Репост из: የእውቀት ካዝና
“ከአላህ በስተቀር በእውነት የሚመለክ አምላክ የለም” የሚለው ቃል መሠረቶች
┈┈•••✿❒🌹❒✿•••┈┈
የዚህ ታላቅ የሆነ ቃል ትርጉምና ዓላማ ግልፅ እንዲሆንልን ከተፈለገ ሁለት መሠረቶችን ማወቁ ግድ ይለናል፡፡
የመጀመሪያው መሠረት፡- «ላ ኢላሃ» (አምላከ የለም) የሚለው ነው፡፡ ይህ ከአላህ ውጪ ባሉ ነገሮች ላይ አምልኮን መሻራችንን ማረጋገጫ ቃል ነው፡፡ ማጋራትን ውድቅ ማድረጊያ ቃል ነው፡፡ ከአላህ ሌላ በሚመለኩ ነገሮች ሁሉ መካድ ግዴታ ነው፡፡ ከአላህ ሌላ ሰውም ሆነ እንሰሳትም ሆነ መቃብርም ሆነ ከዋክብትም ሆነ ሌላ ማምለክ አይቻልም፡፡
ሁለተኛው መሠረት፡- ኢልለ ላህ (ከአላህ በስተቀር) የሚለው ነው፡፡ ይህ ደግሞ አምልኮን ለአላህ ብቻ የምናረጋግጥበት ቃል ነው፡፡ ሶላትን፣ ዱዓእና መመካትን የመሳሰሉ የአምልኮ ዓይነቶችን ሁሉ ለአላህ ብቻ የምናውልበት ማረጋገጫ ነው፡፡
የአምልኮ ዓይነቶችን በሙሉ ልንሰጥ የሚገባው አንድና አጋር ለሌለው አላህ ብቻ ነው፡፡ ከእነዚህ ውስጥ አንዱን እንኳ ከአላሀ ውጪ ላለ ነገር አሳልፎ የሰጠ ከሃዲ ይሆናል፡፡
አላህ እንዲሀ ይላል …“ከአላህም ጋር ሌላን አምላክ ለርሱ በርሱ ማስረጃ የሌለውን የሚግገዛ ሰው ምርመራው ጌታው ዘንድ ብቻ ነው፤ እነሆ ከሀዲዎች አይድኑም፡፡” (አል-ሙእሚን፡117)
ከአላሀ በስተቀር በእውነት የሚመለክ አምላክ የለም የሚለው ቃል ትርጓሜና መሠረቶች እንዲህ በሚለው የአላህ ቃል ውስጥ ተገልጿል… “በጣዖትም የሚክድና በአላህ የሚያምን ሰው ለርሷ መበጠስ የሌላትን ጠንካራ ዘለበት በእርግጥ ጨበጠ አላህም ሰሚ ዐዋቂ ነው፡፡” (አል-በቀራህ፡256)
በዚህ የአላህ ቃል ውስጥ “በጣዖትም የሚክድ” የሚለው ቃል የመጀመሪያ መሠረት የሆነውን “አምላክ የለም” የሚለውን ቃል ሲሆን ያረጋገጠው “በአላህ የሚያምን” የሚለው የጌታችን ቃል ደግሞ ሁለተኛ መሠረት የሆነውን ከአላህ በስተቀር የሚለውን ቃል የረጋግጥልናል፡፡
┈┈•••✿❒🌹❒✿•••┈┈
𝐉𝐨𝐢𝐧👉 https://t.me/Dnel_Eslam