተር ፎቶ ኮፒ እና
4/ ሚል ካርድ ዋናውን ይዛችሁ እንድትመጡ ይሁን።



የምዝገባ ቦታዎች
1/ ዋና ግቢ ላላችሁ በተማሪዎች መሰረታዊ አገልግሎት።

2/ ሆስፒታል ላላችሁ እዛው ሆስፒታል የተማሪዎች ካፌ።

3/ በዕለቱ ከዋና ግቢ ለትምህርት ሆስፒታል የምትሄዱ ተማሪዎች ዋና ግቢ መመለስ ሳይጠበቅባችሁ ከሆስፒታል ተማሪዎች ጋር መመዝገብ ትችላላችሁ።


📍ብሔራዊ መልቀቂያ ፈተና በመውሰድ ለ2019 ዓ.ም ወደ ዋቸሞ ዩኒቨርስቲ ተመድባችሁ የግቢውን ጥሪ እየተጠባበቃችሁ ለምትገኙ ተማሪዎች በሙሉ:-

▰▷በቅድሚያ ወደ ግቢያችን በመመደባችሁ ደስታችንን እየገለፅን የዋቸሞ ዩኒቨርሲቲ ወንጌላውያን ክርስቲያን ተማሪዎች ህብረት ( WCU EvaSUE | ኢቫሱ fellowship) እናንተን ለመቀበል አስፈላጊውን ዝግጅት በማድረግ እየጠበቅናችሁ መሆኑን ልናሳውቃችሁ እንወዳለን።🤗

👉ስለሆነም ስለ ግቢውም ሆነ ስለአካባቢው አጠቃላይ ሁኔታ፣ የሚያስፈልጋችሁን ዝግጅት እንዲሁም ሌሎች አስፈላጊ መረጃዎችን በመስጠት ከወዲሁ በዝግጅታችሁ ልንረዳችሁ ዝግጁዎች ነን።


🚩ለሚያስፈልጋችሁ የትኛውም መረጃ እና እገዛ ከታች በተቀመጠው መረጃ የFellowship ዋና መሪዎች በየትኛውም ሰዓት ማግኘት ትችላላችሁ።

●በረከት አበራ....0937334875 / @bereket_abera_ersulo

●ሰላም ጀማል....+251968608466 / @hilaryjemal

●ፀደቀ ጡሜቦ....
+251934952932/
@tsedeke3

●ምህረቱ መታሎ ....
+251993415820  / @emarindos

●ፀጋ ጤናዬ....
+251919267698 / @Last_19_asset

●በረከት በለጠ....
+251916395696  /  @Beka_1602

●አባተ አቢዶ.....
+251943363811 / @Abate4336


"እናንተ ግን ከጨለማ ወደሚደነቅ ብርሃኑ የጠራችሁን የእርሱን በጎነት እንድትናገሩ የተመረጠ ትውልድ፥ የንጉሥ ካህናት፥ ቅዱስ ሕዝብ፥ ለርስቱ የተለየ ወገን ናችሁ፤"
— 1 ጴጥ.  2:9
#WCU_EvaSUE
#ለሁሉም_ፍሬሽ_ተማሪ_ሼር_ይደረግ!


🏳️በትግራይ ክልል በሚገኙ አራት የመንግሥት ዩኒቨርሲቲዎች ስትማሩ የነበራችሁ ነባር ተማሪዎች እና አዲስ የተመደባችሁ ተማሪዎችን በጊዜያዊነት ከክልሉ ውጪ ወዳሉ ዩኒቨርሲቲዎች ከመመደብ ጋር ተያይዞ የተነሱ ቅሬታዎችን የማጥራት ሥራ እየሠራ መሆኑን ትምህርት ሚኒስቴር ገልጿል።

➪በምደባው ሒደት የቀረቡ ቅሬታዎችን የማጥራት ሥራ ተጠናቆ ተማሪዎቹ በጊዜያዊነት ወደተመደቡበት ዩኒቨርሲቲዎች የሚገቡበት ቀን ይፋ እስከሚደረግ ድረስ፣ ተማሪዎቹ ባሉበት ሆነው በትዕግስት እንዲጠብቁ ሚኒስቴሩ አሳስቧል።
#MOE

