የዙል ሂጃ ትሩፋቶች
የአላህ መልዕክተኛ ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለምእንዲህ ብለዋል : " ምንም ቀን የለም መልካም ስራ በእነርሱ ውስጥ በላጭ አላህ ዘንድ የሆነበት ከእነዚህ አስሩ ቀኖች ውጪ " በኣላህ መንገድ ላይ ጂሀድ ማድረግም ቢሆን ያ ረሱሉላህ ተብለው ተጠይቀው " በአላህ መንገድም ላይ ጂሀድ ማድረግም ቢሆን ምናልባት ሰውየው በህይወቱና በገንዘቡ ወጥቶ በዛው ከቀረ እንጂ "
ዘጠኙን ቀን መፆም በተመለከተ እናታችን ሀፍሳ ባወራችው ሀዲስ ነብዩ መፆማቸውን ሰትገልፅ ዓኢሻ ደሞ ፆመው አያውቁም ትላለች
አንዳንድ የዲን ሊቃውቶች የሀፍሳ ሀዲስ እንከን አለበት ሲሉ ሌሎች ደግሞ ሁለቱንም ሶሂህ ናቸው ብለአው ለማሰማማት ሞክረዋል
ሁሉም የሚስማሙት ፆም መልካም ስራ በሚለው ይገባል በሚለው ነው
ኢብኑ ባዝ አላህ ይዘንላቸውና ዘጠኙን ቀን መፆም ቢዳዓ ነው የሚል አለ ይህ እንዴት ይታያል ተብለው ተጠይቀው መልስ ሲሰጡ እንዲህ የሚል ጃሂል ነው ማስተማር ያስፈልጋል ብለዋል
በእነዚህ ቀናቶች ከሚወደዱ ስራዎች በጢቂቱ
ፀደቃ ማብዛት
ዝክር ማብዛት
ዚያራ ማብዛት
ዳዕዋ ማብዛት
በመልካም ማዘዝ ከመጥፎ መከልከል
ዝምድና መቀጠል
የተጣላን ማስታረቅ
ስጦታ መሰጣጠት
አና የመሳሰሉት ይገኝበታል
ማሳሰብያ
የዘጠነኛውን ቀን መፆም በተመለከተ የአላህ መልእክተኛ " አላህ ዘንድ ያለፈውን አመትና የሚመጣውን አመት ወንጀል ያስምርልኛል ብዬ ተስፋአደርጋለሁ " ብለዋል
https://telegram.me/bahruteka