#ምንም_ህልም_አይደለም
ድንገት ጋደም ስል በደከመው ግኔ
ሲዞር ይታየኛል ታላቅ ነበር ባይኔ
ያ አጉል ዘር ከፋፋይ ጉረኛው ፈላስፋ
በወንድሞች መሐል መርዝ እንዳያስፋፋ
ታርሞ ተነቅሎ ከሀገር ሲጠፋ
ያገር ዕድገት ጠላት የዕድል አሳዳጅ
ጥቅምን ሁሉ ሊያንቅ እንዲያ ሲጎመጅ
በግራ በቀኙ እየዘረጋ እጅ
ሌላውን ሁሉ ገድሎ ለራሱ እሚያበጅ
የጥቅሙ ተካፋይ ሳይሆን አማላጅ
በወንጀል ፈርዶበት ፈራጅ
ሲማቅቅ ሲከርም ሲማቅቅ ሲባጅ
ሲባል የህብ ጠላት የሰይጣን ወዳጅ
በሌላ እንኳ ሳይሆን በስልጣን ሰበብ
የሣንቲሟን ግማሽ የቀማ ከህዝብ
እንደ ሰረቀ ሰው የመንግስት ገንዘብ
በሰንሰለት ታስሮ ታጅቦ በዘብ
ቅጣቱን ሊቀበል ፍርድ ቤት ሲቀርብ
የኢትዮጵያ ህዝብ ከልብ ተቀራርቦ
ባንድ ቃል ተናግሮ ባንድ ልብ አስቦ
የጠላቶቹን አፍ ዘግቶ እና ሸብቦ
አብሮ የዘራውን ባንድ አብሮ ሰብስቦ
ሳይኖር ራብተኛ ሁሉም እህል ጠግቦ
በኢትዮጵያ ወገብ እንደ መቀነት
የተጠመጠመው ለምለሙ መሬት
ከወባ ተላቆ ህዝቡ ሰፍሮእበት
ባለም ታይቶ ማያውቅ የሰሊጥ ብዛት
የጫኝ ያለህ የሚል ጉድ የጥጥ ጭነት
የጤፍ የበቆሎው የስንዴውም ምርት
ተትረፍርፎ ሲቀር ካመት እስካመት
እንደ ተነበዩት ቀድመው ሊቃውንት
አገራችን ሁና የዳቦ ቅርጫት
ለሩቅ ወዳጅና ለቅርብ ጎረቤት
እስከቻልን ድረስ ሁሉም ሰው ተምሮ
ማብራሪያ ተሰጦት በአዋቂዎች ተሞክሮ
ራሱም አስቦ ሁሉም ተመራምሮ
ሙግት ጭቅጭቅን ወዲያ ጥሎ አንቅሮ
እግዜር እንዳዘዘው አንዱ አንዱን አፍቅሮ
ራሱም እንዳየው በለመደው ኑሮ
ባንድ አብሮ እርሻን አርሶ ባንድ አብሮ መንጥሮ
ባንድ አብሮ አጨዳ አጭዶ ባንድ አብሮ ከምሮ
አንዱ ሲዳር አንዱ ዘፍኖ አንዱ ሲሞት ቀብሮ
ስኖር በደስታ ከብሮ ተከባብሮ
ሁሉም ወገናችን ምስጢሩ ገብቶት
ለመደሩ አሰራር ቅጥ መጠን ሰጥቶት
የጋራ መሬቴን ያባቱን ርስት
ደረቁን ለመንደር ሜዳውን ለከብት
ለምለሙን ለእህሉ ጓሮውን ላታክልት
ከፋፍሎ መድቦ ሰርቶ ባንድነት
የመንግስት እርዳታ በቀላል ደርሶለት
ታማሚው መድኃኒት ህፃኑ ትምህርት
ሳይወጣ ሳይወርድ ሲያገኝ በወቅት
ተምሮም ሲሰራ ሰርቶ ሲያገኝ ሀብት
ሲረሳ ግሙ ዕድል መሆን ስራ-ፈት
በዐራቱ ማእዘን በለምለሙ ሜዳ
የወዳደለ ከብት ብዙው ቀንዶ -ጎዳ
ግማሽ ለወተት ሌላው ለፍሪዳ
ከዚህ ላይ ፍየሏ ከዚያ በጓ ወልዳ
የታከመው መንጋ ጤናው ያልተጎዳ
ጠግቦ እየፈነጨ ወደቤት ሲንነዳ
የንዱስትሪውን የርሻው ውጤት አብሮ
በከባድ መኪና በባቡር ተሳፍሮ
በዓለም ሁሉ ሊናኝ ሲጫን በመርከብ
ብዙ ለውጥ ሊያመጣ ወይንም ገንዘብ
ታላላቁ ወንዞች ዓባይ አዋሽ ባሮ
ተከዜ ነው ዋቢ?ምኑስ ምን ተቈጥሮ!