#Goldem


​📍የዋቸሞ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት የነበሩት ዶ/ር Dawit Hayeso የሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ምክትል ርዕሰ መስተዳድር እና የፋይናንስ ቢሮ ኃላፊ ሆነው ተሹመዋል።

▰▷መልካም የስራ ዘመን Our Brilliant President Doctor! ❤️


#Golden

#Golden

636 0 3 10 25

📍ዋቸሞ ዩኒቨርሲቲ Bemanda Solution PLC ጋር የትብብር ስምምነት ተፈራረመ


🔲ዋቸሞ ዩኒቨርሲቲ ዲጂታል ትራንስፎርሜሽንን ለማፋጠንና የቴክኖሎጂ ክህሎትን ለማስፋት Bemanda Solution PLC ኃ/የተ/የግ/ማ ጋር የመግባቢያ ስምምነት ተፈራርሟል።

🔲ስምምነቱ ተማሪዎችንና ሰራተኞችን AI፣ Cloud Computing፣ Ciber Security ፣ Microsoft 365 እና Data Analysis ክህሎት ለማብቃት ያለመ ነው።... More

📍የምክትል ፕሬዚዳንት ዶ/ር ሳራ ሹኩር ዩኒቨርሲቲዎች ዲጂታል ትራንስፎርሜሽንን መቀበል እንዳለባቸው ገልጸው፣ ይህም የትምህርትና የምርምር ጥራትን እንደሚያሳድግ ተናግረዋል።
Bemanda Solution PLC ምክትል ፕሬዚዳንት አቶ ወሰነ ተክለማርያም በበኩላቸው ኩባንያው ለዩኒቨርሲቲው የቴክኖሎጂ ሽግግር፣ የአቅም ግንባታና ስልጠና ድጋፍ እንደሚያደርግ አረጋግጠዋል።
በሥነ ሥርዓቱ የዩኒቨርሲቲው አመራሮች፣ ባለሙያዎችና የኩባንያው ተወካዮች ተገኝተዋል።
የሕዝብና ዓለም አቀፍ ግንኙነት ጽ/ቤት
🔥Let your light shine in the society🔥

#Golden


Репост из: Golden fresh and Remedial materials
ፅድት ያለች Tablet for Sell!!

..........📍𝐋𝐞𝐧𝐨𝐯𝐨
👉 𝗥𝗔𝗠 ▫️𝟰𝗚𝗕
👉 𝗦𝘁𝗼𝗿𝗮𝗴𝗲▫️𝟭𝟮𝟴𝗚𝗕
👉 𝗕𝗮𝘁𝘁𝗲𝗿𝘆 𝗟𝗶𝗳𝗲 ▫️ 4𝗗𝗮𝘆
👉 𝗕𝗼𝗱𝘆&𝗤𝘂𝗮𝗹𝗶𝘁𝘆 ▫️ 𝗕𝗲𝘀𝘁
👉 𝗣𝗿𝗶𝗰𝗲 ▫️ 𝗡𝗲𝗴𝗼𝘁𝗶𝗮𝗯𝗹𝗲
🔥መግዛት የሚፈልግ ቀደም ብሌ ያግኘኝ...።

✨Contact
      ......🗯Telegram ➣ @sisay0119
......🗯Call Us ➣ 0924149344
      ......🗯Call Us ➣ 0920652321


#ለሚፈልግ share...
#GoldenShop


#New_Notice!
#Golden


Репост из: Golden ŴĈÛ Freshman Resources
🛑 የመጀመሪያው ሴሚስተር ወሳኝ ምዕራፍ ነው።

▪️  ይህ መልዕክት ለዘንድሮ ለ 2019 ዓ.ም ፍሬሽማን ተማሪዎች ነው ፥ የፍሬሽማን የመጀመሪያውን ሴሚስተር ውጤት ግቢ ላይ ለምትቆዩበት አምስትና ከዛ በላይ አመታት መሰረት ነው።

