Ali Dawah


Гео и язык канала: не указан, не указан
Категория: не указана


ስለ ኢስላም ጥያቄ አለዎ? ይጠይቁኝ!
Waa'ee Islaamaa gaaffii qabdaa? Na gaafadhaa!
Do you have a question about Islam? Ask Me!

Связанные каналы

Гео и язык канала
не указан, не указан
Категория
не указана
Статистика
Фильтр публикаций


እስቲ ቀለል ያለ ጥያቄ ልጠይቃቹ?

#የኡሥታዝ ወሒድ #ዐቃቢ_ኢሥላም ትምህርቶች ላመላክታችሁ!

በየትናው #ቋንቋ ይፈልጋሉ? ምረጡ እና #ትጠቀሙበታላችሁ።

⭕️ ትክክለኛው #ምርጫቹ ስትነኩ  ብቻ  የሚመጣውን
𝕒𝕕𝕕 በመጫን ቻናሎች ታገኛላችሁ 🛰
       👇👇👇


የቁርአን ሱራህ►⁶
አላህ ራሱ ነው ቁርአንን ከፋፍሎ ያወረደው፦

وَقُرْآنًا فَرَقْنَاهُ لِتَقْرَأَهُ عَلَى النَّاسِ عَلَىٰ مُكْثٍ وَنَزَّلْنَاهُ تَنزِيلًا

►📗[ሱረቱ አል-ኢስራእ 17፤106]
ቁርኣንንም በሰዎች ላይ በዝግታ ላይ ኾነህ ታነበው ዘንድ ከፋፈልነው፡፡ ቀስ በቀስ ማውረድንም አወረድነው፡፡

ቁርአን ሱራ እንዳለው አላህ በቁርአን ላይ ነግሮናል፦

سُورَةٌ أَنزَلْنَاهَا وَفَرَضْنَاهَا وَأَنزَلْنَا فِيهَا آيَاتٍ بَيِّنَاتٍ لَّعَلَّكُمْ تَذَكَّرُونَ

►📗[ሱረት አል-ኑር24፤1]
(ይህች) ያወረድናትና የደነገግናት ሱራ (ምዕራፍ) ናት፡፡ በእርሷም ውስጥ ትገሰፁ ዘንድ ግልጾችን አንቀጾች አውርደናል፡፡

ሱራህ ሦስት፦►ሱረቱል ዒምራን፦~عمران~ዒምራን
(ኢያቄም) የመርየም (ማርያም) አባት ስም ነው።

۞ إِنَّ اللَّهَ اصْطَفَىٰ آدَمَ وَنُوحًا وَآلَ إِبْرَاهِيمَ وَآلَ عِمْرَانَ عَلَى الْعَالَمِينَ

►📗[ሱረቱ አሊ-ዒምራን 3፤33]
አላህ አደምን፣ ኑሕንም፣ የኢብራሂምንም ቤተሰብ፣ የዒምራንንም ቤተሰብ በዓለማት ላይ መረጠ፡፡

ከላይ እንዳየነው አንቀጹ ላይ عِمْرَانَ ~ዒምራን የሚል ቃል አለ ስለዚህ ስሙ እዛው ሱረቱል ዒምራን ላይ አለ ማለት ነው።
ታዲያ ይህንን ስያሜ ነብያችንصلى الله عليه وسلم እና ሰሀቦች ተጠቅመውበታል?አው በሚገባ፦


أَبُو أُمَامَةَ، الْبَاهِلِيُّ قَالَ سَمِعْتُ رَسُولَ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم يَقُولُ ‏"‏ اقْرَءُوا الْقُرْآنَ فَإِنَّهُ يَأْتِي يَوْمَ الْقِيَامَةِ شَفِيعًا لأَصْحَابِهِ اقْرَءُوا الزَّهْرَاوَيْنِ الْبَقَرَةَ وَسُورَةَ آلِ عِمْرَانَ  ‏.‏
 
አቡ ኡማማ እንዲህ አለ፦የአላህ መልእክተኛصلى الله عليه وسلمእንዲህ ሲሉ   ሰምቻለሁ፦.......
ቁርኣንን አንብብ በትንሣኤ ቀን ለሚነበቡት አማላጅ ሆኖ ይመጣልና። ሁለቱን አል-ዛህራወይን [ብሩህ]  አንብብ አል-በቀራ እና ሱረቱ አል ኢምራን.........።

Abu Umama said he heard Allah's Messengerصلى الله عليه وسلم say: .......
Recite the Qur'an, for on the Day of Resurrection it will come as an intercessor for those who recite It. Recite the two bright ones, al-Baqara and Surah Al 'Imran,......

►📕[Sahih Muslim,Book 4,Hadith 1757]

ቁርኣን በዱኒያ ውስጥ በሚሰሩበት ባለቤቶቹ ላይ የትንሳኤ ቀን ይመጣል። ሱረቱል በቀራህ እና ሱረቱል አለ ዒምራን በፊቱ ይሆናሉ፦

عَنْ نَوَّاسِ بْنِ سَمْعَانَ، عَنِ النَّبِيِّ صلى الله عليه وسلم قَالَ ‏"‏ يَأْتِي الْقُرْآنُ وَأَهْلُهُ الَّذِينَ يَعْمَلُونَ بِهِ فِي الدُّنْيَا تَقْدُمُهُ سُورَةُ الْبَقَرَةِ وَآلُ عِمْرَانَ

ነዋስ ኢብኑ ሰምዓን እንደተረከው፦ ነቢዩ صلى الله عليه وسلم እንዲህ አሉ፦ ቁርኣን በዱኒያ ውስጥ በሚሰሩበት ባለቤቶቹ ላይ የትንሳኤ ቀን ይመጣል።ሱረቱል በቀራህ እና ሱረቱል አለ ዒምራን በፊቱ ይሆናሉ።

that the Prophetصلى الله عليه وسلم said: "The Qur'an shall come, and its people who acted according to it in the world. Surat Al-Baqarah and Al 'Imran shall be in front of it.

►📕[Jami` at-Tirmidhi Vol. 5, Book 42, Hadith 2883]

የአላህ ታላቅ ስም በሦስት ሱራዎች ውስጥ ይገኛል በበቀራህ በአለ-ዒምራን እና በጧሀ እናም አል-ዒምራን ፦

، عَنِ الْقَاسِمِ، قَالَ اسْمُ اللَّهِ الأَعْظَمُ الَّذِي إِذَا دُعِيَ بِهِ أَجَابَ فِي سُوَرٍ ثَلاَثٍ الْبَقَرَةِ وَآلِ عِمْرَانَ وَطَهَ ‏.‏

አል-ቃሲም እንደተረከው፦ "የአሏህ ታላቁ ስም በእርሱ በተማጸኑት ጊዜ የሚቀበልበት ነው ይህም በሦስት ሱራዎች በበቀራህ በአለ-ዒምራን እና በጧሀ ውስጥ ይገኛል"።

It was narrated that Al-Qasim said:
The Greatest Name of Allah, if He is called by which He will respond, is in three Surah: Al-Baqarah, Al 'Imran and Ta-Ha.

►📕[Sunan Ibn Majah,  Vol. 5, Book 34, Hadith 3856]

عَنْ حُذَيْفَةَ، قَالَ صَلَّيْتُ مَعَ النَّبِيِّ صلى الله عليه وسلم لَيْلَةً فَافْتَتَحَ الْبَقَرَةَ فَقُلْتُ يَرْكَعُ عِنْدَ الْمِائَةِ فَمَضَى فَقُلْتُ يَرْكَعُ عِنْدَ الْمِائَتَيْنِ فَمَضَى فَقُلْتُ يُصَلِّي بِهَا فِي رَكْعَةٍ فَمَضَى فَافْتَتَحَ النِّسَاءَ فَقَرَأَهَا ثُمَّ افْتَتَحَ آلَ عِمْرَانَ.........

ሑዘይፋህ እንዲህ አለ፡-
ከነብዩ صلى الله عليه وسلم ጋር በአንድ ሌሊት ሰገድኩኝ አል-በቀራህን ማንበብ ጀመረ እና "መቶ ሲደርስ ያጎነብሳሉ ብዬ አሰብኩ.እርሱ ግን ቀጠለ.‘ሙሉ ሱራውን በአንድ ረከዓ ሊያነብ ነው’ ብዬ አሰብኩ. እሱ ግን ቀጠለ. አን-ኒሳእ መቅራት ጀመረ እና (ሙሉውን ሱራ) አነበበ ከዚያም አል-ዒምራን ማንበብ ጀመረ......

►📕[Sunan an-Nasa'i  Vol. 2, Book 20, Hadith 1665]

እንግዲህ ነብያችንصلى الله عليه وسلم እና ሰሓቦች እንደሚጠቀሙበት አይተናል በጣም ብዙ ሐዲስ አለ ግን ገዜ አይበቃንም ነብያችንصلى الله عليه وسلم ሱረቱል ዒምራን ብለው ጠርተውታል ሰሓቦችም እንዲሁ እናም ታላቁ አምላካችን አላህም ሱረቱል ዒምራን ቁጥር 33ላይ آلَ عِمْرَانَ አል-ዒምራን የሚለውን ቃል አስቀምጦልናል እናም በተጨማሪም ይመልከቱ፦
►📕[Sahih al-Bukhari,  Vol. 2, Book 16, Hadith 106]
►📕[Sahih Muslim,  Book 4, Hadith 1759]
►📕[Sunan Abi Dawud,  Book 8, Hadith 1491]
►📕[Sunan Abi Dawud,Book 3, Hadith 1183]

ማጠቃለያ፦►
እንግዲህ ከላይ ጀምረን እንዳየነው
►አላህ ቁርአንን ከፋፍሎ እዳወረደ አይተናል።
►አላህ ቁርአን ሱራ እንዳለው ቁርአን ውስጥ እንደነገረን አይተናል።
►ነብያችንصلى الله عليه وسلمእና ሰሐቦች አል-ዒምራን ~آل عمران~ ብለው እንደተጠቀሙ ከጊዜ በኋላ እንዳልመጣ አይተናል።

سُورَةٌ أَنزَلْنَاهَا وَفَرَضْنَاهَا

►📗[ሱረት አል-ኑር24፤1]
(ይህች) ያወረድናትና የደነገግናት ሱራ (ምዕራፍ) ናት፡፡

ይቀጥላል..............

https://t.me/AliDawah2


የማርቆስ ወንጌል

የማርቆስ ወንጌል እና ስህተቶቹ

ስህተት አንድ፦►“እነሆ፥ መንገድህን የሚጠርግ መልክተኛዬን በፊትህ እልካለሁ የጌታን መንገድ አዘጋጁ ጥርጊያውንም አቅኑ እያለ በምድረ በዳ የሚጮኽ ሰው ድምፅ ተብሎ በነቢዩ በኢሳይያስ እንደ ተጻፈ፥”
  📖[ማርቆስ 1፥2-3]

►ቅሉ ግን ትንቢቱ ያለው ሚልኪያስ ላይ ነው፦“እነሆ፥ መልእክተኛዬን እልካለሁ፥ መንገድንም በፊቴ ያስተካክላል፤ እናንተም የምትፈልጉት ጌታ በድንገት ወደ መቅደሱ ይመጣል፤ የምትወዱትም የቃል ኪዳን መልእክተኛ፥ እነሆ፥ ይመጣል፥ ይላል የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር።”
  📖[ሚልክያስ 3፥1]

ማርቆስ ኬት አምጥቶ ነው ኢሳይያስ የሚለን ?መንፈስ ቅዱስ ነው ወይስ ማርቆስ የተሳሳው ?

