#ተጨማሪ
የ2016 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ መልቀቂያ ፈተና ከወሰዱ ተማሪዋች መካከል፤ ከፍተኛ ውጤት የተመዘገበው በተፈጥሮ ሳይንስ የትምህርት ዘርፍ ነው።
በተፈጥሮ ሳይንስ ዘርፍ ፈተናውን ከወሰዱ 321,536 ተማሪዎች መካከል፤ ከ50 በመቶ በላይ ውጤት ያመጡት 9 በመቶ መሆናቸውን የትምህርት ሚኒስትሩ ብርሃኑ ነጋ (ፕ/ር) ተናግረዋል።
በማኅበራዊ ሳይንስ የትምህርት ዘርፍ ፈተናውን ከወሰዱት 353,287 ተፈታኞች የማለፊያ ውጤት ያስመዘገቡት 2 በመቶ ብቻ እንደሆኑ ሚኒስትሩ ገልፀዋል፡፡
በአጠቃላይ ከፍተኛ ውጤት ያስመዘገቡ ተማሪዎች 1,221 መሆናቸውን ሚኒስትሩ ጠቁመዋል፡፡
ዘንድሮ ሁሉም ክልሎች ባለፈው ዓመት ካሳለፉት ተማሪ የበለጠ ተማሪዎች ማሳለፋቸውን የገለፁት ሚኒስትሩ፤ "በፐርሰንቴጅም በአክቹዋል ቁጥርም ካለፈው የተሻለ ነው" ብለዋል። "ከአክቹዋል ቁጥር ያነሰው የአማራ ክልል ብቻ ሲሆን ክልሉ ያነሰው ደግሞ የተፈተኑት ተማሪዎች ቁጥር ከግማሽ በታች ስለነበር ነው" ብለዋል። ክልሉ ለፈተና ካስቀመጣቸው ተማሪዎች ውስጥ 6.6 በመቶ ተማሪዎች አልፈዋል። ይህም ባለፈው ዓመት ከተመዘገበው 4.1 በመቶ የተሸለ ነው፡፡
ሀገር አቀፍ መልቀቂያ ፈተናውን ከሰጡ ትምህርት ቤቶች መካከል 1,363 ትምህርት ቤቶች ምንም ተማሪ አላሳፉም፡፡ እነዚህ ትምህርት ቤቶች ከሐረር ክልል ውጪ በሁሉም ክልሎች ይገኛሉ፡፡ በአዲስ አበባ አራት፣ በአማራ ክልል 56 እንዲሁም በኦሮሚያ ክልል 553 ትምህርት ቤቶች ምንም ተማሪ አላሳፉም፡፡