❗️የማዋጣውን
ገንዘብ አቋርጫለሁ❗️
🌎አሜሪካ ለዓለም ጤና ድርጅት የማዋጣውን
ገንዘብ አቋርጫለሁ አለች🌎
👉ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ለኮሮናቫይረስ
የሰጠው ምላሽ ቀርፋፋ ነው፤ በአካሄዱም ቻይናን
ማዕከል አድርጓል ላሉት የዓለም ጤና ድርጅት
አገራቸው የምታበረክተውን የገንዘብ መዋጮ
እዲቋረጥ አዘዙ።
👉ይህም ማለት አሜሪካ ለድርጅቱ በየዓመቱ ለድርጅቱ
ትሰጥ የነበረው ገንዘብ እንዲቆም የሚያደርግ ነው
ተብሏል።
👉የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ዋና ጸሐፊ አንቶኒዮ
ጉተሬዝ የትራምፕን ውሳኔ "ጊዜውን ያላገናዘበ
እርምጃ" ሲሉ ተችተውታል።
👉ዶናልድ ትራምፕ ከሳምንታት በፊት ዶ/ር ቴድሮስ
አድኃኖም የሚመሩትን መሥሪያ ቤት ክፉኛ ሲወቅሱ
ነበር። በየዓመቱ የሚሰጡትን መዋጮ ለማጤን
እንደሚገደዱም ጥቁምታ መስጠታቸው ይታወሳል።
👉ትራምፕ እንደሚሉት የዓለም ጤና ድርጅት "መሠረታዊ
ኃላፊነቱን እንኳ" አልተወጣም። የቫይረሱን የስርጭት
ስፋትና አደገኛነት ባላገናዘበ መልኩ እርምጃ አወሳሰዱ
የዘገየና ቀርፋፋም ነበር ብለዋል። ከሁሉም በላይ
ለቻይና ያደላ ሲሉም ተችተውታል።
👉ፕሬዝዳንት ትራምፕ በአሁኑ ወቅት ራሳቸውም
በአገራቸው ጋዜጠኞችና ፖለቲከኞች ለቫይረሱ ባሳዩት
ቸልተኝነት ክፉኛ እየተብጠለጠሉ ይገኛሉ።
👉 አንዳንድ
የፖለቲካ ተንታኞች ትራምፕ በዓለም ጤና ድርጅት ላይ
እየወሰዱ ያሉት እርምጃ የተወሰነ ፋታ ለማግኘትና
ትኩረት ለማስቀየር እንደሆነ ይገምታሉ።
👉ትራምፕ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ "ለደረሰው
ጥፋት ድርጅቱ ተጠያቂ መሆን አለበት" እስከ ማለት
ደርሰዋል።
👉አሜሪካ ለዓለም ጤና ድርጅት የምትሰጠው የገንዘብ
ድጋፍ ለድርጅቱ ወሳኝና የጠቅላላውን 15 በመቶ
የሚይዝ ሲሆን፤ ቻይና በአንጻሩ በፈረንጆቹ 2018/19
ለድርጅቱ ያዋጣቸው ገንዘብ 76 ሚሊዮን ዶላር ብቻ
ነው፤ የአሜሪካ የባለፈው ዓመት መዋጮ 400
ሚሊዮን ዶላር ይደርሳል።
👉"ድርጅቱ ቫይረሱ ከዉሃን የተነሳ ሰሞን ፈጥኖ እርምጃ
ቢወስድ ኖሮ ይህ ሁሉ ቀውስ ባልተፈጠረ ነበር። ከዚያ
ይልቅ ቻይና እየወሰደችው የነበረውን እርምጃ
ሲያንቆለጳጵስ ነበር" ሲሉ ዶ/ር ቴድሮስ የሚመሩትን
ድርጅት ወቅሰዋል፤ ፕሬዝዳንት ትራምፕ።
👉የቢቢሲ የዋይት ሐውስ ሪፖርት በበኩሉ ፕሬዝዳንቱ
ራሳቸው በተመሳሳይ ጊዜ የቻይናን እርምጃ አወሳሰድ
ሲያደንቁ ነበር፤ ይህንንም በትዊተር ሰሌዳቸው
ጽፈውታል ብሏል።
👉የአሜሪካንን እርምጃ በተመለከተ የዓለም ጤና ድርጅት
መሪ ዶ/ር ቴድሮስ መግለጫ ይሰጣሉ ተብሎ
ይጠበቃል።
@bashashaa