ስህተት ሁለት፦►“እርሱም፦ ዳዊት ባስፈለገውና በተራበ ጊዜ፥ እርሱ አብረውት ከነበሩት ጋር ያደረገውን፥ አብያተር ሊቀ ካህናት በነበረ ጊዜ ወደ እግዚአብሔር ቤት እንደ ገባ፥”“ከካህናት በቀር መብላት ያልተፈቀደውን የመሥዋዕትን እንጀራ እንደ በላ፥ ከእርሱም ጋር ለነበሩት እንደ ሰጣቸው ከቶ አላነበባችሁምን? አላቸው።
  📖[ማርቆስ 2፥25/26]

ዳዊት ያልተፈቀደውን የመሥዋዕት እንጀራ በበላ ጊዜ ሊቀ ካህን የነበረ አብያታር ሳይሆን አቢሜሌክ ነበር፦
📖[1ኛ ሳሙኤል 21፥1/6]
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
¹ ዳዊትም ወደ ካህኑ ወደ አቢሜሌክ ወደ ኖብ መጣ፤ አቢሜሌክም እየተንቀጠቀጠ ዳዊትን ሊገናኘው መጣና፦ ስለ ምን አንተ ብቻህን ነህ? ከአንተስ ጋር ስለ ምን ማንም የለም? አለው።
² ዳዊትም ካህኑን አቢሜሌክን፦ የተላክህበትን ነገርና የሰጠሁህን ትእዛዝ ማንም አይወቅ ብሎ ንጉሡ አንድ ነገር አዝዞኛል፤ ስለዚህም ብላቴኖቹን እንዲህ ባለ ስፍራ ተውኋቸው።
³ አሁንስ በእጅህ ምን አለ? አምስት እንጀራ ወይም የተገኘውን በእጄ ስጠኝ አለው።
⁴ ካህኑም ለዳዊት መልሶ፦ ሁሉ የሚበላው እንጀራ የለኝም፥ ነገር ግን የተቀደስ እንጀራ አለ፤ ብላቴኖቹ ከሴቶቹ ንጹሐን እንደ ሆኑ መብላት ይቻላል አለው።
⁵ ዳዊትም ለካህኑ መልሶ፦ በእውነት ከወጣን ጀምረን እኛ ሰውነታችንን ከሴቶች ሦስት ቀን ጠብቀናል፤ የብላቴኖችም ዕቃ የተቀደሰች ናት፤ ስለዚህ ዛሬ ዕቃቸው የተቀደሰች በመሆንዋ እንጀራው እንደሚበላ እንጀራ ይሆናል አለው።
⁶ ካህኑም በእርሱ ፋንታ ትኩስ እንጀራ ይደረግ ዘንድ ከእግዚአብሔር ፊት ከተነሣው ከገጹ ኅብስት በቀር ሌላ እንጀራ አልነበረምና የተቀደሰውን እንጀራ ሰጠው።

አብያታር የአቢሊክ ልጅ ነው፦“ከአኪጦብም ልጅ ከአቢሜሌክ ልጆች ስሙ አብያታር የሚባል አንዱ ልጅ አምልጦ ወደ ዳዊት ሸሸ።”
►📖[1ኛ ሳሙኤል 22፥20]

ታዲያ ዳዊት ያልተፈቀደውን የመሥዋዕት እንጀራ በበላ ጊዜ ሊቀ ካህን የነበረ አብያታር ሳይሆን አቢሜሌክ ነበር ማርቆስ አብያታር የሚለው ከየት አምጥቶ ነው የተሳሳተው የማርቆስ ጸሐፊ ወይስ የጠቀሰው ኢየሱስ ወይስ መንፈስ ቅዱስ ?

ስህተት ሦስት ፦►“ሙሴ፦ አባትህንና እናትህን አክብር፤ ደግሞ፦ አባቱን ወይም እናቱን የሰደበ ፈጽሞ ይሙት ብሎአልና።”
  📖[ማርቆስ 7፥10]

ሙሴ ሳይሆን እግዚአብሔር ነው ያለው ፦

“አባቱን ወይም እናቱን የሚሰድብ ፈጽሞ ይገደል።”
  📖[ዘጸአት 21፥17]

ይህንን ስህተት ማቴዎስ አስተካክሎታል፦

“እግዚአብሔር፦ አባትህንና እናትህን አክብር፤ ደግሞ፦ አባቱን ወይም እናቱን የሰደበ ፈጽሞ ይሙት ብሎአልና፤”
  📖[ማቴዎስ 15፥4]

ማርቆስ ለምን እግዚአብሔር ያዘዘውን ሙሴ የሚለን?

ማቴዎስ አስታክሎታል

https://t.me/AliDawah2




https://vt.tiktok.com/ZSjwVrFms/
አዲስ ቪዲዮ ለቀናል


ይቀጥላል..
https://t.me/AliDawah2


የቁርአን ሱራህ►⁵
አላህ ራሱ ነው ቁርአንን ከፋፍሎ ያወረደው፦

وَقُرْآنًا فَرَقْنَاهُ لِتَقْرَأَهُ عَلَى النَّاسِ عَلَىٰ مُكْثٍ وَنَزَّلْنَاهُ تَنزِيلًا

►📗[ሱረቱ አል-ኢስራእ 17፤106]
ቁርኣንንም በሰዎች ላይ በዝግታ ላይ ኾነህ ታነበው ዘንድ ከፋፈልነው፡፡ ቀስ በቀስ ማውረድንም አወረድነው፡፡

ቁርአን ሱራ እንዳለው አላህ በቁርአን ላይ ነግሮናል፦

سُورَةٌ أَنزَلْنَاهَا وَفَرَضْنَاهَا وَأَنزَلْنَا فِيهَا آيَاتٍ بَيِّنَاتٍ لَّعَلَّكُمْ تَذَكَّرُونَ

►📗[ሱረት አል-ኑር24፤1]
(ይህች) ያወረድናትና የደነገግናት ሱራ (ምዕራፍ) ናት፡፡ በእርሷም ውስጥ ትገሰፁ ዘንድ ግልጾችን አንቀጾች አውርደናል፡፡

ሱራህ ሁለት፦► ሱረቱል በቀራህ፦~بقرة~
በቀራህ ማለት ጊደር (ላም)ማለት ነው።

قَالُوا ادْعُ لَنَا رَبَّكَ يُبَيِّن لَّنَا مَا هِيَ ۚ قَالَ إِنَّهُ يَقُولُ إِنَّهَا بَقَرَةٌ لَّا فَارِضٌ وَلَا بِكْرٌ عَوَانٌ بَيْنَ ذَٰلِكَ ۖ فَافْعَلُوا مَا تُؤْمَرُونَ

►📗[አል-በቀራህ 2፤68]
«ለኛ ጌታህን ጠይቅልን፤ እርሷ ምን እንደኾነች (ዕድሜዋን) ያብራራልን» አሉ፡፡ «እርሱ እርሷ ያላረጀች ጥጃም ያልኾነች በዚህ መካከል ልከኛ የኾነች ጊደር ናት ይላችኋል፤ የታዘዛችሁትንም ሥሩ» አላቸው፡፡

አንቀጹ ላይ بَقَرَةٌ  በቀራህ የሚል ቃል አለ ስለዚህ ስሙ እዛው ሱረቱል በቀራህ ላይ አለ ማለት ነው።
ታዲያ ይህንን ስያሜ ነብያችንصلى الله عليه وسلم እና ሰሀቦች ተጠቅመውበታል? አው በሚገባ፦

عَنْ أَبِي مَسْعُودٍ الْبَدْرِيِّ ـ رضى الله عنه ـ قَالَ قَالَ رَسُولُ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم ‏"‏ الآيَتَانِ مِنْ آخِرِ سُورَةِ الْبَقَرَةِ مَنْ قَرَأَهُمَا فِي لَيْلَةٍ كَفَتَاهُ ‏"‌‏.‏
 
አቡ መስዑድ አል-በድሪ እንደተረከው፡-
የአላህ መልእክተኛصلى الله عليه وسلم እንዲህ ብለዋል፦አንድ ሰው የመጨረሻዎቹን ሁለት የሱረቱ-አል-በቀራህ አንቀጾች በሌሊት ቢቀራ በቂ ነው።

Narrated Abu Masud Al-Badri:
Allah's Messenger صلى الله عليه وسلم said, "It is sufficient for one to recite the last two Verses of Surat-al-Baqara at night."

►📕[Sahih al-Bukhari: Vol. 5, Book 59, Hadith 345 ]

ሱረቱል በቀራህ ከሚቀራበት ቤት ሰይጣን ይሸሻል፦

عَنْ أَبِي هُرَيْرَةَ، أَنَّ رَسُولَ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم قَالَ ‏"‏ إِنَّ الشَّيْطَانَ يَنْفِرُ مِنَ الْبَيْتِ الَّذِي تُقْرَأُ فِيهِ سُورَةُ الْبَقَرَةِ ‏"‏ ‏.‏
 
አቡ ሁረይራ እንዳስተላለፉት የአላህ መልእክተኛصلى الله عليه وسلمእንዲህ ብለዋል፡- ሱረቱል በቀራህ ከሚቀራበት ቤት ሰይጣን ይሸሻል።

Abu Huraira reported Allah's Messenger صلى الله عليه وسلمas saying:
Satan runs away from the house in which Surah Baqara is recited.

►📕[Sahih Muslim,  Book 4, Hadith 1707]

، عَنْ عَائِشَةَ، قَالَتْ لَمَّا أُنْزِلَ الآيَاتُ مِنْ سُورَةِ الْبَقَرَةِ فِي الرِّبَا، خَرَجَ النَّبِيُّ صلى الله عليه وسلم إِلَى الْمَسْجِدِ، فَقَرَأَهُنَّ عَلَى النَّاسِ، ثُمَّ حَرَّمَ تِجَارَةَ الْخَمْرِ‏.‏"

  አኢሻህ እንደተረከችው፦ስለ አራጣ፣ሪባ የሱረቱ አል-በቀራህ አንቀጽ በወረደ ጊዜ፦
ነብዩصلى الله عليه وسلم ወደ መስጊድ ወጡና በሰዎች ላይ ቀሩላቸው ከዚያም ከለከሏቸው።

Narrated `Aisha:
When the verses of Surat "Al-Baqara"' about the usury Riba were revealed, the Prophetصلى الله عليه وسلم went to the mosque and recited them in front of the people and then banned the trade of alcohol.

►📕[Sahih al-Bukhari, 459 Vol. 1, Book 8, Hadith 449]

عَنْ أَبِي مَسْعُودٍ الأَنْصَارِيِّ، قَالَ قَالَ النَّبِيُّ صلى الله عليه وسلم ‏ “‏ الآيَتَانِ مِنْ آخِرِ سُورَةِ الْبَقَرَةِ مَنْ قَرَأَ بِهِمَا فِي لَيْلَةٍ كَفَتَاهُ ‏

አቢ መስዑድ አል-አንሷሪ እንደተረከው፦ ነቢዩምصلى الله عليه وسلمእንዲህ አሉ፦ በሌሊት ከሱረቱል በቀራህ ከመጨረሻው ሁለት አንቅጽ ከቀራ በቂው ነው።

The Prophetصلى الله عليه وسلمsaid, "If one recites the last two verses of Surat al-Baqarah at night, it is sufficient for him (for that night).

►📕[Sahih al-Bukhari, Vol. 6, Book 61, Hadith 560]

እንግዲህ ነብያችን صلى الله عليه وسلم እና ሰሓቦች سُورَةِ الْبَقَرَةِ  ሱረቱ አል-በቀራህ እያሉ እንደሚጠቀሙበት አይተናል በጣም ብዙ ሐዲስ ማምጣት ይቻላል ግን ግዜ አይበቃንም ነብያችንصلى الله عليه وسلم ሱረቱል በቀራህ ብለው ጠርተውታል ሰሓቦችም እንዲሁ  ታላቁ አምላካችን አላህም ሱረቱል በቀራህ ቁጥር 68ላይ በቀራህ የሚለውን ቃል አስቀምጦልናል እናም በተጨማሪም ይመልከቱ፦

►📕[Sahih al-Bukhari,Vol. 3, Book 34, Hadith 297]
►📕[Sahih al-Bukhari, Vol. 6, Book 61, Hadith 571]
►📕[Sahih Muslim, : Book 4, Hadith 1576]
►📕[Sahih Muslim,  Book 4, Hadith 1759]
►📕[Sunan an-Nasa'i,  Vol. 1, Book 10, Hadith 836]
►📕[Sunan Abi Dawud,  Book 3, Hadith 872 ]

ብዙ መጥቀስ ይቻላል ግን ግዜ አይበቃንም ከላይ ያለሁትን ሐዲሳት እንደሚያስረዱን ነብያችንصلى الله عليه وسلم እና ሰሓቦች ይጠቀሙበት እንደነበር ነው።

ማጠቃለያ፦►
እንግዲህ ከላይ ጀምረን እንዳየነው
►አላህ ቁርአንን ከፋፍሎ እዳወረደ አይተናል
►አላህ ቁርአን ሱራ እንዳለው ቁርአን ውስጥ እንደነገረን አይተናል
►ነብያችንصلى الله عليه وسلمእና ሰሐቦች አል-በቀራህ ~البقرة~ ብለው እንደተጠቀሙ ከጊዜ በኋላ እንዳልመጣ አይተናል።

سُورَةٌ أَنزَلْنَاهَا وَفَرَضْنَاهَا وَأَنزَلْنَا فِيهَا آيَاتٍ بَيِّنَاتٍ لَّعَلَّكُمْ تَذَكَّرُونَ

►📗[ሱረት አል-ኑር24፤1]
(ይህች) ያወረድናትና የደነገግናት ሱራ (ምዕራፍ) ናት፡፡ በእርሷም ውስጥ ትገሰፁ ዘንድ ግልጾችን አንቀጾች አውርደናል፡፡


