አይ አንተ
ሳቂታ ፍልቅልቅ ምርጫዬ ናት ብትል
32 ጥርሴ መከደን እስኪያምረዉ ስፍለቀለቅ አይተህ
ገጣጣ ናት እያልክ ስሜን ታጠፋለህ።
ደሞ ሰሞነኛ
የኔነህ ምትለኝ ልቤን አታስተኛ
የኔ ካሉኝማ ሆናለሁ ምርኮኛ
ያልከዉን ሰምቼ
የኔነህ የኔ ነህ ብል ቃሉን አብዝቼ
የኔነህ ከሚባል ፍቅር ጣለሽ አልከኝ
በወዳጅህ ደግሞ ልክፍታም አስባልከኝ።
ፍቅር ሞኛ ሞኙ
ካንተ እያጣበቀኝ
እንደዉ ምን አይነቷ መሻትህ ናት ብልህ...
ከፊቷ ጠቃጠቅ ያለባት ስትለኝ
ፊቴን አበልዤ ማድያት ወረረኝ
መች አርፋለሁ እኔ
ፈልጌ ከማጣት
ከኩራተኛ ሴት
ይይዘኛል ፍቅር ያልከዉን ሰምቼ
ከሌላ ካየኋት አበቃ ነገሩ ያልከዉን ቀምቼ
እንደምንም ብቆይ ናፍቆቴን ገፍቼ
ከሌላ ለምጄ
እዉነትም ወደድከኝ
..
..
ዳሩ ምን ያደርጋል መስፈርታም አረከኝ።
እኔም በተራዬ
እንዳንተ ያልሆነ ወንድ ነዉ ምርጫዬ😜
በትዝታ ወልዴ እንደተፃፈ✍
ሳቂታ ፍልቅልቅ ምርጫዬ ናት ብትል
32 ጥርሴ መከደን እስኪያምረዉ ስፍለቀለቅ አይተህ
ገጣጣ ናት እያልክ ስሜን ታጠፋለህ።
ደሞ ሰሞነኛ
የኔነህ ምትለኝ ልቤን አታስተኛ
የኔ ካሉኝማ ሆናለሁ ምርኮኛ
ያልከዉን ሰምቼ
የኔነህ የኔ ነህ ብል ቃሉን አብዝቼ
የኔነህ ከሚባል ፍቅር ጣለሽ አልከኝ
በወዳጅህ ደግሞ ልክፍታም አስባልከኝ።
ፍቅር ሞኛ ሞኙ
ካንተ እያጣበቀኝ
እንደዉ ምን አይነቷ መሻትህ ናት ብልህ...
ከፊቷ ጠቃጠቅ ያለባት ስትለኝ
ፊቴን አበልዤ ማድያት ወረረኝ
መች አርፋለሁ እኔ
ፈልጌ ከማጣት
ከኩራተኛ ሴት
ይይዘኛል ፍቅር ያልከዉን ሰምቼ
ከሌላ ካየኋት አበቃ ነገሩ ያልከዉን ቀምቼ
እንደምንም ብቆይ ናፍቆቴን ገፍቼ
ከሌላ ለምጄ
እዉነትም ወደድከኝ
..
..
ዳሩ ምን ያደርጋል መስፈርታም አረከኝ።
እኔም በተራዬ
እንዳንተ ያልሆነ ወንድ ነዉ ምርጫዬ😜
በትዝታ ወልዴ እንደተፃፈ✍