▪️ የመጀመሪያው ሴሚስተር ውጤት ፥ የምትገቡበትን ዲፓርትመንት ይወስናል። ከአዲሱ ካሪኩለም  ትግበራ በሗላ ፥ የተማሪዎች የዲፓርትመንት ቅበላ ዋና መመዘኛው የፍሬሽማን ውጤት ነው። ፍሬሽማን 1st Semester ላይ ከፍተኛ ውጤት ያመጣ ተማሪ የሚፈልገውን ዲፓርትመንት መርጦ ይገባል። በተለይም ደግሞ እንደ Medicine, Anesthesia, Pharmacy ና ሌሎችም የጤና ዘርፎች ፥ እንደ Software Engineering ና Computer Science ያሉ የቴክኖሎጂ ዘርፎች ፥ እንደ Law ያሉ የህግ ዘርፎች ብዙ ተማሪዎች ስለሚፈልጓቸው ከብዙ ተማሪዎች ጋ ፉክክር ስለሚኖር 1st Semester ላይ ከፍተኛ ውጤት ካመጣችሁ እነዚህን ተፈላጊ ዘርፎች ታገኛላችሁ።

▪️ የመጀመሪያው ሴሚስተር ውጤት የሚቀጥሉት የግቢ ቆይታችሁ ላይ ተፅዕኖ አለው። በተለይም ፍሬሽማን ላይ ከፍተኛ ውጤት(GPA) ካላችሁ ከፍሬሽማን በሗላ እንኳን ውጤት ቢወርድባችሁ ፍሬሽማን ላይ ያስመዘገባችሁት ውጤት ከፍ አድርጎ ያቆይላችሗል። ስለዚህ ፍሬሽማን ላይ ከፍተኛ ውጤት ማስመዝገብ ዘርፈ ብዙ ጥቅም አለው።

▪️ ስለዚህ አላማውን ትምህርት አድርጎ ዩኒቨርሲቲ የሚሔድ ተማሪ ፥ ይህን ሴሚስተር ሰግጦ ያንብብ። ስታነቡ ደግሞ በብልጠት አንብቡ እንደው ላይብረሪ ውስጥ እስከ ሌሊት 10 ሰአት ማንጋቱ ብቻውን በቂ አይደለም:: የመረጃ ሰው መሆን አለባችሁ ስታነቡ ፅንሰ ሀሳብ ተኮር መሆን አለባችሁ። ይኸ ማለት ይኸ ነው እያላችሁ ብቻ አትሸምድዱ ሞጅሉ ላይ ያሉ ኖቶችን ከስር መሰረቱ ለመረዳት ሞክሩ። የግቢያችሁን ያለፉ አመታትት ፈተናዎች በደንብ ስሩ በምን መልኩ መዘጋጀት እንዳለባችሁ ፍንጭ ይሰጧችሗል።

▪️ የተለያዩ አመታት የፍሬሽማን ኮርሶችን የተለያዩ ግቢዎችን ጥያቄ ተመልካቻለሁ አብዛሀኛዎቹ ግቢዎች ፈተናቸው መማሪያ ሞጁላችሁን መሰረት ያደረገ ነው። ስለዚህ መጀመሪያ ሞጁላችሁን ማንበብ ከሞጁሉ ሰፋ ያለ ተጨማሪ ማብራሪያ ደግሞ ለማግኘት Ai መጠቀም አሪፍ ነው:: ጥሩ አድርጋችሁ Search ካደረጋችሁ ግልፅ የሆኑ ማብራሪያዎችን ከነምሳሌያቸው ታገኛላችሁ:: Even ፈተናዎች ሊወጡበትም ይችላሉ። ልክ አንድ part አንብባችሁ እንደጨረሳችሁ በዛ Part ዙሪያ የወጡ የግቢዎችን ፈተና በደንብ መስራት ይኖርባቹሀል።

📍የጊዜ አጠቃቀማችሁን ለማስተካከል ሞክሩ። ግቢ እንደገባችሁ የመጀመሪያው ሳምንቱ ግቢውን መተዋወቅ ላይ ትኩረት አድርጉ። Orientation ይሰጣል እሱን ተከታተሉ። የግቢውን አሰራር ለማወቅ ሞክሩ። ላይብረሪውን ሆስፒታሉን መመገቢያ ካፌውን ክላሱን ዶርማችሁን ወዘተ scan የምታደርጉበት ሳምንት ለማድረግ ሞክሩ። ከዛ በሗላ አብዛሀኛው ትኩረታችሁ ትምህርታችሁ ላይ ይሁን። በአንድ ጊዜ ሁሉንም አንብቤ ነካክቼ ካልጨረስኩ አትበሉ። ቀስ በቀስ የሚያድግ የሚሻሻል ነገር እየሰራችሁ ሒዱ። ትምህርታችሁን ከስር ከስር አንብቡ። ፈተና ሲደርስ አነባለሁ ብላችሁ አትተኙ። እንደዛ ከሆነ ፈተና ሲደርስ ለማንበብ ብትሞክሩ ቴንሽኑ ራሱ አያስነብባችሁም። ከቻላችሁ ፈተና ከመድረሱ በፊት አጠናቃችሁ የፈተና ሰሞን አዕምሯችሁን ነፃ አድርጋችሁ Relax ለማድረግ ሞክሩ።