ኢየሱስ አምላክ አይደለም በቲክቶክ መንደር አዲስ ቪዲዮ ለቀናል🧶

https://vm.tiktok.com/ZMke2Tv1A/


ሁላችሁም ጅይን በሉ ትጠቀሙበታላችሁ

https://t.me/My_Lord_is_with_me


ቁርአን ወደ ስኬትና ደስታ ይጠራሃል
እንዲሁም ጠንካራ ፣ አዛኝና ጥበበኛ ፣
በሱ ላይ ያለበትና ለሱ የሆነውን ነገር አውቆ
የሚኖር ሰው ሆነህ እንድትኖር ይጠራሃል
ከአንቀጾቹ አትራቅ


እንቀጥል ታዲያ ኢየሱስ ለምን ቃል ተባለ ለሚለው እዛው ባይብል ላይ እንዲህ እናገኛለን

📖ኢሳይያስ 42
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
¹ እነሆ ደግፌ የያዝሁት ባሪያዬ፤ ነፍሴ ደስ የተሰኘችበት ምርጤ፤ በእርሱ ላይ መንፈሴን አድርጌአለሁ፥ እርሱም ለአሕዛብ ፍርድን ያወጣል።
² አይጮኽም ቃሉንም አያነሣም፥ ድምፁንም በሜዳ አያሰማም።
³ የተቀጠቀጠን ሸምበቆ አይሰብርም፥ የሚጤስንም ክር አያጠፋም፤ በእውነት ፍርድን ያወጣል።
⁴ በምድርም ፍርድን እስኪያደርግ ድረስ ይበራል እንጂ አይጠፋም፤ አሕዛብም በስሙ ይታመናሉ።
⁵ ሰማያትን የፈጠረ የዘረጋቸውም፥ ምድርንና በውስጥዋ ያለውን ያጸና፥ በእርስዋ ላይ ለሚኖሩ ሕዝብ እስትንፋስን፥ ለሚሄዱባትም መንፈስን የሚሰጥ አምላክ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦
⁶-⁷ እኔ እግዚአብሔር በጽድቅ ጠርቼሃለሁ፥ እጅህንም እይዛለሁ እጠብቅህማለሁ፥ የዕውሩንም ዓይን ትከፍት ዘንድ የተጋዘውንም ከግዞት ቤት በጨለማም የተቀመጡትን ከወህኒ ቤት ታወጣ ዘንድ ለሕዝብ ቃል ኪዳን ለአሕዛብም ብርሃን አድርጌ እሰጥሃለሁ።
⁸ እኔ እግዚአብሔር ነኝ ስሜ ይህ ነው፤ ክብሬን ለሌላ፥ ምስጋናዬንም ለተቀረጹ ምስሎች አልሰጥም።
⁹ እነሆ፥ የቀድሞው ነገር ተፈጸመ፥ አዲስ ነገርንም እናገራለሁ፤ አስቀድሞም #ሳይበቅል እርሱን #አስታውቃችኋለሁ

ይሄ አንቀጽ ኢየሱስ ሳይወለድ ስለሱ የተነገረ ቃል ነው ለነብያት ኢየሱስ ወደፊት እንደሚወለድ እግዚአብሔር የተስፋ ቃል እደሰጣቸው ይነግረናል ቁጥር 9ላይ
፥ አዲስ ነገርንም እናገራለሁ፤ አስቀድሞም #ሳይበቅል እርሱን #አስታውቃችኋለሁ።ገና ሳይፈጠር ሳይበቅል እንደነገራቸው ግልጽ ነው በሌላም ቦታ፦

የምድር አሕዛብ ሁሉም በዘርህ ይባረካሉ፥ #ቃሌን ሰምተሃልና።”
📖 ዘፍጥረት 22፥18
እግዚአብሔር ለአብርሃም የተስፋቃል እንደነገረው ይነግረናል ኢየሱስ ቃል የተባለው ሳይወለድ በፊት በተስፋቃል ደረጃ ለነብያት ተነግሮ ስለነበረነው።
ኢየሱስ በተስፋ ቃል ለመኖሩ ማስረጃ ከባይብል፦ለአብርሃምና ለዘሩም የተስፋው ቃል ተነገረ። ስለ ብዙዎች እንደሚነገር፦ ለዘሮቹም አይልም፤ ስለ አንድ እንደሚነገር ግን፦ ለዘርህም ይላል፥ እርሱም ክርስቶስ።”
📖 ገላትያ 3፥16
እነዚህ ሁሉ አምነው ሞቱ፥ የተሰጣቸውን የተስፋ ቃል አላገኙምና፤ ዳሩ ግን ከሩቅ ሆነው አዩትና ተሳለሙት፥ በምድሪቱም እንግዶችና መጻተኞች እንዲሆኑ ታመኑ።”
📖 ዕብራውያን 11፥13
“ከዚህም ሰው ዘር እግዚአብሔር እንደ ተስፋው ቃል ለእስራኤል መድኃኒትን እርሱም ኢየሱስን አመጣ።”
📖 ሐዋርያት 13፥23

📖ሐዋርያት 13
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
³² እኛም ለአባቶች የተሰጠውን ተስፋ የምስራቹን ለእናንተ እንሰብካለን፤
³³ ይህን ተስፋ እግዚአብሔር በሁለተኛው መዝሙር ደግሞ፦ አንተ ልጄ ነህ እኔ ዛሬ ወለድሁህ ተብሎ እንደ ተጻፈ፥ ኢየሱስን አስነሥቶ ለእኛ ለልጆቻቸው ፈጽሞአልና።
“”

እነዚህ ሁሉ አናቅጽ ኢየሱስ በቃል ደረጃ ለመኖሩ ማስረጃ ናቸው።
ታዲያ ቃልም ስጋ ሆነ ማለት ምን ማለት ነው የሚለውን እንይ

ቃልም ሥጋ ሆነ፤ ጸጋንና እውነትንም ተመልቶ በእኛ አደረ፥ አንድ ልጅም ከአባቱ ዘንድ እንዳለው ክብር የሆነው ክብሩን አየን።”
📖 ዮሐንስ 1፥14
ቃልም ስጋ ሆነ ማለት ያ በተስፋ ቃል የነበረው አሁን ተወለደ ተፈጠረ ማለት ነው እንጂ የእግዘብሔር ቃል እራሱ ተለውጦ ስጋሆነ ማለት አደለም ለምሳሌ እንይ፦

📖1ኛ ዮሐንስ 1
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
¹ ስለ ሕይወት ቃል ከመጀመሪያው የነበረውንና የሰማነውን በዓይኖቻችንም ያየነውን የተመለከትነውንም እጆቻችንም የዳሰሱትን እናወራለን፤
² ሕይወትም ተገለጠ አይተንማል እንመሰክርማለን፥ ከአብ ዘንድ የነበረውንም ለእኛም የተገለጠውን የዘላለምን ሕይወት እናወራላችኋለን፤

እዚ አንቀጽ ላይ ከመጀመሪያ የነበረው ማለት ለነብያት መጀመሪያ የተነገረ የተስፋቃል ነበረ ማለት ነው።
ከአብ ዘንድ የነበረውንም ማለት መሲሁ እደሚመጣ የተነገረ ቃል በአብ ዘንድ ነበረ ማለት ነው ያተነግሮ የነበረው ቃል ተፈፀመ ማለት ነው።

ኢየሱስ የእግዚአብሔር ቃል አደለም። ምክኒያቱም፦ የተነገረ ቃል ስለሆነ ነው ቃል የተባለው እንጂ እሱ ራሱ ቃል አደለም መስረጃዬም ፦እርሱም ለእግዚአብሔር ቃልና ለኢየሱስ ክርስቶስ ምስክር ላየውም ሁሉ መሰከረ።”
📖 ራእይ 1፥2
እዚ አንቀጽ ላይ የእግዚአብሔር ቃልና ኢየሱስ የተለያዩ መሆናቸውን ቁልጭ አርጎ ያሳያል ምክኒያቱም እና ብሎ ለይቶታልና ።


ቃል ስጋ ሆነ ማለት ያለነብያት ተሰቶ የነበረው የተስፋ ቃል ስጋሆነ ማለት ነው ለምሳሌ፦

“ለኢዩ፦ ልጆችህ እስከ አራት ትውልድ ድረስ በእስራኤል ዙፋን ላይ ይቀመጣሉ ተብሎ የተነገረው የእግዚአብሔር ቃል ይህ ነበረ፤ እንዲሁም ሆነ።”
📖 2ኛ ነገሥት 15፥12
የእግዚአብሔር ቃል ሆነ ማለት የእግዚአብሔር ቃል ዙፋን ሆነ ማለት ሳይሆን የተነገረው ነገር ተፈፀመ ማለት ነው።

ኢየሱስ ሰው የሆነው በቃል ነው ኢየሱስ ሥጋ የሆነው በቃል ነው።

ቀን ቀጥሮአልና፥ በዚያም ቀን #ባዘጋጀው ሰው እጅ በዓለሙ ላይ በጽድቅ ሊፈርድ አለው፤ ስለዚህም እርሱን ከሙታን በማስነሣቱ ሁሉን አረጋግጦአል።”
📖 ሐዋርያት 17፥31

ስለዚህ ወደ ዓለም ሲገባ፦ መሥዋዕትንና መባን አልወደድህም ሥጋን ግን #አዘጋጀህልኝ፤”
📖 ዕብራውያን 10፥5

#አዘጋጀህልኝ #ማለት መፈጠሩን ያሳያል ኢየሱስ በቃል ነው ስጋ የተዘጋጀለት ተዘጋጀ ማለት ተፈጠረ ማለት ነው ለምሳሌ፦
ቀኑ የአንተ ነው ሌሊቱም የአንተ ነው፤ አንተ ፀሓዩንና ጨረቃውን #አዘጋጀህ።”
📖መዝሙር 74፥16
#አዘጋጀህ ማለት #ፈጠርክ ማለት ነው ብርሀን ይሁን አለ ሆነ ያዘጋጃቸው ደሞ በቃሉ ነው ኢየሱስም የተዘጋጀው በቃል ነው ማለት ነው።
ምክኒያቱም ፦ሁሉ በእርሱ ሆነ፥ ከሆነውም አንዳች ስንኳ ያለ እርሱ አልሆነም።”
📖 ዮሐንስ 1፥3
ሁሉ በቃል ከሆነ ኢየሱስ ደሞ ሥጋ የሆነው በቃል ነው ማለት ነው
አይ ቃሉ እራሱ ተለውጦ ሰው ሆነ ካልን ያቃል በምን ድነው ሰው የሆነው ምክኒያቱም ሁሉ በቃል ሆነስለሚል ።

📗(16:40)

إِنَّمَا قَوْلُنَا لِشَيْءٍ إِذَا أَرَدْنَاهُ أَن نَّقُولَ لَهُ كُن فَيَكُونُ

ለማንኛውም ነገር (መኾኑን) በሻነው ጊዜ ቃላችን ለእርሱ «ኹን» ማለት ብቻ ነው፤ ወዲውም ይኾናል፡፡

ምንጭ 1፦ 📖የ1954 እትም 📖1980 እትም ግሪክ እና ግእዝ
📗ቅዱስ ቁርአን

ሊኩን ከስር አለላቹ የሁሉም መጽሐፍት👇



ቀጥተኛው መንገድ #ኢስላም #ብቻ ነው ወገኖች ጥሪ አቀርብላቹዋለሁ ኑ ።🤲



https://t.me/AliDawah2


በመጀመሪያው ቃል ነበረ፥ ቃልም በእግዚአብሔር ዘንድ ነበረ፥ እግዚአብሔርም ቃል ነበረ።”
📖ዮሐንስ 1፥1
" εν αρχη ην ο λογος και ο λογος ην προς τον θεον και θεος ην ο λογος "
📕 (ΚΑΤΑ ΙΩΑΝΝΗΝ 1: 1)
📖የ1879እና ግእዙም እደዚነው ያስ ቀመጡት ግሪኩም
ግሪኩ ፦#και #θεος #ην #ο #λογος "
(kai theos in o #logos " )

