በእግዚአብሔር ለተወደዳቸውና ቅዱሳን ልትሆኑ ለተጠራችው በየስፍራው ላላቸው ወገኖች ሁሉ; የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ ጸጋና ሰላም ይብዛላችሁ::
በቸርነትህ ዓመትን ታቀዳጃለህ፥ ምድረ በዳውም ስብን ይጠግባል። የምድረ በዳ ተራሮች ይረካሉ፥ ኮረብቶችም በደስታ ይታጠቃሉ። ማሰማርያዎች መንጎችን ለበሱ፥ ሸለቆችም በእህል ተሸፈኑ፤ በደስታ ይጮኻሉ ይዘምራሉም። መዝሙር 65:11
የኢትዮጵያ ሐዋርያዊት ቤተክርስቲያን ኦዲዮቪዥዋልና ስነ-ጽሑፍ ክፍል፥ በዘማሪት ዮርዳኖስ መለስ የተዘጋጀውን አዲስ የዝማሬ ሰንዱቅ (Album) ለመታነጽና ለበረከት እንዲሆንላችሁ እነሆ ሲል በታላቅ ደስታና ምስጋና ነው።
ይሀንን አልበም አዘጋጅታ፥ ለእግዚአብሔር ክብርና ለቤተክርስቲያን መታነጽ ያበረከትችልን እህት ዮርዳኖስን፥ በዝግጅቱ የተሳተፉትን ሁሉ እግዚአብሔር እንደባለጸግነቱ መጠን እንዲባረካቸው እየጸለይን፥ ጌታ ቢፈቀድ፥ ብንኖርም፥ በጥቂት ቀናት እጃችሁ ባለው ስልክ ላይ በሚገኘው Apostolic Song መተግበሪያ ላይ ዝግጁ ይሆናል::
በኢትዮጵያ ያላችሁ ተጠቃሚዎቻችን ዝማሬዎቹን ለማውረድ የምትጠቀሙበትን ኮድ በቴሌግራም ቦት
t.me/ApostolicPayBot ላይ ማግኘት የምትችሉ ሲሆን ከኢትዮጵያ ውጪ ያላችሁ ደግሞ ክሬዲት ካርድ በመጠቀም አልበሙን ማግኘት እንደምትችሉ እንገልፃለን።
የኦዲዮ ቪዥዋልና ስነ-ጽሑፍ ክፍል
ሚያዚያ 2016 ዓ.ም