▪️ በተለይ ለፍሬሽማን ተማሪዎች ስለ ግቢ የተጋነነ መረጃ ነው የሚሰጣችሁ። ሌላ አለም እንደሆነ ተደርጎ ነው የሚነገራችሁ ነገር ግን ምንም የተለየ ውስብስብ ነገር የለውም። በወሬ አትሸበሩ! አዲስ Environment ነው ፣ አዲስ Life Style ነው ፥ አዲስ መምህራን ናቸው ፥ ከቤተሰብ ትርቃላችሁ ለህይወታችሁ ሐላፊነት የምትወስዱት እናንተ ናችሁ። ልዩነቱ ይኼ ነው። ከዛ ውጪ ግቢ ማለት ይኸ ነው በዚህ ወጥቶ በዚህ ገብቶ የሚሏችሁን አትስሙ። ሌላው ትልቁ ነገር የጓደኛ ተፅዕኖ ከምታገኙት ነፃነት ጋ ተደማምሮ እያሳሳቀ ገደል እንዳይከታችሁ የአላማ ሰው ሁኑ በራሳችሁ አቋም እና እምነት ብቻ ተጓዙ።

🥳 በተረፈ ፈታ በሉ። አትጨናነቁ ያላችሁን ህይወት Enjoy አድርጉት:: የአላማ ሰው ሁኑ። እንወዳችሗለን በርቱ


🎉 መልካም ዜና ለዋቸሞ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች በሙሉ! 🚀

🎓 WACHEMO UNIVERSITY | ASPIRE INSTITUTE
Aspire Leaders Program (ALP) Cohort 4 – 2026 Full Scholarship Application!

━━━━━━━━━━━━━━━━━━━━

🇪🇹 ዋቸሞ ዩኒቨርሲቲ ከአሜሪካው Harvard University ባለሙያዎችና መምህራን ጋር በመተባበር የተዘጋጀው የ100% ሙሉ ስኮላርሽፕ የአመራር እና ሙያ ክህሎት ማሳደጊያ ኦንላይን ስልጠና እድል አዘጋጅቷል!

━━━━━━━━━━━━━━━━━━━━

🎯 Criteria of Selection (የምርጫ መስፈርቶች)
• Wachemo University student (Graduating or Remedial)
• Strong potential for leadership and community impact
• Demonstrable need (for scholarship)
• High academic standing
• Low-income students (ዝቅተኛ ገቢ ያላቸው)
• First-generation students (የመጀመሪያ ትውልድ)
• Age 18–29 only (ዕድሜ 18–29 ብቻ)

━━━━━━━━━━━━━━━━━━━━

📅 Important Dates (ወሳኝ ቀናት)
• Registration Deadline: Before October 7, 2026
• Orientation Date: October 7, 2026

━━━━━━━━━━━━━━━━━━━━

🎁 Program Benefits (የፕሮግራሙ ጥቅሞች)
• 💯 100% Full Scholarship
• 🗓️ 6-Week Interactive Online Program
• 🎯 Leadership & Career Readiness Skills
• 💰 Seed Funding & Mentorship Opportunities
• 🌍 Global Networking with International Students
• 🎓 Access to Harvard Faculty & Educators

━━━━━━━━━━━━━━━━━━━━

🔗 Registration Links / የማመልከቻ ሊንኮች:

1️⃣ Aspire Leaders Program – Register Here:
https://engage.aspireleaders.org/registration?refer=wachemo-university

2️⃣ Wachemo University – Microsoft Form:
https://forms.cloud.microsoft/r/cbNrdRQwzY

━━━━━━━━━━━━━━━━━━━━

📞 For Details / Consult:
Office of International and Partnership Director, Wachemo University

#WachemoUniversity #AspireLeaders #Scholarship #ALP2026



Показано 13 последних публикаций.