እግዚአብሔር ቃል ነበረ ነው የሚለው
λογος (logos)ማለት ትርጉሙ ቃል ንግግር አመክኒዎ ማለት ነው። ለምሳሌ፦

ከደቀ መዛሙርቱም ብዙዎች በሰሙ ጊዜ፦ ይህ የሚያስጨንቅ #ንግግር ነው፤ ማን ሊሰማው ይችላል? አሉ።”
📖ዮሐንስ 6፥60
ግሪኩ ፦πολλοι ουν ακουσαντες εκ των μαθητων αυτου ειπον σκληρος εστιν ουτος ο #λογος τις δυναται αυτου ακουειν "
📕(ΚΑΤΑ ΙΩΑΝΝΗΝ 6: 60)
polloi oun akousantes ek ton mathiton aftou eipon skliros estin outos o #logos tis dynatai aftou akouein "
እዚህ አንቀጽ ላይ ንግግር ለሚለው የገባው ቃል (#λογος #logos)እንደሆነ አንባቢ ልብ ይለዋል
ፈጣሪ ከአፉየሚወጣው ቃል ሎጎስ ይባላል ለምሳሌ፦
#ከአፌ የሚወጣ #ቃሌ እንዲሁ ይሆናል፤ የምሻውን ያደርጋል የላክሁትንም ይፈጽማል እንጂ ወደ እኔ በከንቱ አይመለስም።”
📖ኢሳይያስ 55፥11
ስለዘህ የእግዚአብሔር #ቃል #ከአፉየሚወጣ #ቃል እንጂ አካል አበጅቶ እራሱን የቻለ አምላክ አደለም
እግዚአብሔርም፦ ብርሃን #ይሁን አለ፤ ብርሃንም #ሆነ።”
📖ዘፍጥረት 1፥3
እዚ አንቀጽላይ ብርሃን ይሁን ከማለቱ በፊት ብርሃን ሌላ ነገር ነበረ ማለት አንችልም ፈጣሪ ኹን በሚለው ቃሉ ነው
ሁሉን ነገር የፈጠረው እርሱ ተናግሮአልና፥ ሆኑም፤ እርሱ አዘዘ፥ ጸኑም።”📖መዝሙር 33፥9

እርሱ ብሎአልና፥ #ሆኑም፤ እርሱም አዝዞአልና፥ ተፈጠሩም፤ የእግዚአብሔርን ስም ያመስግኑት።”
📖መዝሙር 148፥5
እነዚህ አናቅጽ ላይ እዳየነው እግዚአብሔር ሁሉን ነገር የፈጠረው በቃሉ ነው ማለትነው።
ሁሉ #በእርሱ ሆነ፥ ከሆነውም አንዳች ስንኳ ያለ እርሱ አልሆነም።”
📖ዮሐንስ 1፥3
እንደምናየው እዛው አንቀጽ ቁጥር 3 ላይ ሁሉ ነገር በቃል እንደሆነ ይነግ ረናል ቃል የፈጣሪ ባህሪ መሆኑን ደሞ

እግዚአብሔርም ቃል ነበረ።”

“በምሥራቅ በኩል ወደ ሰማየ ሰማያት ለወጣ ለእግዚአብሔር ዘምሩ፤ የኃይል #ቃል የሆነ ቃሉን፥ እነሆ፥ ይሰጣል።”
📖መዝሙር 68፥33
እዚ አንቀጽ ላይ ደሞ እግዚአብሔር ቃል ነበረ ማለት እግዚአብሔር ተናጋሪ ነበረ ማለት እደሆነ በግልጽ አስቀምጧል
እግዚአብሔር ቃል ነበረ ማለት እግዚአብሔር ተናጋሪ ነበረ ማለት ነው። ለምሳሌ ፦
ከእርሱም የሰማናት ለእናንተም የምናወራላችሁ መልእክት፦ እግዚአብሔር #ብርሃን ነው ጨለማም በእርሱ ዘንድ ከቶ የለም የምትል ይህች ናት።” 📖1ኛ ዮሐንስ 1፥5
እግዚአብሔር ብርሃን ነው ማለት አብሪነው ማለት ነው ስለዚ እግዚአብሔር ቃል ነበረ ማለት እግዚአብሔር ተናጋሪ ነው ማለት ነው
ቃልም በእግዚአብሔር ዘንድ ነበር ማለት ደሞ ንግግር የሱ ባህሪነው ማለት ነው።
ለምሳሌ ፦
የጠለቀውንና የተሠወረውን ይገልጣል፤ በጨለማ ያለውን ያውቃል፥ ብርሃንም ከእርሱ #ጋር (ዘንድ) ነው።”
📖 ዳንኤል 2፥22
እዚ አንቀጽ ላይ ደሞ ብርሃን ከሱ ጋር (ዘንድ) ነው ማለት እራሱን የቻለ አካል ነው ማለት ሳይሆን አብሪነት የሱባህሪ ነው ማለት ነው ልክ እንደዚሁ ቃልም ከእግዚአብሔር ዘንድ ነበር ማለት ንግግር (ቃል) የእግዚአብሔር ባህሪ ነው ማለት ነው ሌላም ምሳሌ እንይ፦

📖መዝሙር 62
¹ ነፍሴ ለእግዚአብሔር የምትገዛ አይደለችምን? መድኃኒቴ ከእርሱ #ዘንድ ናትና።
² እርሱ አምላኬ #መድኃኒቴም #ነውና፤ እርሱ መጠጊያዬ ነው፥ እጅግም አልታወክም።

እንደምናየው ከሆነ አምላኬ መድሐኒቴ ነው ማለት መድሐኒት አምላክ ነው ማለት አደለም እግዚአብሔር አዳኝ ነው ማለት ነው ስለዚ እግዚአብሔር ቃል ነበረ ማለት
እግዚአብሔር ተናጋሪ ነበረ ማለት ነው ደሞ እዚው አንቀጽላይ መድኃኒቴ ከእርሱ #ዘንድ ነው ይላል መድሐኒት የሚባል ሌላ አካል እግዚአብሔር ዘንድ አለ ማለት ሳይሆን ማዳን የሱ ባህሪ ነው ማለት ነው
እደዚሁ ቃልም በእግዚአብሔር ዘንድ ነበረ ማለት መናገር የሱ ባህሪ ነው ማለት ነው።እደዚው አይነት አናቅጽ ብዙ አሉ

እግዚአብሔር ረዳቴ ነው፥ እኔም በጠላቶቼ ላይ አያለሁ።”
📖መዝሙር 118፥7

እግዚአብሔር ረዳቴነው ማለት ረጂዬ ነው ማለት ነው ።
እግዚአብሔር ቃል ነበረ ማለት ተናጋሪ ነበረ ማለት ነው።
“ረዳቴ ሰማይና ምድርን ከሠራ ከእግዚአብሔር ዘንድ ነው።”
📖መዝሙር 121፥2
ረዳቴ ከሱ ዘንድ ነው ማለት
ረጂነት የእግዚአብሔር ባህሪ ነው ማለት ነው።
ስለዚህ ቃልም በእግዚአብሔር ዘንድ ነበረ ማለት መናገር ወይም ንግግር የሱ ባህሪ ነው ማለት ነው።
“ኃይልና ጥበብ በእርሱ ዘንድ ናቸው የሚስተውና የሚያስተው ለእርሱ ናቸው።”
📖ኢዮብ 12፥16
ጥበብ ና ሐይል አካል አላቸው እንደማንለው ሁሉ ቃልም ባህሪ እንጂ
አካል ያለው ነገር አደለም።

“እግዚአብሔር ጥበብ ይሰጣልና፤ ከአፉም እውቀትና ማስተዋል ይወጣሉ፤”
📖 ምሳሌ 2፥6
ጥበብና ማስተዋል ከአፉ የሚወጡ ባህሪያት እጂ ራሳቸውን የቻሉ አካል አደለም።

ከአፉም ሕጉን ተቀበል፥ በልብህም ቃሉን አኑር፤”
📖 ኢዮብ 22፥22
የእግዚአብሔር ቃል ከአፉ የሚወጣ ነው።
“በእግዚአብሔር ዘንድ ጥበብና ኃይል አለ ለእርሱ ምክርና ማስተዋል አለው።”
📖 ኢዮብ 12፥13
ጥብና ሓይል የሱ ባህሪያት ናቸው ስለዚህ በዚህ መልኩ እንረዳዋለን ማለት ነው።
“ከአፌ የሚወጣ ቃሌ እንዲሁ ይሆናል፤ የምሻውን ያደርጋል የላክሁትንም ይፈጽማል እንጂ ወደ እኔ በከንቱ አይመለስም።”
📕 ኢሳይያስ 55፥11
“እግዚአብሔር በጥበብ ምድርን መሠረተ፥ በማስተዋልም ሰማያትን አጸና።”
📖 ምሳሌ 3፥19
ምድርን በኃይሉ የፈጠረ፥ ዓለሙን በጥበቡ የመሠረተ ሰማያትንም በማስተዋሉ የዘረጋ እርሱ ነው።”
📖 ኤርምያስ 10፥12
“ከማኅፀን የሠራህ፥ የሚቤዥህ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ ሁሉን የፈጠርሁ፥ ሰማያትን ለብቻዬ የዘረጋሁ ምድርንም ያጸናሁ እግዚአብሔር እኔ ነኝ ከእኔ ጋር ማን ነበረ?”
📖 ኢሳይያስ 44፥24
“የእግዚአብሔር ቃል ወደ እኔ እንዲህ ሲል መጣ፦” 📖ሕዝቅኤል 23፥1
የእግዚአብሔር ቃል ለነብያት ራእይ ሆኖ ይመጣል እንጂ እራሱን የቻለ አካል ያለው ነገር አደለም።

“ስለዚህ የእግዚአብሔር ቃል ከእግዚአብሔር ዘንድ ወደ ኤርምያስ እንዲህ ሲል መጣ፦”
📖 ኤርምያስ 34፥12
ዘንድ የሚለው አንዳንዴ ውስጥ በሚለው ይመጣል ለምሳሌ ፦

📖ኢዮብ 28
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
¹³ ሰው መንገድዋን አያውቅም በሕያዋን ምድር አትገኝም።
¹⁴ ቀላይ፦ በእኔ #ውስጥ የለችም ይላል፤ ባሕርም፦ በእኔ #ዘንድ የለችም ይላል።
እዚ አንቀጽ ላይ #ዘንድ የሚለው ውስጥ በሚል ይመጣል ዘንድ ማለት ውስጥ ማለት ነው።ለምሳሌ፦
“ከእንግዲህ ወዲያ ጣዖት ለኤፍሬም ምንድር ነው? እኔ ሰምቼዋለሁ፥ ወደ እርሱም እመለከታለሁ እኔ እንደ ለመለመ ጥድ ነኝ፤ ፍሬህ በእኔ ዘንድ ይገኛል።”
📖 ሆሴዕ 14፥8
እዚጋር እንደምናየው ዘንድማለት ውስጥ ማለት እደሆነ ግልጽ ነው ምክንያቱም አንድ ዛፍ ፍሬው ከሱ የተለየ አካል አደለም ከውስጡ የሚወጣ ነው።
👇


ቃል (#λογος =#logos)እና ኢየሱስ ፦

የመጽሐፉ ባለቤቶች ሆይ! በእኛና በእናንተ መካከል ትክክል ወደ ኾነች ቃል ኑ፡፡ (እርሷም) አላህን እንጅ ሌላን ላንገዛ፣ በርሱም ምንንም ላናጋራ፣ ከፊላችንም ከፊሉን ከአላህ ሌላ አማልክት አድርጎ ላይይዝ ነው፤ በላቸው፡፡ እምቢ ቢሉም፡- እኛ ሙስሊሞች መኾናችንን መስክሩ በሏቸው፡፡📗(3:64)


قُلْ هُوَ اللَّهُ أَحَدٌ

በል «እርሱ አላህ #አንድ ነው፡፡
📗(112:1)


قُلْ إِنَّمَا يُوحَىٰ إِلَيَّ أَنَّمَا إِلَٰهُكُمْ إِلَٰهٌ وَاحِدٌ ۖ فَهَلْ أَنتُم مُّسْلِمُونَ

«ያ ወደኔ የሚወረደው አምላካችሁ #አንድ አምላክ #ብቻ ነው ማለት ነው፤ ታዲያ እናንተ ፍጹም ታዛዦች ናችሁን» በላቸው፡፡
📗(21:108)

“እስራኤል ሆይ፥ ስማ፤ አምላካችን እግዚአብሔር #አንድ እግዚአብሔር ነው፤”
📖(ዘዳግም 6፥4)
“ኢየሱስም መልሶ እንዲህ አለው፦ ከትእዛዛቱ ሁሉ ፊተኛይቱ፦ እስራኤል ሆይ፥ ስማ፤ ጌታ አምላካችን #አንድ ጌታ ነው፥”
📖(ማርቆስ 12፥29)

“በስሜም የሚናገረውን ቃሌን የማይሰማውን ሰው እኔ እበቀልለታለሁ።”
📖( ዘዳግም 18፥19)


