🌿መውሊድ🌿
💥የረሱልም ሆነ - የመሲሁ ኢሳ
ልደት ሚባል የለም - ከሸሪዓ ማሳ።💥
💥ኡለሞች በማስተማር - ቢዚ የሆኑበት
ኩቱቦች በመፃፍ - ያስጠንቀቁበት።💥
💥የኢርቢሉ ንጉስ - በቅርብ የጀመረው
ጉድፍ የተመላ - መውሊድ ቢድዓ ነው።💥
💥ቢድዓ እንደሆነ - ሁሉም ተስማምተዋል
ሀሰና ሰይዓ - ብለው መድበዋል።💥
💥ሙስሊሙ ኡማ ሆይ - ስማኝማ ወገን
ማጣመምህ ለምን - ነብዩ ያሉትን።💥
💥ቢድዓ ሁሉ ጥመት - ጥመት ወደ እሳት
ገልፀዋል ረሱል - በሀዲሱ መልክት።💥
💥ሀሰና የለውም - ቢድዓ ጥመት ነው
ዛሬ ካልባነንን - መች ነው ምንነቃው።💥
💥ነብዩ አላሉም - ሰይዓ ሀሰና
ቢድዓን ትታቹ - ግቡ ወደ ሱና
ግድ የለሽ አንሁን - ቁንጣሪ መና
ህይወትን እንምራ - በሰለፎች ፋና።💥
💥መውሊድ ይከበራል - ኢድ ነው ብለህ ካልከኝ
መረጃህን አምጣ - በከንቱ አታድክመኝ።💥
💥የታል ያከባበሩ ዝርዝር - ከመረጃ ሰነድ
ዶሮ ወይስ በሬ - ሚሰዋው ለመውሊድ
የታል የኢድ ሰላት - ለመውሊድ ሚሰገድ
በል ንገረኝ አሁን - ሁሉን አንድ በአንድ
በጉንጭ አልፋ ሙግት - ሰዓታችን አይሒድ።💥
💥መረጃ ካጠረህ - መውሊድ ለምትለው
አንቺ ወሃብያ ን - ታዲያ ምን አመጣው።💥
💥መውሊድ ካላወጣሽ - ነብዩን አትወጂም
እያልክ አትወርፈኝ - ፈራጅ አይደለህም
ፈጠራ ሰርቼ - ሙብተዲዕ አልሆንም።💥
💥ከልብ ለመውደዴ - ማስረዳት አያሻኝ
በዲን ላይ ቢድዓ - ሳልጨምር እንዳሻኝ
ደሊል ተደግፌ - ኢባዳ ሰራሁኝ
ያለማንገራገር - ሱናን ተከተልኩኝ
ነቢን ለመውደዴ - ምላሽ እንዲሆነኝ።💥
💥እንዲያውም ልንገርህ - መውሊድ ብሎ ማለት
በመሰደቅ ሽፍን - ሚስኪን ሚልጡበት
የፍየሏ ቅጠል - ለጉድ ሚበላበት
ሰለዋት ተብሎ - የሚጨፈርበት
እንዘክር እያሉ - ድቤ ሚመቱበት
ወንድ ከሴት የማይለይ - ኢኽቲላጥ ያለበት
ስሜት በመከተል - ዘና የሚሉበት
መውሊድ ብሎ ማለት - ፈሳድ የሞላበት
የቢድዓ አውራ - ሚሸነግሉበት።💥
💥ለተራበ ሚስኪን - ሰደቃ ለማውጣት
ዚክር ለመዘከር - ለማውረድ ሰለዋት
ምን የሚሉት ፈሊጥ - መከፋፈል ቀናት
ያልተሰራ ኢባዳ - ካመት እስከአመት
ቀዳ ነው ሚወጣው❓በመውሊዱ ዕለት❓።💥
💥በዲን በሸሪዓ - በማይታወቅ ውል
ጥፋትን በላይህ - ከምታግተለትል
በምላስህ ብቻ - ወደድኩኝ ከምትል
ሱሪህን አሳጥር - አሳድግ ፂምህን
ፀጉር አታበላልጥ - ተወው መንዙማህን
የነብዩ ሱና - መገለጫህ ይሁን።💥
💥አንቺም የነቢ ወዳጅ - ተናፋቂ እንስቷ
ከመዝለልሽ በፊት - በነሺዳ እሩምታ።💥
💥ከወንዶች ራቂ - ቅልቅሉን ትተሽ
እንኳን ልታዜሚ - አይሰማ ድምፅሽ
በኒቃብ ተዋቢ - ሜካፑ ይቅርብሽ።💥