ለሐበሾች ጥቅም ኃይሉ ተወስኖ
ግማሹ ለጉልበት ግማሹ ለመብራት ሌላውም ወስኖ
ይውልና ሁሉ በየመልኩ ሆኖ
ብርሃን ብቻ ሁኖ ገጠሩ ከተማው
በሁሉም ቀን ሲሆን ተገፎ ጨለማው
በጭራሽ ሲረሳ ኩራዙና ሻማው
ናፍጣ ችርቻሮ ሥራ መሆን ሲቀር
በከተማው ኪዎስክ እንዲሁም በመንደር
በዚያም በዚህም ሲያንጎራራ ፋብሪካ
መሬትን ሊያስወስድ ቆፋሪው መኪና ዘቅዝቆ ሲያሽካካ
ጎበዙ ሠሪ ሕዝብ ባገሩ በሥራው በኑሮው የረካ
"ወዮለት !ጠላት እርሷን ለሚነካ!
ታላቋ ኢትዮጵያ ለዘላለም ትኑር!"እያለ ሲያወካ
ይኽ ብቻ አይደለም ከዚህ የሚበዛ ይህን የመሰለ
ዞትር እየመጣ ባኔ ላይ ተሳለ።
ይህ አጉል ሕልም ይሆን የምኞት ቅጅት
ዓለም እስከምታልፍ የማንደርስበት?
ወይስ የሚቻል ነው የፈጠጠ እውነት?
የሚያደክም ምክር የባዕዳን ትንቢት
ሳይኖረን ሳይገባን ሐኬት
አብረን በማስወገድ ያለብንን ችግር
ሁላችን ከሠራን ባንድ ልብ ላንድ አገር
ምኑም ህልም አይሆንም ከዚህ ሁሉ ነገር።
የምዕራብም ሰዎች ይኸንን ከሠሩ
የምሥራቅም ሰዎች ይኸንን ከሠሩ
በኛስ አገር ቢሆን ምንድን ነው ችግሩ
ሕዝቡ ተባባሪ ባለጸጋ ምድሩ ።
ምንጭ" ሬት እና ማር "የግጥም መፅሐፍ
✍🏽...ከአቤ ጉበኛ
━━━━━━✦✗✦━━━━━━━
➳➳➳ ሼር ያድርጉ!! ➢➢➢
@efremsyum
@efremsyum
➟➟➟➟➟➛➟➟➟➟➟
ድንገት ጋደም ስል በደከመው ግኔ
ሲዞር ይታየኛል ታላቅ ነበር ባይኔ
ያ አጉል ዘር ከፋፋይ ጉረኛው ፈላስፋ
በወንድሞች መሐል መርዝ እንዳያስፋፋ
ታርሞ ተነቅሎ ከሀገር ሲጠፋ
ያገር ዕድገት ጠላት የዕድል አሳዳጅ
ጥቅምን ሁሉ ሊያንቅ እንዲያ ሲጎመጅ
በግራ በቀኙ እየዘረጋ እጅ
ሌላውን ሁሉ ገድሎ ለራሱ እሚያበጅ
የጥቅሙ ተካፋይ ሳይሆን አማላጅ
በወንጀል ፈርዶበት ፈራጅ
ሲማቅቅ ሲከርም ሲማቅቅ ሲባጅ
ሲባል የህብ ጠላት የሰይጣን ወዳጅ
በሌላ እንኳ ሳይሆን በስልጣን ሰበብ
የሣንቲሟን ግማሽ የቀማ ከህዝብ
እንደ ሰረቀ ሰው የመንግስት ገንዘብ
በሰንሰለት ታስሮ ታጅቦ በዘብ
ቅጣቱን ሊቀበል ፍርድ ቤት ሲቀርብ
የኢትዮጵያ ህዝብ ከልብ ተቀራርቦ
ባንድ ቃል ተናግሮ ባንድ ልብ አስቦ
የጠላቶቹን አፍ ዘግቶ እና ሸብቦ
አብሮ የዘራውን ባንድ አብሮ ሰብስቦ
ሳይኖር ራብተኛ ሁሉም እህል ጠግቦ
በኢትዮጵያ ወገብ እንደ መቀነት
የተጠመጠመው ለምለሙ መሬት
ከወባ ተላቆ ህዝቡ ሰፍሮእበት
ባለም ታይቶ ማያውቅ የሰሊጥ ብዛት
የጫኝ ያለህ የሚል ጉድ የጥጥ ጭነት
የጤፍ የበቆሎው የስንዴውም ምርት
ተትረፍርፎ ሲቀር ካመት እስካመት
እንደ ተነበዩት ቀድመው ሊቃውንት
አገራችን ሁና የዳቦ ቅርጫት
ለሩቅ ወዳጅና ለቅርብ ጎረቤት
እስከቻልን ድረስ ሁሉም ሰው ተምሮ