بِسْمِ اللَّهِ الرَّحْمَٰنِ الرَّحِيمِ

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ በጣም አዛኝ በኾነው፡፡📗(1:1)

ዩሐንስ 1:1 እውን ኢየሱስ አምላክ ነው ይላልን የሥላሴያውያን ቅዠት ሲጋ ለጥ
ቅዠት 1 ፦“በመጀመሪያው እግዚአብሔር ነበረ፥ እግዚአብሔርም በእግዚአብሔር ዘንድ ነበረ፥ እግዚአብሔርም እግዚአብሔር ነበረ😂።”
የነሱ የቅዠት አስተሳሰብ ይሄን ይመስላል ምን ማለት ነው ይሄን ህፃን ራሱ እንደዚ አይቃዠም ቅዠታቸው ይቀጥልና እግዚአብሔር ሥጋ ሆነ 😂

መልሱን ያንብቡ ፦📕


اقْرَأْ بِاسْمِ رَبِّكَ الَّذِي خَلَقَ

አንብብ በዚያ (ሁሉን) በፈጠረው ጌታህ ስም፡፡📗(96:1)
👇👇

John 1 (ግዕ) - ዮሐንስ
1: ቀዳሚሁ ቃል ውእቱ፡ ወውእቱ ቃል ኅበ እግዚአብሔር ውእቱ፡ ወእግዚአብሔር ውእቱ ቃል።


ቲክታክ ላይ አዲስ ቪዲዮ ለቀናል ግቡና እዩት Share Like Copy Link Comment ማድረግ እንዳትረሱ ኢንሻአላህ ይቀጥላል....

https://vm.tiktok.com/ZMhodVHgv/


ማሳያ ስምንት፦ለኢየሱስ ህይወት መሰጠቱ መፈጠሩን መናገሩ እና ሰዎች መናገራቸው፦
ዮሐንስ 5፥26 አብ በራሱ ሕይወት እንዳለው እንዲሁ ደግሞ ለወልድ በራሱ  ሕይወት እንዲኖረው ሰጥቶታልና።”
ዮሐንስ 6፥57 “ሕያው አብ እንደ ላከኝ እኔም ከአብ የተነሣ ሕያው እንደምሆን
ምሳሌ 8፥22 *እግዚአብሔር ከሁሉ በፊት ፈጠረኝ*፥ (1980 አዲስ ትርጉም)
Proverbs 8፥22 “The LORD made me as he began his planning, (International Standard Version)
ራእይ 3፥14 በእግዚአብሔርም ፍጥረት መጀመሪያ የነበረው እንዲህ ይላል፦”
 ቆላስይስ 1፥15 የፍጥረት ሁሉ በኵር ነው”*።
ኢሳይያስ 49፥5-6 ያዕቆብን ወደ እርሱ እንድመልስ እስራኤልንም ወደ እርሱ እንድሰበስብ ባሪያ እሆነው ዘንድ ከማኅፀን ጀምሮ *የሠራኝ* እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፡— እርሱም፡— የያዕቆብን ነገዶች እንድታስነሣ ከእስራኤልም የዳኑትን እንድትመልስ ባሪያዬ ትሆን ዘንድ እጅግ ቀላል ነገር ነውና እስከ ምድር ዳር ድረስ መድኃኒት ትሆን ዘንድ ለአሕዛብ ብርሃን አድርጌ ሰጥቼሃለሁ፥ ይላል።ሃይማኖተ-አበው ዘቄርሎስ 76:21 ይመልከቱ፦
ኤፌሶን 4፥24 “ለእውነትም በሚሆኑ ጽድቅና ቅድስና እንደ እግዚአብሔር ምሳሌ የተፈጠረውን አዲሱን ሰው ልበሱ።”
ኤፌሶን 2፥5“ከወደደን ከትልቅ ፍቅሩ የተነሣ በበደላችን ሙታን እንኳ በሆንን ጊዜ ከክርስቶስ ጋር ሕይወት ሰጠን፥ በጸጋ ድናችኋልና፥”

ኢየሱስ ህይወት ከተሰጠው ከተፈጠረ የፈጠረው ማነው ኢየሱስ የተፈጠረ ከሆነ ፈጣሪ ሊሆን አይችልም።

ማጠቃለያ

►እግዚአብሔር ሰው ካልሆነ ኢየሱስ ሰው ከሆነ ኢየሱስ ሰው ያልሆነውን እግዚአብሔር መሆን አይችልም።

►እግዚአብሔር የሰው ልጅ አይደለም ኢየሱስ ደግሞ የሰው(የማርያም)ልጅ ነው እግዚአብሔር የሰው ልጅ ካልሆነ ኢየሱስ የሰው ልጅ ያልሆነውን እግዚአብሔር ሊሆን አይችልም።

► ኢየሱስ አምላክ ላለመሆኑ በጣም ብዙ ማስረጃ መቅረብ ይቻላል ቅሉ ግን ትርፉ ማድከም ነው።

►ኢየሱስ የፈጣሪ ነብይ መልእክተኛ መሲህ እንጂ አምላክ አይደለም ክርስቲያኖች ሆይ ፍጡርን ከማምለክ ፈጣሪን ወደ ማምለክ እንድትመጡ የዘውትር ጸሎቴ ነው።

https://t.me/AliDawah2


ወልድ ኢየሱስ እግዚአብሔር ነውን?

እግዚአብሔር ወልድ
እግዚአብሔር ወልድ በግሪክ Θεός ὁ υἱός God the son ሲሆን ባይብል ላይ ይህ አጠራር በፍጹም የለም ነገር ግን በ 325 AD በኒቂያ ጉባኤ ለኢየሱስ የተሰጠ  ነው፣ ባይብል ላይ እግዚአብሔር አብ በግሪክ Θεός ὁ Πατρὶ God the father የሚል እንዳለ እላይ ተመልክተናል ለማስታወስ ያክል" 2ኛ ጢሞቴዎስ 1፥2 ቲቶ 1፥4 1ኛ ጴጥሮስ 1፥2 2ኛ የዮሐንስ 1፥3 ያዕቆብ 1፥27 ይሁዳ 1፥1 ተ
ይመልከቱ።
ኢየሱስ እግዚአብሔር እንዳልሆነ ባይብል ቁልጭና ፍትው አድርጎ ይነግረናል፦
ማሳያ አንድ፦ እግዚአብሔር ሰው አይደለም ኢየሱስ ሰው ነው፦
ዘኍልቁ 23፥19 እግዚአብሔር ሰው አይደለም።
“ሆሴዕ 11፥9 እኔ አምላክ ነኝ እንጂ ሰው አይደለሁምና።
በተቃራኒው ደግሞ ኢየሱስ በጣም ብዙ ቦታ ሰው ተብሏል፦
“ሐዋርያት 2፥22 "የእስራኤል ሰዎች ሆይ፥ ይህን ቃል ስሙ፤ ራሳችሁ እንደምታውቁ፥ የናዝሬቱ ኢየሱስ እግዚአብሔር በመካከላችሁ በእርሱ በኩል ባደረገው ተአምራትና በድንቆች በምልክቶችም ከእግዚአብሔር ዘንድ ለእናንተ የተገለጠ ሰው ነበረ።
“ሐዋርያት 17፥31 ቀን ቀጥሮአልና፥ በዚያም ቀን ባዘጋጀው ሰው።
ኢየሱስ ሰው ከተባለ ከተባለ እግዚአብሔር ሰው ካልሆነ ኢየሱስ እንዴት  ሰው ያልሆነውን እግዚአብሔር ሊሆን የሚችለው?

ማሳያ ሁለት፦ እግዚአብሔር የሰው ልጅ አደለም ኢየሱስ የሰው ልጅ ነው፦ ዘኍልቁ 23፥19 “እግዚአብሔር የሰው ልጅ አይደለም።
በተቃራኒው ደሞ ኢየሱስ የሰው ልጅ ነው፦
ማቴዎስ 12፥40“ እንዲሁ የሰው ልጅ
ማርቆስ 9፥9 የሰው ልጅ ከሙታን እስኪነሣ ድረስ።
  ኢየሱስ የሰው ልጅ እንደተባለ ጥቅስ በቁና ማምጣት ይቻላል ለናሙና ሁለቱ በቂ ናቸው ኢየሱስ የሰው ልጅ ከተባለ እግዚአብሔር ደሞ የሰው ልጅ ካልሆነ ኢየሱስ የሰው ልጅ ያልሆነውን እግዚአብሔር እንዴት ሊሆን ይችላል?

ማሳያ ሶስት፦ ኢየሱስ አምላክነትን መካዱ፦
ሉቃስ 18፥18/19 ከአለቆችም አንዱ፦ ቸር መምህር፥ የዘላለምን ሕይወት እንድወርስ ምን ላድርግ? ብሎ ጠየቀው።”“ኢየሱስም፦ ስለ ምን ቸር ትለኛለህ? ከአንዱ ከእግዚአብሔር በቀር ቸር ማንም የለም።”
ኢየሱስ ቸር ሲባል አው ቸር ነኝ ከማለት ይልቅ አንዱ እግዚአብሔር ብቻ ነው ቸር እኔ ቸር አይደለሁም በማለት ማልሷል ታዲያ ኢየሱስ ቸር ካልሆነ እግዚአብሔር ቸር ከሆነ ኢየሱስ ቸር የሆነውን እግዚአብሔር እንዴት ሊሆን ይችላል?

ማሳያ አራት፦ ከኢየሱስ አብ መብለጡ ፦
ዮሐንስ 14፥28 ከእኔ አብ ይበልጣልና። ዮሐንስ 10፥29 የሰጠኝ አባቴ ከሁሉ ይበልጣል፥
ኢየሱስ አምላክ ከሆነ እንዴት አብ ከሱ ይበልጣል?

ማሳያ አምስት፦ኢየሱስ ወደ እግዚአብሔር መጸለዩ፦
ሉቃስ 6፥12በነዚህም ወራት ይጸልይ ዘንድ ወደ ተራራ ወጣ፥ ሌሊቱንም ሁሉ ወደ እግዚአብሔር ሲጸልይ አደረ።”
ማቴዎስ 26፥39 ጥቂትም ወደ ፊት እልፍ ብሎ በፊቱ ወደቀና ሲጸልይ
“ማቴዎስ 26፥41 ደግሞ ሁለተኛ ሄዶ ጸለየና፦
  ማቴዎስ 26፥42 “ደግሞ ሁለተኛ ሄዶ ጸለየና፦
ኢየሱስ አምላክ ነው ካላቹ ወደማነው የሚጸልየው?ወደራሱ? ኢየሱስ ሚጸልይ ከሆነ ጸሎትን የሚቀበለውን እግዚአብሔር እንዴት መሆን ይችላል?
ማሳያ ስድስት፦ኢየሱስ አምላክ አለኝ ማለቱ ሌሎቹም የኢየሱስ አምላክ በማለት መናገራቸው፦
ኢየሱስ አምላክ እንዳለው ከራሱ አንደበት፦
ማቴዎስ 27:46 በዘጠኝ ሰዓትም ኢየሱስ፡- ኤሎሄ ኤሎሄ ላማ ሰበቅታኒ? ብሎ በታላቅ ድምፅ ጮኸ። ይህም፡- የእኔ አምላክ የእኔ አምላክ ፥ አንተ እኔን ስለ ምን ተውኸኝ? ማለት ነው።
ዮሐንስ 20:17 ኢየሱስም። ገና ወደ አባቴ አላረግሁምና አትንኪኝ፤ ነገር ግን ወደ ወንድሞቼ ሄደሽ። እኔ ወደ አባቴና ወደ አባታችሁ ወደ “አምላኬ” እና ወደ አምላካችሁ ዓርጋለሁ ብለሽ ንገሪአቸው አላት።
ራእይ 3፥2፤ ሥራህን በአምላኬ ፊት ፍጹም ሆኖ አላገኘሁትምና የነቃህ ሁን፥ ሊሞቱም ያላቸውን የቀሩትን ነገሮች አጽና።
ራእይ 3፥12 ድል የነሣው በአምላኬ መቅደስ ዓምድ እንዲሆን አደርገዋለሁ፥ ወደ ፊትም ከዚያ ከቶ አይወጣም፤ የአምላኬን ስምና የአምላኬን ከተማ ስም፥ ማለት ከሰማይ ከአምላኬ ዘንድ የምትወርደውን አዲሲቱን ኢየሩሳሌምን፥ አዲሱንም ስሜን በእርሱ ላይ እጽፋለሁ።