💥ባጢል ከነገሰበት - ከፈሳዱ መድረክ
ሰተር በይ እቤትሽ - ክብርሽ አይፍረክረክ።💥
💥ሒጃቡን ልበሺ - ይሸፈን ውበትሽ
ከቀልብ በሽተኛ - ይሁን መጠበቂያሽ።💥
💥ረሱልን እንደወደዱ - እንደ ሰሀብያት
ቤትሽ ይስፋሽ ላንቺ - ደጅ ላይ ከመውጣት።💥
💥ከሰለፉነ ሷሊህ - ተቀድቶ አቂዳቹ
ከሰለፍዮች ጋር - ከተደመራቹ
ከአህባሹ መንጋ - ከጥመት ወታቹ
ሱናውን ስትሰሩ - ቢድዓ ትታቹ
ወደድን ስትሉ - አሁን አመናቹ።💥
💥በጣም ያስደንቃል - መጣረሱ ወቅቱ
ቋሚ ጊዜ - የለው በየሀገራቱ
ቅጥ አምባር የጠፋው - የቃጥባር አብሬቱ
የሚወጣው መውሊድ - አይነቱ ብዛቱ።💥
💥ኧረ ምኑ ቅጡ - አያልቅም ቢወራ
ክፍተቱ ማየሉ - የመውሊድ ፈጠራ።💥
💥ፊታቸው ገርጥቶ - አይናቸው እስኪያብጥ
ነብዩን ያስቆጣ - ሚንበሩ እስኪናጥ።💥
💥በእርሳቸው ዘመን - ባልተከሰተበት
ዑማው እንዲርቀው - ቆመው ያስተማሩት
ለቢድዓ እኮ ነው - የተንዘፈዘፉት።💥
💥አዲስ ምናመጣው - ምኑ ተያዘና
ስሩ የተባለውን - መቼ ጨረስንና።💥
💥ሰው ሰራሽ የሆነ - አዳዲስ ፈጠራ
አንድ አያደርገንም - ማንም ቢያወራ።💥
💥ቢድዓ እስከሆነ - የ'ውነት ይለየናል
ሱናውን እንያዝ - አንድነት ይመጣል።💥
https://t.me/joinchat/Z9p634m9BQJmOWY0
💥የረሱልም ሆነ - የመሲሁ ኢሳ
ልደት ሚባል የለም - ከሸሪዓ ማሳ።💥
💥ኡለሞች በማስተማር - ቢዚ የሆኑበት
ኩቱቦች በመፃፍ - ያስጠንቀቁበት።💥
💥የኢርቢሉ ንጉስ - በቅርብ የጀመረው
ጉድፍ የተመላ - መውሊድ ቢድዓ ነው።💥
💥ቢድዓ እንደሆነ - ሁሉም ተስማምተዋል
ሀሰና ሰይዓ - ብለው መድበዋል።💥
💥ሙስሊሙ ኡማ ሆይ - ስማኝማ ወገን
ማጣመምህ ለምን - ነብዩ ያሉትን።💥
💥ቢድዓ ሁሉ ጥመት - ጥመት ወደ እሳት
ገልፀዋል ረሱል - በሀዲሱ መልክት።💥
💥ሀሰና የለውም - ቢድዓ ጥመት ነው
ዛሬ ካልባነንን - መች ነው ምንነቃው።💥
💥ነብዩ አላሉም - ሰይዓ ሀሰና
ቢድዓን ትታቹ - ግቡ ወደ ሱና
ግድ የለሽ አንሁን - ቁንጣሪ መና
ህይወትን እንምራ - በሰለፎች ፋና።💥
💥መውሊድ ይከበራል - ኢድ ነው ብለህ ካልከኝ
መረጃህን አምጣ - በከንቱ አታድክመኝ።💥
💥የታል ያከባበሩ ዝርዝር - ከመረጃ ሰነድ
ዶሮ ወይስ በሬ - ሚሰዋው ለመውሊድ
የታል የኢድ ሰላት - ለመውሊድ ሚሰገድ
በል ንገረኝ አሁን - ሁሉን አንድ በአንድ
በጉንጭ አልፋ ሙግት - ሰዓታችን አይሒድ።💥
💥መረጃ ካጠረህ - መውሊድ ለምትለው
አንቺ ወሃብያ ን - ታዲያ ምን አመጣው።💥
💥መውሊድ ካላወጣሽ - ነብዩን አትወጂም
እያልክ አትወርፈኝ - ፈራጅ አይደለህም