ማብራሪያ ተሰጦት በአዋቂዎች ተሞክሮ
ራሱም አስቦ ሁሉም ተመራምሮ
ሙግት ጭቅጭቅን ወዲያ ጥሎ አንቅሮ
እግዜር እንዳዘዘው አንዱ አንዱን አፍቅሮ
ራሱም እንዳየው በለመደው ኑሮ
ባንድ አብሮ እርሻን አርሶ ባንድ አብሮ መንጥሮ
ባንድ አብሮ አጨዳ አጭዶ ባንድ አብሮ ከምሮ
አንዱ ሲዳር አንዱ ዘፍኖ አንዱ ሲሞት ቀብሮ
ስኖር በደስታ ከብሮ ተከባብሮ
ሁሉም ወገናችን ምስጢሩ ገብቶት
ለመደሩ አሰራር ቅጥ መጠን ሰጥቶት
የጋራ መሬቴን ያባቱን ርስት
ደረቁን ለመንደር ሜዳውን ለከብት
ለምለሙን ለእህሉ ጓሮውን ላታክልት
ከፋፍሎ መድቦ ሰርቶ ባንድነት
የመንግስት እርዳታ በቀላል ደርሶለት
ታማሚው መድኃኒት ህፃኑ ትምህርት
ሳይወጣ ሳይወርድ ሲያገኝ በወቅት
ተምሮም ሲሰራ ሰርቶ ሲያገኝ ሀብት
ሲረሳ ግሙ ዕድል መሆን ስራ-ፈት
በዐራቱ ማእዘን በለምለሙ ሜዳ
የወዳደለ ከብት ብዙው ቀንዶ -ጎዳ
ግማሽ ለወተት ሌላው ለፍሪዳ
ከዚህ ላይ ፍየሏ ከዚያ በጓ ወልዳ
የታከመው መንጋ ጤናው ያልተጎዳ
ጠግቦ እየፈነጨ ወደቤት ሲንነዳ
የንዱስትሪውን የርሻው ውጤት አብሮ
በከባድ መኪና በባቡር ተሳፍሮ
በዓለም ሁሉ ሊናኝ ሲጫን በመርከብ
ብዙ ለውጥ ሊያመጣ ወይንም ገንዘብ
ታላላቁ ወንዞች ዓባይ አዋሽ ባሮ
ተከዜ ነው ዋቢ?ምኑስ ምን ተቈጥሮ!
ለሐበሾች ጥቅም ኃይሉ ተወስኖ
ግማሹ ለጉልበት ግማሹ ለመብራት ሌላውም ወስኖ
ይውልና ሁሉ በየመልኩ ሆኖ
ብርሃን ብቻ ሁኖ ገጠሩ ከተማው
በሁሉም ቀን ሲሆን ተገፎ ጨለማው
በጭራሽ ሲረሳ ኩራዙና ሻማው
ናፍጣ ችርቻሮ ሥራ መሆን ሲቀር
በከተማው ኪዎስክ እንዲሁም በመንደር
በዚያም በዚህም ሲያንጎራራ ፋብሪካ
መሬትን ሊያስወስድ ቆፋሪው መኪና ዘቅዝቆ ሲያሽካካ
ጎበዙ ሠሪ ሕዝብ ባገሩ በሥራው በኑሮው የረካ
"ወዮለት !ጠላት እርሷን ለሚነካ!
ታላቋ ኢትዮጵያ ለዘላለም ትኑር!"እያለ ሲያወካ
ይኽ ብቻ አይደለም ከዚህ የሚበዛ ይህን የመሰለ
ዞትር እየመጣ ባኔ ላይ ተሳለ።
ይህ አጉል ሕልም ይሆን የምኞት ቅጅት
ዓለም እስከምታልፍ የማንደርስበት?
ወይስ የሚቻል ነው የፈጠጠ እውነት?
የሚያደክም ምክር የባዕዳን ትንቢት
ሳይኖረን ሳይገባን ሐኬት
አብረን በማስወገድ ያለብንን ችግር
ሁላችን ከሠራን ባንድ ልብ ላንድ አገር
ምኑም ህልም አይሆንም ከዚህ ሁሉ ነገር።
የምዕራብም ሰዎች ይኸንን ከሠሩ
የምሥራቅም ሰዎች ይኸንን ከሠሩ
በኛስ አገር ቢሆን ምንድን ነው ችግሩ
ሕዝቡ ተባባሪ ባለጸጋ ምድሩ ።
ምንጭ" ሬት እና ማር "የግጥም መፅሐፍ
✍🏽...ከአቤ ጉበኛ
━━━━━━✦✗✦━━━━━━━
➳➳➳ ሼር ያድርጉ!! ➢➢➢
@efremsyum
@efremsyum
➟➟➟➟➟➛➟➟➟➟➟