ኢሳይያስ61:1-2 የጌታ የእግዚአብሔር መንፈስ በእኔ ላይ ነው፥ ለድሆች የምሥራችን እሰብክ ዘንድ እግዚአብሔር ቀብቶኛልና፤ ልባቸው የተሰበረውን እጠግን ዘንድ፥ ለተማረኩትም ነጻነትን ለታሰሩትም መፈታትን እናገር ዘንድ ልኮኛል። የተወደደችውን የእግዚአብሔርን ዓመት “”አምላካችንም”” የሚበቀልበትን ቀን እናገር ዘንድ፥ የሚያለቅሱትንም ሁሉ አጽናና ዘንድ ልኮኛል።
ማርቆስ 12:29 ኢየሱስም መልሶ እንዲህ አለው። ከትእዛዛቱ ሁሉ ፊተኛይቱ። እስራኤል ሆይ፥ ስማ፤ ጌታ “”አምላካችን”” አንድ ጌታ ነው።

ሰዎችም ኢየሱስ አምላክ እንዳለው ተናግረዋል ፦ ሰወች የተናገሩለት ደሞ ይኸው፦
ራእይ 1:6 መንግሥትም ለአምላኩ”” እና ለአባቱም ካህናት እንድንሆን ላደረገ፥
ሚክያስ 5:4፤ እርሱም ይቆማል፥ በእግዚአብሔርም ኃይል በአምላኩ”” በእግዚአብሔር ስም ግርማ መንጋውን ይጠብቃል፤ እነርሱም ይኖራሉ፤ እርሱ አሁን እስከ ምድር ዳርቻ ድረስ ታላቅ ይሆናልና።
በተጨማሪም “የኢየሱስ ክርስቶስ አምላክ” በማለት ኢየሱስ አምላክ እንዳለው ተናግረዋል፦
ኤፌሶን 1:17 የክብር አባት የጌታችን “”የኢየሱስ ክርስቶስ አምላክ”” እርሱን በማወቅ የጥበብንና የመገለጥን መንፈስ እንዲሰጣችሁ እለምናለሁ።
2ኛ ቆሮንጦስ1:3 የርኅራኄ አባት የመጽናናትም ሁሉ አምላክ የሆነ የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ አምላክና አባት ይባረክ።
2ኛ ቆሮንጦስ 11:31 ለዘላለም የተባረከ የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ አምላክና አባት እንዳልዋሽ ያውቃል።

ማሳያ ሰባት፦መልእክተኛ ነኝ ማለቱ ሰዎችም መልእክተኛ ነው ማለታቸው፦
ኢየሱስ በአንደበቱ፦
ዮሐንስ 8፥42 እርሱ ላከኝ እንጂ ከራሴ አልመጣሁምና።
ዮሐንስ 7፥28 እኔም በራሴ አልመጣሁም፡ ነገር ግን እናንተ የማታውቁት የላከኝ እውነተኛ ነው።
ዮሐንስ 8፥26 ዳሩ ግን የላከኝ እውነተኛ ነው፥ እኔም ከእርሱ የሰማሁትን ይህን ለዓለም እናገራለሁ።
ዮሐንስ 7፥16 ትምህርቴስ ከላከኝ ነው እንጂ ከእኔ አይደለም።
ዮሐንስ 14፥24 የምትሰሙትም ቃል የላከኝ የአብ ነው እንጂ የእኔ አይደለም።
ማቴዎስ 10፥40 እናንተን የሚቀበል እኔን ይቀበላል፥ እኔንም የሚቀበል የላከኝን ይቀበላል።
ማቴዎስ 15፥24 እርሱም መልሶ፦ "ከእስራኤል ቤት ለጠፉት በጎች በቀር አልተላክሁም" አለ።
ከሰዎች፦
ማቴዎስ 11፥10 "እነሆ መንገድህን በፊትህ የሚጠርግ መልክተኛዬን በፊትህ እልካለሁ" ተብሎ የተጻፈለት ይህ ነውና።
ገላትያ 4፥14 ነገር ግን እንደ አምላክ መልእክተኛ ἄγγελον" አዎን እንደ ክርስቶስ ኢየሱስ ተቀበላችሁኝ።
ሚልክያስ 3፥1 የምትወዱትም የቃል ኪዳን መልእክተኛ እነሆ ይመጣል፥ ይላል የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር።

ኢየሱስ መልእክተኛ ነው ከተባለ የማን መልእክተኛ የእግዚአብሔር ከተባለ ኢየሱስ የእግዚአብሔር መልእክተኛ እንጂ እግዚአብሔር አይደለም ማለት ነው።መልእክተኛ ከላኪ እንዴት እኩል ሌሆን ይችላል?“እውነት እውነት እላችኋለሁ፥ ባሪያ ከጌታው አይበልጥም። መልእክተኛም ከላከው አይበልጥም።” ዮሐንስ 13፥16 ስለዚህ ኢየሱስ መልእክተኛ ከሆነ እግዚአብሔር ላኪ ነው።


ከዚህ ቀደም "ክርስቶስ ማነው?" በሚል ርዕስ በኡሥታዝ አሕመዲን ጀበል ተዘጋጅቶ የቀረበው መጽሐፍ በወንድም ጀማል ኸድር በኦሮሚኛ ቋንቋ ተተርጉሞ ለአንባብያን በቅቷል።

መጽሐፉን ማግኘት የምትፈልጉ አየር ጤና አንሷር መሥጂድ መጽሐፍ መደብር ያገኙታል።

ለተጨማሪ መረጃ፦
ወንድም አብዱ: +251920781016
ወንድም ጀማል: +251913463746
ይደውሉ!


የማቴዎስ ወንጌል

የማቴዎስ ወንጌል እና ስህተቶቹ

ስህተት አንድ፦በዘካርያስ የተነገረውን ትንቢት ኤርሚያስ ነው ማለቱ፦

“በዚያን ጊዜ በነቢዩ በኤርምያስ የተባለው፦ ከእስራኤል ልጆችም አንዳንዶቹ የገመቱትን፥ የተገመተውን ዋጋ ሠላሳ ብር ያዙ፥”
  📖[ማቴዎስ 27፥9]

ቅሉ ግን ይህንን ትንቢት የምናገኘው ዘካርያስ ላይ ነው፦
“እኔም፦ ደስ ብሎአችሁ እንደ ሆነ ዋጋዬን ስጡኝ፤ ያለዚያ ግን ተዉት አልሁ። እነርሱም ለዋጋዬ ሠላሳ ብር መዘኑ።”እግዚአብሔርም፦ የተስማሙበትን የከበረውን ዋጋዬን በግምጃ ቤቱ ውስጥ አኑረው አለኝ። እኔም ሠላሳውን ብር ወስጄ በእግዚአብሔር ቤት ባለው በግምጃ ቤቱ ውስጥ አኖርሁት።”
  📖[ዘካርያስ 11፥12/13]

ማቴዎስ ከየት አምጥቶ ነው ኤርሚያስ ነው የሚለን?

ስህተት ሁለት፦ የዮዳሄ ልጅ ዘካርያስ ሞት የበራክዩ ልጅ ዘካርያስ ነው ማለቱ፦

“ከጻድቁ ከአቤል ደም ጀምሮ በቤተ መቅደስና በመሠዊያው መካከል እስከ ገደላችሁት እስከ በራክዩ ልጅ እስከ ዘካርያስ ደም ድረስ በምድር ላይ የፈሰሰው የጻድቅ ደም ሁሉ ይደርስባችሁ ዘንድ።”
  📖[ማቴዎስ 23፥35]

ኢየሱስ የተናገረው ክስተት በ2 ዜና 24፥20/21ተጠቅሷል ፦

“የእግዚአብሔርም መንፈስ በካህኑ በዮዳሄ ልጅ በዘካርያስ ላይ መጣ፤ እርሱም በሕዝቡ ፊት ቆመና፦ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ የእግዚአብሔርን ትእዛዝ ለምን ትተላለፋላችሁ? መልካምም አይሆንላችሁም፤ እግዚአብሔርን ስለ ተዋችሁ እርሱ ትቶአችኋል አላቸው።”“ተማማሉበትም በንጉሡም ትእዛዝ በእግዚአብሔር ቤት አደባባይ ውስጥ በድንጋይ ወገሩት።”
  📖[2 ዜና 24፥20/21]
በመሰዊያው መካከል ተወግሮ የተገደለው የዮዳሄ ልጅ ዘካርያስ እንጂ የበራክዩ ልጅ ዘካርያስ አደለም በራክዩ ከየዮዳሄ ልጅ ዘካርያስ ሞት ከብዙ ከአስርት ዓመታት በኃላ የኖረ የነቢዩ ዘካርያስ አባት ነው፦

“በዳርዮስ በሁለተኛው ዓመት በስምንተኛው ወር የእግዚአብሔር ቃል ወደ አዶ ልጅ ወደ በራክዩ ልጅ ወደ ነቢዩ ወደ ዘካርያስ እንዲህ ሲል መጣ፦”
 📖[ዘካርያስ 1፥1]

ታዲያ ማቴዎስ ከየት አምጥቶ ነው የበራክዩ ልጅ ዘካርያስ የሚለን?

ስህተት ሦስት ፦ የሌለ ትንቢት እንዳለ አድርጎ መናገሩ፦

“በነቢያት፦ ናዝራዊ ይባላል የተባለው ይፈጸም ዘንድ፥ ናዝሬት ወደምትባል ከተማ መጥቶ ኖረ።”
  📖[ማቴዎስ 2፥23]
ይህ ትንቢት በየትኛውም የነቢያት መጽሐፍ ላይ የለም።
ማቴዎስ ከየት አምጥቶ ነው?

https://t.me/AliDawah2


የቁርአን ሱራህ ►⁴

አላህ ራሱ ነው ቁርአንን ከፋፍሎ ያወረደው፦

وَقُرْآنًا فَرَقْنَاهُ لِتَقْرَأَهُ عَلَى النَّاسِ عَلَىٰ مُكْثٍ وَنَزَّلْنَاهُ تَنزِيلًا

►📗[ሱረቱ አል-ኢስራእ 17፤106]
ቁርኣንንም በሰዎች ላይ በዝግታ ላይ ኾነህ ታነበው ዘንድ ከፋፈልነው፡፡ ቀስ በቀስ ማውረድንም አወረድነው፡፡

ቁርአን ሱራ እንዳለው አላህ በቁርአን ላይ ነግሮናል፦

سُورَةٌ أَنزَلْنَاهَا وَفَرَضْنَاهَا وَأَنزَلْنَا فِيهَا آيَاتٍ بَيِّنَاتٍ لَّعَلَّكُمْ تَذَكَّرُونَ

►📗[ሱረት አል-ኑር24፤1]
(ይህች) ያወረድናትና የደነገግናት ሱራ (ምዕራፍ) ናት፡፡ በእርሷም ውስጥ ትገሰፁ ዘንድ ግልጾችን አንቀጾች አውርደናል፡፡

ሱራህ አንድ፦►ሱረቱል ፋቲሓህ ፦~فاتحة~
ፋቲሓህ ማለት መክፈቻ ማለት ነው።

وَلَقَدْ آتَيْنَاكَ سَبْعًا مِّنَ الْمَثَانِي وَالْقُرْآنَ الْعَظِيمَ

►📗[ሱረቱ አል-ሒጅር 15፤87]
ከሚደጋገሙ የኾኑን ሰባትንና ታላቁንም ቁርኣን (በሙሉ) በእርግጥ ሰጠንህ፡፡

ከሚደጋገሙ የኾኑ የተባለው ሱረቱል ፋቲሓህ መሆኑን ነብያችንصلى الله عليه وسلمነግረውናል፦

عَنْ أَبِي هُرَيْرَةَ، قَالَ قَالَ رَسُولُ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم ‏"‏ الْحَمْدُ لِلَّهِ أُمُّ الْقُرْآنِ وَأُمُّ الْكِتَابِ وَالسَّبْعُ الْمَثَانِي ‏"‏ ‏.‏

አቢ ሁረይራ ረ.ዐ እንደተረከው፦ “የአላህ መልእክተኛصلى الله عليه وسلمእንዲህ አሉ፦አልሐምዱሊላህ የቁርኣን እናት፣ የመጽሐፉ እናት እና ሰባት የተደጋገሙ (አናቅጽ)ናቸው።

Narrated Abu Hurairah:
that the Messenger of Allah صلى الله عليه وسلم said: "Al-Hamdulillah is Umm Al-Qur'an and Umm Al-Kitab and the seven oft-repeated."

