የድጅታል መታወቂያ አመዘጋገብ አላማና የህግ ተጠያቂነት፦
✍🏿 የዲጅታል መታወቂያ አዋጅ ሁሉን አቀፍ ወጥና አስተማማኝ በሆነ ሁኔታ የተመዝጋቢዎችን መረጃ በመያዝ ሕጋዊ መሠረት እንዲኖረው ለማድረግ በዲጂታል መታወቂያ ሥርዓቱ ውስጥ ባሉት አካላት መካከል የሚኖረውን ግንኙነት በሕግ የሚመራበትን ስርአትን የሚያበጅ ነው።
✍🏿 የዲጅታል መታወቂያ አዋጅ ዓላማዎች፦
👉🏿 ነዋሪዎች በየትኛውም የሀገሪቱ ክፍል ሲንቀሳቀሱ በቀላሉ የመታወቅ መብታቸው እንዲረጋገጥ በማድረግ ለሰብአዊ መብቶች አከባበር እና ለመልካም አስተዳደር መሻሻል አስተዋፅኦ ማድረግ ፣
👉🏿 አገልግሎት ማግኘት የሚፈልጉ ግለሠቦችን በቀላሉ ለመለየት የሚያስችል የዲጂታል መታወቂያ ሥርአት በመዘርጋት በአገልግሎት ሰጪ እና አገልግሎት ተቀባይ መካከል እምነት አንዲጎለብት ማድረግ፣ ሕገ-ወጥ ተግባራትን መከላከል ፣
👉🏿 ሀገር አቀፍ የዲጂታል መታወቂያ ሥርአት ሀገራዊ ፖሊሲዎች፣ ስትራቴጂዎች እና ዕቅዶች ሲቀረፁ እና የልማት ሥራዎች ሲከናወኑ ድግግሞሽን መቅረፍ፤ በዚህም የሃብት ብክነትን መቀነስ እና አካታችነትን ማጎልበት ፣
👉🏿 የዜጎችን የዲሞግራፊክ እና የባዮሜትሪክ መረጃ ለመሰብሰብ የሚያስችል እንዲሁም በዘርፉም ሆነ በክልል አደረጃጀት ያልተገደበ በብሄራዊ መረጃ ተናባቢ የሆነ ስርአት በመዘርጋት ሌሎች መንግሥታዊ ላልሆኑ አካላት የመታወቂያ ሥርኣት የመረጃ ምንጭ ሆኖ ማገለገል አገልግሎት ተኮር የሆኑ የመታወቂያ ሥርአት ወደ ዲጂታል መታወቂያ ሥርአት እንዲሸጋገሩ ማጠናክር ነው፣
✍🏿
የወንጀል ተጠያቂነት፦
👉🏿 ሥልጣን ባለው አካል የተሠጠ ዲጂታል መታወቂያን እንደ ሕጋዊ መታወቂያ ለመቀበል ፈቃደኛ ያልሆነ ወይም ማንነትን ብቻ በማረጋገጥ የሚሰጡ አገልግሎቶችን በዲጂታል መታወቂያ ለመስጠት ፍቃደኛ ያልሆነ ወይም በዚህ አዋጅ ላይ የተመለከተውን የመተባበር ግዴታ የተላለፈ ማንኛውም ሰው ከ10ሺ ብር እስከ አንድ መቶ ሺ ብር በሚደርስ የገንዘብ መቀጮ ይቀጣል።
👉🏿 መታወቂያ ለማግኘት አስፈላጊ ከሆኑት መረጃዎች ውጪ ሌሎች መረጃዎችን የሰበሰበ ማንኛውም መዝጋቢ አካል ከአስር ሺህ ብር እስከ አንድ መቶ ሺህ ብር በሚደርስ የገንዘብ መቀጮ
ይቀጣል::
👉🏿 ዲጂታል መታወቂያ ለማግኘት የተሰበሰቡ መረጃዎችን ሆነ ብሎ ለሶስተኛ ወገን አሳልፎ የሰጠ ማንኛውም ሰው ከአንድ ዓመት እስከ አምስት ዓመት ወይም እንደነገሩ ክብደት ክብደት እስከ ስምንት ዓመት በሚደርስ ፅኑ እስራት ይቀጣል::
👉🏿 ከላይ የተመለከተው ጥፋት የተፈፀመው የሕግ የሰውነት መብት በተሰጠው አካል ከሆነ ከሶስት መቶ ሺ ብር እስከ ስምንት መቶ ሺ ብር በሚደርስ የገንዘብ መቀጮ ይቀጣል::
👉🏿 ድርጊቱ የተፈፀመው በቸልተኝነት ከሆነ ቅጣቱ ከስድስት ወር እስከ አንድ ዓመት በሚደርስ ቀላል እስራት ወይም ከአስር ሺህ ብር እስከ ሰባ ሺህ ብር በሚደርስ የገንዘብ
መቀጮ ይሆናል::
(ከህግ ተጠየቅ)
https://www.facebook.com/61570012570305/posts/pfbid02YmC8g6RhKsdeqBFHien8EYEDF6oRpHLoVeSBDRGZE7iotqduVP64qQR1jwS3zZNEl/?app=fbl