#Updates
#መረጃ
የምግብ አገልግሎትን በተመለከተ...
ከታኅሳስ 1 ጀምሮ Non cafe ለሆኑ ተማሪዎች በቀን 100 ብር ሂሳብ በየወሩ የሚሰጥ ይሆናል። ነገር ግን አዲሱ ጭማሪ በጀት ወደ ዩኒቨርሲቲው ስላልደረሰ አሁን ላይ ለተማሪዎች የሚከፈለው በነባሩ በጀት ማለትም በቀን 22 ብር ተሰልቶ ነው። አዲሱ ጭማሪ በጀት እንደደረሰ ከ 22 ብር ላይ ቀሪው ክፍያ ወደ ኋላ ተሰልቶ በድምሩ 100 ብር የሚከፈል ይሆናል።
NonCafe መመዝገብ የሚፈልግ ተማሪ ካለ በየግቢው ባሉ የተማሪዎች አገልግሎት ጽ/ቤት መመዝገብ ይችላል። ለሚያስፈልጋችሁ እገዛ በግቢያችሁ ያሉ የተማሪዎች ኅብረት ያግዛችኋል።
የNonCafe ክፍያ ይዘገያል? (ለሚለው ጥያቄ):
በመደበኛ ሁኔታ አይዘገየም። ሆኖም ግን በጥሬ ገንዘብ እጥረት እና የተማሪዎች NonCafe ምዝገባ መዘግየት ምክንያት ሊዘገይ እንደሚችል ማሰብ ተገቢ ነው።
የካፌ ተጠቃሚ ተማሪዎችን በተመለከተ:
ከትምህርት ሚኒስቴር አዲስ የምግብ ሜኑ እንደተላከ ይታወቃል። ሆኖም ግን በቀን 100 ብር የሚያወጣ ሜኑ እንዲተገበር ያዛል። አሁን ላይ ባለው የምግብ ሜኑ እንኳን ዩኒቨርሲቲው በቀን ከ100 ብር በላይ እያወጣ ነው። ስለዚህ አዲሱ ሜኑ በቀን 100 ብር ሂሳብ ይተግበር ሲባል የምግብ መጠኑም ሆነ ጥራቱ አሁን ላይ ካለው እንደሚቀንስ ማሰብ ይስፈልጋል። ምክንያቱም አሁን እየተበላ ያለው ከ 100 ብር በላይ ስለሆነ። የአዲሱን የምግብ ሜኑ የዝግጅት ምጣኔ (Ratio) ማየት ትችላላችሁ፤ አብዛኛዎቹና ዋና ምግቦች ላይ ተቋሙ አሁን ከሚያቀርበው በእጥፍ የቀነሰ ምጣኔ ነው የተላከው።
ዩኒቨርሲቲው እንደ ቀድሞ መንግሥት ከመደበው በተጨማሪ ድጎማ ያድርግ ለሚለው:
ይህ የዩኒቨርሲቲው ወቅታዊ ሁኔታና ተቋማዊ ውሳኔ ላይ የሚታሰብ ሲሆን የእኛ የተማሪዎች የመብት ጥያቄ አይደለም። ነገር ግን በትምህርት ሚኒስቴር የተላከ መመሪያ እንደመሆኑ ሁሉም ዩኒቨርሲቲዎች ሊባል በሚችል ደረጃ መመሪያውን ይከተላሉ። ሆኖም እኛ እንጠይቃለን።
እንደ ተማሪዎች ኅብረት እየሰራን ያለነው: ቢያንስ አሁን ካለው የምግብ ሜኑ በጣም የቀነሰ እንዳይሆን ለማድረግ ነው። በአዲሱና በነባሩ መካከል ስላለው ልዩነት በዝርዝር ማወቅ ከፈለጋችሁ በየግቢያችሁ ያሉ የተማሪዎች ኅብረት ጽ/ቤት በመሄድ መረዳት ትችላላችሁ።
ተማሪዎች ኅብረት ይህን ሁሉ ርቀት እየተጓዘ መሆኑን ልትገነዘቡት ይገባል። በእስካሁኑ በአካልም በመልእክትም ስታግዙን ለቆያችሁ ተማሪዎች በእውነቱ ከልብ እናመሰግናለን። አሁንም በቅንነት ለማገዝ የምትሹ በየግቢያችሁ ወዳሉ የተማሪዎች ኅብረት ጽ/ቤት በመቅረብ አዎንታዊ አስተዋጽኦ እንድታደርጉ እናሳስባለን።
👉 BDU-CSU bot
Share Share Share
➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖
Bahir Dar University Students' Union Head Office
@bducsu