Репост из: [ኢብን ሽፋ - Ibn Shifa]
የተውሒዷን ሀገር ሳዑዲን በተለያየ መንገድ የማጠልሸት ሴራ
—————ክፍል 2
አይ ሳዑዲ!
ጠላቶቿ መዘርዘር የሚችሉት ጥቂት ኃጢያቶቿን ቁጭ ብለው ይለቃቅማሉ፣ እኛ ደግሞ ሌተ ከቀን መልካም ስራ በመስራት ደፋ ቀና እያለች መልካም ስራዋን አብዝታ ቆጥረን ልንዘልቀው አልቻልንም!!
ስለ እነዚያ በኢስላም ስም ስለሚነግዱ ነጋዲዎች ንገሩኝ እስኪ? ቁጭ ብለው የሙስሊሙን ደካማ ጎን ጠብቀው ከማስተጋባት በስሜት እንዲጋልብ ከማድረግ የዘልለለ ለእስልምና ምን ውለታ ነው የዋሉት??
ንጉሶቿ ከየትኛውም ፖለቲካ እችላለሁ ከሚሉ የአለማችን ፖለቲከኞችና የሀገር መሪዎች የላቀ የፖለቲካ ብቃት ያላቸው ንጉሶች ናቸው!። ይህን የፖለቲካ ብስለትና ብቃትም እንደ ሀገራቸውና እንደመላው የአለም ሙስሊም ሀገራት ነባራዊ ሁኔታ ጋር በማነፃፀር የላቀ ጥቅም በሚያስገኝ መልኩና ጉዳትን በሚከላከል መልኩ በአግባቡ ይጠቀሙበታል!። የማንም በዲኑ ስም የሚነግድ የፖለቲካ ነጋዴ ጩሀት ያለ አቅጣጫ እንዲሄዱ አያደርጋቸውም!።
አንዳንድ ሰዎች ለሳዑዲና ለንጉሶቿ ያለቸው ጥላቻ፣ አንዳንዴ የሚከሰቱ ኃጢያቶቿ እነሱ እንዲኖሩባቸው ከሚመኙዋቸው ከባባድ ወንጀሎች ህጋዊ ሆነው ከተስፋፉባቸው፣ ሺርክና ሰዶማዊናት በግልፅ በመንግስት ደረጃ ፈቃድ አግኝተው ከተንሰራፉባቸው ሀገራት አንፃር እሩብ ያህል እንኳን ሀገሪቷ ላይ ኃጢያት ተንሰራፍቶ አይደለም!!
የሚደንቀው ሁል ጊዜ አል-ኢኽዋን አል-ሙስሊሚን ሳዑዲን ለማጠልሸት የሚጥሩበትን መንገድ እንደየ ቦታው መለያየታቸው (መቀያየራቸው) ነው።
- ሸሪዓን ለሚወደውና ለሚደግፈው ለሙስሊሙ የህብረተሰብ ክፍል ልክ ለዲኑ እንደተቆረቆረ "ሳዑዲ ሸሪዓን ጥሳ እንዲህ አደረገች፣ እንዲህ አደረገች፣ በቃ እኮ አሁንማ ተበላሸች፣ አለቀላት፣ በአውሮፓዎች ቀኝ አገዛዝ ወደቀች…ወዘተ" እያሉ ያታልሉታል።
- አውሮፓዎች ጋር ሲሄዱ ደግሞ "ሳዑዲ አንባገነን ናት፣ ዲሞክራሲን አታከብርም፣ ሴቶችን አፍናለች፣ በነፃነት መናገር የለም…" የመሳሰሉትን እያሉ ሳዑዲ ላይ ያነሳሱዋቸዋል። ሁልጊዜም ትግላቸው ሳዑዲን እንደ ቱኒዚያ፣ሶሪያ፣ግብፅና ሊቢያ… ለማውደም ነው። እኔን ይበልጥ የሚገርመኝ ደግሞ እዚሁ ቁጭ ብሎ ሙስሊሙ ማህበረሰብ ሳዑዲን እንዲጠላ የሚያራግቡ የነ ሰልማነል አውዳ ቡችሎች ናቸው!።
በውስጧ ያሉት ኢኽዋኖች ለሳዑዲ ባላቸው ጥላቻ ከውጮች አይሻሉም፣ ውጪ ያሉት ከውስጦች አይሻሉም፣ ሆኖም ግን አላህ በረህመቱ ከሺዓም፣ ከአይሁድም፣ ከኢኽዋንም፣ ተንኮልና ሴራ ጠብቋታል!። ኢንሻአላህ ወደፊትም ይጠብቃታል!!።
አመራሮች ላይ ችግሮች የሉም ፍፁም ናቸው ማለቴ እንዳልሆነ ይሰመርበት!፣ ነገር ግን እንደ ኢስላም ሙስሊሙ ህብረተሰብ መሪውን ሲሳሳት በዓሊሞቹ መምከር ማስመከር ነው እንጂ፣ እየተቹ ከተቻለ ለጠላት አሳልፎ መስጠት፣ ይህ ካልተሳካም የእርስበርስ ጦርነት ቀስቅሶ የሙስሊሙን ደም ማፋሰስና ሸሪዓዊ ነገሮች እንዲወድሙ ማድረግ የዘመናዊ ኸዋሪጆች የኢኽዋኖች ልዩ መገለጫ እንጂ ፈፅሞ ሸሪዓው ያስቀመጠው የሙስሊሞች ስርኣት አይደለም!።
እኔ ሙስሊሙን ህብረተሰብ አደራ የምለው ነገር ቢኖር፣ የተውሒዷን ሀገር ሳዑዲንና ዓሊሞቿን አላህ እንዲጠብቅ፣ መሪዎቿን ሲሳሳቱ አላህ እንዲያስተካክላቸው ከልብ ዱዓ እንዲያደርግ ነው።
✍🏻 ኢብን ሽፋ (t.me/ibnshifa)
#join ⤵️ ቴሌግራም ቻናል
https://telegram.me/IbnShifa