►📕[Jami at-Tirmidhi, Vol. 5, Book 44, Hadith 3124]

በተጨማሪም ይመልከቱ►
►📕[Sahih al-Bukhari,  Vol. 6, Book 61, Hadith 528]
►📕[Sahih al-Bukhari,  Vol. 6, Book 60, Hadith 226]
►📕[Sahih al-Bukhari,  Vol. 6, Book 60, Hadith 227]

የአላህ መልእክተኛصلى الله عليه وسلم ሱረቱል ፋቲሓህን በስሙ ጠርተዋል? አው በሚገባ፦

አንድ ሰው ፋቲሓህን ሳይቀራ ሰላት ከሰገደ ውድቅ መሆኑን ሲነግሩን بِفَاتِحَةِ الْكِتَابِ
የመጽሐፉ መክፈቻ ፋቲሓህ ብለው ተጠቅመዋል፦

عُبَادَةَ بْنِ الصَّامِتِ، أَنَّ رَسُولَ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم قَالَ ‏"‏ لاَ صَلاَةَ لِمَنْ لَمْ يَقْرَأْ بِفَاتِحَةِ الْكِتَابِ ‏"‌‏.‏
 
ኡባዳ ቢን አስ-ሳሚት እንደተረከው፦
የአላህ መልእክተኛ صلى الله عليه وسلم እንዲህ ብለዋል፦
በሶላቱ ውስጥ የመጽሐፉ መክፈቻ ፋቲሓን ያልቀራ ሰላቱ ውድቅ ነው።

Narrated 'Ubada bin As-Samit:
Allah's Messenger صلى الله عليه وسلم said, "Whoever does not recite Al-Fatiha in his prayer, his prayer is invalid." 

►📕[Sahih al-Bukhari Vol. 1, Book 12, Hadith 723]

ነብዩ صلى الله عليه وسلم እራሳቸው بِفَاتِحَةِ الْكِتَابِ ‏"‌‏.‏ የመጽሐፉ መክፈቻ ፋቲሓህ
ብለው ይጠቀሙ ነበር ሌላም ተመሳሳይ ሐዲስ እንመልከት፦
 
عُبَادَةَ بْنِ الصَّامِتِ، يَبْلُغُ بِهِ النَّبِيَّ صلى الله عليه وسلم ‏"‏ لاَ صَلاَةَ لِمَنْ لَمْ يَقْرَأْ بِفَاتِحَةِ الْكِتَابِ ‏"‏ ‏.‏
 
ዑባዳህ ኢብን አል-ሳሚት እንደተረከው፦ የአላህ መልእክተኛ صلى الله عليه وسلم እንዲህ ብለዋል ፡-የመፅሃፉን መክፈቻ ሱረቱል ፋቲሓን ያልቀራ ሰው ምንም ሶላት የለውም ።

Ubadah ibn al-Samit reported from the Messenger of Allahصلى الله عليه وسلم
He who does not recite Fatihat al-Kitab is not credited with having observed the prayer.

►📕[Sahih Muslim,Book,4 Hadith 37]


عُبَادَةَ بْنِ الصَّامِتِ، عَنِ النَّبِيِّ صلى الله عليه وسلم قَالَ ‏"‏ لاَ صَلاَةَ لِمَنْ لَمْ يَقْرَأْ بِفَاتِحَةِ الْكِتَابِ ‏"‏ ‏.‏

ዑባዳህ ቢን ሳሚት እንደተረከው፦ነብዩصلى الله عليه وسلم እንዲህ ብለዋል ፡- “የመፅሃፉን መክፈቻ ሱረቱል ፋቲሓን ላልቀራ ሰው ምንም ሶላት የለውም ።

It was narrated from Ubadah bin As-Samit that :
The Prophet صلى الله عليه وسلم said: "There is no Salah for one who does not recite Fatihatil-Kitab."
►📕[Sunan an-Nasa'i,Vol. 2, Book 11, Hadith 911]

በተመሳሳይ መልኩ ቲርሚዚ ዘግቦታል፦
►📕[Jami at-Tirmidhi,  Vol. 1, Book 2, Hadith 247]
ኢብኑ ማጃህም ዘግቦታል፦
►📕[Sunan Ibn Majah,  Vol. 1, Book 5, Hadith 837]
እናም ነብያችን صلى الله عليه وسلم ራሳቸው እና ሰሀባዎች ፋቲሓህ ብለው እነደሚጠቀሙ ተመልክተናል፦
በተጨማሪም ይመልከቱ►
►📕[Sahih al-Bukhari, Vol. 1, Book,12Hadith 726]
►📕[Sahih al-Bukhari,  Vol. 1, Book 12, Hadith 729]
►📕[Sahih Muslim,  Book 4, Hadith 1760]
በጣም ብዙ ሐዲስ አለ ላለማርዘም ይሄ በቂ ነው።
ማጠቃለያ፦
እንግዲህ ከላይ ጀምረን እንዳየነው
►አላህ ቁርአንን ከፋፍሎ እዳወረደ አይተናል
►አላህ ቁርአን ሱራ እንዳለው ቁርአን ውስጥ እንደነገረን አይተናል
►ነብያችን صلى الله عليه وسلم እና ሰሐቦች አል-ፋቲሓህ~ الفاتحة~ ብለው እንደተጠቀሙ ከጊዜ በኋላ እንዳልመጣ አይተናል።

سُورَةٌ أَنزَلْنَاهَا وَفَرَضْنَاهَا وَأَنزَلْنَا فِيهَا آيَاتٍ بَيِّنَاتٍ لَّعَلَّكُمْ تَذَكَّرُونَ

►📗[ሱረት አል-ኑር24፤1]
(ይህች) ያወረድናትና የደነገግናት ሱራ (ምዕራፍ) ናት፡፡ በእርሷም ውስጥ ትገሰፁ ዘንድ ግልጾችን አንቀጾች አውርደናል፡፡

ይቀጥላል .................

https://t.me/AliDawah2


ቁርአን ሱራህ እንዳለው አላህ በቁርአን ላይ ነግሮናል፦³
يَحْذَرُ الْمُنَافِقُونَ أَن تُنَزَّلَ عَلَيْهِمْ سُورَةٌ تُنَبِّئُهُم بِمَا فِي قُلُوبِهِمْ ۚ قُلِ اسْتَهْزِئُوا إِنَّ اللَّهَ مُخْرِجٌ مَّا تَحْذَرُونَ

►📗[ሱረቱ አል-ተውባህ 9፤64 ]
መናፍቃን በልቦቻቸው ውስጥ ያለውን ነገር የምትነግራቸው ሱራ በእነርሱ ላይ መውረዷን ይፈራሉ፡፡ «አላግጡ አላህ የምትፈሩትን ሁሉ ገላጭ ነው» በላቸው፡፡

وَإِذَا مَا أُنزِلَتْ سُورَةٌ فَمِنْهُم مَّن يَقُولُ أَيُّكُمْ زَادَتْهُ هَـٰذِهِ إِيمَانًا ۚ فَأَمَّا الَّذِينَ آمَنُوا فَزَادَتْهُمْ إِيمَانًا وَهُمْ يَسْتَبْشِرُونَ

►📗[ሱረቱ አል-ተውባህ 9፤124]
ሱራም (ምዕራፍ) በተወረደች ጊዜ ከእነሱ (ከመናፍቃን) ውስጥ ማንኛችሁ ነው ይህች (ምዕራፍ) እምነትን የጨመረችለት የሚል ሰው አልለ፡፡ እነዚያ ያመኑትማ የሚደሰቱ ሲኾኑ እምነትን ጨመረችላቸው፡፡

ከላይ እንደ ተመለከትነው አላህ ራሱ ቁርአን  سُورَةٌ ሱራህ እዳለው ነግሮናል።

አላህ ቁርአንን  ከፋፍሎና ቀስበቀስ  እንዳወረውም  ቁርአን ላይ ነግሮናል፦

وَقُرْآنًا فَرَقْنَاهُ لِتَقْرَأَهُ عَلَى النَّاسِ عَلَىٰ مُكْثٍ وَنَزَّلْنَاهُ تَنزِيلًا

►📗[ሱረቱ አል-ኢስራእ 17፤106]
ቁርኣንንም በሰዎች ላይ በዝግታ ላይ ኾነህ ታነበው ዘንድ ከፋፈልነው፡፡ ቀስ በቀስ ማውረድንም አወረድነው፡፡

نَزَّلَ عَلَيْكَ الْكِتَابَ بِالْحَقِّ مُصَدِّقًا لِّمَا بَيْنَ يَدَيْهِ وَأَنزَلَ التَّوْرَاةَ وَالْإِنجِيلَ

►📗[ሱረቱ አሊ-ዒምራን 3፤3]
ከርሱ በፊት ያሉትን መጻሕፍት የሚያረጋግጥ ሲኾን መጽሐፉን (ቁርኣንን) ባንተ ላይ ከፋፍሎ በእውነት አወረደ፡፡ ተውራትንና ኢንጂልንም አውርዷል፡፡


ወደ ነብዩصلى الله عليه وسلمአንድ የቁርአን አንቀጽ ሲወርድ ቁርአንን የሚጽፉ ጸሐፊዎች ይህንን አንቀጽ እንዲህ በሚባለው ሱራህ ውስጥ አድርገው ይሉ ነበር፦

حَدَّثَنَا ابْنُ عَبَّاسٍ،..........رَسُولُ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم مِمَّا يَأْتِي عَلَيْهِ الزَّمَانُ وَهُوَ تَنْزِلُ عَلَيْهِ السُّوَرُ ذَوَاتُ الْعَدَدِ فَكَانَ إِذَا نَزَلَ عَلَيْهِ الشَّىْءُ دَعَا بَعْضَ مَنْ كَانَ يَكْتُبُ فَيَقُولُ ضَعُوا هَؤُلاَءِ الآيَاتِ فِي السُّورَةِ الَّتِي يُذْكَرُ فِيهَا كَذَا وَكَذَا وَإِذَا نَزَلَتْ عَلَيْهِ الآيَةُ فَيَقُولُ ضَعُوا هَذِهِ الآيَةَ فِي السُّورَةِ الَّتِي يُذْكَرُ فِيهَا كَذَا........."

ኢብኑ አባስ እንደተረከው፦ .......የአላህ መልእክተኛصلى الله عليه وسلمአንዳች የቁርኣን ክፍል በሚወርድላቸው ጊዜ ከጸሀፊዎቹ አንዱን ይጠሩና ይህንን አንቀጽ እንዲህ ተብሎ በሚጠራው ሱራህ ውስጥ አስቀምጡት ይሉ ነበር። አሁንም በድጋሚ የተወሰኑ የቁርኣን አንቀጾች ሲወርድላቸው እነዚህን አንቀጾች እንዲህ ተብሎ በሚጠራው ሱራህ ውስጥ አስቀምጡት ይሉ ነበር........።

Narrated Ibn 'Abbas..........
the the messenger of Allahصلى الله عليه وسلم....... So when something was revealed, he would call for someone who could write, and say: "Put these Ayat in the Surah which mentions this and that in it." When an Ayah was revealed, he would say: "Put this Ayah in the Surah which mentions this and that in it........"

►📕[Jami` at-Tirmidhi  Vol. 5, Book 44, Hadith 3086]
በተጨማሪም ፦

رَسُولُ اللَّهِ صَلَّى اللَّهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ مِمَّا يَأْتِي عَلَيْهِ الزَّمَان وَهُوَ تنزل عَلَيْهِ السُّور ذَوَات الْعدَد فَكَانَ إِذا نزل عَلَيْهِ الشَّيْء دَعَا بعض من كَانَ يَكْتُبُ فَيَقُولُ: «ضَعُوا هَؤُلَاءِ الْآيَاتِ فِي السُّورَةِ الَّتِي يُذْكَرُ فِيهَا كَذَا وَكَذَا»

ኢብኑ አባስ እንደተረከው፦......የአላህ መልእክተኛصلى الله عليه وسلمአንዳች የቁርኣን ክፍል በሚወርድላቸው ጊዜ ከጸሐፊዎቹ አንዱን በመጥራት፦ይህንን አንቀጽ እንዲህ ተብሎ በሚጠራው ሱራህ ውስጥ አስቀምጡት ይሉ ነበር።

►📕[Mishkat al-Masabih, : Book 8, Hadith 112]

አንድ ሱራህ ከሌላው ሱራህ የሚለየው፦‏ ‏ بِسْمِ اللَّهِ الرَّحْمَنِ الرَّحِيمِ ማለትም  በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ በጣም አዛኝ በሆነው” በሚል ቃል ነው፦
  قَالَ كَانَ النَّبِيُّ صلى الله عليه وسلم  لاَ يَعْرِفُ فَصْلَ السُّورَةِ حَتَّى تُنَزَّلَ عَلَيْهِ ‏{‏ بِسْمِ اللَّهِ الرَّحْمَنِ الرَّحِيمِ ‏}‏ ‏

ኢብኑ አባስ እንደተረከው የአላህ መልእክተኛصلى الله عليه وسلمሁለት ሱራዎች አይለያዩም ነበር በመካከላቸው በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ በጣም አዛኝ በሆነው የሚለው ቃል ወደ እርሳቸው ቢወርድላቸው እንጂ።