ፈጠራ ሰርቼ - ሙብተዲዕ አልሆንም።💥
💥ከልብ ለመውደዴ - ማስረዳት አያሻኝ
በዲን ላይ ቢድዓ - ሳልጨምር እንዳሻኝ
ደሊል ተደግፌ - ኢባዳ ሰራሁኝ
ያለማንገራገር - ሱናን ተከተልኩኝ
ነቢን ለመውደዴ - ምላሽ እንዲሆነኝ።💥
💥እንዲያውም ልንገርህ - መውሊድ ብሎ ማለት
በመሰደቅ ሽፍን - ሚስኪን ሚልጡበት
የፍየሏ ቅጠል - ለጉድ ሚበላበት
ሰለዋት ተብሎ - የሚጨፈርበት
እንዘክር እያሉ - ድቤ ሚመቱበት
ወንድ ከሴት የማይለይ - ኢኽቲላጥ ያለበት
ስሜት በመከተል - ዘና የሚሉበት
መውሊድ ብሎ ማለት - ፈሳድ የሞላበት
የቢድዓ አውራ - ሚሸነግሉበት።💥
💥ለተራበ ሚስኪን - ሰደቃ ለማውጣት
ዚክር ለመዘከር - ለማውረድ ሰለዋት
ምን የሚሉት ፈሊጥ - መከፋፈል ቀናት
ያልተሰራ ኢባዳ - ካመት እስከአመት
ቀዳ ነው ሚወጣው❓በመውሊዱ ዕለት❓።💥
💥በዲን በሸሪዓ - በማይታወቅ ውል
ጥፋትን በላይህ - ከምታግተለትል
በምላስህ ብቻ - ወደድኩኝ ከምትል
ሱሪህን አሳጥር - አሳድግ ፂምህን
ፀጉር አታበላልጥ - ተወው መንዙማህን
የነብዩ ሱና - መገለጫህ ይሁን።💥
💥አንቺም የነቢ ወዳጅ - ተናፋቂ እንስቷ
ከመዝለልሽ በፊት - በነሺዳ እሩምታ።💥
💥ከወንዶች ራቂ - ቅልቅሉን ትተሽ
እንኳን ልታዜሚ - አይሰማ ድምፅሽ
በኒቃብ ተዋቢ - ሜካፑ ይቅርብሽ።💥
💥ባጢል ከነገሰበት - ከፈሳዱ መድረክ
ሰተር በይ እቤትሽ - ክብርሽ አይፍረክረክ።💥
💥ሒጃቡን ልበሺ - ይሸፈን ውበትሽ
ከቀልብ በሽተኛ - ይሁን መጠበቂያሽ።💥
💥ረሱልን እንደወደዱ - እንደ ሰሀብያት
ቤትሽ ይስፋሽ ላንቺ - ደጅ ላይ ከመውጣት።💥
💥ከሰለፉነ ሷሊህ - ተቀድቶ አቂዳቹ
ከሰለፍዮች ጋር - ከተደመራቹ
ከአህባሹ መንጋ - ከጥመት ወታቹ
ሱናውን ስትሰሩ - ቢድዓ ትታቹ
ወደድን ስትሉ - አሁን አመናቹ።💥
💥በጣም ያስደንቃል - መጣረሱ ወቅቱ
ቋሚ ጊዜ - የለው በየሀገራቱ
ቅጥ አምባር የጠፋው - የቃጥባር አብሬቱ
የሚወጣው መውሊድ - አይነቱ ብዛቱ።💥
💥ኧረ ምኑ ቅጡ - አያልቅም ቢወራ
ክፍተቱ ማየሉ - የመውሊድ ፈጠራ።💥
💥ፊታቸው ገርጥቶ - አይናቸው እስኪያብጥ
ነብዩን ያስቆጣ - ሚንበሩ እስኪናጥ።💥
💥በእርሳቸው ዘመን - ባልተከሰተበት
ዑማው እንዲርቀው - ቆመው ያስተማሩት
ለቢድዓ እኮ ነው - የተንዘፈዘፉት።💥
💥አዲስ ምናመጣው - ምኑ ተያዘና
ስሩ የተባለውን - መቼ ጨረስንና።💥
💥ሰው ሰራሽ የሆነ - አዳዲስ ፈጠራ
አንድ አያደርገንም - ማንም ቢያወራ።💥
💥ቢድዓ እስከሆነ - የ'ውነት ይለየናል
ሱናውን እንያዝ - አንድነት ይመጣል።💥
https://t.me/joinchat/Z9p634m9BQJmOWY0