The prophetصلى الله عليه وسلمdid not distinguish between the two surahs until the words “In the name of Allah, the Compassionate, the merciful” was revealed to him. 
►📕[Sunan Abi Dawud  Book 2, Hadith 787]

እያንዳንዱ ሱራህ ሲጀምር በبِسْمِ اللَّهِ الرَّحْمَنِ الرَّحِيمِማለትም በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ በጣም አዛኝ በሆነው ብሎ ነው ከአንድ ሱራህ በቀር እሱም 9ኛው ሱራህ ►ሱረቱል ተውባህ ነው።
  ሱረቱል ተውባህ በ بِسْمِ اللَّهِ الرَّحْمَنِ الرَّحِيمِ  ባይጀምርም 27ኛ ሱራህ ►ሱረቱል ነምል ላይ ደግሞት እናገኛለን፦

إِنَّهُ مِن سُلَيْمَانَ وَإِنَّهُ بِسْمِ اللَّهِ الرَّحْمَـٰنِ الرَّحِيمِ

►📗[ሱረቱ አል-ነምል 27፤30]
«እርሱ ከሱለይማን ነው፡፡ እርሱም በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩኅ በጣም አዛኝ በኾነው፡፡

የቁርአን ሱራህ እያንዳንዱ ስም በውስጡ ይገኛል ከሶስት ሱራዎች በስተቀር እነርሱም፦ ሱረቱል ፋቲሓህ ሱረቱል አንቢያ እና ሱረቱል ኢኽላስ ናቸው ሌሎቹ 111 ሱራዎች ስማቸው በውስጣቸው ይገኛል።

የቁርአን ሱራዎች በውስጣቸው እንዳሉና ስማቸውን ነብያችንصلى الله عليه وسلم እና ሰሀቦች  ይጠቀሙባቸው እንደነበር ከጊዜ በኋላ የተሰየሙ እንዳልሆኑ እንመልከት፦

ይቀጥላል ........

https://t.me/AliDawah2


~የቅዱስ ቁርአን ሱራህ~²
            ▾
1►ሱረቱል-ፋቲሓህ
2►ሱረቱል-በቀራህ
3►ሱረቱል-ዒምራን
4►ሱረቱል-ኒሳእ
5►ሱረቱል-ማኢዳህ
6►ሱረቱል-አንዓም
7►ሱረቱል-አዕራፍ
8►ሱረቱል-አንፋል
9►ሱረቱል-ተውባህ
10►ሱረቱል-ዩኑስ
11►ሱረቱል-ሁድ
12►ሱረቱል-ዩሱፍ
13►ሱረቱል-ረዕድ
14►ሱረቱል-ኢብራሂም
15►ሱረቱል-ሒጅር
16►ሱረቱል-ነሕል
17►ሱረቱል-ኢስራእ
18►ሱረቱል-ከህፍ
19►ሱረቱል-መርየም
20►ሱረቱል-ጣሀ
21►ሱረቱል-አንቢያ
22►ሱረቱል-ሐጅ
23►ሱረቱል-ሙእሚኑን
24►ሱረቱል-ኑር
25►ሱረቱል-ፉርቃን
26►ሱረቱል-አሹዐራ
27►ሱረቱል-ነምል
28►ሱረቱል-ቀሶስ
29►ሱረቱል-ዐንከቡት
30►ሱረቱል-ሩም
31►ሱረቱል-ሉቅማን
32►ሱረቱል-ሰጂዳህ
33►ሱረቱል-አህዛብ
34►ሱረቱል-ሰበእ
35►ሱረቱል-ፈጢር
36►ሱረቱል-ያሲን
37►ሱረቱል-ሷፍፋት
38►ሱረቱል-ሷድ
39►ሱረቱል-ዙመር
40►ሱረቱል-ጋፊር
41►ሱረቱል-ፉሲለት
42►ሱረቱል-ሹራ
43►ሱረቱል-ዙኽሩፍ
44►ሱረቱል-ዱኻን
45►ሱረቱል-ጃሢያህ
46►ሱረቱል-አሕቃፍ
47►ሱረቱል-ሙሐመድ
48►ሱረቱል-ፈትሕ
49►ሱረቱል-ሑጁራት
50►ሱረቱል-ቃፍ
51►ሱረቱል-ዛሪያት
52►ሱረቱል-ጡር
53►ሱረቱል-ነጅም
54►ሱረቱል-ቀመር
55►ሱረቱል-ረሕማን
56►ሱረቱል-ዋቂዓህ
57►ሱረቱል-ሐዲድ
58►ሱረቱል-መጀደላህ
59►ሱረቱል-ሐሽር
60►ሱረቱል-ሙምተሒናህ
61►ሱረቱል-ሶፍ
62►ሱረቱል-ጁምዓህ
63►ሱረቱል-ሙናፊቁን
64►ሱረቱል-አተጋቡን
65►ሱረቱል-ጦላቅ
66►ሱረቱል-ተሕሪም
67►ሱረቱል-ሙልክ
68►ሱረቱል-ቀለም
69►ሱረቱል-ሐቃህ
70►ሱረቱል-መዓሪጅ
71►ሱረቱል-ኑሕ
72►ሱረቱል -ጂን
73►ሱረቱል-ሙዘሚል
74►ሱረቱል-ሙደሢር
75►ሱረቱል-ቂያማህ
76►ሱረቱል-ኢንሳን
77►ሱረቱል-ሙርሰላት
78►ሱረቱል-ነበእ
79►ሱረቱል-ናዚዓት
80►ሱረቱል-ዐበስ
81►ሱረቱል-ተክዊር
82►ሱረቱል-ኢንፊጣር
83►ሱረቱል-ሙጠፍፊን
84►ሱረቱል-ኢንሺቃቅ
85►ሱረቱል-ቡሩጅ
86►ሱረቱል-ጣሪቅ
87►ሱረቱል-አዕላ
88►ሱረቱል-ጋሺያህ
89►ሱረቱል-ፈጅር
90►ሱረቱል-በለድ
91►ሱረቱል-ሸምስ
92►ሱረቱል-ለይል
93►ሱረቱል-ዱሃ
94►ሱረቱል-ኢሻራሕ
95►ሱረቱል-ቲን
96►ሱረቱል-ዐለቅ
97►ሱረቱል-ቀድር
98►ሱረቱል-በይናህ
99►ሱረቱል-ዘልዘላህ
100►ሱረቱል-ዓዲያት
101►ሱረቱል-ቃሪዓህ
102►ሱረቱል-ተካሡር
103►ሱረቱል-ዐስር
104►ሱረቱል-ሁመዛህ
105►ሱረቱል-ፊል
106►ሱረቱል-ቁረይሽ
107►ሱረቱል-ማዑን
108►ሱረቱል-ከውሠር
109►ሱረቱል-ካፊሩን
110►ሱረቱል-ነስር
111►ሱረቱል-መሰድ
112►ሱረቱል-ኢኽላስ
113►ሱረቱል-ፈለቅ
114►ሱረቱል-ናስ
ናቸው።
ለ13  ዓመት 86 ሱራዎች የወረዱት በመካ ነው በመካ የዘረዱ ሱራዎች መኪያህ ይባላሉ እነሱም፦►

መኪያህ
1►ሱረቱል-ፋቲሓህ  ►2►ሱረቱል-አንዓም
3►ሱረቱል-አዕራፍ     ►4►ሱረቱል-ዩኑስ
5►ሱረቱል- ሁድ        ►6►ሱረቱል-ዩሱፍ
7►ሱረቱል- ኢብራሂም ►8►ሱረቱል-ሒጅር
9►ሱረቱል- ነሕል     ►10►ሱረቱል-ኢስራእ
11►ሱረቱል- ከህፍ   ►12►ሱረቱል-መርየም
13►ሱረቱል-ጣሀ      ►14►ሱረቱል-አንቢያ
15►ሱረቱል- ሙእሚኑን►16►ሱረቱል-ፉርቃን
17►ሱረቱል- አሹዐራ  ►18►ሱረቱል-ነምል
19►ሱረቱል-ቀሶስ   ►20►ሱረቱል-ዐንከቡት
21►ሱረቱል-ሩም    ►22►ሱረቱል-ሉቅማን
23►ሱረቱል-ሰጂዳህ ►24►ሱረቱል-ሰበእ
25►ሱረቱል-ፈጢር   ►26►ሱረቱል-ያሲን
27►ሱረቱል- ሷፏፋት ►28►ሱረቱል-ሷድ
29►ሱረቱል-ዙመር   ►30►ሱረቱል-ጋፊር
31►ሱረቱል-ፉሲለት  ►32►ሱረቱል-ሹራ
33►ሱረቱል-ዙኽሩፍ ►34►ሱረቱል-ዱኻን
35►ሱረቱል- ጃሢያህ►36►ሱረቱል-አሕቃፍ
37►ሱረቱል-ቃፍ      ►38►ሱረቱል-ዛሪያት
39►ሱረቱል-ጡር      ►40►ሱረቱል-ነጅም
41►ሱረቱል-ቀመር ►42►ሱረቱል-ዋቂዓህ
43►ሱረቱል- ሙልክ►44►ሱረቱል-ቀለም
45►ሱረቱል-ሐቃህ►46►ሱረቱል-መዓሪጅ
47►ሱረቱል- ኑሕ ►48►ሱረቱል-ጂን
49►ሱረቱል-ሙዘሚል►50►ሱረቱል-ሙደሢር
51►ሱረቱል-ቂያማህ►52►ሱረቱል-ሙርሰላት
53►ሱረቱል-ነበእ►54►ሱረቱል-ናዚዓት
55►ሱረቱል-ዐበስ►56►ሱረቱል-ተክዊር
57►ሱረቱል-ኢንፊጣር►58►ሱረቱል-ሙጠፍፊን
59►ሱረቱል-ኢንሺቃቅ►60►ሱረቱል-ቡሩጅ
61►ሱረቱል-ጣሪቅ ►62►ሱረቱል-አዕላ
63►ሱረቱል- ጋሺያህ►64►ሱረቱል-ፈጅር
65►ሱረቱል- በለድ►66►ሱረቱል-ሸምስ
67►ሱረቱል-ለይል►68►ሱረቱል-ዱሃ
69►ሱረቱል-ኢሻረሕ►70►ሱረቱል-ቲን
71►ሱረቱል-ዐለቅ ►72►ሱረቱል-ቀድር
73►ሱረቱል-ዓዲያት►74►ሱረቱል-ቃሪዓህ
75►ሱረቱል-ተካሡር►76►ሱረቱል-ዐስር
77►ሱረቱል-ሁመዛህ►78►ሱረቱል-ፊል
79►ሱረቱል-ቁረይሽ►80►ሱረቱል-ማዑን
81►ሱረቱል-  ከውሠር►82►ሱረቱል-ካፊሩን
83►ሱረቱል-መሰድ ►84►ሱረቱል-ኢክላስ
85►ሱረቱል-ፈለቅ ►86►ሱረቱል-ናስ
ናቸው።

ለ 10 ዓመት ደግሞ 28 ሱራዎች የወረዱት በመዲና ነው የመዲና ሱራዎች መደኒያህ ይባላሉ።እነሱም፦►

መደኒያ፦
1►ሱረቱል-በቀራህ   ►2►ሱረቱል-ዒምራን
3►ሱረቱል-ኒሳእ      ►4►ሱረቱል-ማኢዳህ
5►ሱረቱል- አንፋል  ►6►ሱረቱል-ቱውባህ
7►ሱረቱል- ረዕድ   ►8►ሱረቱል-ሐጅ
9►ሱረቱል- ኑር      ►10►ሱረቱል-አህዛብ
11►ሱረቱል- ሙሐመድ►12►ሱረቱል-ፈትሕ
13►ሱረቱል-ሑጅራት►14►ሱረቱል-ረሕማን
15►ሱረቱል-ሐዲድ►16►ሱረቱል-መጀደላህ
17►ሱረቱል-ሐሽር►18►ሱረቱል-ሙምተሒናህ
19►ሱረቱል-ሶፍ   ►20►ሱረቱል-ጁምዓህ
21►ሱረቱል-ሙናፊቁን►22►ሱረቱል-አተጋቡን
23►ሱረቱል-ጦላቅ►24►ሱረቱል-ተሕሪም
25►ሱረቱል- ኢንሳን►26►ሱረቱል-በይናህ
27►ሱረቱል-ዘልዘላህ►28►ሱረቱል-ነስር
ናቸው።

ይቀጥላል .......
https://t.me/AliDawah2

Показано 20 последних публикаций.